አድራሻ አድራሽ።
• አድራሻ አድራሽ።
«ለቁጣ የዘገየ ፍቅሩም የበዛ ነው።"
እግዚአብሄር ለቊጣ የዘገየ፤
ፍቅሩሩ የበዛ፤ ኃጢያትን
እና ዐመፃን ይቅር የሚል ነው።
(ዘኁልቊ ፲፬፤፰።)
«ፕሬዝዳንት ትራምፕ የሕዳሴው ግድብ ጉዳይን "ቅድሚያ ሰጥተው" እንደሚመለከቱት ተናገሩ» ዘገባው የBBC ነው።
ኢትዮጵያ አለመጋበዟ ይጎረብጣል። ለምን ስለምንን ያነሳሳል።
#ምዕራፍ ፲፱።
ኢትዮጵያ የመንፈስም፤ የፓን አፍሪካኒዝምም አዳራሽ አድራሽም ናት። በG7 ጉባኤ ላይ ያውም #ፈረንሳይ ላይ በተካሄደ ዕድሉን አለማግኜቷ ከተሟጋች አንፃር ሳይሆን እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሁኔታው ሊያሳዝነን ይገባል።
የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት እና ጠቅላይ ሚር አብይ የቀረበ ግንኙነት እንዳላቸው አያለሁና። የኢትዮጵያ የመንፈስ ልቅእና በልዕልና ያላት፤ ቀደምትነት፤ የአፍሪካ አንድነት እና በተመድ ምስረታ ላይ ያላት የሙሉዑነት ተሳትፎ፤ በነፃነት ዙሪያም ያለት ብቃት እና ክህሎት ዘመን #ሊጠቀጥቀው የማይገባ ዕንቁ ጉዳይ ነው።
ኢትዮጵያ የቀደመ ሥልጣኔዋ "ምን አላት እና ለካሪክለም የሚያበቃት" የሚል #የዛለ መንፈስ እንዳለ ባውቅም፤ ኢትዮጵያዊነት ግን ሊማሩት የሚገባ የዕውቀት ዘርፍ መሆን የሚችል የልቀት ማዕከል ነው። ከዚህ አንፃር የግብጽ እና የኬኒያ ውክልና የአፍሪካን አህጉራዊ አቅም የሚፈትን ገጠመኝ ነው ብዬ አስባለሁኝ። ኬኒያም ይሁን ግብጽ መወከላቸው እንዳለም ሆኖ፤ ኢትዮጵያን አግልሎ መነሳት ግን ትክክል ነው ብዬ እኔ በግሌ አላምንበትም።
ኢትዮጵያ በቅኝ ለተገዙ አገሮች በግንር ቀደምትነት ታግላ ያታገለች የክፋ ጊዜ የተግባር አርበኛ ናት። በተመድም ተሳትፎ ተርፎ የሚቀና የድርጊት ተሳትፎ ትናንትም የነበራት፤ ዛሬም ያላት ሁለገብ አገር ናት። ርህርህናዋ ስለ ሰው ልጅ ነፃነት ስለመሆኑም በተሳተፈችባቸው ዓለም ዓቀፍ ሁነቶች ያስመሰከረች ዝቀሽ ታሪክ ያላት አገር ናት።
#የ2026ቱን የG7 አገራት ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያ ያለመገኜቷ ሁኔታ የዲፕሎማሲ ስስነት፤ የጥረት ኩስምንና አድርገው የሚዩት እንዳሉ አውቃለሁኝ። እኔ ያዬሁበት አንግል ግን ከዚህ አንፃር አይደለም። የኢትዮጵያ መንግሥት በጥንቃቄ ሊያዬው እና በባለሙያ ምርምር ሊያደርግበት የሚገባ ጉዳይ ነው። ገራሚው ጉዳይ ባለቤቷ በሌለችበት ስለ እሷ በተደጋጋሚ በከሳሿ በግብጽ መቅረቡንም አዳምጠናል። ይህንን የሚሞግት፤ ይህንን የሚመክት አቅም በእጅጉ ያስፈልጋል። ክስ ተከሳሽ በሌለበት እንዴት???
ይህን አቅልሎ ማዬት አይገባም። ኢትዮጵያ ከግብጽም ይሁን ከኬኒያ አንሳ የታየችበት ሁነት በአደብ ሊታይ ይገባል። የፕሮቶኮል #ዝንፈትም አለው። እርግጥ ነው በዘመነ አብይዝም ፕሮቶኮል የሚባል ፕሮፌሽናል መዋቅር የለም። ልሙጥም ነው። እድገቱም፤ ባህሉም ተቆርጦ ተጥሏል። ምን አልባት የኦሮሙማ ባህሉ ሊሆን ይችላል። መደመር በለው ብልጽግና ማዕቀፋ በኦሮሙማ የፖለቲካ ስፕሪት የተገራ ነው። ለዚህም ነው ኢትዮጵያን እየገዛ ኢትዮጵያን የሚፃረር፤ የሚፈትን ክስተቶች ላይ የሚያተኩረው።
ሌላው የታሪክ ተሳትፎ ሹልከትም አለበት። በዚህ የዓለም ውክልና ላይ ኢትዮጵያ የቆየ ታሪክ አላት። አንቱም ናት። ስለሆነም ይህ ግለት ለቀጣይ ትውልድ የሚያስተላልፈው መልዕክትም ጤነኛ አይደለም። ለትውልድ ሥነ - ልቦናን አድራሽነቱ #ዝቅታን የሚያስተላልፍ ወይንም የሚያደርስ ነው።
በየትኛውም የውክልና አዳራሽ ስትገኝ በሁሉም አጋጣሚ ውስጥህ የሚለውን ማካፈል፤ ማቅናት እና መሸመት፤ ማጋራት እና ማጋረት፤ አዲስ አማራጭ Opportunity ሆነ አዲስ ወዳጅነት ይገኝበታል። ዲፕሎማሲ ቤት ተቀምጦ ብቻ አይደለም ለስኬት የሚበቃው። እርግጥ ነው ኢትዮጵያ በ2026ቱ የG7 ስብሰባ አለመገኜት አቅልለው የሚዩ አዳምጫለሁኝ። ሽንፈት አይደለም፤ በውስጡ የያዘው መልዕክት ግን ሊጠና ይገባዋል። ቀርቶባታልም።
"#የቤተ ዘመዱ ይታያል ጉዱ።"
ይህን መንፈስ አጉልቶ ያብራራ መንፈስም አዳምጫለሁኝ። ለግብጽ ወይንስ ለኢትዮጵያ ለማን አቅም ይዋጣል የሚል ዓይነት፤ ለህሊና ዳኝነት የተወሰኑ ነጥቦቼን ላቅርብ።
1) ኢትዮጵያዊነት ስትኖርበት የሚሰጥ ጸጋ እንጂ በፕሮፖጋንዳ የሚገኝ የዕውቀት ዘርፍ አይደለም።
2) የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ጉዳይ ማንም መትሮ፤ ወይንም ሠፍሮ፤ ወይንም ከንድቶ ሊሰጠን አለመቻሉ ሊታወቅ ይገባል።
3) ኢትዮጵያዊነት በገብያ ህግ የማይተዳደር ስለመሆኑ ሊታወቅ ይገባል።
4) ኢትዮጵያዊነት ከየትኛውም የምድር ፈላስፋ በላይ ስለመሆኑም ሊረሳ አይገባም።
5) በእያንዳንዱ #በአቃተ፤ በሳሳ ጉዳይ ላይ ኢትዮጵያዊነት መስፈሪያ ወይንም እንደ የጉልት ገብያ አለመሆኑን ግንዛቤ ሊያገኝ ይገባል።
6) ኢትዮጵያዊነት ይህ እና ያኛው ይቀርብኛል ተብሎ ለመያዣ በወለድ አገድ ወይንም #በአራጣ የሚያዝ ማንነት አይደለም።
6) ኢትዮጵያዊነት ፈቅደህ፤ ወደህ፤ በውስጡ ስትኖር የምታገኜው የነፍስህ እርካታ የሚያዝህ ነው የሚሆነው።
#የህሊና ፍትህ ምራቁን ለዋጠ ሰብዕና ካፒቴን ቢሆን ምርጫዬ ነው።
1) "ሙቱልን። ቅበሩን አትበሉን።" ሞታችን ተናፍቆ፤ ቀብራችን ተገፍትሮ ብትን አፈር ለማኝነታችን ታውጇል። በአደባባይ። ይህ ዘግናኝ አገላለጽ በአገር ደረጃ መግለጫ ሊሰጥበት ይገባ የነበረ፤ ለተናጋሪውም ከሥልጣን ማውረድ የሚያስችል፤ መንግሥት በይፋ #ይቅርታ ሊጠይቅበት የሚገባ ሲኦላዊ ዕይታ ነበር።
የኢትዮጵያ መንግሥት ኢትዮጵያዊነትን ማስቀጠል በኽረ ጉዳዩ ባይሆንም፤ ቢያንስ ለእሱ የአገዛዝ ዘመን አቅም የማሰባሰብ ብልህነት ቢኖረው መልካም ጎዳና ነበር። ግን በውስጡ "እሰይ ነገረልኝ፤ አስታጠቀልኝ" የሚል ይመስለኛል። ውጭ ተወልደው ለሚያድጉ ልጆች ተስፋማዋ አገራቸውን እንዳያስቡ ያደረገ #ወንጀልም ነበር። ይህን የሚሰቀጥጥ ግለት ተሸክሞ ግብጽን ለመታገል አብራችሁ ካልቆማችሁ ትመዘናላችሁ? ህም። ኢትዮጵያዊነታችሁ እጃችሁ ከምን? ወይንም "የቤተ - ዘመዱ ይታያል ጉዱ" ሊባል አይገባም። መብት አልባ ግዴታ አይጠየቅምና። ቅጥቀጣ፤ ጭፍለቃ እኮ ነው በስደት ለምንኖር ኢትዮጵውያን የተፈጸመብን።
2) ኢትዮጵያዊነት ከግለሰብ አምልኮ በላይ ከፍ ሲል …… "ለማኝ ነን። ለማኝ ጥገኛ ነው። ጥገኛ ሉዓላዊነት የለውም" ዓመት አልሞላውም። ይህን ጊዜ የእናትም ልጅ ቢሆን መመጎት መወገዝ ነበረበት፤ ናላን ብጥብጥ የሚያደርግ ፈተና ነውና። ኢትዮጵያ ከውስጥ ብትኖር ወጥቶ መሞገት ያቃተው ነፍስ፤ ዛሬ "በነገረ ግብጽ ልትታዩ ነው ሊል" አይገባም።
ይህም ብቻ አይደለም የኢትዮጵያ መሪ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ፤ ውጭ ጉዳይ ሚኒስተራቸው ዶር. ጌዲዮን ጢሞቲወስ እንደምን ከአቻ አገራት ጋር እኩል ሊቆሙ ይችላሉ? የሥነ - ልቦና ስብራት ይፈጥራል ብዬ ጽፌበታለሁኝ። የG7 መገለል በእራስ የተሰራ #ገመናም ሊሆን ይችላል። እራስህን አጣጥለህ፤ አቅለህ ክብርን አጋጦ መጠበቅ አይቻልም።
3) ንስር እና ቁራ የፈጣሪ ፍጥረቶች ናቸው። በዕውቀት ዘርፍም የባይወሎጂ አካሎች ናቸው። ምርምር ተቋማትም አሉት። ቱሪዝምም ነው። በእግዚአብሄር ፍጥረታት ሥራ መግባትም የተገባ አልነበረም። ይህም ሆኖ ጨዋ፤ ጭምት፤ አድማጭ፤ ችግር ቻይ የሆነ የህዝብ መንፈስን "#ቆሻሻ፤ ቁራ" ወዘተ ማለት አድራሹ እና ተደራሹ እርስ በርሱ ይላተማል።
ይህን ደፍሮ ማረም፤ ደፍሮ ማሄስ ለዛሬ ሳይሆን ነገን ለማበርከት ይረዳል፤ የትናንት ሰማዕታትን አጽማቸው ወጥቶ ሲጠቀጠቅ፤ ሰላሙን እንዳያገኝ ሲደረግ ኢትዮጵያ አገሬ ለሚል ዜጋ በድፍረቱ ሊገሰጽ ይገባ ነበር። አቅም ሲጠየቅ የአቅም ቅስም ሰባሪ ንግግሮች ሆኑ፤ ድርጊቶች በግልጽ እና በትህትና ሊነገር ይገባል። አገር ከሁሉም በላይ ከሆነችብን። የትኛውም የዘመናይነት አገር ውጭም አገር ውስጥም የኢትዮጵያዊነት ጥሪት ነው። የሌላ አገር ዜግነት ቀርቶ የስደተኝነት ጥያቄ ዕውን የሚሆነው በኢትዮጵያዊ ዜግነት ነው። አድራሻውም አድራሹም እሱ በእሱ ነው ዝሃ እና #ሐሩ።
4) "ድንቅ ህዝብ። ጀግና ህዝብ፤ በምን ልካስ?" ይህ ደግሞ የኢትዮጵያዊነት ጨዋነት ዘመንን ሲያስደምም፤ ከግለሰብ ልዕልና ይልቅ ለፈርኃ እግዚአብሄር፤ ለህግ እና ለህጋዊነት የመገዛት አቅሙ ቁሞ ያስተማረበት የዊዝደም ልዕልና በልቅና ነበር። ይህን የጨመተ ህዝብ አቋምህን፤ ውሳኔህን፤ ድጋፍህን እኛ እንለካልሃለን ማለት ድፍረትም ነው።
#ይልቅ። የናፈቀኝ እኔ በግሌ ፖለቲካል ፓርቲ የለለኝ ምልክታዊ ተግባር …… ይናፍቀኛል።
ኢትዮጵያን በዓውራነት የሚመራው ብልጽግና …… በትህትና የማሳስበው ……
1) እስረኛ ከመጨመር፤ አፈናን ከማስቀጠል፤ ፍርሃትን ከመቀጣጠል ተቆጥቦ፤ በየቦታው ለእስር የዳረጋቸውን ወገኖችን ይፍታ።
2) የሚመራው ህዝብ ተዘዋውሮ ይሠራ ዘንድ ወጥቶ የመግባት መብቱን ያስጠብቅ።
3) በአንድ በኩል ያዘነበለውን የፕሮጀክት ወረፋ ለመላ ኢትዮጵያ ያዳርስ። ጊዜያዊ እና ጥቃቅን መላሾወችን ገታ አድርጎ ትውልድን እኩል ሊያድን የሚችል ሚዛናዊ ተግባር ይሥራ። 12 ቢሊዮን አውሮፕላን ማረፊያ ስትሰራ አንድ በጭቃ ምርጊት የተሰራ አዳራሽ፤ ውሃ መጠጣት ያልቻለ ታሪካዊ ከተማ፤ መብራት ወረፋ የሚጠበቅበት ቦታ እንዳለም ይታወቅ።
4) ሰው ቀደም መርኽ ይከተል። ከመሪ ሰብዕና፤ ከፖለቲካ በፊት የተፈጠረው ሰው ነው። ሰው በኢትዮጵያ ይከበር።
5) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ላይ የመዘዘውን ባለ ፬ ሰይፍ ወደ አፎቱ ይመልስ።
6)) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ላይ የጀመረውን አሉታዊ #ዴሞክራፊ ያቁም።
7) ዕውነተኛ ሂደት ይወጥን። ከፋኝ ካሉ ወገኖች ጋር በማናናቅ ሳይሆን አክብሮ ይነጋገር፤ ይወያይ፤ የሚሰጠውን ነገርም ይድፈረው።
5) የፕሮጀክት ቅደም ተከተሉን እርማት ይስራበት። የህዝብ ጥያቄ እንጂ የመሪ መሻት ብቻውን አገርን ሊያስቀጥል አይችልም። ሲከር ይበጠሳል። ሲሞላም ይፈሳልና። ህዝብ ምን ይላል፤ ላም እረኛ ምን አለን? ይደመጥ።
6) ከበዓታቸው የተፈናቀሉ፤ በየመጠለያው ያሉ ወገኖቻችን ዜጎቼ ብሎ ይቀበል። ይርዳ፤ ያግዝ። ከቦታው ተገኝቶ ያጽናና። መንደር ሰርቶም ያስቀምጥ። ግዴታው ነው። ችሮታ አይደለም። የእስከ ዛሬው ቅጣት ይበቃል።
7) የበጀት ድልድሉን አንድ ቦታ የቆለለውን ደግሞ ደጋግሞ አይቶ ለማስተካከል ይሞክር።
ስምንት) የደህንነት ቢሮው #ከጥቃት በፊት ይቀድም ዘንድ ጥረት እንዲያደርግ አቅም ይመግብ።
8)) በኢትዮጵያዊነት ላይ እራሱ ብልጽግና የሚጥለውን ጫን ተደል በደል፤ ግለት፤ ተጫኝነት፤ የመቀያዬጥ ስውር ፍላጎት፤ የትውስት መንፈስን ለማሸከም የሚያደርገውን ጥረት ሁሉ ይሰብበት። እሱንም እራሱን ስለማያድነው።
9) የሃይማኖት ልዩነትን ያቁም። በሃይማኖት በማንነት የክት እና የዘወትር ስውር ዘመቻውን ያቁም። የዜግነት ሲሶ እና እርቦ የለምና።
10) ስጋት፤ ጭንቀት፤ ፍርሃት የፖለቲካ ሥራ ማስኬጃ ከማድረግ ይቆጠብ።
11) አካሎቹን ይረም። የሚዲያ የቦርድ አባል የተሳዳቢ መደበር ከማድረግ ይልቅ፤ የተቀጡ፤ ለአንደበታቸው የተቆጠቡ ሰብዕናወችን መፍጠር እና ማሰማረት ቀዳሚ ተግባር ማድረግን ይልመድ። የድል አጥቢያ አርበኛወቹ ዘለፋ፤ ግልምጫ፤ ዛቻ መራራ ሆኗል። ለነገሩ ፓርላማም ዘላፊ ቤተኛ ይሁንልኝ ተብሎ ተፈቅዷል። ወዘተ ……
12) በዜጎች መካከል፤ በጆግራፊያዊ አቀማመጥ፤ በዘር ሐረግ ማንነት፤ በሃይማኖት ያለው ንጹህ ዲስክርምኔሽን ይቁም። ሁሉም ዜጋ እኩል ይታይ። ዕድሉም እኩል ይከፋፈል።
13) ሰላም ያላስከበረ የሰላም ሚኒስተር በሰፊ በጀት ኤኮኖሚን ከማንቀዝ የተፈናቃይ የመልሶ ማቋቋሚያ ተግባር በጀቱ ቢሰራበት መልካም ነው።
#የሃይማኖት ተቋማት።
በውጭ አገር ሰብዓዊ ተግባራት፤ የትምህርት ዕድል ወጪን በመሸፈን፤ ኑሮን መምራት ለማይችሉ ሰፊ ድጋፍ የሚያደርጉ የሃይማኖት ተቋማት ናቸው። መንግሥትን በዚህ ዘርፍ ተቋማቱ ሊረዱ ይገባል። የጋራ የወል ተቋም ሊኖራቸው ይገባል። ለድንገተኛ የተፈጥሮ አደጋም ቢሆን ተቋማቱ ፕሮጀክት ነድፈው ሊሳተፋ ይገባል።
የታሰሩ ወገኖችን፤ የታመሙ ወገኖችን፤ የተፈናቀሉ ወገኖችን በየቦታው እየተገኙ ማጽናናት፤ አይዟችሁ ማለትን የሃይማኖት ተቋማቱ ቢከውኑት ከዚህ በላይ ጽድቅ እኮ የለም።
#ልባም ጉዳይ።
ጠቅላይ ሚር አብይን አውቃቸዋለሁ ብሎ ደፍሮ የሚናገር ሰብዕና ይኖራል ብዬ አላስብም። #ዓይነታቸው ብዙ ስለሆነ።
ብዙ አብዮች ናቸው ኢትዮጵያን የሚመሯት። በያንዳንዱ ሎጎ ላይ፤ በየለቱ የንግግር ዘይቤ ላይ፤ በሚመረቁ የትልም ዓይነቶት ላይ፤ ተቀድሞ ፍንጭ በሚሰጡ ጉዳዮች ላይ #ቀመር መስራት አይቻልም። አብይዝም አሳቻ ጎዳና ነውና።
ለዚህም ነው ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ውስብስቡን የህወሃትን የደህንነት መዋቅር ተቋቁመው እዚህ መድረስ የቻሉት። ሌላው እኮ አልቻለም። ግብጽን በሚመለከት ይሁን፤ የህዝብ እልቂትን፤ የፍላጎታቸው አድራሻ አድራሽነታቸውን እንዲሁም የሳቸው ሃሳብ አድራሻ አድራሽ ሁነት መተንበይ አይቻልም። ማወቅም ቀርቶ መጠርጠርም ጋዳ ነው።
#የቤርሙዳ ትርያንግልን ሚስጢር የትኛው ሳይንቲስት ፈታው? ምን አልባት ዘመን የቁልፋን መክፈቻ ሊያገኜው ይችላል። ይህ ደግሞ የሂደት ተልዕኮ ነው። መለካካቱ፤ አቅሎ ማየቱ፤ ማጣጣሉ፤ መተንበዩ ብዙ አያዋጣም። ይልቁንስ ጠቃሚው መንገድ በራስ አቅም ውስጥ ምኞትን መጥኖ መነሳት ይበጅ ይመስለኛል።
#መብት {} ግን ግዴታ ተወጡ። እኔ ከእናንተ የምፈልገውን ስጡኝ። ከእኔ ግን አትጠብቁ።
ይህ ብልጽግና እንደ መርኽ የሚቀበለው ጉዳይ ይመስለኛል። በተጨማሪም የብልጽግና ደጋፊወች፤ ተባባሪ ሰብዕናወችም የሁላችሁ ህሊና የውስጥ ሰሌዳው የእኔን መሻት ይዘግብ፤ ግን ወቀሳ ነቀሳ አልባ። ሲቸግርን ብቻ ተፈላጊ ናቸሁ። እንዲሁም ተከታያቸውም የራሱን ህሊና ፈቅዶ እንዳስረከበው ሁሉ የእኛንም ህሊና አስረክበን በቀፎ እንኖር ዘንድ ይሻል። ይህ ስስታምነት ነው። ይህ መንፈስን መዝረፍን መጠማት ነው። ቢታረሙ ጥሩ ነው።
#እንደ እርገት።
ሥልጣን ገብያ ነው። ሞቆ የሚበርድ።
ሥልጣን የውሃ ሙላት ነው። ሞልቶ የሚጎድል።
ሥልጣን ኢቤንት ነው ደምቆ የሚበተን።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን።
ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ.
Sergute©Selassie.
20/06/026.
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ