ጭነት ያዬለበት #በአለን #ቁምነገራ ላይ ነው። #ኖረን ነው ፍዳው የጠና።
"እግዚአብሄር ለቁጣ የዘገዬ፤ ፍቅሩ የበዛ፤
ኃጢአትንና ዐመፃን ይቅር የሚል ነው።"
ዘኅልቁ ፲፬፤፲፰።
#ምዕራፍ ፲፱።
ዝም ብላችሁ እሰቡት ያለውን የማንነት ቀውሳም ሾተላይ። ከእራስ ጸጉሩ እስከ እግር ጥፍሩ የማንነት ቀውስን ብትፈትሹት #እኛ እራሱ ለምን ተባልን ነው። እኛ ኢትዮጵውያን ይህም አለን፤ ያም ነበረን ወንጀል ነው የማንነት ቀውስ ፌስታ ላይ ላለ ሰብዕና። የክፋ ሃሳብ ሰራዊት ነው የማንነት ቀውስ ጠንሳሽ። አቤቱ ቅናት፤ በራስ የመተማመን አቅም ሙሽሽነትም።
አንድ አይሉ #ሁለት የፌደል ገበታ ከነ ሙሉ ሥርዓቱ ስዋሰው ስለምን ኖረን? ኧረ አቡጊዳን ስናክለው ሦስት ይሆናል።
ጥርት ያለ በአርበኝነት የጸደቀ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ስለምን ኖረን?
የቤተ - እግዚአቤሄር ቋንቋ ሊቁ #ግዕዝ ስለ ምን ተፈጠረ?
የዕውቀት መግቢያ በር #የየኔታ ማዕደ ገበታ ስለምን ኖረን?
የአማርኛ ቋንቋ ቅኔው፤ ለዛው፤ ስልተ ምርቱ፤ #ዝልቅ የትርጓሜ አቅሙ ለምን ኖረው? በቅቶ ስለተገኜ በዓለም ዓቀፍ የፊደላት ቀን ተመራጭ ነው። በዩንቨርስቲ በሌሎች አገሮች ይሰጣል። የሥራ ቋንቋም በአደጉ አገሮች መሆን ችሏል።
ብሄራዊ #የድል መታሰቢያ ቀናት ለምን ኖረን?
ስለምን #ነፃ ህዝብ እና አገር ተባልን? ህመም በሽታ እኮ ነው።
ስልጡን የአመጋገብ ሥርዓታችን ስለምን አለን? በዶሮ ወጥ ላይ ሁሉ ተዘምቷል እኮ።
ህብራዊ የሸማ የአለባበሥ ሥርዓታችን በጥበብ፤ በጥልፍ፤ በብር እና በወርቅ በቀደምቶቹ ስለምን አለን?
ባህላዊ የተለያዩ መጠጣችን ለአዋቂም ለልጆችም ስለምን የእኛ ሆኑ?
ቅኝ አለመገዛት ስለምን #የእኛ ብቻ ሆነ?
የህሊና #ሎጓችን ለአብዛኞቻችን ስለምን ኢትዮጵያኒዝም ሆነ?
የህግ፤ የሥርዓት ደንባችን ይሉንታን ጨምሮ የተፃፈውም ያልተፃፈውም ህጋችን ለምን ነበረን?
የአክብሮት በዓላት ስለምን #ኖሩብን?
ትናንት፤ ከትናንት በስትያ፤ ከትናንት በስቲያ፤ በስትያም ……… የምንናገረው #ዕውነት ስለምን ኖረን?
በያንዳንዱ የመኖር ዘይቤ ሲወራረስ የመጣው ባህላዊ ትውፊታችን ለምን ዛሬን #አስቀጠለ? ወዘተ ……
ይህ ነው ጦርነት የታውጆበት። በየዘመኑ ፍልሚያው ስለምን ቀደምት ኢትዮጵያን ያበጃት ኦርጋኒክ ተፈጥሮ፤ መኖርን ያሰለጠኑ ሁለገብ ጥበባት፤ ስዕል፤ ቅርሳ ቅርስ፤ ዕደ ጥበብ፤ ሥነ ጹሁፍ፤ ሥነ ግጥም ሁሉ ለምን ነበሩን።
#አለን የምንለው ሁሉ ለምን #ጠፍ ሁኖ አልጠበቀነም ነው፤ እራስን የሚታገለው የውስጥ የሃሳብ ግሽፈት እና #መሻገት ትውልድን በየዘመኑ እየገበረ ፈቅ ለማለት የማይቻል የሆነው። ቻይና ከ፶ ዓመታት በፊት እና ዛሬ? እኛ ከ፶ ዓመታት በፊት እና ዛሬ መመዘን ነው።
የሚገርመው ትናንትን የሚያብራራ፤ ነገን የሚያበራ ሃቅ እና ዕውቀት ባላንጣ ነው። " ኑ ኢትዮጵያን እንሥራት" የሚል ሚዲያ በዚህ ዘመን ማየት ያንገሸግሻል። በተሰራች አገር፤ በተበጀች አገር ላይ ቁጭ ብሎ #የቅልጣን ፖለቲካው ያቅለሸልሻል።
ስደቱ፤ እስሩ፤ መታገቱ፤ መታፈኑ "የድሮ ሥርዓት ናፋቂወች ነው" በትረ መንግሥቱ ይሁን መንበረ መንግሥቱ እኮ ፋንታዚ ላይ የተንሳፈፈ አይደለም። ያ የሚጠላ ቀደምትነት በሠራው ሥርዓተ መንግሥት ተፈናጦ ዳጭ ሃሳቡን ይዘራል። በዓቱ፤ ባድማው፤ ወግ ልማድ ሥርዓቱ እኮ አህጉርን ያቀና የተጋድሎ ታምራት ነው። መንበረ ሥልጣኑ የአርቲፊሻል ባሎን አይደለም።
#የማንነት ቀውስ መጀመሪያ የሚያፈርሰው እራስን ነው።
ጠልቶ ነው የሚነሳው። ስለሆነም በፈረሰ ማንነት ድክረቱ እራስን እንዲጨነግፍ ያደርጋል። በጭንጋፍ እሳቤ ዛሬን ለማሳደር፤ ነገን ለመቀበል ፈጽሞ አይቻልም። አገር ምላስ ላይ ያለች ቅጥል ወይንም ቅጠላ ቅጠል አይደለችም። አገር እራሱ ውስጡ ሰብዕናው ሞራሉ - ዲስፕሊኑ - ደም እና አጥንቱ ውህድ ሆነው ኢትዮጵያዊ ሰው ሆኖ የተፈጠረበት ትንግርታዊ #ትንፋሽ ነው።
ዛሬ የምትሰራ፤ ዛሬ ተለጣጥፎ ውሎ በማያድር ዲስኩር ሆነ አሉታዊ ዴሞግራፊ የምትፈጠር አይደለችም ፈላስፊት እናት ኢትዮጵያ። ኢትዮጵያ ክብሯ ሆነ ልዕልናዋ አልፋ #ኦሜጋ ነው። እራሷ አቅዳ በአንጡራ የልጆቿ ሃብት የሠራችው የአባይ ግድብ የውጭ አገር መንፈስ አሳታፊ ስላልሆነ፤ አሁንም ቅድምም በኃያላን አገር መሪወች አጀንዳ የሚሆንበትን ምክንያት አጥኑት። እራስን ችሎ መቆም ምን ያህል የሌላ መንፈስን ናፋቂ አድርጎ ጉጉትማ እንዳደረገው።
የሌለው ፈጥሮ፤ ዘርፎ፤ ቀምቶ፤ የራሱ ለማድረግ ይጥራል። የእኛ ደግሞ የተገላቢጦሽ ነው። ለምን ሳባ? ለምን ሮሃ? ለምን ላሊበላ? ለምን አክሱም? ለምን ዓድዋ? ለምን #ጊዮን፤ ለምን ፋሲል፤ ለምን ገዳማት ወዘተ ኖረን ነው እኮ ትግሉ። ለምን አለን? ለምን ኖረን? ይህ በውነቱ ደዌ ነው። ከድዌም ቹፌ። እያሳከከ ደም የሚተፋ ………
እኔ እና አንድ ኬኒያዊት እህቴ በሉ በህል አሳዩ ብንባል ለመምረጥ እኔ እቸገራለሁኝ፤ ከብዛቱም ከጥልቀቱም አንፃር። እሷ ግን የአውሮፓውያን መሰል ጉዳይ በአጭር እና በፍጥነት ታቀርባለች። እኔ በአደብ የማቀርበው ይለያል። የእኛ ብቻ ነውና። እና በተመልካች ዘንድ ብርቁ የቱ ነው?
እኛ ሳናከብረው - ---- የከበረ፤
እኛ ሳናደምቀው ---- የደመቀ፤
እኛ ሳናስጌጠው በፋክት ያጌጠ ተወዳጅ፤ ሳቢ፤ አጓጊ ቁምነገር በማንነታችን በኢትዮጵያዊነት ውስጥ አለ። ተነቦም፤ ተተርጉሞም፤ ተመስጥሮም የማይዘለቅ።
ይህን ወጥ እና ተፈጥሯዊ ሁለገብ ጸጋ እና በረከት መበረዝ፤ መከለስ፤ አላውቅህም ብሎ መግፋት፤ #መጫን፤ ማሳደድ፤ የሆነ ቅርፊት ነገር ፈጣጥሮ መለጣጠፍ ውድቀት እንጂ ሥልጣኔ አይደለም። ያልነበሩ ጉዳዮችን በነበረ ቀደምት ቅርስ እና ውርስ መለጣጠፍም ቅርፊት ይሆናል። መዋህድ አይችልም እና። ተፈጥሯዊ ማንነት አርቲፊሻል ማንነት ጋር ተዋደው ሊዘልቁ ስለማይችሉ።
#አለን! ያለን ማንነት ፈጠረን፤ ሲፈጥረን ደግሞ አፋችን ሞልተን በምንናገርበት #የነፃነት ሙሉ አቅም ነው። መዳን ይሁን መሻል ያለውን ወዶ እና ተቀብሎ፤ ዘመን ሰጥ ቁምነገሮችንም በልኩ ቀደምቱ ላይ ዲስክርምኔሽን እንዳይፈጸም በጥንቃቄ ሊሆን ይገባል። ለኢትዮጵያ ብርቅ እና ድንቅ የሚሆን አንዳችም ነገር የለም። በጥንታዊነቷ በሁሉም ሂደት ያለፈች ብርቱ እና ትጉህ አገር ስለሆነች።
ትጋት የኮፒራይት ሽሚያ ተኮር፤ የትውስት ናፍቆት ከሆነ ቀደምቱ ማንነት ኦርጋኒክ ስለሆነ ከልጥፍጥፋ ጋር አብሮ ለመጓዝ ይቸግርለዋል። ለዚህ ነው እኔ ኢትዮጵያ የከበደችን ለሁላችን ነው የምለው።
ሳይንቲስቷ ኢትዮጵያ ከአንድ ሰብ ሰብዕና በላይ ፍጹም በላይ ናት። ሁሉዬ ኢትዮጵያ ከየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ይሁን ተጽዕኖ ፈጣሪም በላይ ናት። ብልህነት በዊዝደም በውህድ ያበጇት አገር ናትና።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
01/07/026።
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነው።
See less
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ