ማንዴላይዝም የጽናት የእርቅ እና የምህረት እሽታ ካሪክለም ነው።

 

ማንዴላይዝም የጽናት የእርቅ እና የምህረት እሽታ ካሪክለም ነው። 
 
• "ባለቤቱ ያቀለለውን አሞሌ ባለዕዳው አይቀበለውም" ሆነ እንጂ።
 
#አገርኛ የመንፈስ ቴራፒ ነው። አገር የህይወት መንገድ ናት።
 
ከቶስ #ሰው መሆናችን ያላግባባን ምን ያግባባን?
 
" ፍቅራችሁ ያለ ግብዝነት ይሁን። ክፋውን ነገር ተጸየፋት፤ ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ፤ በወንድማማች መዋደድ፤ እርስ በእርሳችሁ #ተዋደዱ፤ እርስ በእርሳችሁ #ተከባበሩ። ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ለጌታ ተገዙ፤ በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ታገሱ፤ በጸሎት ጽኑ፤ ቅዱሳንን በሚያስፈልጋቸው እርዱ፤ #እንግዶችን ለመቀበል #ትጉ። (ሮሜ ምዕራፍ ፲፪ ቁጥር ከ፱ - ፲፫።)
 
ደቡብ አፍሪካ .... Religion in South Africa ...
Religion in South Africa
Wikipedia
https://en.wikipedia.org › wiki › Relig...
·
"Religion in South Africa · Christianity (85.3%) · Traditional faiths (7.80%) · No religion (3.10%) · Islam (1.60%) · Hinduism (1.10%) · Others (1.10%)."
 
#ምዕራፍ ፲፱።
 
እኔ ከወንጌል ውስጥ የሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ መልዕክታት ሁሉ ይመስጡኛል። ሮሜ ግን ይበልጥብኛል። ለመዝሙር የሚሆን ግጥምም ነበረኝ። የሆነ ሆኖ ዘመናችን ይቃኛል። ዛሬ ያለንበት ዘመን ከፊተኛው የፈተና ጊዜ ጋር እንደምን እንደሚገናኝ ያሳያል። የጎደለብንን፤ ያጎደልንበትን ሳስበው የሁሉም አሉታዊ መነሻ እና መድረሻ #የክፋ ሃሳብ ጽንት፤ ብቅለት፤ ስብለት ስለመሆኑ ያብራራልናል። 
 
እንግዳ ለመቀበል ሲተጋ በሆቴል አገልግሎት ይሁን በመንገድ አገልግሎት፤ ወይንም በቢሮ አስተዳደር እና አመራር የራስ እራስስ ከበዕቱ የሚነቀልበት ሁኔታ የት የማያስደነግጥበት ገጠመኝ ከዬት ይመደብ ያሰኛል። 
 
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አቅሙ ያን ያህልም ቢሆን #ማንዴላይዝምን በምድሩ፤ በባድማው ለማስፈጸም ትጋት አለው ወይ? ለነገሩ ደቡብ አፍሪካ ባለው ጥቁር // ጥቁርን በዚህ ልክ ሲጠላ፤ ደፍሮ "ውጡልኝ፤ አልፈልጋችሁም" ሲል ተመድ የተፈጠረበት፤ የተደራጀበት፤ ማንነቱን የሚመራበት የታህሳስ 10/1948ቱ ድንጋጌ የለም፤ ተትቷል ማለት ይሆን?
 
#የአፍሪካ ህብረት የተወጠነበት ቁም ነገር፤ መሠረታዊ ዓላማ እና ግብስ በቃ ፍሬም ብቻ ይሆን ግድግዳ ላይ የተለጠፈ?
#ቀደም ባለው ዘመን ከትራንፒዝም በፊት በሰብዓዊ መብት ጥሰት ጉዳይ ቁንጮ የነበረው የአውሮፓው ህብረትስ ዝምታው እስከምን ድረስ ይሆን? 
 
#የአሚንስት ኢንተርናሽናልን ጨምሮ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የተቋቋሙት የሰብዓዊ መብትን ጉዳይ የህሊናቸው ሎጎ ያደረጉትስ ይህ ጉዳይ አይመለከተነም ባዮች ናቸውን። 
 
በዚህ ረገድ የዓለም የጤና ሚኒስተር ጄኒራል ዶር ቴወድሮስ አድኃኖም ቀድመው ድርጊቱን ማውገዛቸው፤ ለተጠቂወች ያሳዩት ውግንና አንቱ ነው። በዚህ አጋጣሚ አመሰግናቸዋለሁኝ። 
 
ሌላው ግን ደቡብ አፍሪካ "እስራኤል በጋዛ ላይ ፈጸመች ለሚባለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት" በዓለም ዓቀፋ የህግ ተቋም ተጠያቂ የምትሆንበትን ጉዳይ አበክሮ የሠራ አገር፤ በራሱ መንግሥታዊ አስተዳደር ስለሚፈጸም የጨለማ ተግባር የማቀላጠፍ መሻትን አይመለከተው ሆኖ ወይንስ እራሱ እሱ ፈቅዶት ይሆን?
 
የሆነ ሆኖ ልባም አገሮች በሚችሉት ሁሉ ዜጎቻቸውን ከአውሬው ክፋ ሃሳብ ጭካኔ እንዲወጡ ጥረት እያደረጉ ነው። የዲፕሎማሲ ግንኙነቱን ሁሉ ያቋረጡም አሉ። በኢትዮጵያ በኩል ጠንካራ፤ ጥርት ያለ የፖለቲካ አቋም ሊኖር ይገባል ባይ ነኝ። ኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካ የብሪክስ ማህበርተኛ እንደሆኑ አውቃለሁኝ። ሁሉም ዓይነት ብሄራዊ፤ አህጉራዊ፤ ሉላዊ ተቋማት ግን ከሰብዓዊ መብት በላይ ሊሆን አይገባም። ተቋማቱ የሚደራጁት ለሰው ከሆነ????
 
ለአንድ ሰብዓዊ፤ ተፈጥሯዊ መንግሥት አምላክ አለኝ የሚለው፤ ከአምላኩ በታች ሊበልጥበት የሚገባው የዜጎቹ #ህይወት ነው። ዜጎቹ በአገርም፤ በውጭም ሲሳደዱ ገለልተኝነት የእርምጃው #ተባባሪነት ነው።
 
#በደቡብ አፍሪካ ንቅናቄው ጸረ ጥቁር ነው። 
 
ዓለማችን ትሁን አህጉራችን ካለ እኛ ሳቢ ቀለም ድርቅ የመታው ሸንበቆ ነው። የአፓርታይድን ማንነት ከውስጥ ያልወጣ ክፋ መንፈስ፤ አግላይ መንፈስ፤ ተጫኝ መንፈስ ፈቃድ የተሰጠው ስለመሆኑ ያመለክታል። ዘመኑ ለእኔ ቢጤ ስደተኛ እጅግ ከባድ፤ አስፈሪ ስለሆነ ሶልዳሪቲ ለማግኜት ጋዳ ነው። የአፍሪካ ህብረት ግን የተደራጀበት ቁም ነገር ይህ ነውና ፊት ለፊት ወጥቶ ሊሞግት፤ ጸረ - ጥቁር እንቅስቃሴ ሊያስቆም ይገባል። 
 
እስያ፤ መካከለኛው ምስራቅ፤ ምዕራብውያን እና አውሮፓውያን ይህ የመከራ ቋት ጨካኝ ሃሳብ የሚነካቸው አይመስለኝም። መከራው የጸናው በእኛው ጠይማን ላይ ይመስለኛል። 
 
የሆነ ሆኖ ይህ ወሳኝ የህልውና ጉዳይ የአፍሪካ አገሮችም ኢትዮጵያን ጨምሮ ከደቡብ አፍሪካ ጋር ያላቸውን ማናቸውንም #ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሁሉ እንደ ገና በዬካቢኒወቻቸው በርጋታ፤ በአደብ፤ በአቅል እና በአቅም በተጠና ሁኔታ አጀንዳቸው አድርገው ሊወያዩበት፤ ሊወስኑበት የሚገባ ጉዳይ ነው። ከሚገደሉት፤ ከሚሳደዱት የራሳችን ወገኖች ጋር መቆም በእጅጉ ያስፈልጋል።
 
ፓን አፍሪካኒዝምን የሚያቀነቅኑ ሁሉ በዚህ ጉዳይ ግልጽ አቋም በማሳየት ከተገፋ፤ ከተጠሉ፤ ከተገለሉ፤ ከሚገደሉ፤ ከሚማገዱ #ሰማዕታት ጎን ሊሆኑ ይገባል። "ቁርጥ ያጠግባል" ይላል የጎንደር ሰው። ከጥቁር ጋር መጥቆር፤ ከጥቁርነት መክሳት፤ ከጠይምነት ጋር መጎሳቆል ዛሬ ካልተፈቀደለት ነገ አህቲ የምንለው አፍሪካዊ ህብረት #ይበተናል። የሚፈለገውም ይህ ነው።
 
ትግሉን ዘለግ አድርጋችሁ ስታዩት የአፍሪካ ህብረትን ከተቻለ የመንቀል፤ ካልተቻለ የመነቅነቅ- የማዳከም - ተስፋ የማሳጣት ጉዳይም ሊኖርበት ይችላል። 
 
የቆዳ ቀለም የውስጥ ኦርጋናች ልብስ ነው። የእኔ ልብ ቅርጹም ይሁን ፋንክሽኑ ከአንድ ደቡብ አፍሪካ ዜጋ ጋር ተመሳሳይ ነው። የደማችን ቀለምም እንዲሁ ወጥ ነው ቀይ እንጂ ዥንጉርጉር አይደለም። 
 
ሰው መሆናችን ያላግባባን ምን ያግባባን? ማንስ #ሰለሰውነታችን ለእኛ ለራሳችን ለሰወች ያስተምረን?
የምትችሉ ሁሉ በምትችሉት ልክ ይህን የጥቁር ጥላቻ ሃሳብ መታገል #የጽድቅ ሥራ መሆኑን ተገንዝባችሁ መውጫ አጥተው ለጨለመባቸው ሁሉ ድምጽ ልንሆንላቸው ይገባል። የእኛም ወገኖች አብረው ተጠቂወች ናቸው።
 
ማንዴላይዝም ያስተዋለ ሃሳብ ነው። ሃሳቡን ፍልስፍናዊ ማድረግ ይችላል የአፍሪካ ህብረት። በፓን አፍሪካኒዝም ውስጥም የማንዴላይዝምን ፍልስፍና ዕውን ለማድረግ #ጠይማን ልንተጋ ይገባል። ማንዴላይዝም ካሪክለም የመሆን አቅም አለው። በዚህ ዙሪያ ተሰርቶበት ቢሆን ኖሮ፤ ማንዴላይዝም ይህን ያህል በባዕቱ ተፈናቃይ አይሆንም ነበር። 
 
// ማንዴላይዝም የይቀርታ ንጹህ ህሊና፤
/// የምህረት ቸር አስተሳሰብ፤
/// ከእራስ ጋር የመታረቅ ጉልበታም ፍልስፍና ነው።
/// ማንዴላይዝም ቂምን እና በቀልን የተጸየፈ። ጥላቻን #አክ ያለ፤
//// የሥልጣን ምቾትን በሰብዕናው ልክ መጥኖ ሆኖ የተገኜ የሚስጥሮች ልዕልናዊ አቅም ነው፣ ሥልጣን በቃኝ ያለ፤
//// አብሮ የታገለን፤ አብሮ ገፈት የቀመሰን ወገንን፤ አካልን ከድል መባቻ ጀምሮ ያልደረመሰ፤ #ያልመነጠረ፤ በሴራ ፖለቲካ ያላጫረሰ፤ ይልቁንም አክብሮ እቅፍ ድግፍ አድርጎ ያሻገረ፤ አብሮ ጸሐዩን ያዩ ዘንድ በከፍተኛ ሞራል እራሱን የገራ፤ የቀጣ የሰብዓዊነት የውሃ ልክ ነው። አብነትነቱ ጉልላት ነው።
 
#በማንዲላይዝም ቲወሪ ውስጥ እራስን አግልሎ የተነሳበት መርህ ከሰብ ጥላቻ እና ፋክክር ጽድት አድርጎ፤ ኃላፊነቱን የወጠነ እና ያሳካ ነው። ይህንን በጣም የጸደቀ #ሐዋርያዊ ጉዞ ሊያስቀጥሉት የሚገባው የደቡብ አፍሪካ የፖለቲካ ሊቃናት፤ በተለያዩ ሙያወች ያሉ የደቡብ አፍሪካ ሙሁራን ሊሆኑ ይገባ ነበር። አሁን እምናዬው ነገር ግን በባዕቱ ማንዴላይዝም #እየተጠቀጠቀ መሆኑን ነው። 
 
የአፍሪካ ሙሁራንም አጀንዳቸው ሊያደርጉት የሚገባ የህሊና ጉዳይ ነው። ይህን አሳዛኝ ሰቅጣጭ የአረመኔነት ገጠመኝ መላ የአፍሪካ ሊቃናት፤ ሊሂቃን #ባሊህ ሊሉት ይገባል። የአፍሪካ ህብረት አስቸኳይ የመሪወች ጉባኤ ሊጠራበት ይገባል። ራውንዳ ላይ የተፈጸመው አውሬያዊ ተግባር በአህጉራችን በእማማ አፍሪካ ተደግሞ ማዬት ለትውልዱ መራራ ገጠመኝ ነው።
 
የዓለም የሃይማኖት ተቋማትም በቸልታ ሊዩት አይገባም። የእኔ ጉዳይ ብለው አጀንዳቸው በማድረግ ሊሠሩበት ይገባል።
በዚህ ዙሪያ ሰሚናሮች፤ ወርክሾፖች፤ ፓናል ዲስከሽኖች በጥራት እና በትጋት ይከወን ዘንድ የአፍሪካ ህብረት ሊተጋ ይገባዋል። ማንዴላይዚም በመላ አፍሪካ ተፈቅዶ፤ ተናፍቆ ሊሠራበት የሚገባ ፍልስፍናዊ መንገድ ሊሆን ይገባል። 
 
እርግጥ ነው የደቡብ አፍሪካ ጠይሞች ብዙ ዋጋ ለከፈሉበት ነፃነት ተጠቃሚነታቸው ጥያቄ ውስጥ ሊገባ አይገባም። ሊከበሩ፤ ሊመሰገኑ ይገባል። ለነፃነታቸው በተደረገው ተጋድሎ ኢትዮጵያን የመሰለ ደግ ደጋፊ፤ እሩህሩህ ካፒቴን መርሳትም አይገባም። እኛ ቀለማችን ዳማ እና ጠይም ነን ውጡ ከሚባሉት መደብም ነን። 
 
የሆነ ሆኖ የኢትዮጵያ መንግሥት ጉዳዬ ብሎ ሊተጋ ይገባል። ዜጎቹን አለሁላችሁ ሊል ይገባል። የታይታ ሳይሆን ከልብ እና ከዕውነት። ለሰብአዊነት ቅርፊት ትዕይንት አያስፈልግም። ፈጣን ተጨባጭ ንቅናቄ ማድረግ ይገባል።
 
አገር አለኝ ማለት ልዩ የህሊና #ቴራፒ ነው። አገራዊነት ፈውስም፤ መድህንም፤ መንገድም። አገር የህይወት መንገድ ናት። ኢትዮጵያ መንግሥት እንዲኖራት ከምፈልግበት ወሳኝ ጉዳይ ይህን መሰል የህልውና ችግር እንዲህ ሲገጥም አቤት የሚባልበት ብቻ ሳይሆን አገር ያለው ዜጋ እና አገር የሌላቸው ኩርድሾች የሚያዩትን ስቃይ እኔው እራሴ በቅርበት ስለማውቀውም ነው። አገረ ኢትዮጵያ መቀጠሏ ለየትኛውም ውጪያዊ ጥቃት መካች አመክንዮ ነው። 
 
ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የሰብአዊ መብት ጥሰት፤ የዜግነት ሉዓላዊነት በብዙ ፈተና ውስጥ እንዳለ ጠፍቶኝ አይደለም። በሚገባ አውቀዋለሁኝ።
 
// ለመወቃቀስም አገር መኖር ያስፈልጋል።
/// ለመካሰስም አገር ያስፈልጋል።
/// ተስፋን ለመሰነቅ አገር ያስፈልጋል። 
 
ውጩ የሚጋረፍ ቋያ ነው። መንፈሱ ጥሩ አይደለም -- ለስደተኛ። ይህን "ረጅም ጦር ባይወጉበት ያስፈራሩበት" ይላሉ ባለቅኔወች ጎንደሮች። አገር አለኝ የሚል ስደተኛ እና አገር አልባው በብዙ ነገር እኩል አይታይም። ጋሻ መከታ ያስፈልጋል ቋሚ የመንግሥት ሥርዓት ያስፈልጋል። መጠጊያ። 
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
02/07/026.
 
እግዚአብሄር እኛን ስለሰጠን አብዝተን እናመስግነው። አሜን።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።