ልጥፎች

ከዲሴምበር 10, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ኢትዮጵያዊነት የመንፈስ ንባብ ነው፤ በ2014 ፖስት ተደርጎ የነበረ።

ምስል
ኢትዮጵያዊነት የመንፈስ ንባብ ነው - ለእኔ! „ስለ ጽዮን ታላቅ ቅናት ቀንቻለሁ። በታላቅም ቁጣ ስለ እሷ ቀንቻለሁ።“ ትንቢተ ዘካርያስ ምዕራፍ ፰ ቁጥር ፪ ከሥርጉ ©ሥላሴ Sergute©Selassie ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ 11.01.2014 ·        ማግባቢያ ለመቅደሙ እና ለዕለቱ ጡሑፍ። ውዶቼ ይህ ጹሑፍ በ2014 ነው የተፃፈው። ያን ጊዜ ጠቢቡ ቴዲ አፍሮ በሳተመው "ጥቁር ሰው" ላይ ወጀብ የጠናበት ጊዜ ነበር። እነ አቶ ጃዋር መሃመድ ወደፊት የመጡበት ያዙኝ ልቀቁኝ ይሉበት የነበረበት ዘመን ነው። ጠንከር ያሉ ፓኢልቶኮች ተከፍተው ኢትዮጵያዊነት ሲብጠለጥል የነበረበት ወቅት ነበር። በአንድ ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ድግስ ኢትዮጵያ ተወክላ በእንሱ ዘመቻ እንዲቀር የተደረገበት ጊዜ ነበር ጠቢቡ ቴዲ አፍሮ። እነሱም ደስታውን እያጣጠምን ነው ያሉበት ወቅት ነበር። ዛሬም ታሪክ ራሱን ይደግማል እንዲሉ ዘመን ራሱን ደግሞ እንሆ ትግራይ ላይ ሌላ የጦርነት አዋጅ ነጋሪት አለ። ጦርነቱ በኢትዮጵያዊነት ላይ ነው። እትዮጵያዊነት አሸናፊ ሆኖ ስለወጣ። ኢትዮጵያዊነትን በጥልቀት ማዬት ከተሳነን ለድጋሚ ሌላ ጦርነት እንጋለጣለን። የሃሳብ ጦርነቱ ይሁን፤ በሃሳብ ጦርነቱ ውስጥ የጥቃት ሰለባ የሚሆኑ ዜጎች እንደሚኖሩ ማሰብ ግን ይገባል። እነሱም ከጠራው መስመር ጋር ለመሆን ማሰብ እና መቁረጥ ይኖርባቸዋል። የትግራይ መሳፍንታት ህልም ቁሞ ቀር ከሆነ እንሆ ሦስት ዓመት ተቆጠረ።  የአማራ የህልውና የማንነት ተጋድሎ የተጀመረ እለተ አቡዬ ሐምሌ 5 ዕለት የታላቋ ትግራይ ኢትዮጵያዊነትን ጥሶ ለማለፍ የነበረው ህልም አፈር ድሜ ጋጠ ። ምክንያቱ ለወያኔ ሃርነት ትግራይ የማህል አገር መዳራሻ፤ ...