ኢትዮጵያዊነት የመንፈስ ንባብ ነው፤ በ2014 ፖስት ተደርጎ የነበረ።

ኢትዮጵያዊነት የመንፈስ ንባብ ነው - ለእኔ!
„ስለ ጽዮን ታላቅ ቅናት ቀንቻለሁ።
በታላቅም ቁጣ ስለ እሷ ቀንቻለሁ።“
ትንቢተ ዘካርያስ ምዕራፍ ፰ ቁጥር ፪

ከሥርጉ ©ሥላሴ Sergute©Selassie
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ 11.01.2014


·       ማግባቢያ ለመቅደሙ እና ለዕለቱ ጡሑፍ።

ውዶቼ ይህ ጹሑፍ በ2014 ነው የተፃፈው። ያን ጊዜ ጠቢቡ ቴዲ አፍሮ በሳተመው "ጥቁር ሰው" ላይ ወጀብ የጠናበት ጊዜ ነበር። እነ አቶ ጃዋር መሃመድ ወደፊት የመጡበት ያዙኝ ልቀቁኝ ይሉበት የነበረበት ዘመን ነው። ጠንከር ያሉ ፓኢልቶኮች ተከፍተው ኢትዮጵያዊነት ሲብጠለጥል የነበረበት ወቅት ነበር። በአንድ ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ድግስ ኢትዮጵያ ተወክላ በእንሱ ዘመቻ እንዲቀር የተደረገበት ጊዜ ነበር ጠቢቡ ቴዲ አፍሮ። እነሱም ደስታውን እያጣጠምን ነው ያሉበት ወቅት ነበር።

ዛሬም ታሪክ ራሱን ይደግማል እንዲሉ ዘመን ራሱን ደግሞ እንሆ ትግራይ ላይ ሌላ የጦርነት አዋጅ ነጋሪት አለ። ጦርነቱ በኢትዮጵያዊነት ላይ ነው። እትዮጵያዊነት አሸናፊ ሆኖ ስለወጣ። ኢትዮጵያዊነትን በጥልቀት ማዬት ከተሳነን ለድጋሚ ሌላ ጦርነት እንጋለጣለን። የሃሳብ ጦርነቱ ይሁን፤ በሃሳብ ጦርነቱ ውስጥ የጥቃት ሰለባ የሚሆኑ ዜጎች እንደሚኖሩ ማሰብ ግን ይገባል። እነሱም ከጠራው መስመር ጋር ለመሆን ማሰብ እና መቁረጥ ይኖርባቸዋል።

የትግራይ መሳፍንታት ህልም ቁሞ ቀር ከሆነ እንሆ ሦስት ዓመት ተቆጠረ።  የአማራ የህልውና የማንነት ተጋድሎ የተጀመረ እለተ አቡዬ ሐምሌ 5 ዕለት የታላቋ ትግራይ ኢትዮጵያዊነትን ጥሶ ለማለፍ የነበረው ህልም አፈር ድሜ ጋጠ። ምክንያቱ ለወያኔ ሃርነት ትግራይ የማህል አገር መዳራሻ፤ የአማራ መንፈስ እና የአማራ አንጡራ ተፈጥሯዊ አቀማመጥ ነበር ለዛ ድል ያበቃው።

አብረውት ጫካ እና ዱሩን መከራውን የተጋፈጡትን እንደ አልባሌ የትም መወርወራቸው አልበቃ ብሎ፤ ወረራውም መቀናጣቱም አልበቃ ብሎ፤ እንደ ሌባ በረት ገልብጠው ገብተው ነፍስ ለማጥፋት ሲጥሩ ከሰማይ ዱብ ያለባቸውን ውርደት እያቃተታቸው መጎንጨት ግድ አላቸው። 

አማራ የተሠረበትን እግር ብረት ወርውሮ ለአንዲት ሉዕላዊት አገር "የኦሮሞ የጋንቤላ ደም ደሜ ነው፤ ድምጻችን ይሰማ፤ ደንበራችን ይከበር፤ የወያኔ የግፍ አገዛዝ ይቁም እሰረኞች ይፈቱ" ብሎ በጀግንነት በሙሉ ለበ ሙሉነት የ አባቶቹን ሌጋሲ ሊያሰቀጥል በ መላ ጎጃም እና በጎንደር አደባባይ ላይ ወጣ። የማሌሊት የመርዝ ጥንስ ውርደታቸውን የጠጡት የዛን ጊዜ ነበር። የቀደሙት ጋሼ ጃግሬያቸው ሳጅን አዲሱ ለገሰ እና ሳጅን በረከት ስምዖን ላይ ታች ቢባዝኑም ትግሎ ቀጥሎ ዛሬን አምጦ ውጦ ሁሉንም ነጻ አውጣ። የተደሞው ሚስጢር ይህ ነው። የወያኔ ሃርነት ትግራይ ራዕዬ ታላቅነትም አከተመ ህልሙም ትዕቢቱም ኩራቱም ሞሸሸ።

አማራ በውስጡ ያለው ቅንነቱ በራሱ ጊዜ ፈጣሪ እዝነ ልቦናውን ያልነሳቸው ሊቃውንታት ቢመረምሩት ሚስጢር አለበት። በዛን ጊዜ ስጽፋቸው የነበረው ጹሑፎችም የ እድምታ ሊቃውንት ተጋድሎውን እንዲያመሳጥሩት ነበር። ለነገሩ እነሱም አቅም አልነበራቸውም። 

አማራ ሲፈቅድ እና አሻም ሲል የሚሆነውን ማዬት ነው። የዚህ ለውጥ ህሊና የአማራ ተጋድሎ እና የብአዴን ተጋድሎውን አድመጭ አርበኞች ናቸው። ቁልፉ ደግሞ ኮ/ደመቀ ዘውዱ ናቸው። ኮነሬሉ ተገፉ። ግፉን ተሸክመው ተቀመጡ፤ ያም አልበቃ ብሎ ድፈረት አሰኛቸው ጥጋባቸው ጣሪያ የነካው የወያኔ ሃርነት ሊቃናት። በድፍረታቸው ልክ ጥቃትን እያንገሸገሻቸው ጨለጧት።
  
የአሁን የተክሊል ሥርዓት፤ የአሁኑ መሬት አንቀጥቅጥ የሰላማዊ ሰልፍ መሰናዶ ጥቃትን ለመቀበል አለመፍቀድ ብቻ ሳይሆን የትግራይን ህዝብ ሲያታልሉ የኖሩበት የበላይነት ዘመን ማክተሙን ለማጽናናት ነው። ከእጃቸው ምንምም የሚመኩበት ነገር የለም። ገንዘብ ነው አላቂ ነው። የመንፈስ ጥሪት የላቸውም። በበዛ ሁኔታ ተጠሉ። በሰው ዘንድ መጠላት ደግሞ በፈጣሪም መጠላት ነው። 

ቁሙው ነው እያለቁ ያሉት። አሁን ለብሰው ከረባት አስረው ብናያቸውም ዕብናቸውን ደመነፋሳቸው ነው ያለው። በዬትኛውም የኢትዮጵያ ክልል እንደ ዜጋ መንቀሳቀስ አይችሉም። ከተጋሩ ውጪ አለኝ የሚሉት አንድም የመንፈስ ጥሪት በዬትኛውም ኢትጵያዊ ዜጋ የለም። ተጠልተዋል። እነሱ ሲነሱ ህዝብ ይንገፈገፋል። ግፋቸው አዋረዳቸው። ውሸታቸው እርቃናቸውን አሰቀረው

ስለዚህ ቀሪ ዕድላቸው ያሉ መስለው፤ ተክሊል ለብሰው አከርካሪውን መተነዋል ያሉትን ኦርቶዶክስን ተዋህዶን ተጠልለው ነግሠው ቀሰው ጵጵሰው ለትግራይ ህዝብ መታዬት ነው። የኦርቶዶክስ ተዋህዶን መከራ ለማዬት በዬሁኔታው የሚካሄደው ስብሰባ ላይ ያሉትን ሁኔታዎች ከውስጥ ሆኖ ማዬት ነው። 

ምን ያህል አማንያን ሆነው የፖለቲካ ሊሂቃን ድርቀት እንዳለበት። በላፈው ጊዜ የሴት አፈ ጉባኤ የሰላም ኮንፈረስ ነበር። ሦስቱም የፕሪዚደዬሙ ሰብሳቢዊች  የእስልምና ዕምነት ተከታዮች ናቸው። ይህ መልካም ነገር ነው። ነገር የተረሳ የተዘለለ የኢትዮጵያውያነት ጣዕም መኖሩን ማሰብ ይገባል። ይህ የሆነበት ምክንያት ስልታዊ በሆነ ሁኔታ የተዋህዶ ልጆች ከፖለቲካው መድረክ መገለላቸው፤ ተቀበረው እንዲቀሩ በመደረጉ እዚህ ደረጃ የመድረስ አቅም አልነበራቸውም።

የሆነ ሆኖ እንዲ እራቁት ያስቀሩትን ሃይማኖት ዛሬ ደግሞ አንተ መጠለያዬ ሁን፤ አስከበረኝ፤ አቀስስኝ አክሊሊህን ደፍተህ መባሉ ሌላ አማራጭ የላቸውም። አለን ማለት ግድ ይላቸዋል። ይህ ሁሉ ነገር የገቡት ቃል መና ስለቀረ የማጽናኛ ካሊም ነው። ከዚህ አንጻር ነው ሊታይ ሊፈተሽ የሚገባው የዶር ደብረጽዮን ገብረሚኬኤል ንግግርም ስብሰባም፤ ሰላማዊ ሰልፍ መሰናዶም።

በሳቸው ዘመን ነው ይህን የመሰለ እርቃንን መለመላን የመቅረት አጋጣሚ የተፈጠረው። በታሪክ እያለ የሞተ ድርጅት ቢኖር የወያኔ ሃርነት ትግራይ ድርጅት ብቻ ነው። ማንፌስቷቸው በራሱ ጊዜ ተቃጥሏል። ስለዚህ ለማጽናኛ የሄሮድስ መለስ ዜናዊ ፎቶ ይዘው መውጣት ግድ ይላቸዋል። ይህን ሲይ ጤነኛ ሰው ለዛ የመልስ ምት፤ ለዛ ሙግት፤ ለዛ ጊዜ ማጥፍት አይገባውም። ለተሸነፈ መንፈስ በተሸነፈበት መንፈስ ውስጥ ያለውን ገናና ተግባር መፈጸም ነው።  „ሙያ በልብ“ ይሉታል ጎንደሮች እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ሲገጥማቸው።

የተቀበረው ቅድስት ኦርቶዶከስ ሃይማኖት ሆነ አማራ ድል ላይ ናቸው - ዛሬ ላይ። ስለ አማራ ራሱ ዳር ዳር ያለ አውንታዊ ዕይታ በዚህ ባ ሁኑ ንግግራቸው አዳምጫለሁኝ። አንድም ህሊና ያለው የታመመ ካልሆነ በስተቀር ለወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ ልቡን ይሰጣል ተብሎ አይታሰብም ካለ ጅሎ የቅማንት አቀንቃኝ በስተቀር። አፋር እንደሆን ከ እንግዲህ አይገኝም። ተነቀለ የወያኔ ሃርነት ተስፋ አፋር ላይ። አከተመ ተስፋ ማቀቀ ተስፋ መረማማጃ ከእንግዲህ የለም። 

ይህን ድል የመጠበቅ ለዚህ ድል አጥር ክትር የመሆን፤ ለዚህ ድል ዘብ መቆም ይጠበቅባቸዋል የአማራ ልጆች በሙሉ። የትግራይ ሰላማዊ ሰልፍ ትዕይነቱ ሽንፈታቸው የታወጀበት ትርኢት ነው። አዲስ አባባ የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ስታከበር በኢትዮጵያ በጀት የሚተዳደረው ወያኔ ሃርነት ትግራይ ደግሞ የራሱን አካሄደ። ቲያትሩ ይህ ነበር። 

የሆነ ሆኖ የትም የሚኖር ኢትዮጵያዊ እህት ወንድሞቹን ልጆቹን ተጋሩን ማቀፍ እንደ አባት አዳሩ ማድረግ ያለበት ነው። እጣት ገማች ተብሎ አይቆረጥም፤ እንድትድን መንከባከብ ነው። እነሱ የሚፈልጉት አንድ ሌላም ነገር አለ። „የማይገርፉት ልጅ ሲቆጡት ያለቅሳል“ ሆኖ ሽንት በኮዳ ባርከፈከፉበት፤ በኤልኮፍተር በተደገፈ ውጊያ ጨፍጭፈው ለደረሰው በደል፤ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች በፎቅ ተወርውረው፤ የተበሳጨ ህዝብ የፈጸመው ግድፈት እንደ ድርሳን ይደግሙታል ይሰልሱታል፤ የሚሊዮን ህዝብ ኑሮ ተፈናቅሏል፤ ቁሞ ከመኖር የተሰረዘ ዜጋ እኮ አለ። የተሰወረ፤ የተሰደደ፤ አካሉ የጎደለ ስንቱ ግፍ ይዘርዘር ... 

አገር እርቃኗን ነው ያለችው። በቀን 600 ወገን አቧራ ለብሶ እሬሳ ታፍሷል። በሳምንት 700 ሺህ ወገን ተፈናቅሏል። ይህ የአሁኑ የማዕት አውርድ ቱማታ አሁንም ህዝብ ለህዝብ ሌላ እሰጣ ገባ እንዲገጥም ነውና ኢትዮጵያዊነትን ዋጥ ማድረግ የሚጠይቅበት ጊዜ ነው።

እኔን የሚያሰጋኝ የተጋሩ ሊሂቃን የእውነት ፍርቻ ሳይሆን እውነት ደፋሪው እዮር ቁጣውን የላከ ለታ ያቺ ምድር ምን ልትሆን እንደምትችል ነው። ስለ ምድሪቱ እንዲሁም ስለእናቶች እና ስለ ልጆቻቸው አስባለሁኝ።

ዛሬ ለ100 ዓመት የታቀደው ህልም ተቀብሯል። ከሰሏል። በልዞ አሮ ቀርቷል። ስለሆነም የዚህ ሁሉ የናዚዝም ፈላስፋን የሄሮድስ መለስ ዜናዊን አጽማቸውን ተንተርሰው መተኛት ግድ ይላቸዋል። የሙቱን መንፈሱን የሙጥኝ ማለት ግድ ይላቸዋል። ይህ እራሱ ለእነ አቦይ ስባሃት ነጋ የሚመች ሆኖ አይደለም። የአቶ መለስ ዜናዊ አቀንቃኞች መድረኩ ላይ ተባረዋል። ነገር ግን አሁን ያን መንፈስ ይምጣልን የሚሉት እነ ዶር ደብረጽዮን ጎንደሮች እንደሚሉት „ሲያጣ የጦመውን“ ነው። ወረዳ ላይ አኮ ነበር ዶር ደብረጽዮንን የላኳቸው አቶ መለስ ዜናዊ። እና በደል ይረሳልን? እእ። መውጫ ጠፍቶ ነው ፎቶ ተይዞ የተወጣው ከ አንገት በላይ ነው። ማጣፊያው አጠረ። 

ከእኛ የሚጠበቀው አቅለ ቢስ ሳንሆን፤ የጤፍ ጠላ ሳንሆን፤ ከላይ ከላይ ሳንፈላ ልናስተውለው የሚገባው ትልቁ ቁም ነገር በዬትም ቦታ የሚኖሩ የትግራይ ልጆችን በኢትዮጵያዊነት ማዕቀፍ ውስጥ በማዬት ይህን ወጀብ ማሳለፍ ይገባናል ባይ ነኝ። አብሶ ጦሩ የሚጎሰመው ጎንደር እና ወሎ ላይ ስለሆነ በጎንደር እና በወሎ የሚኖሩ የሰላም ሐዋርያት እዛው በክልሉ የሚኖሩትን ወንድም እህቶቻቸውን፤ ልጆቻቸውን በፍቅር እና በአክበሮት እንደ አባት አዳሩ የማዬት ግዴታ አለባቸው። ኢትዮጵያዊ ዜጋ አገሩ አንጡራ ሃብቱ ናትና።

አጤ ዮሖንስ ደሙን ያፈሰሳበት መሬት ዛሬ ለትግራይ ልጆች ባዕድ ይሁንልን ዓይነት ነው የወያኔ ሃርነት የጦርነት ጉሰማው። የፈለጉትን ይበሉ ትግራይ ያሉ መሪዎችን እና የተጋሩ ቤተሰቦች፤ ውጭም ያሉት ያሻቸውን ይበሉ ይህን ፈተና ታግሰን ማለፍ ይገባል። ያ እንዳለፈው ሁሉ ይህም ያልፋል። ለሚያልፍ ቀን ሰውን ያህል ክቡር ፍጡር ሊከፋው ሊገፋ አይገባም። ለዚህ ነው ይህን ጹሑፍ በድጋሜ በብሎጌ ላይ እንድለጥፍ የተገደድኩት እንጂ በወቅቱ ዘሃበሻ አውጥቶልኝ ነበር። ስለሆነም ጹሑፉ በዛ ዘመን የተጻፈ ስለሆነ የሚጨመርበት የሚቀነሰበት አይኖርም። ኢትዮጵያዊነት አያሞትም፤ አያረጅም። ኢትዮጵያዊነት ቀን ጥሎትም ራፊ ከማንም ከምንም አይለምንም።

ኢትዮጵያዊነት እሸት ነው። የተመሰገነው የአማራ ህዝብ ይህን ማንነት ይዞ 27 ዓመት ራሱን አጥቶ አቆይቶታል፤ ልጆቹንም በኢትዮጵያዊነት ሥነ - አምክንዮ ኮትኩቶ አሳድጓል። እራሱ ለውጡ የመንፈስ ማረፊያው ይኽው የ አማራ ህዝብ ነው። በሎቢ ተግባርም አማራ እን ኦሮሞ አይደለም የተጋው። እኛው ነን ስንፋለምለት የቆዬነው። አብሶ ኢትዮጵያዊነት መንጥዮሹን አሁን አጋዥ አግኝቷል ዶር ለማ መገርሳ እና ዶር አብይ አህመድ። እነሱ ሚሊዮን ናቸው። ደቡብ ህዝብም መከራው እንደ አማራ ባይሆንም ውስጡን አላሸፈተም ነበር። ለዚህም ይመሰገናል።

መከራው ቢገዝፍም ቀን የወጣለት ማንነት ቢኖር አማራነት እና ኢትዮጵያዊነት ነው። አማራ ሲያልፍለት ኢትዮጵያዊነት ያልፍለታል፤ ኢትዮጵያዊነት ሲያልፈለት አማራነት ያልፍለታል። አማራ ቀና ሲል ኢትዮጵያዊነትም ቀና ይላል። በኢትዮጵያዊነት ውስጥ ባህል፤ ቋንቋ፤ ወግ፤ ልማድ፤ ሃይማኖት፤ ትውፊት ታሪክ ሁሉም በሚስጥር በውህደት ነጥሮ ይገኛል። በዚህ ማንነት ውስጥ ሁላችንም አለን።

·       እንሆ በምልሰት … የቀደመው ጡሑፌ … ሲሰኘኝ ዕለት በድምጤ እሰራዋለሁኝ። ለዛ ያድርሰን።

ሰንበትን እንደ መክለፍት በእኛነት ዙሪያ ልል አሰብኩ። …  … አብሶ ሩሄን በትዝታ በሚያባክኑኝ ዬውስጥ - ለውስጥ የመንፈስ ሃዲዶች ዙሪያ ትንሽ ማለት ወደድኩ። የጹሑፉ ጥራት እስተዚህም ነው። ግን የሃሳቤ ፍሰት ማንነቴን ስለሚዳስስልኝ፤ ፍቅሬን - ትዝታዬን ይመግበኛል። ኢትዮጵያዊነት ንባብ ነው። ሲፈቀድልን ብቻ ማንበብ እንቻላለን። 

ኢትዮጵያዊነት ትርጉም ነው፤ ሲፈቀድልን ብቻ መተርጎም እንቻላለን። ኢትዮጵያዊነት ሚስጢር ነው ሲፈቀድልን ብቻ ነው፤ ቁልፉን መክፈት ማመሳጠርም የሚችለው። ኢትዮጵያዊነት የመኖር ሕይወት ነው ሲፈቅድልን መታደስ ይቻላል፤ የህይወቱ ንባብብም ጣዕም ይኖረዋል፤ ለዛውም አምሮብን። ኢትዮጵያዊነት መንፈስ ነው፤ ሲሰጠን ብቻ ዓይናችን ይከፈታል …. በስተቀር ዲዳ ሃሳብ ማስተናገድ ዕጣችን ይሆናል። ይህ ደግሞ ቅርስ አልባ ባዶነት፤ እርሾ አልባ ዘርየለሽ መሆን ነው። አያድርስ!

ኢትዮጵያዊነት ፍጹም ተወዳዳሪነት የማይገኝለት ተናፋቂ ማንነት ነው። ናፍቆቱ ውስጥን እንደ አሻው ገዝቶ አፍርህን በህሊናህ ስትቃኘው ፍውሰትን ያድልኃል፤ው ደግሞ ውበቱ ይቆጣጠርኃል። ስትፈቅድለት ትድናለህ። እሺ ስትለው ትፈወሳለህ፤ በስተቀር ግን ጉጉ ማንጉግ የሆነ አንካሳ መንፈስ ይጨፍርብኃል …፤ እስኪበቃው ያጨቀይኃል። አሸንፈውና ውጣ! … አሸናፊነትን ዋጥ አድርገውና ውስጥህን አሳምርብት …. ጌጥ ይጣላልን?

እንጀራን ስትወደው፤ ሽሮ ሰፍ ሲያደርግህ፤ ቁርጡ ሲታይህ፤ ቆሎው ሰፍ ሲያደርግ፤ ምቸት አብሹ ውል ሲልህ፤ ክትፎው ሲመጣብህ‘ ሚጥሚጣዋን ስትዳስሳት፤ ቆጮን ስታላምጠው፤ ጭኮውን ቀረብ አድርገህ ስታሸተው፤ ዳቦው በእንሰት ወይንም በኮባ ተደፍቶ ከነክብሩ በሞገስ  በቁንዶ በርበሪ ለምለም ዝንጣፊ ወይንም ጉዝጓዝ ተሽሞንሙኖ ሲታይህ፤ አንባሻው ሲሸትህ፤ ንፍሮው ሽው ሲልህ፤ ዝግኑ - ጥብሱ - ቅቅሉ - ጎረድ  ጎረዱ፤ ዝልቦው፤ ቦዘናው፤ ገንፎው ቅንጨው፤ ጨጨብሳው፤  ፍርፍሩ ሲያሰኝህ ዕወቀው ይህ ስሜት ውስጥህን ገዝቶ አንተነትህን የሰጠህ ስለመሆኑ። በጣም በእርግጠኝነት  ከዚህ ፈጽሞ አታመልጥምና ውበቱን አጊጥበት! ….

 …. አንተን አሳምሮ የሚገልጸህ ተራጓሚህ መሆንህን አትዝለለው፤ እርቀህ የማትርቀው ወስጥህ ነውና - አድምጠው።

ቄጤማው ለሽ ብሎ … ረከቦቱ ተኮፍሶ፤ ጭሱ ትጉልል - ትጉልል እያለ ሀገር ምድሩን ሲያካልለው፤ ማዕዛው የእጣኑ ዝንቅንቁ ጨስጨስ ሲል፤ ፍንጃሉ ወይንም ስኒው ላይ የፈረስ ጭራ መስሎ ቆረር ሲል፤ ጤናዳሙ ጣል ብሎ ወይ በወተት ወይ እንዲሁ፤ ጨው ሆነ ማጣፈጫ ታክሎበት ፉት ፉት - ትኩስ ትኩሱን፤ ዳበስ አድርገው - ሁንለት።  

የቡና ቁርሱ በቀለምሽሽ ተሽሞንሙኖ ቀረብ ሲል ቸርፈስ፤  ዘንጣፌ ሚጢሚጣዋ በተን ብላበት፤ ወይ ዳቦዋ … በህብረት በአብሮነት ሰምሮ ከልብህ ከት ብለህ ስትስቅ - ስትተራራብ … ያ ነው ፎሎቄው አንተነትህን የሰጠህ ኢትዮጵያዊነት። ይህን ዘለህ ወይንም ጨፍልቀህ ልትሄድ ብትል አይሆንም ---  አትችልም በፍጹም፤ እባክህን አትግደርደር።

አንተ ማለት የዚህ ውጤት ጭማቂ ነህ። ማንነትህ የተቀዳው ከዚህ ማርን ከሚያዘንብ ባህል ነው። እዚህ ላይ ያለው ንባብ ልዩ ነው … ይጣፍጣል፤ መንፈስን በሽብሸባ ዘና ያደርጋል፤ በዜማ ይቃኛል። ግን ትጉህ አንባቢ ይሻል - ስትታደል ይገለጽላኃል በስተቀር …. አንተን እራስህን ተላልፈኸዋል …. ተመለስ! የተፈጥሮ መስተውትህን ድጠህ አትስበረው። ይህ ቅልቅል ግን ውህድ ውብ ቅመም ቁንጅናህ እንዲሆን …. አብስለው።

ዋው! ስንቱ ይዘርዘር …. የንብ አውራ በመሰለ ሽንጣም ሞሰብ፤ ሌማት፤ ጥራር፤ ሰብሰብ ብለህ ስተታድም፤ ስትጎራራስ፤ በሞቴ አፈር ስሆን፣ ይህችን ይሀችን ብቻ! ብቻ በእኔ ሞት ወይንም በእከሌ ወይንም በእከሊት ሞት እየተባልክ በአፍ በእፍህ ፍቅርን ተጥቅልሎ ስትጎርስ ዬት እንደተቀዳህ ሹክ ይልኃል፤ ጣዕሙን ኑርበት - ለራስህ ብትል። አድምጠው አንተን እራስህን አግኝተህ አንገትህን ቀና አድርገህ እዬው፤ የነፃነት ቅኔ ዘጉባኤ በራስ መተማመን ስሜት እንዲፈነድቅ የረዳህ አንትን በአንተነትህ የፈጠረህ ቅዱስ መንፈስ ነው። የራስህም ጌታ እንድትሆን …. ያደርግኃል። አስተውል እባክህን? 

… ምንጩ ይህ ነው የማንነትህ ፈርጥ። ስታከበረው ማን እንደ አንተ ጌታ! ውስጥህ የባዕድ ሽፍትነት እንደይጨፍርበት ካልፈቀድክ፤ አንተ ዬዛ የጥቁር አንበሳ ደም ትውፊት ስለመሆንህ አሳምሮ ይነገርኃል - ያስተምርኃል። የዚህ ልዑቅ ንጥር አካል ቤተኛ - ተጋሪ መሆንህ ተሰጥቶኃልና እንኳን ደስ አለህ። …. እንዳይሾልክብህ ግን ጠብቀው!

… ያደክበት፣ ያ … ሜዳማ መስክ? ወይንም ያ … ጋራ ሸንተረሩ - ጅረቱ - ፋፏፈቴው የእነ-ባሮ፤ ፤ ዬእነ -አንገረብ የእነ-ጣና የእነ-አባይ፤ የእነ-መረብ፤ የእነ-ቀኃ፤ የቢሸፍቱ ሐይቅ ወዘተ የሌሎችንም ዋናና ገባር ወንዞች፤ ሐይቆች፤ጠረን - ስበት ከልብ ሆነህ መርምረው፤ እዬተራጨህ ትጫወትበት የነበረው ንፁህ አዬር በቅንነት ቅዘፈው፣ ሂድበትበት፤ ዋኝበት፤ ተፈጥሮህ የተቀመረበት የአንት ጸጋ ነው፤ ውስጥህን አሳምርበት፤ የአንተ ልዩ መለያ የተቀረጸበት መንፈስ ነው። በልጅነት ጊዜ ሰኞ ማክሰኞው፤ ቅልሞሹ፤ ገበጣው፤ ድብብቆሹ፤  በማዕድ ጥያቄ ተጠይቆ ላልመለሰ መሸነፉን እድምተኛው ሲወስንበት ፍርዱን ተቀብሎ ተሸናፊው የማይበላውን እንዲባላ በድምጽ ብልጫ ሲወሰንበት፤ ወርርዱ፤ ያ ውድና ደግ የልጅነት ዘመንህ የሰጠህ - የለገሰህ - የሸለመህ ረቂቅ ፍቅርን ካሰብከው በመንፈስህ እንዲሸራሸር ከፈቀድክለት እሱ ነው ተነስቶ የማይጠገብ ኢትዮጵያዊነት ማለት … አትረሳውም አይደል? ወደ ዛ … አዎንታዊ ዕውነት የህሊና ዓይን ላከው … ትበራለህ!

የምንጩን ውኃ ገለጥ - ገለጥ አድርገህ ፎልፎል የሚለውን ጎንበስ ብለህ ጠጥተህ ስትራካ እሱ ነው የአንተነትህ ቅኝት - እሺ! ተከታይህም ተራው ሲደርስ ትራፊ ነው ሳይል ተጎንብሶ ጥሙን ሲያረካ አንተ የተቀዳህበት ማንነት እሱ ነው ወርቅ ጸጋ ተመቸው! በቆሬ - በግሬራ - ወተቱ ከዛው ታልቦ ትኩሱን በርከክ ብለህ ስትጎነጭ አቤት ፍሰኃው! ይህ ለውስጥህ በገፍ ማንነትህ ያበቀለ መክሊትህ ነውና አጣጥመው! እርጎውን በፋጋ ጎንበስ ብለህ ውስጥህ ራስ ስታደርግበት፤ እርጎው በጉርና ተገፍቶ ቅቤው ሲወጣ፤ ትኩሷና አናትህን ረጠብ ስታደርግህ ነጮቹ ያልደረሱበት ሳውና ይሉኃል ይህ ነው።

ይህ ማንነት ተቀድቶ ያማያልቅ የኤዶም ገንት ነው … ግን ሚስጢር የመተርጎም ብቃቱ ካለህ፤ ከላይ … ከላይ የማታነበንብ ከሆንክ ብቻ …. ይህ መንፈስ ነው ማንነትህ የጸደቀበት - የበቀለበት - ያፈራበት። አትለፈው ----  ነገ ውስጡን አታገኘውማና ጠንቀቅ ነዋ!  አንተ ከሸፍትክበት እሱም ጀርባውን መስጠቱ አይቀሬ ነው - በጊዜ! …. በአንኮላው - በዋንጫው - በብርሌው ጥሩው ገፈታውን እፍ እፍ ብለህ ለቀቅ ስታደርገው፤ በተኃዋን በብርሌ ቆረር እያደረክ ወደ ሰራዊቶችህ ስትልከው፤ ቡቡኙንም ጥምህን ሲያባርር ረጠብ የሚያደርግህ ያ ውስጥነት ህይውት እስበው፤ ፍቀድና ….  ዘና አድርገህ አጣጥመው … አስላው …. ቁጠረው ….  ሥፍር ቁጥር የሌለው ሐሤት ታገኝበታለህ። ያ ሐሤትህ የተጸነሰበት ጀግናው ማንነትህ፤ የነጠረው የአንተነትህ ጮማ ነው ….

ቁምጣዋን፤ ቦላሌዋን፤ ሽርጡን፤ ሳንጃውን - ኮልቱን - አልቢኑን - ግልቢያውን - ዋናውን ጉዞውን - ሁሉንም ከልብህ ሆነህ እሰባቸው፤ በምልሰት ጊዜ ሰጥተህ አጫውታቸው፤ ይሰጥህ የነበረውን ደስታ ምልሰት አድርገልት፤ ያ ነው ውዱ ዕሴትህ፤  ሙሉ ወርዱ፤ ሽብሽብዎ በመቀነት ሸብ ሲል፤ ጃኖው ቀለማሙ ህይወት፤ ጥልፋማ ማንነትህ የተወለደበት ውስጥህ ነው …. ከመንፈሰህ ጋር ስለመሆንህም አረጋግጥ …. ጤናማነትን ይሸልምኃል።

·       እርገት።
ኢትዮጵያዊነት ጥሪኝ አለው። ኢትዮጵያዊነት ሥራዓትን ፈጥሮ ጨዋነትን ያበቀለ፤ መቻቻልን ውጦ በውስጡ ያጸደቀ፤ ትእግስትን ተቀበሎ ውስጥን የሚዳኝ የፍቅር ቤት ነው። እያንዳንዱ የአመጋገብ፤ የአኗኗር፤ የዕምነት፤ የወግና የልምድ ሞራሉ ልራቅህ ቢባል የማይቻል፤ መስጥረን፤ ተሸሽገን፤ ተቆራኝተን እዬኖርን ግን ቅብ ሽፍትነት ብታቆለባባስ ትርፉ ትዝብት ብቻ ነው ውጤቱም ባዶነት።

ምስጋናዬ ከልብ ነው። ኑሩልኝ የኔዎቹ።

ወስጤን ከሽኖ ጌጠኛ ያደረገው፤ የውበቴ ማርዳ፤ የመንፈሴ ዘውድ፤ ኢትዮጵያዊነት ይኑር ለዘለዓለም!
ፈተናን ከመፈጠሩ በፊት አሸንፎ የተፈጠረ ማንነት - ኢትዮጵያዊነት!


እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

መሸቢያ ጊዜ

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።