ጎንደር ክፍል - አራት፤ ማጠቃለያ።
ጎንደር ክፍል - አራት የጎንደር መንፈስ ይጠራል። ከሥርጉተ ሥላሴ 05.06.2014 (ሲዊዘርላንድ - ዙሪክ) „የእግዚአብሄር ቃል የነጠረ ነው። በርሱ ለሚታሙኑ ሁሉ ጋሻ ነው።“ (መዝሙር ምዕራፍ ፲፯ ቁጥር ፴) „የበለጠና የከበደ ኃላፊነት እንደሚጠብቀኝ ባውቅም ለእኔ የከበደኝ ግን ከጎንደር ህዝብ መለዬቴ ነው“ ጓድ አበበ በዳዳ የጎንደር ክ/ ኢሠፓ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳይ ኃላፊ ለጂንካ የክ/ ኢሠፓ አንደኛ ጸሐፊ ሆነው ሲሄዱ መሸኛቸው ላይ የተናገሩት ነበር። የጎንደር አቀራረብና የአያያዝ ሙያው ከውስጥና በመሆን ሰንደቅ የከበረ ነው። ጎንደር ኖሮ መለዬት ትዝታዎቹ በቀላሉ ሊፋቁ የማይችሉ፤ እንዲያውም ትውስታዎች እያመረባቸውና ወዘናቸው እዬፈካ በናፍቆት አሳምረው የሚያሹ፤ በራሳቸው ጊዜ በመንፈስ ቤተኛ መሆን የሚችሉ፤ ተመክሮን ያስመቹና ያሰበሉ የመልካምነት ...