"የአመንዝራም ዓይን ድግዝግዝታን ይጠብቃል፤" ቅርናት።
የደመቀ መኮነን ቅርናት።
የሥጋ ሸክም ለልኳንዳ ቤት እንጂ ሐገርን ለማታደግ
የቀብር ደመር ነው።
ከሥርጉተ
- ሥላሴ
28.02.2017 (ከጭምቷ
- ሲዊዘርላንድ።)
„የአመንዝራም ዓይን ድግዝግዝታን ይጠብቃል፤ የማንንም ዓይን አያዬኝም ይላል፤ ፊቱን ይሸፍናል። ቤቶቹን በጨለማ ይነድላሉ፤ በቀን ይሸሸጋሉ፤ ብርሃን አያውቁም። የጥዋት ብርሃን ለእነርሱ ሁሉ እንደሞት ጥላ ነው፤ የሞትን ጥላ ድንጋጤ ያውቃሉና።
(መጸሐፈ እዮብ ምዕራፍ ፳፬ ቁጥር ፲፭ እስከ ፲፯)
· ስለ አቶ በረከት ፊያሽኮ!
የኢትዮጵያ ሃብት ከሆኑ አንስት መረጃ ልነሳ - ዛሬ።
እንዲህ
ይላሉ ጸሐፊ ወ/ሮ/ት ሰርካለም ጌታሁን
„እረ ለመሆኑ ደመቀ መኮነን ማን ነው? እዉን አማራ ነውን?“ –
ጸሐፊዋ ወ/ሮ/ት ሰርካለም ጌታሁን በቀጠለም ይህን ውስጥን የሚመረምር ውርዴት፤ ከንቱንትን፤ እንሰሳዊ ግብርን ፈትሹት ይላሉ ጸሐፊዋ። ፈተና ሰጥተውናል። ማለፍም መውደቅም የዬግል ምርጫችን ነው።
„ደመቀ የመጀመሪያ ድግሪውን በባዮሎጅ ይዞ ነበር። የደመቀ የዮንቨርሲቲ ጒደኛ ማሩ ዛሪ በሂወት የለም። ከነባለቤቱ ኤድስ የሚባል ቀሳፊ ከቀሰፋቸው ሰነበተ። ማሩ ከደመቀ ቀድሞ በመወየኑ ከፍ ያለ ስልጣን ነበረው። ሚስቱም ለተወሰነ ጊዜ በርሀ ስለነበረች ለሱአም ውለታ ተብሎ ማሩ የብአዴን ምሁራን ምልመላና ማደራጃ መምሪያ ዎና ተጠሪ ነበር። ትልቅ ስልጣን ነው። ማሩ ድጋፍ ካልሰጠ ማንም የአማራ ምሁር ሹመት አይሰጠውም ነበር። ወደ ማሩና ደመቀ ግንኙነት እመለሳለው። ደመቀም ጎጃም ቡሪ አስተማሪ ሆነ። እዛ እያስተማረ እያለ ለአቅም አዳም ያልደረሰች ተማሪ ማርክ እጨምርልሻለው ብሎ በማታለል ደፈራት። የልጅቱ ቤተሰቦች እጅግ አበዱ ደመቀንም እንገላለን ብለው መግቢያ መውጫ አሳጡት። ሽማግሌ ገባና ” በቃ ተውት ምን ይደረጋል” ብሎ ሸመገለና ደመቀ ይቅርታ ጠይቆ ልጅቱን እንዲአገባት ተደረገ። እርሱአም የዛሪ ባለቤቱ እና የሶስት ልጆች እናት ወይዘሮ አለሚቱ ካሳየ ናት።“
·
የገበርዲን ሰቆቃ፤
አሰቡት ወገኖቼ „ለአቅመ አዳም ያልደረሰች ተማሪ።“ ይህ እንሳሳዊ የዘገጠ ሰብዕና ነው ዛሬ ለጠ/ ሚር ሹመት የታጨው? ይህ በሥጋ ገብያ የበሸቀጥ ሰብዕና ነው ዓይኑን በጥሬጨው አሽቶ የልዕልት ኢትዮጵያ ቁንጮ እና ምልክት፤ የዛች ገናና፤ ተፈሪ ሐገር መሪ ለመሆን የሚቋምጠው። አንዲት ቃል አውጥቶ፤ አንዲት ሃሳብ አመንጭቶ የማይደመጠው አለቅት መንፈስ ነው ዛሬ በከረባት እና በገበርዲን ተጥቅልሎ ጥቁር ሞት ለውርዴት ለኢትዮጵያ በደገሰላት በአቦይ በረከት ስምዖን አጋፋሪነት ወደ ህልሙ በገፍ ታዳጊ ወጣቶችን አሰለፎ የስጋ ሱስ ምኞቱን ወደሚያሳካበት መንበር እዬገሰገሰ ያለው?
ይሄ ጭምልቅልቅ ያለ የበከተ ስብዕና ሊሰሙትም፤ ምስሉን እራሱ ሊያዩትም ይቀፋል። አዬ አንተ አሳረኛ አማራ ስንቱን ጉድ ተሸከምክ? አዬ ፍዳህ? ይሄ ያንተ ያልሆነ መንፈስ ተለጥፎብህ በማንነትህ ተነግዶ፤ ተጠጥልሎብህ፤ አብልተህ፤ አጠጥተህ፤ አሳድገህ ደግሞ ለጭምቅሉ ስብዕና በአንተ ሥም ያለ ትውልድ ደሙ ውክል እንዲሆን ገሃነሙ አቦይ በረከት ስምዕኦን በዬነ። እንዴት ይቀፋል። እንዴስ ያንቀጠቅጣል። እንዴትስ ይመራል። እንዴትስ በቁጭትን ይለበልባል፤ እንዴትስ እልህሃዊ ነበልባልን በ
ዓራቱም ማዕዘን ይልካል። ደሙ ያልሆነ ጉድ አቅሙ ባልሆነ የኢትዮጵያ ውክልና ለመሳቂና ለመደለቂያ መታሰቡ በራሱ ድፈረት ነው። ሃፍረትም።
·
የገመና ዝልቦ!
አበስኩ
ገበርኩኝ! ይህን ገመና ተሸክሞ ሥልጣነ መንበሩን ለዚህ በሥጋ ፈቃድ ለረከሰ እና ለበከተ ከንቱ ፍጥረት መንፈስ የአቦይ በረከት ስምዖን ደመንፈስ በስብሰባ ሴራ እና ሸር በድር ተጠምዷል። ይህ የሥጋ ሸክም ሥሙ እራሱ ቢሮው አይመጥነውም። ህንጻው እራሱ አይመጥነውም። አጸያፊ ስብዕና ተሸክሞ እንዴት እሰተዛሬ ቀጠለ? ይህ እኮ የበከተ ነገር ነው። ይህ የረከሰ መንፈስ የቅድስት ኢትዮጵያ ቁንጮ መለያ ምልክት ሊሆን ቀርቶ መታሳቡ እራሱ ድፈረትም፤ የትውልድ ውርዴትም ነው። ቆሻሻ ነገር እኮ ነው ሴቶችን አስገድዶ መድፈር። ለዛውም ታዳጊ ወጣትን። አደራ ተስጥቶ አደራውን ቅርጭም
አድርጎ የበላ ውርዴ። ቀድሞ ነገር ለመምህርነት ሰብዕና ታማኝነት የሌለው እንዴትስ ለሀገር መሪነት? አግዚኦ! ስለአንች አንቺ መከረኛ ኢትዮጵያ! ኡኡ! ኢትዮጵያ አንቺ አሳረኛ እናት ሐገር! ኤልዩሄ ስለአንቺ አንቺ የቀደምት ሥልጣኔ ዘር። የዛሬ የምናምንቴ የመርከሻ አንባ መረማማጃ የሆነሽው ናፍቆቴ ፍደኛ ምነው መከራሽ እንዲህ ጠና?
·
የትውልድ ታሪክ ሃሞታዊ ህልም ትልም…
Ethiopian - Yemaleda Kokeboch Season 3 Ep 32A
የማለዳ ኮከቦች የትወና ውድድር ፈጠራ በዓለም አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያው ነው። መስራቹ ገጣሚ ፍጹሜ አሰፋ ለዛች ምስኪን ታዳጊ ወጣት ለሰማዕቷ ሃና ላንጎን የሴት እህቶቹ መከራ ግድ ስለሚለው የጻፈውን ወስጥ ነበር ተዋናይት ኤልሲ አሰፋ ተወዳዳሪ በነበረች ጊዜ ያቀረበችው። አንደኛም ወጥታበታለች ሌሎችም ሥራዎቿ ታክለው። ወስጡን አግኝታዋለች የሰቀቀኑን። በዚህ ውስጥ የሴረኛውን በረከት ግዑዝ ፍጥረት አቶ እንሳሳን ደመቀ መኮነን ም/ጠሚ ማየት ይቻላል። የወ/ሮ ካሳዬ የዛች ቅጽበትን እሬታ በመንፈስ አብሮ መሆንን ለዚህ
ጥቃት ሰለባ የሆኑ ሁሉ በዚህ ውስጥ በማዬት መፍትሄው ላይ መታደም ግድ ይላል።
የማከብራችሁ የጹሁፌ ታዳሚዎች የሀገሬ
ልጆች መግቢያው ላይ ብዙም ሳይረቅ 6.15 ደቂቃ ላይ ስለሚጀምር በጥቂቱ የህሊና ግርፋቱን ቋያ ማዬት ይቻላል። ሙሉውን ታች ላይ ለጥፌያዋለሁኝ። የጭካኔው ክርፋቱ ግማቱ ታዩታላችሁ። ተዋናይት ኤልሳቤጥ አሰፋ ጥሩ አድርጋ ነበር ምሬቱን፤ መከራውን ከውስጥ አድምጣ የሠራችው ድንቅ ሥራ ነበር። ይሄ የሥጋ ከንቱነት አብዮት ስለሚያስፈልጋው ነው ዛሬ በዚህ ዙሪያ መጻፍ የፈለኩት። የሥጋ ፈቃዱን መግራት እና መቆጠር የማይችል ማዬት ቀርቶ መስማት የታሪክ ተጠያቂ በቅጣት ያመጣል እና።
ይህን ገመና ተሸከሚ እዬተባለችን ነው አሁን ኢትዮጵያ። 17 ዓመት የሚያስፈርድ ጉድ በሽማግሌ ድርድር አግብቶ ተኮፈሶ ይገኛል ይህ እንሰሳዊ ስብዕና። ያቺ መከረኛም በጭካኔ ከቀደዳት ጋር መንፈሷ ወልቆ፤ ህሊናዋን በግፍ ከተረተረው አረመኒያዊ እንሰሳ ጋር ለባህሉ ሲባል ተጋብታ ሞታ ውስጥ ሞታ ትኖራላች። የዕድሜ ልክ እስረኛዋ ወ/ሮ ካሳዬ የኔም፤ የእኛም፤ የሁላችንም እስረኛ የመንፈስ እህታችን እንሆ ዕድሜ ይፍታህ ተፈርዶባት ከድናው ግን ነቅዛ ትኖራለች። ከተፈጥሮ ገዳዮዋ ጋር በጥቋቀር ሦስት ጉልቻዎች ተከዝና ህማማት ላይ ናት። ይህቺ መከረኛ በቁሟ ከስላ ያን የሰቀቀን ቅጽበት በጥቁር ጠቁራ ደም እያመጠች ትኖራለች። ከቶ ቀዳማይ እመቤት ብትሆን አደባባዩን እንዴት ታዬው ይሆን? ሌላ
የመከራ ዕወጃ፤ ሌላ የግማድ መቃብራዊ ህይወት።
·
እፍረት በድፍረት ክስመት።
ይህ ጭምልቅልቅ ያለ ታሪክ ተይዞ ከረባት፤ ገበርዲን፤ ወንበር እግዚኦ! እፍረት ማጣት። እግዚኦ ስለ አንቺ እናት ሀገር ኢትዮጵያ? እናት ሐገር ኢትዮጵያ እራሱን መግዛት የተሳነውን እንሰሳ ጉደኛሽን ተሸክምሽ። እናት
ሐገር ሽፍን ክውን አድርጋ ከነግማቱ መሸከሟ ላይበቃ፤ አሁን ደግሞ ለሌላ የተንጣራራ ቁንጮነት መሳቂያነቷን በዓለም አደባባይ በሚደያ ለማስናኘት የሴራው ቦንዳ የአቦይ በረከት ስምዖን መንፈስ ጉድቡን ይዞ እዬተንደፋደፈ ነው። እንደገና አንገት ለመድፊያ፤ እንደገና እንኩትኩት ብሎ ለመሰበር። ስለምን ይህ ተፈለገ? አቤቶ በረከት ስምዖን የነገን ኢትዮጵያ ተስፋ መቅበር፤ ማነኮት 27 ዓመት የሰሩበት እና የተሳካላቸውም የደባ ረግረግ ነው። በዚህ ውስጥ አማራን፤ ጎንደርን በመዳፋቸው ውስጥ
እንዴት ሲመትሩት እንደኖሩት ኦህዲዶች ዛሬ ይገለጥላቸዋል?
ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሐገሮች በተለይም
ከኤርትራ አንሳ መታዬቷ የህሊና ድሎት ለኤርትራዊው አቦይ በረከት ስምዖን ትንሳዔ ስለሆነ። ክስመቷ የታቀደ ነው። ለሴራው ቦንዳ አቶ በረከት ኢትዮጵያ የቆሻሻ ሥነ- ምግባር ማጠራቀሚያ ጉድጓድ ብትሆን ምን ሲገዳቸው? ከዚህ በላይ ግማትስ ምን ሊመጣ? ታዳጊ ወጣትን? … ይመራል፤ ያንገሸግሻል፤ ይኮሰኩሳል፤ ይፈትናል። ይህ ሰው መንፈሱ የሰው ሳይሆን የጭራቅ ነው። ታዳጊ ወጣት ልጃችሁን፤ የእህት ልጃችሁን፤ የምታውቋትን ትንሽ ልጅ ሁሉ በዚህ ጨካኝ ሰው መንፈስ ውስጥ አድርጋችሁ በእኔ ቢደርስ ብላችሁ እንደ ሰው እስኪ ከውስጣችሁ ታደሙበት-
ክብረቶቼ።
እንዲህ ያለ ቆሻሻ፤ እጅግም የወረደ ስብዕና ሊሰሙት የሚቀፍ፤ ሊያደምጡት የሚያሸማቅቅ አተላዊ ሰብዕና ደብቁኝ ማለት ነበረበት። ሸግሽጉኝ እባካችሁን ከነሽሁራሬ ማለት ነበረበት። ለነገሩ እኛ የነጻነት ራህብተኞች ይህ የበደነ ድንዙዝ፤ በቁሙ የሌለ ሰብዕና ገበርዲን እና ከረባት ለብሶ ስለሚጎራደድ አንድ ቀን አጀንዳችን ሆኖ አለማዋቁን አውቃለሁ። አሁን ይህን ሰለመኖሩ፤ ቁሞ ስለመሄዱ ግድ የማይሰጥን ቅዝቃዜ ተሸከሙ እዬተባል ነው? ወይንም ሌላውን የበረዶ ክምር አቶ ሽፈራው ሽጉጤን፤ ሲራጅ
ፌጌሳ፤
·
ምሬት በእሬት።
ሴረኛው አቦይ በረከት ስምዖን ልቅናውን የሚያዘክሩ የኢትዮጵያ ልጆች ብቅ ሲሉ አይደለም ገና ሽኩክሽታ ሲኖር እያደኑ ክንፈ የደህነንት ማሰልጠኛ እንዲበላው ያስደርጋሉ። ወይ ደግሞ ገዳዩ ያልታወቀ መከራ ይጠብቃል። ሰላዩ አቶ በረከት ስምዖን ሴላቸውን በስውር አደራጅተው የኢትዮጵያን አከርካሪያውን እዬሰበሩ እንዳትሞትም እንዳትድንም አድርገው ገዟት - ገዘገዟት - አዛጓት። የተፈጠሩት ለዚህ ነው ኢትዮጵያን ለማጥፋት - ናዚ።
ይህን
ጸያፍ ሥጋ የኢትዮጵያ መንፈስ ቁንጮ ሆኖ ሊታይ ይሆን? ለአንድም ቀን ቀርቶ ለአንዲትም ሰከንድ የኢትዮጵያ አምላክ አያደረግው አምላኬ። መስማቱ እራሱ ይቀፋል።
·
ግማቱ።
ግማቱ
ከሩቁ ይገፈትራል። ክርፋቱም አያስቀርብም። ጥንባቱ በርቀት ይጋረፋል። ማሰቡ እራሱ በዚህ በሱባኤ ሰዓት ይከብዳል።
ከሁሉ በላይ
የሚቀፍ ነው ይህ የሴሰኝነት ጭካኔያዊ አረመኔያዊ ሰብዕና። የአሰተሳሰብ ድህነቱ፤ ደንጋጠነቱን፤ በራስ መታማመኑ
ርቃናዊነቱ፤ ምስቅልቅ
- ድብልቅልቅ ያለው
የመስሎነት ወዝዋዜው፤ ጭምልቅ ያለው
የታሪክ ድርሳን፤
ልፈስፍስ ያለው
ህሊና ሆነ የማደረግ አቅሙ ውሽልሽልነት፤ በጠቅላለ በከንቱንት የከተመ ከንቱ
ስብዕና ይዞ ነው የቀረበው
ሬሳው የበረከት
መንፈስ። ኦህዲድ
ጀግናው ጥግ አልቦሽ አድርጎ አከርካሪውን ስለመታው።
የድንጋጤ ቀዬ መስርቶ ሴራውን በቦንዳ ይመትራል።
የአቦይ
በረከት የባንዳነት ተልዕኮውን ማወራረጃ
የሞት የሽረት
ትግል ናት ይህቺ ወቅት።
አዬሯ ተስናጋ ውጪ ነፍስ
ግቢ ነፍስ እያለች ነው። ግን እንዴት እና እንዴት ይሆን ፍልሚያው ለተስፋ ወይንስ ለቅብረት?
·
ለመሆኑ።
ይህን ወራዳ
ተፈጥሮ፤ ይህ ውራጅ መንፈስ፤
ይህ ጉራጅ
ስብዕና፤ ይህ ሴትን በተለይ
ታዳጊ ወጣቶችን
በመድፈር የበከተ
ውርዴ መንፈስ
ብሄራዊ ተልዕኮውን ለመወጣት
ይቻለዋልን የእነ እንኩቶ ማህበር? ወይንስ በሐገራዊ ራዕይ ከሙሉ አቅም
እና ብቃት
ጋር በተሟላ
ሰብዕና ዲስፒሊን
እና ታይቶ በማይታውቅ ትሁት አያያዝ ይዞ አደራዊ ራዕዩን ያቀረበው የኦህዲድ
ሙሉ ቁማና ለፈተና መፍቻ
አቅም ይሸለመው ይሆን?
ወይንስ ታዳጊ
ወጣቶች ለሥጋዊ
ፈቃድ በሰልፍ
የሚደረደሩበት የአርክቦታ ካቢኔ እንደስትሪ ከፍታ ላይ ኢትዮጵያ ትጠበቅ?
ከበፊቱ በላይ
የስብሰባው ታዳሚዎች
የኢትዮጵያ ልጆች
ግማድ ነው።
ውርዴት ተሸክሞ
ወደ መቃብር
ተያይዞ መስመጥ
ወይንም የተስፋ
በር አስከፋች
ተስፋ ሰንቆ
የትውልድ አደራን ለመወጣት ለሁሉም እኩል
የሆነች ብሩህ
ኢትዮጵያን ታሪክ
ፈጥሮ ኩራት
መሆን? ተጋድሎው
ይቀጥላል? ቸር ወሬ ያሰማን፤..
·
ክወና። እስቲ
አብረን እናልቅስ።
እንዴትስ
የልጅ አደራን ያላወጣ ከብታዊ ስብዕና ለጠ/ሚር ሃላፊነት እጩ ሆነ ይቀርባል? ሲታሰብ እራሱ ያንገፈግፋል - ያንገሸግሻል።
ሲጻፍ እራሱ በእንባ ጎርፍ ቀለም ነው። ይህ የጉድ ቁልቁለት ሰው ለማለት የሚያስችል አይደለም። ጸያፍ ከንቱነት!
·
የኔ ውዶች የውስጤ
ተደሞዎች፤
ይህን „የእታላሜን“ ከላይ የለጠፍኩት
ቆራጣ ነው። ይሄኛው ግን ሙሉው የቀረበበት ነው። ሙሉውን
ለማዬት ካልፈቀዳችሁ ከሚጀምርበት 22. ደቂቃ
ከ17 ሰከንድ
ላይ መጀመር ትችላላችሁ - በትህትና። … ታዩና እንዴት
ገመናው ውስጣችን
እርር ኩምትር
ማድረግ ብቻ ሳይሆን ማህጸን
እንደሚያቀድ ሚስጢሩን
ታገኙታላችሁ። ደም ያስለቅሳል።https://www.youtube.com/watch?v=qTj4NonqtwM
Ethiopian
- Yemaleda Kokeboch SE 3 EP 22 B
ገጣሚ ፍጹሜ
አስፋው ለሴት
እህቶቹ ያለው
ልባዊ አክብሮት
እና ፍቅር
ከውስጡ ነው፤
የውስጣችን ሰቀቀን
የሚጋራው እንደ
እኛው የዘመን
ተገፊዎች ጥቁር
ቀሚስ ለብሶ
ነው ህቅታችን
የሚያዳምጠው። ሐዘናችን
ለመጋራት ያለው
ትጋት ቅርባችን
በመሆን ራሱን
ገብሮ ነው፤
መከፋታችን ለማድመጥ
ያለው አትኩሮት
ይመስጣል፤ ወንድሜ
በሆንክልኝም ያሰኛል፤
ስሜታችን ሲጎዳ
አብሮ እሱም
ቁስል ስለማለቱ
ሳስበው የእኛ
መከራ ዘመን
እንዲያበቃ የሴቶች
የአኩልነት ተሟጋች
እንደሆኑት ልክ እንደ ዶር.
አብይ አህመድ
ብለው፤ ዕምነቴን
ብጥልልበት አይጠቀምኝም። ውድ ወጣት
ነው። ታሪካዊ
ድርሻውን በመታመን
የተወጣ - ተምሳሌት። ማግስታችን! ተባረክ
የኔ ድምጽ!
በተረፈ ኤልሲ
አሁንም በሞጋቾች
እያዬሁሽ ነው።
ወርቅ ነሽ።
በርቺልኝ እመቤቴ።
ሁልጊዜ ግን ለፍጹሜ ጸልይለት። እሱ ባይኖር
አንችን አናገኝሽም ነበር። እንደ አንቺ ምዕራፍዬን አያት
ዘንድ ደግሞ
እጸልያለሁኝ።
!ዳኝነት!
በተረፈ ይህ ጨካኝ መንፈስ
ከእንዴት ዓይነት
መንፈስ ጋር ተፎካካሪ ለመሆን
እንደታሰበ ደግሞ
ስለ እናታችሁ፤ ስለ ትዳር አጋራችሁ፤ ስለ እህታችሁ፤ ስለ ሴት ጓደኛችሁ፤ ስለ አክስታችሁ እንዲሁም
ስለ ሴቶች
መከራ ግድ የሚላችሁ የቅኖች ቤተኞች ሁሉ ታደሙበት እና መዝኑት - አሁንም በትህትና። ሚዛን
ለራስ ነው ይላሉ ጎንደሬዎች።
·
ሚዛን።
Ethiopia
Dr abiy የሰዉ ልጆች ልዩ ብቃት ክፍል አንድ
Ethiopia
Dr abiy የሰዉ ልጆች ልዩ ብቃት ክፍል ሁለት
በተረፈ
የኔዎቹ ስለነበረን ውስጣዊ የ እኛዊነት መከራን በወልዮሽ የማድመጥ ጊዜ ዘንከት ያለ ምስጋናዬን ሸልሜ ልሰናበት።
በቃችሁ
ይበለን አሜን።
ኢትዮጵያዊነት
ከመፈጠሩ በፊት መከራን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።
እግዚአብሄር
ይስጥልኝ። መሸቢያ ጊዜ - አክባሪያችሁ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ