"የኢትዮጵያ መንግሥት ጥሰት የፈጸሙ ኃላፊዎችን ከስልጣን እንዲያነሳ የአሜሪካ የዓለም አቀፍ ወንጀል ፍትህ ቢሮ ኃላፊ መከሩ BBC" በማስተዋል ይደመጥ።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cvg69094qgeo "የኢትዮጵያ መንግሥት ጥሰት የፈጸሙ ኃላፊዎችን ከስልጣን እንዲያነሳ የአሜሪካ የዓለም አቀፍ ወንጀል ፍትህ ቢሮ ኃላፊ መከሩ" "የኢትዮጵያ መንግሥት፤ በሰብአዊ መብት ጥሰት የሚከሰሱ ባለስልጣናትን፤ "በተለይም የሠራዊት አባላትን በአስተዳደራዊ ፈቃድ" ከስልጣን እንዲያነሳ የአሜሪካ የዓለም አቀፍ ወንጀል ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አምባሳደር ቤዝ ቫን ስካክ መከሩ። በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች "የሚፈጸሙ ያሉ ጥሰቶች" በቀጠሉበት ሁኔታ ሁሉን አቀፍ የሽግግር ፍትህን መተግበር "አስቸጋሪ" ካልሆነም "የማይቻል" እንደሆነ ተናግረዋል። እንደ የጦር ወንጀል እና በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል ያሉ የሰብአዊ መብት ጉዳዮች በተመለከተ የአሜሪካውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርን የሚያማክረውን ቢሮ የሚመሩት አምባሳደር ቤዝ ይህንን የተናገሩት ረቡዕ ታሕሳስ 9፤ 2017 ዓ.ም. ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ ነው። የትናንቱ መግለጫ፤ አምባሳደር ቤዝ ከሕዳር 29 እስከ ታህሳስ 2፤ 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ የነበራቸው ቆይታ ላይ ያተኮረ ነው። "በኢትዮጵያ እና በመላው አፍሪካ የተጀመሩ የሽግግር ፍትህ እና ተጠያቂነት ሂደቶችን ለማጠናከር" ወደ ምስራቅ አፍሪካ ተጓዙት አምባሳደሯ፤ ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣናት ጋር መገናኘታቸውን እና የፍትህ ሚኒስቴር ባዘጋጀው የሽግግር ፍትህን የተመለከተ ውይይት ላይ መካፈላቸውን ገልጸዋል። የዓለም አቀፍ ወንጀል ፍትህ ቢሮ ኃላፊዋ፤ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የኢትዮጵያን የሽግግር ፍትህ ሂደት ለመደገፍ ፍላጎት እንዳለው የገለጹ ሲሆን "እስካሁን ባለው ...