እውነት ነውን የካፒቴን ማስረሻ ሰጤ #ወላጆች #ታስረዋልን?
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
እንዴት ሰነበታችሁ ማህበረ ቅንነት? ዕውነት ነውን የካፒቴን ማስረሻ ወላጆች ታስረዋልን??? ይህ ከሆነ #እርግማንን ትውልዱ ተጎንብሶ ያፍሳታል። የአማራ ወላጆች በአማራ ልጆቻቸው ከመታሰር፤ ከመንገላታት በላይ ምን #እርግማን አለና። ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ በዘመነ ህወሃት እስር ቤት አሳሩን ያዬ መከረኛ ወጣት ነው። በእስራት ዘመኑ ሁሉ ቤተሰቦቹ አብረው ተንገላተዋል።
በዘመነ አብይዝም መቅድም ላይ ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ መላ ኢትዮጵያን #ተንከራቶ የአማራን ወጣቶች በአካል ተገኝቶ #በመንፈስ አደራጅቷል። በዚህ ንቅናቄው ስጋት የገባው የአብይዝም አገዛዝ አፍኖ ሊወስዳቸው ካሰባቸው ወጣቶች አንዱ እንደነበር ነብዬ ብጄ አሳምነው ጽጌ ነግረውናል።
በኋላም ከእነ ዘሜ ጋር ወጣቶችን በማሰልጠን መጠነ ሰፊ ተግባር ፈጽሟል። በአንድ ቃለ ምልልሱ ላይ ወደ አማራ ትግል ለምን እንደገባ ሲጠዬቅ #አታጋይ ጠንካራ #የዜግነት የፖለቲካ ድርጅት ባለመኖሩ ስለመሆኑ ሲናገር ሰምቸዋለሁ። ሚሊተሪ የሚቀድምበት ብሄራዊ ጉዳይ ነውና።
በዚህ ምክንያት ይመስለኛል #ባልደራስን የተቀላቀለው። ምንም እንኳን ባልደራስ በአደረጃጀቱ የአዲስ አበባ ቢሆንም። የአደረጃጀት መርሁ ፈጽሞ ባይፈቅድም። የሆነ ሆኖ ሶስቱ ዘሜ፤ ማስሬ፤ አስረሱ የሚያስደስት አንድነት፤ ብቃት እና ችሎታ ያላቸው ወጣቶች የአማራን ትግል ችግር በጥንቃቄ ቀድመው የተረዱ ወጣቶች ናቸው።
የአባት አደሩን ፋኖ #በማዘመን እረገድም #ባልተበላለጠ ተሳትፎ ተመክሯቸውን በእኩልነት ያጋሩ ድንቅ ወጣቶች ናቸው። በመሃል ክፍፍል የፈጠሩባቸው በተደራጁበት፤ በአደራጁትም የፖለቲካ ድርጅት #ለስኬት ያልበቁ፤ ማህበራዊ መሰረታቸውን ያጡ የአማራ ሊቃናት ናቸው። ይህ እጅግ የሚያሳዝን ግድፈትም ነው። በወቅቱ ጽፌበታለሁም።
በህግ - አስረሱ፤ በፖለቲካ - ዘሜ፤ በሚሊተሪ - ማስሬ በአህትዮሽ ቢሰሩ፤ ጥበብ እና ዲስፕሊን ተቀናጅተው ብቻ ሳይሆን ተዋህደው ምንኛ ታምር፤ ምንኛ ዕፁብ ትንግርት በሆነ ነበር። ለትውልድም #ዕሴታዊ ብሩህ ምዕራፍም ነበር። ጥንካሬውም ከብረት ቁርጥራጭ የተሰራ በሆነ ነበር። ሦስቱም የሚናፍቁኝ፦ የምሳሳላቸው ትንታጎች ናቸው። ትግሉን በቲም መምራትም ይቻል ነበር። ሦስቱም በእኩል #ስታተስ። እምየ ሲዊዘርላንድ ፯ ሊቃናት ናቸው በሚደንቅ ስልጡን ዊዝደም የሚመሯት።
የማስሬ እህትን አብይዝም ጫካ ለጫካ ከአራስ ልጇ ጋር ሲያሰቃያት ነበር። ይህ ጥቃት ነው ለማንኛውም የአማራ ልጅ። የአማራ ህዝብ በአቅሙ፤ በችሎታው፤ በዊዝደሙም በዬዘመኑ ተጠቂ ነው። ለሌላው ትንሳኤም #አንጋች እና #ማገዶም ነው። ይህ ሊቆረቁረን፤ ሊጎረብጠን ሲገባ እኛው እራሳችን የአቅማችን፤ የፀጋችን፤ የስጦታችን ተፃራሪ፤ ተዋጊ ሆነን ከተገኜን የትውልድ ተስፋ ይጠነዝላል፤ #ይወይባልም። ያለብን አሳር አነሰን ወይ??? ያለብን መታደን ጥቂት ሆነ ወይ? የለብን መገፋት ሁለት ፍሬ ነው ወይ??
በሃሳብ ልዩነት ይህን ያህል መገፋፋት ለአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ፈጽሞ አስፈላጊ አይደለም። የአማራ ህዝብ መከራ ገና ለብ አላደረገነም መሆኑን የሚያሳዩ ብዙ በጣም ብዙ ፋክቶች አሉ። በጥሞና ለሚመረምራቸው። የፈተናወቻችን የማሸነፍ አቅም ያለውም ከሌላው የተሻለ #የዲስፕሊን መርህን መከተል ነበር። መሻል፤ ተሽሎ መገኜት ለልቅና እና ልዕልና ያበቃል። የአማራ ሚሊዮን ልጆች ቤተሰብ አላቸው። ሥራ መስራት ይገባቸዋል። ይህ እንደ ወንጀል ሊቆጠርባቸውም አይገባም። በሰማይ መና መኖር ስለማይቻል።
ወላጆቻችን በየዘመኑ ከሚመጡ የኢትዮጵያ ገዢወች የሚወርድባቸው #ማት፤ #ምጣት ይበቃቸዋል። የፍትህ ትግል እራስን የሚቀጣ፤ እራስን የሚያሰጋ፤ ለእኛ ሳይቀር #የሚርድ ከሆነ ድካሙ ከንቱ ይሆናል። በአማራ ሞት፤ ስቃይስ ስንቱ መኖሩ አበበለት???
የሆነ ሆኖ በፍፁም፤ በፍፁም የአማራ ወላጆች፤ የአማራ ቤተሰቦች ሆነ መላ የኢትዮጵያ ህዝብ፤ ፓን አፍሪካኒስቱ ኃይል ሁሉ የአማራን የማንነት እና የህልውና ተጋድሎን #ሊፈሩት አይገባም። #ስጋታቸው ሊሆን አይገባም። ሰዋዊነት፤ ተፈጥሯዊነት ነው #አቨው እና #እመውን ለዊዝደም ያበቃው። ውርሳችን፤ ቅርሳችን የቀደሙት የጥበብ አውድማ ሊሆን ይገባል። ይህን የውስጥ ዶግማ ማድረግ ከእያንዳንዱ በግል፦ ከሁሉም በጋራ የሚጠበቅ ግዴታም ነው።
#ካለምንም #ቅድመ ሁኔታ #የካፒቴን ማስረሻ ወላጆች #ይቅርታ ተጠይቀው በክብር ይፈቱ ዘንድ እጠይቃለሁኝ። ሥርጉትሻ የትግሉ ደባል አይደለችም። ብዙ ዋጋ ከፍላበታለች። ለማስሬ ቤተሰቦች ቀጣይም በቂ ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል። እባካችሁ ብልህ ሁኑ።
ህዝብ አታስከፋ። ህዝብ ከፋኝ ካለ ጉዞው የፀቀደ ቢሆን እንኳን ህዝብ አድሞ በቃችሁን ሊል ይችላል። ጦርነት ሁሉን የሚያሳጣ ክስተት ነውና። በራስ ላይ ጥንቃቄ አለመውሰድ የተከፈለው መስዋዕትነትን ጎዳና ተዳዳሪ ያደርገዋል። በማስተዋል ያልተመራ፤ በትዕግስት የማይተዳደር ተጋድሎ ስኬቱን መተለም አይቻልም።
የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ኢትዮጵያ የፖለቲካ ድርጅት ተፈጥሮላት መመራት ከጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ የታለፈበትን መርዛዊ፤ በቀላዊ፤ ምቀኛዊ፦ ጨካኝ የልምድ መስመር ፈጽሞ ሊከተል አይገባውም። ስለማይጠቅመው። ልምዱ #የእርግማን ክምርም ስለሆነ።
የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ - ስክነት፦ #አደብ - ትንፋሹ፤ ጥሞና - ህይወቱ፤ ትዕግስት - መርሁ፤ ሰባዕዊነት - ህሊናው፤ ተፈጥሯዊነት - መርሁ ሊሆን ይገባል። #ቅንነትን ምራኝ ማለትም ይኖርበታል። በሌላ በኩል ግድፈትን ለማረም ፈጣን፤ ውዳሴን ለመቀበል ዳተኛ ሊሆንም ይገባል ተጋድሎው።
የገዘፈ ተልዕኮ ይዞ ከበቀል ጋር መዋዋል እራስን ያተናል። እኔ ገና ባልደራስ እና ህብር ኢትዮጵያ ከዘሜ፤ ከማስሬ እና ከአስረሱ ጋር ባህርዳር ላይ ሊመክሩ አህዱ ሲሉ ነበር ተው ያልኩት። በብዙ አመክንዮዊ ምክንያቶች። በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላም እረኛ ምን አለን ከጆሮው የሚያንጠለጥል የለም። ለዚህም ነው ዝምታዬ። ዝም ይሻል ከሆነ በማለት።
ቸር አስበን፦ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፦ ቀና እንሁን። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
18/12/2024
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ትዕግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።
ፍቅርም ሲያልቅ ትዕግስት ይሰደዳል።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ