ልጥፎች

ከማርች 9, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ብሄራዊ ጥሪ እና ዕድምታው ተነሆድዕቃው።

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  የዓለም አቀፍ የሴቶች  ቀን ብሄራዊ ጥሪ እና ዕ ድ ም ታ ው  ተነሆድዕቃው። „እግሮች እንዳይናወጡ አረማመዴን በመንገድህ አጽና“  መዝሙር ፲፭ ቁጥር ፭ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 09.03.2019 ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ። ·               ክብር ሆይ!  ቅንነተዎትን እባከዎት ለኦነጋውያን ምርኮኛ አያድርጉብን! መክፈቻ። ጤና ይስጥልኝ ውዶቼ እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ ወይ? የኢትዮጵያ ፖለቲካ የሴራ ፖለቲካ በመሆኑ ከዚህ የሴራ ፖለቲካ የምንሻገርበት ቀዳዳን ለመጠቀም ብልህነት እና ማስተዋል እንጂ ግትርነት ሆነ ጥርጣሬ አግባብ ስላልነበረ የኦህዴድን / ኦሮማራን / ጉዞ አቅርበን የእኛ አድርገን የማዬታችን ጉዳይ የተገባ ነበር። ይህም በመሆኑ ዛሬ ያለው መተንፈሻ ቧንቧ ተገኝቷል።   ልብን የገለጡ ቅንነቶች ሁልጊዜም በፈጣሪያቸው ዘንድ የተከበሩ ናቸው። እኔ እንደ ተዋህዶ ልጅነቴ የትኛውም አካል ዓላማ አለኝ ብሎ ሲነሳ በቅንነት ልቤን ንጹህ አድርጌ ነው የምቀበለው። ወይንም የማይመቸኝ ከሆነ ዝም ነው የምለው። አልደግፍም አልቃወምም። ለምሳሌ በግንቦት 7 ምስረታ ይሁን፤ በግንቦት 7 የኤርትራ ጉዞ ቅኑን ልቤ ለግሻለሁኝ። ለዛውም ያን ያህል ወጀብ በነበረበት ወቅት እነሱም አይዞሽ ሳይሉኝ።  ድርጅቱ በተመረዘመበት የስሜን ኢትዮጵያ ጠል ፖለቲካ አማካኝነት። እኔ ግን በምችለው ሁሉ ጉዲት እስክባል ድረስ ከዚህም ያለፉ የግል የሰላም ህወከቶችን አክሎ አሰተናግጃለሁኝ። ያን በማድረጌ ግንቦት 7 ፈተናው ሳያልፍ ሲቀር ...