የዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ብሄራዊ ጥሪ እና ዕድምታው ተነሆድዕቃው።
እንኳን ደህና መጡልኝ።
የዓለም አቀፍ የሴቶች
ቀን ብሄራዊ ጥሪ እና
ዕድምታው ተነሆድዕቃው።
„እግሮች እንዳይናወጡ አረማመዴን በመንገድህ አጽና“
መዝሙር ፲፭ ቁጥር ፭
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
09.03.2019
ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ።
ክብር ሆይ! ቅንነተዎትን እባከዎት ለኦነጋውያን ምርኮኛ አያድርጉብን!
መክፈቻ።
ጤና ይስጥልኝ ውዶቼ እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ
ወይ? የኢትዮጵያ ፖለቲካ የሴራ ፖለቲካ በመሆኑ ከዚህ የሴራ ፖለቲካ የምንሻገርበት ቀዳዳን ለመጠቀም ብልህነት እና ማስተዋል እንጂ
ግትርነት ሆነ ጥርጣሬ አግባብ ስላልነበረ የኦህዴድን / ኦሮማራን / ጉዞ አቅርበን የእኛ አድርገን የማዬታችን ጉዳይ የተገባ ነበር። ይህም በመሆኑ
ዛሬ ያለው መተንፈሻ ቧንቧ ተገኝቷል።
ልብን የገለጡ ቅንነቶች ሁልጊዜም በፈጣሪያቸው ዘንድ
የተከበሩ ናቸው። እኔ እንደ ተዋህዶ ልጅነቴ የትኛውም አካል ዓላማ አለኝ ብሎ ሲነሳ በቅንነት ልቤን ንጹህ አድርጌ ነው የምቀበለው።
ወይንም የማይመቸኝ ከሆነ ዝም ነው የምለው። አልደግፍም አልቃወምም።
ለምሳሌ በግንቦት 7 ምስረታ ይሁን፤ በግንቦት 7
የኤርትራ ጉዞ ቅኑን ልቤ ለግሻለሁኝ። ለዛውም ያን ያህል ወጀብ በነበረበት ወቅት እነሱም አይዞሽ ሳይሉኝ።
ድርጅቱ
በተመረዘመበት የስሜን ኢትዮጵያ ጠል ፖለቲካ አማካኝነት። እኔ ግን በምችለው ሁሉ ጉዲት እስክባል ድረስ ከዚህም ያለፉ
የግል የሰላም ህወከቶችን አክሎ አሰተናግጃለሁኝ። ያን በማድረጌ ግንቦት 7 ፈተናው ሳያልፍ ሲቀር አይጸጽተኝም። ቅንነት የሚጎዳው ተቀላቢውን እንጂ ቀላቢውን አይደለም። ስለምን እዮር አለና።
የሆነ ሆኖ ያን ያህል የምደግፈው እና የምሳሳለት
ድርጅት ተልዕኮ ብክል ሲሆን ደግሞ ወጥቼ ሞግቼዋለሁኝ። እሱ አቅም ቢኖረው እኮ እኔን አይደለም ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ሌላ ጥግ
ፍርፋሪ ፍለጋ ኢህአዴግን ባልፈለገ ነበር። እሱ እራሱ ግንቦት 7 አቅም ስሌለው እኮ አሁንም ኢህአዴግ ውስጥ ሄዶ
የውስጥ ሱሪ ነው የሆነው። እኔም በ2016 በፍጹም ተቆርቋሪነት ከ2017 ጀምሮ ደግሞ በሞጋችንት
ሞግቼዋለሁኝ።
ጸሐፊ ሚኪ አማራ እንደሚነገረን ፎርቹን መረጃን መሰረት
አድርጎ ሶስት ቀን ሚኒሊክ ቤተመንግሥት፤ ሁለት ቀን ለማ ቤተመንግሥት፤ አንድ ቀን ታከለ ቤተመንግሥት ሊቀምንበሩ ፕ/ብርሃኑ ነጋ
እንደሚያሳልፉ እያዳመጥን ነው። ለ3 ዓመት የሥራ ኮንተራትም በተቋቋሙት ሁለት ኮሚሽኖች መስራቾቹ በመደበኛ ገብተው
እዬሠሩ ነው። ይህ ሁሉ
የሰብዕዊ መብት ረገጣ እዬተካሄደም ጭጭ ስለሆነ አንድ ሌላ ጹሑፍ „ግንቦት 7 አረገ ወይንስ ሠረገ“ የሚል ጠንከር ያለ ጹሑፍ በድምጽ
አዳምጫለሁኝ።
ምን ለማለት ነው ጽናት እውነት ባለበት ቦታ መሆን
ይገባዋል። ሲደግፉም ሲቃወሙም በምክንያት። ከእኔ በላይ ስለ ለውጡ ትፍስህነት የጻፈም የሞገተም የለም። በዛው ልክም በጥዋቱ ነው
አብይ ሆይ! በሚለው አቤቱታዬ ወቀሳዬንም ያስከተልኩት። በጎ ሲሰሩ እያበረታታሁ እክል ሲገጥመው ለውጡ ደግሞ
የተገባውን ትችት አቅርቤለሁኝ። ያለፉት አንዳችም ነገር የለም።
· መቆያ።
በሌላ በኩል ግን በዚህን ያህል በመውረድ እንዲዝህ
በመሰለ ውሎ ጉዞው በሌላው ኢትዮጵያዊነት ጠረን በነጠፈበት ሴራ ውስጥ ለኦሮሞ ኢንፓዬር ሙሉ ለሙሉ
ይሰራሉ ዶር ለማ መገርሳ ብዬ አላሰብኩኝም።
በዛ በ18 ቀኑ የግንባሩ ስብሰባ መጨረሻ የሰጡት
መግለጫ እራሱ ብዙ አልሰራንበትም እንጂ ኢትዮጵያዊነትን እስከ 10 ዓመት አቅም የሚገናባ ዲስኩር ነበር። ልባቸው መሰበሩ፤ ትህትናቸው፤
ራሳቸውን ዝቅ አድርገው መቀረባቸው፤ የአንደበታቸው ጣዕሙ ሁሉ ዲያቢሎስ
አድርጎ ሥሎ አልሻህም ለማለት የሚያስችል አልነበረም። እርግጥ ነው ከነሻው የተቃወሙ ሰዎች አሉ። ያ የሁሉም ቢሆን እና ለውጡ ባይጀመር
ተብሎ ቢታሰብ ደግሞ መርግ ነገር ፊት ለፊታችን ይገጥመናል። የምንመካበት የተደራጀ እና የሚመጥን አቅም ፈጽሞ አልነበረንም፤ አሁንም
የለንም።
· ጭረት።
እኔ ጥርጣሬ የገባኝ የሚኒሶታ ስብሰባ ላይ የንግግራቸው
ቶን መቀየር ነበር ከእንቅልፌ ያን ጊዜ ያባነነኝ። የሆነ ነገር አሳከከኝ። እህቴም አሜሪካ ስሜቱ ተሰምቷት ይህንኑ
ነው ያለችኝ። ያ ሁሉ ሰው እያረገደላቸው በስሜን አሜሪካ „ለማ ለማ“ እዬተባሉ ሚኒያ ላይ ሲደርሱ ግን ሌላውን ዜጋ በማረራቅ እንኳን ኖራችሁልኝ ብቻዬን ነበርኩኝ አይነት ነበር የድምጹ ምቱ። በወቅቱም ጽፌበታለሁኝ።
ከዛ ቀጥሎ ብልጭ ድርግም በሚለው ክስተታቸው ለሳቸው
የሚደረገው ልዩ ጥበቃውን በተለይ የዓመቱ ምርጥ ሰው ሲባሉ ሳይ ምንድን ነው ነገሩ ብያለሁኝ ጽፌማለሁኝ። ምክንያቱም ዶር ገዱ አንዳርጋቸው
ያን ያህል ጥበቃ አልነበራቸውም እና።
ጠ/ሚር አብይ አህመድ ወደ ኤርትራ ራሴ ሄጄ ኦነግን
በድጋሜ አናግራለሁ ብለውን በስሜን አሜሪካው ጉብኝታቸው ወቅት ነገር ግን ዶር ለማ መገርሳ በአቋራጭ ወደ ኤርትራ የሄዱት፤ የተነጋገሩበት
ውሳኔ ዝግነት፤ እና የወለጋ ጦስ፤ የኦሮሞ ድርጅቶችን አክቲቢስቶችን
ለማሰበሳብ የሚያደርጉት ልዩ ጥረት እና ትትርና ሁሉ አቅምን የመገንባት ስለመሆኑ ይረዳኝ ስለነበር ባንድም በሌላም ስጽፈው ነው
የባጀሁት። ይህንንም በ አሉታዊ አላዬሁትም ነበር።
ነገር ግን በሚያሰባስቧቸው መንፈሶች ጫና በግንባሩ
ላይ በማካሄድ እራሰቸውን ከዛ ነፃ በማደረግ ፍላጎታቸውን ያስፈጽማሉ የሚል ዕሳቤ ነው የነበረኝ እንጂ እንዲህ ገማናቸው ኢትዮጵያን
የማፍረስ ማንፌስቷቸው በይፋ በ አደባባይ ይወጣል ብዬ አልተነበይኩም። ተጨማሪ አቅም ግን እንዳስፈለጋቸው እና ብአዴን መጫን እንዳሻቸው
አቅጣጫው አመለካች ነበር።
ከሁሉ በላይ የሰኔ 16 ጨምሮ የሐምሌው ዝምታ ሌላ
ነገሮችን ቢጫጭርብኝ በወደ አሉታዊ ተግባር ቀጥ ብዬ ለመሸጋገር አልደፈርኩኝም። በማስተዋል ነገሩን መመርምር ነው የፈቀድኩት። በመሰከረሙ
ጉባኤ ግን ይፋ የሆነ አማራን የማግለል ጉዳይ ሲከሰት ይህንኑ በዝርዝር ጽፌያለሁኝ።
አብሶ የአቶ ታከ ኡማን ንግሥና ለማጉላት የኦህዴድ
ጉባኤ ላይ ሦስተኛ ሰው አድርጎ መውጣት እሳቸውን ከፍ አድርጎ ለማሳየት የተሄደበት ደንበር፤ የክብርት ወ/ሮ ዳግማዊ ሞገስ መገፋት
እና የትራንስፖርት ሚር መሆን/ የአቶ ደመቀ መኮነን ለማስነሳት የነበረው ትግል፤ የአቶ ንጉሡ ጥላሁን ተለይቶ
መቀመጣል ወደ ኤርትራ
መሄድ፤ ለኦህዴድ ጉባኤ መወከል፤ ለኢህአዴግ ጉባኤ መግለጫ አንባቢ መሆን እነዚህ ሁሉ የዶር ለማ መገርሳ ፈቃድ ስለመሆኑ በዬጊዜው
ጽፈዋለሁኝ።
ሌላ ሳይጠቀስ የማይታለፈው በአቶ ጃዋር መሃመድ አቀባበል
ላይ ዶር ለማ መገርሳ በኦነግ አርማ ባሸበረቀ ስብሰባ ላይ ለመገኘት
መፍቀዳቸው እና ገፃቸው
እንዴት ብርሃን እንደሆነ ላስተዋለው የሚያስበልጡት ነገር እንዳለ ምልክት ይሰጥ ነው። የመስከረም 5 ዕድምታም ሌላው መራራ መከራ ነበር … የሻሸመኔው፤ የቡራዩ ሰብዕዊ
መብት ረገጣ እና ዝመታቸውንም ተቃውሜ ጽፌያለሁኝ።
አሁን ማህል ላይ ስለማልቋረጥ ጹሑፌን በመደበኛ የሚከታተሉት
ወገኖቼ ያውቁታል። ይህም ሆኖ እሳቸው እጅግ የምሳሳላቸው ሰው ናቸው። ቢያንስ ለኦሮሞ እናቶች ተቆርቋሪ መሆናቸው በአንድ እጅ ማጨብጨብ
ቢሆንም እንደ መልካም አጋጣሚ ነው የማዬው።
ስለሆነም ሲጠፉ ራሱ ጠፉብኝ ብዬ እጽፋለሁኝ። አመማቸው
ሲባል እጨነቃለሁኝ። በሁሉም ነገር የሚደረገውን ግፍ አድሎም አያለሁኝ። እታዘባለሁኝ። አብሶ በውጪ ዓለም እነሱ ብቻ ዕውቅና እንዲያገኙ
እየሰሩ መሆኑን በጥልቀት እረዳለሁኝ ይህም ሆኖ ግን ሚዛኑን የጠበቀ እሳቤ እይታ ነው የነበረኝ።
ክብር ለሳቸው ይሁን እና የወለዳቸውን ማህጸን ይበርከውና
ዶር አብርሃም አለሙ በተረጎሙት ጉዳይ ላይ ግን ከአንድ ሰብዕዊ፤ ተፈጥሯዊ መሪ የሚጠበቅ ሳይሆን አዶልፍ ሂትለር በኢትዮጵያ የተፈጠረ ያህል ነው የተሰማኝ። እሳቤው ፋሽዝም ነው። ትልሙም ሰካራም ነው።
በሌላ በኩል የአብይ መንፈስ መቀልበሱን አውቃለሁኝ። በእገታ ውስጥ መሆኑን እረዳለሁኝ። ነገር ግን ይህን ያህል ኢትዮጵያን ከሥሯ የሚነቀል
የፖለቲካ ሴራ እና ልበ እባብነት አብሶ በ አቶ ለማ መገርሳ ይኖራል ብዬ አለሰብኩኝም። ቅን ነኝ እና። የበዛ ገርነት እና ቅንነት
ነው ያለብኝ። ሰውን ማመን ጸጋዬ ስለሆነ። ስለሆኑም በሳቸው የአቋም መዝበጥ ከተጎዱት ሰዎች አንዷ እኔ ነኝ።
ጠ/ሚር አብይ አህመድ በሚመለከት አሁንም በድፍረት
እምናገረው የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚ/ር በነበሩበት ጊዜ እና ከዛም ኢንሳ ሲሰሩ በነበሩበት ጊዜ በአንድም በሌላም ስመረመርው ፍጹም
የሆነ የሰብ ተቆርቋሪነት ይታይባቸው እንደነበር ነው እኔ እምረዳው።
ግጥማቸውም በጽኑ የአገር ፍቅር ያለባቸው ስለመሆኑ
ነው የሚነግረን። ፍቅር አክባሪ በመሆናቸው በስጦታ ያምናሉ። ለኢትዮጵያ የዋሉ ሰዎችን ያከብራሉ። ዛሬ መንፈሳቸውን ሳስተውለው ድንቅ የሚባሉትን የኦሮሞ ደም ያለባቸውን ብቻ እዬነቀሱ ሲያወሱ አዳምጣለሁኝ።
ይህ ተፈጥሯቸው አልነበረም። ሰውኛ ግድፈት ስለመሆኑ ግን እቀበለዋለሁኝ። ፕርፌክሽን አልጠብቅም ሰው ናቸውና።
በኢትዮጵያዊነታቸው የሚኮሩ እንጂ የማያፍሩ ስለመሆኑ
ነው ይገባኛል፤ ማናቸውም ንግግራቸው ከልቤ አጥንቼዋለሁኝ። በበዛ ቅንነት እና በበዛ ሰው አማኝነት ውስጥ እንደ ሰከኑ ነው እኔ
እማስበው።
በመሪ ደረጃ ከጄ/ ፈንታ በላይ፤ ከዶር ኮነሬል ጎሹ
ወልዴ ጋር እኩል እማዬቸው ብቁ መሪ ናቸው። እሳቸውን የሚመጥን ተዝቆ የማያልቅ የሃሳብ አቅም ያለው ሊሂቅ የፖለቲካ አላዬሁም እኔ።
ይህ ይጎድላቸዋል እምለው የለኝም። ሰብዕናቸው ሙሉ ነው። የተረጋጉ ናቸው። የበዛ ትዕግስት አላቸው፤ አራት ዓይናማ ተናጋሪ እና
ሃርድ ወርከር ናቸው። ለሥራ ነፍሳቸው ከብረት ቁርጥራጭ ነው የተሠራው፤፡
በኦሮሞ ሊሂቃን ይህ የአማራን ትሩፋት ትውፊት መንፈሳዊ
ሥነ - ልቦና ከመፍራት የመነጬ መጫን በሚመለከት ጠ/ሚር በሆኑ ማግስት በጥዋቱ ስለዬሁም
ሳላድር ሳላውል ወቅሻቸዋለሁኝ። አለመሻላቸው፤ አለማሻሻላቸውን
በትናንቱ የባህርዳር ቆይታቸውም አዳምጫለሁኝ።
ከዚህ ባሻገር ባለው ግን አሁን አዲስ መረጃ እዬወጣ
ነው አቶ አዲሱ አረጋ ሁሉን እዬተገናብትነ ያለውን ተልዕኮ ለሚዲያ ባናወጣውም ሦስቱ ዶር ለማ መገርሳ፤ ዶር አብይ አህመድ ከንቲባ
ታከለ ኡማ ሌት እና ቀን ለኦሮሞ
አገርንት ታላቅነት እዬሰሩ ስለመሆኑ እዬተደመጠ ነው።
Ethiopia: ታከለ ኡማ በአዲስ አበባ የኦሮሚያን ልዩ ጥቅም ለማሳካት ቀን ከሌት እየሰሩ መሆኑን አቶ አዲሱ አረጋ ቂጤሳ በአንደበታቸው አረጋግጠዋል፡፡
እኔ እንደማስበው አብይ የሚፈለገው አቅሙ፤ ክህሎቱ፤
ተቀባይነቱ፤ ተዝቆ የማያልቀው የማድመጥ ብቃቱ፤ ትህትናውን የኢትዮጵያን
ህዝብ ህሊና አደንዝዞ ለታላቋ ኦሮሞ እንዲገብር እንጂ ወደውት አምነውት አይደለም። እነሱ ኢትዮጵያ የምትባል አገር አይደለም ማደግ
ሥሟን መስማት አይፈልጉም።
የጠ/ሚሩን ማናቸውንም አቅሙን መበዝበዝ እና ሞቦጥቦጥ
ግን ይሻሉ። ዶር ለማ መገርሳ እና አቶ ታከለ ኡማን ደግሞ ለማንገስ ተተኪ አድርጎ ለማቀርብ ነው እዬተሠራበት ያለው። አብሶ አቶ
ታከለ ኡማ ዶር አብይ አህመድ እግር ሥር እየሄዱ ያላቸውን ሁሉ መክሊት ቦጥቡጠው ታከለ ኡማን አጤ የማድረግ ሂደት ነው ያለው።
ምክንያቱም ከዚህ ላይ „ለማ
ፊቱ ኦሮሞ ይመስላል“ የፕ/ መራራ ጉዲና ፍልስፍና ጋር አጣምራችሁ
ውዴቼ እዩት … አብይ ፊቱ ኦሮሞ አይመስልም በእነሱ ፍልስፍና።
ማንም ድርጅት ህወሃትን ጨምሮ በአብይ መንፈስ የመገልገል
ፍላጎት አለው። ይህም አባ ቅንዬ ደልድለው ሌላው እንዲወደሰብት፤ እንዲነግሥበት እንጂ አብይ አንዲቀጥል አይደለም። ይህን ያጋለጠው
የሰኔ 16ቱ የምስጋና ቀን ነበር።
የኦህዴድ
ሞተር ~ ዶክተር አቢይ
ማን ናቸው?
ሞትን እኮ ያሰናዱት ለሳቸው ነው የራሳቸው ሰዎች
ናቸው ሊያስገዱላቸው የነበሩት። ፍትህ የምታለቅሰውም ለዚህ ነው። ዶር ለማ መገርሳ ከእንግዲህ አንድ የኦሮም ልጅ በፈለገው ወንጀል
እንዲቀጣ፤ እንዲጠዬቅ በህግ አይፈቅዱም። የመንጋ ሰልፈኞቻቸው ለሳቸው ጌጣቸው እና ክብራቸው ጋሻቸው እና መኩሪያቸው ናቸው።
በሌላ በኩል በ4 ወራት ውስጥ ስንት መነፈንቅል ነው
የተሰናዳላቸው ለጠ/ሚር አብይ አህመድ። ፈጽሞ ስለማያምኗቸው ነው ውጭ ሲወጡ ጋርዶቹ እራሱ ተልዕኮ የሚሰጣቸው። በሌላ በኩል እገታ ውስጥ ነው ያሉት። ስለዚህ እኔ ዶር አብይን እንደ ዶር ለማ እና እንደ ሌሎቹ ላያቸው ከእነሱ ጋር አብሬ ልወቅጣቸው
አልችልም። ሞታቸውን ቀን ከሌት አብረው እዬሠሩበት መሆኑ ይታወቃል።
በሌላ በኩል ዶር አብይ አህመድ ሊቀርቧቸው የሚገቡ
ሰው ኮ/ጎሹ ወልዴ ቢሆኑ ነው እኔ እምመርጣው። ከዛ ውጭ ያለው እሳቸውን ፈንቅሎ ለመቀመጥ ያደባ ነውና። ኮ/ጎሹ ወልዴ ግን ስልጣንም
አይፈልጉም በዛ ላይ ንጹህ እና ቅን ሰው ናቸው። በህሊናቸውም ዴታ ናቸው። ስለሆነም የመንፈስ ጥጋቸውን በእኒህ ቅን ሰው ልቦና
ውስጥ ቢያደርጉ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ቢጠቀሙ እንጂ አይጎዱም።
ይህ ማለት በሃሳብ ከድርጅታቸው ጋራ በሰፋ ልዩነት
ላይ ቢለያዩም ግን በፍቅር መያዝ ይኖርበታል። ያን የመከራ ጊዜ አብሮ ማሳለፍ ቀላል አይደለም፤ ነገር ግን ለሳቸው ቅኖች የሚሰጠቱን
የፍቅር አቅም ኢትዮጵያውያን አሳልፈው በስጠት ለኦሮማማ ለቅኝ ተገዢነት ለማሰለፍ ቆርጠው ከተነሱ በሳቸውም ላይ ቢሆን አይማረኛ ላልምርህ አይቀሬ
ነው። አሁን ግን ተስፋዬን ማሟጠጥ አልችልም። ‚ለተባረከች አገር የተባረከ ትውል‘ ሞቶ
ያስረኛል። እኔ ተስፈኛ ነኝ። ግን በሁሉም ዘርፍ አስተውሎት ያስፈልጋል። በግብር ይውጣም በጅምላም መጎዝ የተገባ አይደለም።
· የጠ/ሚር አብይ ብሄራዊ ጥሪ አቅሙ ስለማን ኢንቤስት እንዲደረግ ፈለገ።
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ የዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በዓል ላይ ያደረጉት ንግግር
ውዶቼ አሁን ወዳ ዋናው እርስ ጉዳዬ ልግባ። ጠ/ሚር
አብይ አህመድ ብሄራዊ ጥሪ አቅርበዋል። ለኢትዮጵያ ሴቶች። ጀግኑልኝ ከፍ ብላችሁ ከችግር በላይ ውጡ እና ልክ እንደ ንስር ማለት
ነው፤ አገሬን ወደ ሰላም አቅጣጫ ምሩልኝ እያሉን ነው። ቢሆን ጥሩ ነው።
ግን ለማን ተብሎ ነው አቅም
የሚባክነው? በግሪደር ስለሚታረሱት አራሶች? ወይንስ በሚሊዮን የሚቆጠሩትን ከቀዬ አፈናቅሎ በማያውቁት ሥነ
- ልቦና፤ በማያውቁት የአኗኗር ዘይቤ፤ በማያውቁት ሁኔታ ሰብዕዊ መብታቸው ተጥሶ ዲስክሪምነሽ ስለታወጀባጀው የጅጅጋ አካባቢ ወገኖች?
ወይንስ ለፖለቲካ ትርፍ የሚነገድባቸውን ነፍሶችን
መንፈስ አቃጥሎ አንድዶ ለማሞቅ ይሆን ሴቶች አቅም የሚያዋጡት? ቀድሞ ነገር ይህን እናድርግ ብለው ቢነሱስ ዋስትና አላቸውን አርበኛ
ሴቶች? አንድ የአገር ፓትርያርክ እኮ ማህበረ ምዕመኑን ማመን አቅቶት በበዛ ጭንቀት እና ፍርሃት በወታደር ጥበቃ ነው ነፍሱ ተንጥልጥላ
ያለችው? ቅዱስ ሲኖደስም እዬተደፈረ ነው በመንጋዎቻቸው፤ ለነገሩ ይህን የሚያስፈጽመው እራሱ ኦህዴድ ነው። ሌላ ዶር ፓትርያርክ
ማዘጋጀቱን እኔ አስተውላለሁኝ።
· አፍዝ አደንዝዝ።
አሁን አንድ ዲስኮር ዶር ብርሃነመስቀል አበበ ሳተናው
ላይ ተለጥፎ አነበብኩኝ።
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ(ቲም ለማ)
በኢትዮጵያ እያመጡት ያለው
ለውጥ በምስራቅ
አውሮፖ እና በሶቬት
ህብረት ከ1989
ጀምሮ ከተካሄደው
በብዙ መልኩ
ይመሳሰል (ብርሃነመስቀል አበበ)
በፈለገው ሚዛን ከአገር ሉዕላዊነት አይበልጥም ማናቸውም
ነገር። ርዕሰ መዲና የሌላት አገር እንፈጥራለን እኮ ነው ተጋድሎው። ኦሮሞ እንደ አገር እንድትቀጥል በይፋ በዓዋጅ
በማስጨነቅ፤ በመጫን ተተግቶ እዬተሠረባት ትርፍና ኪሳራ ሂሳብ የሚያስገባ ምንም ነገር የለም።
አውሮፓውያኑም እኮ ለዚህ የበቁት በብሄር ፖለቲካ
ሳይሆን በአይዲኦሎጂ ፓለቲካ ከውስጣቸው በመመራካቸው ነው። ጀርመን አሁን ለ አውሮፓ የጀርባ አጥንት ናት። ናዚም ማርክሲዝም
የተሞከረባት አገር ናት።
ግን በብሄራዊ ሰንደቅዓላማዋ አትደራደርም። አቅም አላቸው ዶር አብይ አህመድ እና ዶር ለማ መገርሳ
በልሙጡ በአባት አያቱ፤ በ እነ ኮ/ አብዲሳ አጋ ቅደመ ትውፊት የተጋድሎ ዓርማ ለብሶ ለሰከንድ የመቆም? ዶር ብርሃነ መሰቀል ዶር
ለማ መገርሳ ኢትዮጵያዊ ፖፕሊስት ናቸው ብለው እንደማይሞግቱኝ ነው። ለነገሩ አብይ „የኦነግ ወራሽ ነው“ እኮ ብለውናል። ሰው በዝምታ
አለፈው እኔ ግን ሞግቻለሁኝ። ለሳቸውም አያድርገው ለእኛም አያድርግብን ብዬ … አሁን ግን „የፈሩት ይወርሳል እዬሆነ ነው …
„
ራሱ ምዕራባውያኑ ያያሉ ያዳምጣሉ፤ ያስተርጉማሉ ነገ
የስደቱ ማዕበል እነሱን እንደሚውጣቸው ያውቃሉ፤ ስለዚህ ትርፉ ሆነ እውቅናውን በአፍ ጢሙን ለመድፋት አንድ ፋክስ ይበቃዋል።
ዕውነት ለመናገር ትእግስቱም፤ አደቡም፤ አቅሉም
የለም። በወራራ አገር አይገነባም። ይህን እንደ ውርስ እና እንደ ቅርስ በ21ኛው ምዕተ ዓመት ላድርገው ተብሎ መታሰቡ እራሱ እብደት ነው። እሺ የሚል የለምና።
ትርፍ ማለት ነፃነት ነው። አሁን ነፃነት ያለው የኦሮሞ
ደም ያለበት ብቻ ነው። ቢዘርፍ፤ ቢገድል አይጠዬቅም ኦሮሞ ድም ካለበት። ለመሆኑ ጠ/ሚር አብይ አህመድን በመርዝ የበከለው ሰው
ማን ነው? አንጂነር ስመኛው በቀለንስ ማን አስገደለው? የሰኔ 16 እኮ ከሶቆቃው ማግስት የህመምተኞች ጉብኝቱ እንዴት እና እንዴት
እንደነበር ልብ ብሎ ያሰተዋለው ነበርን? በረዶ ቀዝቃዛ ነበር። „ሁሉን ቢናገሩት ሆድ ባዶ ስለሚቀር“ ነው ዝም የተባለው። ያ ድንገተኛ
አደጋ ከውስጥ የገባ አልነበረም። መክሸፉ ጸጸት አይሎበት ነበር። ሰው ተገድሎ ተዘቅዝቆ የሚሰቀለብት መንፈስ
ማህበረተኝነት?
እነዛ የጋሞ ንጹሑን አማርኛ ቋንቋ ተናጋራችሁ ተብለው የታረዱበት፤ የተደፈሩበት፤ የተፈናቀሉበት ላይበቃ የረዷቸው ንጹሁሃን ወደ እስር የተጋዙበት እኮ ነው የኦዴፓ ታሪክ? ጭካኔ አረመኔነት ነው ገዝፎ የወጣው።
አሁን ንቅንቅ ብሎ ኦዴፓን ተቃውሞ ቢወጣ ህዝብ
ይሰቀላል። በሰላ ፋስ ይተረተራል፤ ይፈለጣል። ለህግ ከሆነ ተቃውሞ በሜጫ በዱላ ሲሆን ለህግ ቆሚያለሁ የሚለው አዴፓ ስለምን ዝም
አለ? እራሱ በህግ ጥሰተ ውስጥ ስላለ ነው። ገዢ ከሆነ ጀምሮ ያልጣሰው ህግ የለም ቻረት ጥሶ እኮ ነው ከንቲባ የሾመው።
ጭካኔን ፍልስፍና ህግ አይመራውም። ፋሺዝምን፤ ናዚዝምን፤
አፓርታይድን ህግ አልመራቸውምና። እኛም ጉዟችን ይህን ነው የሚነገረን።
እና ድምጽ አልባዎቹ ኢትዮጵያ ሴቶች ለዚህ ነውን
ጀግነው የሚወጡትን? ለጃዋርውያን ሜጫ? ለክርስትና ፍልሰት? ቀጣዩ ጉዞ እኮ ኢትዮጵያ ዕምነት አልቦሽም ልትሆን
ትችላለች? የኦህዴድ መንገዱ አይታወቅም። በውነቱ እኔ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ድርጅታቸውን ወይንም ንጹሃንን
ግፉዕን መምረጥ ያለባቸው ይመስለኛል? ሁለት አግር አለኝ ብሎ በ አንድ ጊዜ ሁለት ዛፍ መውጣት አይቻልምና …
· ስከንት፡፤
በሳቸው ትክሻ የሚጠራቀመው አቅም ቆም ብሎ እራሱን
መመርመር ይኖርበታል። አሁን በእኔ መንፈስ ያሉ እሳቸው ብቻ ስለሆኑ። ብቻቸውን
ከአቶ ካሳሁን ጎፌ ጋር ቁመው ይታዩኛል። ጤና ይሁኑ፤ ክፉ አይንካቸው እንጂ እኔ ዶር ለማ መገርሳን ከእንግዲህ እማያቸው በዛ ለዛ
እና ወዘና እይደለም። ከሰው በላይ ማንም የለም። በኢትዮጵያ
ህዝብ ጨከኑበት። ለሳቸው ሰው ማለት የኦሮሞ ደም ያለበት ብቻ ነው።
ያሾሟቸውን ከውጭ አስመጥተው እንኳን ብናያቸው ኦሮሞ ደም ያላባቸው ብቻ ናቸው።
የፈለገ ጠንካራ ይሁን፤ የፈለገ ብቁ ይሁን ከኦሮሞ ደም ውጪ ዕውቅና አያገኝም። ለቀጠሮም ዶር ለማ መገርሳን ለማግኘት ከዚህ ውጪ
የሚቻል አይመስለኝም። ወይንም ተዛኛው ወገን ያልሆነ …
ዜግነት ትናንትም ባዕት አልነበረውም ዛሬም ባዕት የለውም። ተፈጥሯቸውን ራሳቸው ገልብጠው ስላቀበሩት ዶር ለማ መገርሳ መታመንን ያህል ታላቅ የህሊና ሚስጢር እራሳቸው ክደው ስላሳዩን፤
መንፈሳችን ውስጥ የተቀመጠ ነገር ቢኖር የቀደመው ለዛቸው ብቻ እንጂ የሚቀጥል ተስፋ አይደለም። እንዲያውም
አፍሪካ ያሰጋታል የሳቸው የፖለቲካ መስመር። ቁልጭ ያለ ናዚዝም ነውና ዴሞግራፊ የህዝብ አሰፋፈርን ተዋፆ መቀዬር፤ ቋንቋን ለመጫን
መሯሯጥም …
በሌላ በኩል የዜግነት ፖለቲካ መርሃችን የሚሉት የሚከባከቡት
ይህን የተሸፈነ ገመና እንዲጋርዱላቸው ነው። እስፈጻሚ እና ተፈጻሚ ጋሻ ጃግሬ አድርገው ሸር አድርገው እያዞሯቸው የሚገኙት። አገር
እንዲገቡ ያደረጉት ደግሞ ውጭ ሆነው እንዳያሳጧቸው ነው።
ቆሞስ ኢንጂነር ስመኘው ሞት ግብጽ ጋር ሰላም ለማወረድ
ነው። የዜግነት ፖለቲካ አራማጆች ፈተና ከዚህ ላይ ነው። ከ አክቲቢስቶቻቸው ጀምሮ ትንፍሽ የለም። ስለ ኢንጂነሩ ደመከልብነት አንድም
የዜግነት ፖለቲካ ቤተኛ ሲያነሳ ሰምቼ አላውቅም። ዜጋ ግድ የሚል ከሆነ እሳቸውም ዜጋ ናቸውና።
ለውጡን በውጭም በውስጥም ባለ አማራ አቅም ካገኙ
በሆዋላ እሳቸው አጭዋች ነበሩ ዶር ለማ መገርሳ። ጨዋታውን ደግሞ አሳምረው አሽከርክረውታል። ከእንግዲህ ግን በፈለገው ቀመር የምትባክን
አቅም ሊኖር አይገባም ለኦሮማራ ለከሰረው ጥምረት።
ልባቸው አይገኝም። አርቀውናል፤ ጠልተውናል፤ አግለውናልም።
በሁለቱ የኦሮሞ ነገሥታት ለዶር ለማ መገርሳ እና ለኢ. ታከለ ኡማ ቀጣይ ንግሥና መባከን ተግ ማለት ይኖርበታል። አሁን የፕሬስ
ጉባኤ ግርዶሽ ስራበት ነው ልክ እንደ „ጣና ኬኛ፤ ልክ እንደ አባይ ኬኛ ልክ እንደ ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነው።“ በዶር ለማ መገረሳ
የተሰጠው ትእዛዝ? ግን ማነው ጠ/ሚሩ?
እንጥፍጣፊ ያለችው የተስፋ በጠ/ሚር አብይ አህመድ
ነው እሱንም አረጋጋ ተብሎ ነው አሁን ድንገተኛ ጋዜጣዊ መግለጫ እንዲደረግ የተፈለገው። ኦዴፓዎች ዘርክራኮች
ስለሆነ አቅሉም ስለሌላቸው በሌላው ደግሞ ይዘረግፉታል። በ አንዱ ሲሰፋላቸው በሌላው ይተረተራል። ተዘባርቀዋል እነሱ
እራሳቸው፤ ምዕራባውያን ልክ ናቸው አገር መምራት አይችሉም ያሉት። የተሰበሰበሰውን፤ የተከወነው ሁሉ የ የኢትዮጵያ አማላክ ትናጋቸው
ላይ ልኮ በጥዋቱ ሁሉም ይፋ ሆኗል።
ከአንግዲህ የ16ኛው መቶ ክፍለዘመን ወረራ ይፈጸምብኝ
ብሎ የሚወስን ደመነፍስ ካለ አብሶ ውጭ እዬኖረ ያ ሬሳ መሆን አለበት። የኦሮምኛ ቋንቋ ቢሆን ኢትዮጵያዊው
ሁሉ ግዕዝ ነው ማጥናት የሚያስፈልገው።
ታሪኩን፤ ትውፊቱን፤ ልባምነቱን ለማፈለስ ከሚታትር
ጋር መሰለፍ አያስፈልገውም። የጋሞ ምስኪኖች አማርኛ ተናጋራችሁ ነው የተፈጁበት ምክንያት። ወልቃይት ጠገዴ ላይም አማርኛ ተናገራችሁ
ነው ህውሃት ፍዳ የሚያስከፍለው። እሺታ ነገን ማመተብ ያስፈልገዋል።
አማርኛን ደቡብ ላይ ለመበወዝ እኮ ነው አሁን አዲሱ
የደቡብ ሽንሸና ኦነጋውያኑ የጀመሩት። ጤነኞች ቢሆኑ ምን በነበረ። ቋንቋ የ ዕውቀት ዘርፍ ነው። ግን ከ እነሱ አገር ንክኪ አለው
ነገር ሁሉ በጥንቃቄ መታዬት ይኖርበታል። አንድ መንደር በኦሮምኛ ተጠራ ብሎ እኮ ነው እርስተኛ ነን ልቀቁ የሚሉት። እርስተኝነት
በሁለመናናት ነው እንጂ በተናጠልነት አይደለም።
ስለዚህ ሚስጢሩን የኢትዮጵያ ህዝብ ለማወቅ ግዕዝን
በሁለተኛ ቋንቋነት አስተማሪ ቀጥሮ ያስተምር። በዚህ ላይ ግርባው ብአዴንም ራሱን ማጥፈት መቼስ ለምዶበት የለም ጠንካራ አቋም ሊኖረው
ይገባል። ግንቦት 20 ሞቶዬ ብሎ አማራን ሲአስጨፈጭፍ እንደኖረው ሁሉ አሁን ደግሞ ሌላ ማዕት ከመከተሉ በፊት ተግ ብሎ ጊዜ ሰጥቶ
ይዬው … ቀድሞ ነገር ለደከመበት ምን አገኘበት? ዕውቅና እናዳያገኝ ነው እኮ የተሠራበት …
እነሱ ተሰጥቷቸው የሚጠግቡ
አይደሉም፡፤ ፍላጎታቸው እራሱም አጋሰስ ነው አይጠረቃም ስስታምም ነው ምኞታቸው ሁሉ። የጥቅም ጥያቄ ወደ ባለቤትነት ጥያቄ ነው ዘው ብለው የገቡት። ሞቀላቸው፤
ደመቀላቸው። ሁለተኛ ቋንቋ አማራ ካስፈለገው የደጉን የጋሞን ያጥና … ደግነት እንጂ ጉለበተኝነት ህሊናን አይገዛምና።
እስካሁን በቅንነት ብዙ ነገር አጥተናል። በየዋህነት
ብዙ ነገራችን ገብረናል። ከእንግዲህ ግን ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚጠቅመው ምንድነው እንጂ ለኦሮሞ ህዝብ በተናጠል በልዩ ሁኔታ የሚጠቀምው
ምንድነው ለሚለው ጋሬ ፈረስ
መሆን ከጅልነትም በላይ እብደት ነው። ሁሉንም በማስተዋል መመርመር ያስፈልጋል።
· መደራጀት ነው ድል!
ሌላው አዲስ አባባ ጉዳይ ካለተደራጁ ድል የለም።
እቆረቆራለሁ የሚል ሁሉ ማቄን ጨርቄን ሳይል አዲስ አበቤ የሚል ፖለቲካል ፓርቲ ያደራጅ እና ፊት ለፊት ይፋለም። ብሄር አልቦሹ አዲስ አባባ ከምርጫ በኋዋላ መኖሪያ የለውም። ለምርጫ ደግሞ የግድ መደራጃት ያስፈልጋል።
የዜግነት ፖለቲካ የሚቀነቀነው ለኦነግ ፍላጎት ስኬት
ነው። ለዛ አገር አፍርስ ቡድን ለም መሬት ለመሆን ነው። ስለዚህ አቅም አለኝ የሚል ሁሉ ውጭ አገርም ፓርቲውን አደራጅቶ ይታገል።
ግን አደራ ከግንቦት 7 ጋር ንክኪ እንዳይኖር ግንቦት
7 የነካው ሁሉ ስለሚፈርስ፤ ስለሚናድ። ቀስተዳመና ሲጠጋ ቅንጅት ከሰመ፤ የአትዮጵያ አርበኞች ግንባር እና የ የአቶ ሞላ ድርጅት
ጋር ልጣመር ነው ብሎ ሲጠጋ ቲፒዴኤም ከሁለት ተተረተረ፤ የኢትዮጵ
አርበኞች ግንባር ውህደትም ፈራረሰ፤ አገር ውስጥ የሚታገል አለኝ ሲል ሽግግር መንግሥት ነኝ ብሎ ሲያስብ የኢንጂነር ይልቃልን ሰማያዊውን ከሁለት ተሰነጠቀ፤ አገር ሊገባ ሲያስብ ቀሪው ሰማያዊ ፈርሻሉሁ አለ፤ ቀደም ብሎም አገራዊ ንቅናቄው በራሱ ጊዜ ተንዶ ፈራረሰ አሁን ደግሞ ቤተ መንግሥት ውሎ ሲመጣ ኦህዴድ እንዲህ
አይሆኑ ሆኖ ተዝረከረከ … ይኸው ነው ዕጣ ፈንታው … የማያሳካለት ህልመኛ ሁልጊዜ እንደወደቀ ነው … ይደክማል ግን ካለ ቅብዕ
አይሆንም …
ስለዚህ ራሱን የቻለ አቅም ያለው ድርጅት መፍጠር
ለአዲስ አባቤዎች ግድ ይላችሁዋል አንጋጣችሁ ችሮታ ከምትጠብቁ፤ እናንተም ከፉክክር ወጥታችሁ አደብ ያለው ነገር በሥርዓት እና በመርህ
መፈጸም ትቻላለችሁ። በስተቀር ግን ራስ ገሊቦ ይሆናል … ድርጅት በእጅጉ ያስፈልጋል … ለአዲስ አበቤዎች ይህንንም እኔ ዛሬ አይደለም
የጻፍኩት። መስከርም ላይ ጉዳዩ መነሳት አሁን የለበትም በሚባልበት ጊዜ ነው የጻፈኩት። ዕውነት ወገኗ ራሱ
ዕውነት ነውና።
በሌላ በኩል አይጸጽትሽም ወይ የሚል መልዕክት መጥቷለኛል።
እንዴ? ምኑ ነው የሚጸጽተኝ? ያ ድጋፍ ባይኖር እኮ ህወሃት ጓዙን ጠቅልሎ መቀሌ አይመሽግም ነበር። የነፃነት አርበኞች አይፈቱም
ነበር። ሞትም ዕድሜ ልክ እስራትም በሌሉበት የተፈረደባቸው ነፃ አይወጡም ነበር፤ ኤርትራ እና ኢትዮጵያ ቁጭ ብለው ለመነጋገር አይበቁም
ነበር፤ ሴት ፕሬዚዳንት አይኖረንም ነበር፤ ሴት 50% ካቢኔ ላይ አትኖርም ነበር … በዚህ ጤነኛ መንፈስ ጤናዬ ሙሉ ለሙሉ ተመልሷል።
በተጨማሪም ይህን መሰል አዲስ የሚዲያ ገብያ አገር
ላይ አይታይም ነበር፤ የኢትዮጵያ ደማቁ አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ጎላ ብሎ
ደምቆ ኮራብሎ ደልደል ብሎ ከጎንደር ከጎጃም ባለፈ በመላ ኢትዮጵያ አይውለበለብም ነበር … ተፎከካሪዎችም ሲረጋገሙ ባጅተው በአንድ
አዳራሽ አይታደሙም ነበር … ይህን ትርፍ ተንተርሶ ካሳ ክፍሎ ነው ችግሩ …
አገር ንደን አዲስ አገር እንገንባ ነው ጦርነቱ፤
ተጋድሎው የአማራ ተጥሶ ድልሙ ጉልላለቱም ለኦነግ ይሁን መባሉ ነው እንጂ ሂዳቱማ አትራፊ እኮ ነው የነበረው። ያን ጊዜ በርትተን
ባናግዘው እንደለመደብን በጥዋቱ ተቀቅልብሶ ሌላ ድርብ መስዋዕትነት ያስከፍል ነበር። አሁንም የሚፈለገው ይኼው ነው።
ጠለፋው እና እገታው ነው ፍዳ ያመጣው … ኦሮማራ
አቅሙ ተጠለፈ በጃዋርውያን … ጥሪቱን ሁሉ ተዘረፈ፤ ለዛውም የመንፈስ
… ወንድ ጠፋ … ያው አንስቶችን አድማጭ ስሌለን። እኔማ እኮ ለብርቱ የሰባዕዊ መብት ተሟገች በጥዋቱ ነበር የተናገርኩት
… አሁን እሱም ጮኺ ሆኗል …
የሆነ ሆነ ለዛ መልካም ጊዜ ዶር ለማ መገርሳን አመሰግናቸዋለሁኝ።
ዘግይተው መርዛቸውን መግለጣቸውም ለበጎ ነው። ብዙ አትርፈንበታልና። ቀጣዩ ደግሞ አሸናፊው ኢትዮጵያዊነት ይሆናል። ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ
የተፈጠረ ሚስጢር ነውና።
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ