#እኛዊነት።
እንኳን ወደ ከበቡሽ ሚዲያ በሰላም መጡልኝ። " የሰው ልጅ መንገድን ያዘጋጃል እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል። " ( ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱ ) ዕለተ ሮብ ማዕዶተ ተናኜ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ሕይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። # እ ኛዊነት ። እ ኛዊነት ትውፊት ነው። እኛዊነት ሰዋዊነት ነው። እኛዊነት ተፈጥሯዊነት ነው። እኛዊነት መኖር ነው። እኛዊነት ትውልድ ነው። እ ኛዊነት አደራ ነው። እኛዊነት አገራዊነት ነው። እኛዊነት መርኃዊነት ነው። እኛዊነት ብሔራዊነት ነው። እኛዊነት የጀገነ ነው። እ ኛዊነት ኃላፊነት ነው። እኛዊነት ተጠያቂነት ነው። እኛዊነት ቤተሰባዊነት ነው። እኛዊነት እሸታዊነት ነው። እ ኛዊነት መታመንን መቀበል ነው። እኛዊነት ዕውነትን ማፅደቅ ነው። እኛዊነት ቤተኝነት ነው። እኛዊነት የመሆን ጎዳና ነው። በ እኛዊነት ውስጥ እኔዊነት በአብሮነት በህብራዊነት አለ። እኛዊነትን የካደ ነፍስ እኔዊነትን ሰርዞታል። አንድ ሰብዕና ብቻውን አልቆመም እና። ያ እኛዊነትን የካደ የከዳ ሰብዕና እኔነቱ በተፈጥሮ ፀጋ ውስጥ የተገኜ ነው። ካለ ሴት ወይንም ካለ ወንድ አልተፈጠረምና። መ ኖርን ያኖረው ፅንሰት ከተፀነሰበት ዕለት ጀምሮ በአብሮነት ፏፏቴ ይበቅላል። እናት መኖርን ስታኖር ምግብ ያስፈልጋታል። ምግቡ በህብራዊ...