#እኛዊነት።

 

 

 እንኳን ወደ ከበቡሽ ሚዲያ በሰላም መጡልኝ።

"የሰው ልጅ መንገድን ያዘጋጃል

እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።"

(ምሳሌ ፲፮ ቁጥር )

 

ዕለተ ሮብ ማዕዶተ ተናኜ

በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና

በቢሆነኝ የተብራራ ብራ

በሰብለ ሕይወት አዝመራ

ለራህብ የሚራራ።

 


 

#ኛዊነት

 

ኛዊነት ትውፊት ነው።

እኛዊነት ሰዋዊነት ነው።

እኛዊነት ተፈጥሯዊነት ነው።

እኛዊነት መኖር ነው።

እኛዊነት ትውልድ ነው።

 

ኛዊነት አደራ ነው።

እኛዊነት አገራዊነት ነው።

እኛዊነት መርኃዊነት ነው።

እኛዊነት ብሔራዊነት ነው።

እኛዊነት የጀገነ ነው።

 

ኛዊነት ኃላፊነት ነው።

እኛዊነት ተጠያቂነት ነው።

እኛዊነት ቤተሰባዊነት ነው።

እኛዊነት እሸታዊነት ነው።

 

ኛዊነት መታመንን መቀበል ነው።

እኛዊነት ዕውነትን ማፅደቅ ነው።

እኛዊነት ቤተኝነት ነው።

እኛዊነት የመሆን ጎዳና ነው።

 

እኛዊነት ውስጥ እኔዊነት በአብሮነት በህብራዊነት አለ። እኛዊነትን የካደ ነፍስ እኔዊነትን ሰርዞታል። አንድ ሰብዕና ብቻውን አልቆመም እና። እኛዊነትን የካደ የከዳ ሰብዕና እኔነቱ በተፈጥሮ ፀጋ ውስጥ የተገኜ ነው። ካለ ሴት ወይንም ካለ ወንድ አልተፈጠረምና።

ኖርን ያኖረው ፅንሰት ከተፀነሰበት ዕለት ጀምሮ በአብሮነት ፏፏቴ ይበቅላል። እናት መኖርን ስታኖር ምግብ ያስፈልጋታል። ምግቡ በህብራዊነት ቅብብሎሽ የበቀለ ነው። ዳቦ እንውሰድ። ስንዴ፤ ገብስ፤ ማሽላ ሊሆን ይችላል። ማን አመረተው? ቀድሞ ነገር ምግብ ለመሆን ማን ፈለሰመው? ማን ሃሳቡን አፈለቀው? ከፈለቀስ በኋላ ከስንዴ ዳቦነት እስከ ኬክነት በምን ሂደት አለፈ? ልብሱን፤ ማጣፈጫውን፤ ውኃውን፤ ነዳጁን፤ኤሌትሪኩን፤ እሳቱን፤ ኩራዙን፤ ፋኑሱን፤ ማረሻውን፤ ሞፈር ቀንበሩን፤ ወዘተ ወዘተ

ንድም ቅንጣት የመኖር ጥበብ፤ የመኖር አኗኗሪ ግብ ሁሉ ከሰው ሰው፤ ከትውልድ ወደ ትውልድ በቅብብሎሽ የበቀለ ነው። ይህን ጥሰህ የእኔ የእኔ ብትል ተፈጥሮን በፍራክሽን ብትሸነሽነው የካድከውም በክህደት የሰመጥከውም አንተው ነህ። ይህ ጥበብ የገባው ማህበረሰብ ነው ላቂያ የሚባለው። ላቂያነት እራስን ማወቅ ነው። እራስን ፈልጎ ማግኜት ነው።

ማን ነኝ? በማን ውስጥ ተገኜሁ? እንደምን ተፈጠርኩኝ? እንደምን ተገኜሁኝ? በምን ሂደት አለፍኩኝ? የሚል ጭምት ሰብዕና ትርምስ የለበትም። የብቻው የሆነ ቅንጣት ነገር የለውም። አሁን እኔ እፅፋለሁኝ። በአማርኛ ቋንቋ። ይህ ትውፊት የሸለመኝ ሥጦታ ነው። አማርኛ ቋንቋ ባይፈጠር አልፅፍም። ኮንፒተሩም ባይኖር አይዘምንም። ፌስቡኩም ካፒቴን ባይሆን አንገናኝም። በምድር ውስጥ የእኔ የሚባል ነገር የለም። ኑሮም አያውቅም። ይህ የእኔ ፍልስፍና ሊከብድ ይችል ይሆናል። ግን መርኃዊም፤ ዕውነትም ነው።

ንድ ሰው ብቻውን መኖርን ማኖር አይቻለውም። ይህ ቅዥትን በማህበረ ኦነጉ ኦህዴድ ሳይ ይገርመኛል። ገና ለፅንሰት ያልበቁ መሆናቸውንም አያለሁኝ። ዛሬን ማን ሰጣቸው? ዛሬንስ ማን አኖረላቸው? መልስ የላቸውም። ባለመፈጠራቸው ውስጥ ያለው የሃሳብ ድህነት ለግርድነት እንኳን አይበቃም። ለዚህ ነው ተፈጥሮን እዬገደሉት የሚገኙት። አለመታደል።

ላኔታችን የሚመራት እኛዊነት ነው። ድርጅት ሲፈጠር እኛዊነት ነው። ድርጅት ፈጥረህ አብሮነትን፤ ህብራዊነትን እኛዊነትን ሰርዘህ አይሆንም። ቅንጣት ነገር ብቻውን አይበቅልም፤ አይፀድቅም፤ አያሰብልም። ምንም ነገር። በአንዱ ውስጥ ሌልኛው፤ በሌልኛው አንደኛው በመስተጋብር ተዋህደው ነው የተፈጠሩት የሚፀድቁትም።

 

ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

07/04/2021

ጎዳናዬ ሰውኛ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።