ጥበብ ማለት ነገን ማሰብ ነው።
ጥበብ ማለት ነገን ማሰብ ነው። „መባህን አግባ አስበህ ስንዴህን አግባ፤ የተቻለህን ያህል መሥዋዕትነትህን አብዝተህ አቅርብ።“ መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፴፰ ቁጥር ፲፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ 04.10.2018 ከጭምቷ ሲወዘርላንድ ውዶቼ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው የኢህአዴግን ጉባኤ ስከታተል። የእህት ነው የሚባሉትንም የእነሱንም እንዲሁ። የአንዳቸውንም ጉባኤ ተከታታይ አላውቅም። እንቅልፍ ክኒን ቫልዬም መግዛት አያስፍልገኝም ነበር። ለውሸትም መጋዝን ቤት አልነበረኝም። አሁን የሁሉንም ተከታትያለሁኝ። ትግራይ ላይ አንዲት ቀና ሴት ወደ ክልሉ ምክር ቤት ተመርጠዋል። ጤነኛ መንፈስ ነው ያላቸው። ከሁሉም ትግራይ ያሳዝናል። አሁንም በገመድ ተጎተት እዬተባለ ነው። ለውጥ ናፈቀው ግን ተገደበበት። ወደ እርእስ ጉዳዬ ስገባ ማሰብ ጥሩ ነገር ነው። ጥበብ ማለትም ነገን ማሰብ ማለት ነው። ለዛሬ መገኘት ትናንትን መርሳት ማተበ ቢስነት ነው። ዛሬን ለማግኘት የቀድሞው ጠ/ ሚር የነበሩት አቶ ሃይለማርያም ደስአለኝ ያደረጉት መልካም ነገር ሊረሳ አይገባውም። በሌላ በኩል ም/ጠ ሚር አቶ ደመቀ መኮነን የወሰዱት እርምጃ ደግሞ ራስን መስጠት ብቻ ሳይሆን የአማራን ህዝብ ታሪክ፤ ትውፊት፤ ትሩፋት፤ ዕድል፤ የሥነ - ልቦና ልዕልና፤ ተጋድሎ፤ እና ትንሳኤ አሳለፍው ነው የሰጡት። የድርጅቱንም የቀድሞውን ብአዴን የዛሬውን አዴፓንም ዕንቁ ተስፋውን አሳልፈው ፈቀደው ነው የሰጡት። ማድረግ የሚቻለው ሥልጣን ሲኖር ነው። ክብሩ መጎሱ የተለዬ ነው። ያን አልሻም ማለት መቼም ለኢትዮጵያ ፖለቲካ ድርሳን ያጽፋል። ይህን ዕድልን አሳልፎ መስጠት ለዛውም ሲነሪቲው እዬፈቀደ፤ መርሁ እዬፈቀደ ፈጽሞ በህልም...