#የጭምቱ የጓድ ገዛህኝ ወርቄ ሌጋሲ በህይወት እያለሁ ይደገማል ብዬ አላስብም ነበር። ግን ሆነ።
#የጭምቱ የጓድ ገዛህኝ ወርቄ ሌጋሲ በህይወት እያለሁ ይደገማል ብዬ አላስብም ነበር። ግን ሆነ። • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ወታደራዊ ሥልጠና ላይ መሆናቸውን አስታወቁ https://www.bbc.com/amharic/articles/c9ly0pxpvz7go #ምዕራፍ ፳። የፃፍኩት ታሪክ ነው። ለዛውም የማይገኝ ታሪክ። ማንበብ እና መመርመር የትውልዱ ተግባር ነው። የአገሬን ዜና ያልተከታተልኩ የማንን? ማዶ ማዶ የሚይ ሰብዕና የለኝም። መነሻዬም መድረሻዬም የአገሬ የኢትዮጵያ ውስጥነት ነው። ትችት ቋት አይገፋም። ታሪክን፤ ሂደትን፤ ተጨባጭ ሁኔታን በቅንነት፤ በአውንታዊነት ማዬት፤ ሲያስፈልግም መሞገት ይገባል። ደንበር ለየትኛውም ምልከታ ሊሠራ አይገባም። ፔጁ የእኔ ነው። የምደክምበት። እኔ ደግሞ ተንጠልጣይ አይደለሁም የራሴ ጎዳና ያለኝ ሴት ነኝ። የትኛውም ሰብዕና የእኔን እኔነት ሊያዝ፤ በፈለገው አቅጣጫ ሊቀይስ አይችልም። ነፃነቴ ውድ ናት። የማውቀውን ዕውነት ነው የፃፍኩት። #ጠብታ ። ገርሞኛል። ደንቆኛልም። እኔ በህይወት እያለሁኝ እንዲህ የጭምቱ ጓድ ገዛህኝ ወርቄ #ሌጋሲ ይደገማል ብዬ ፈጽሞ አስቤው አላውቅም። #እንዲህም ሆነ ……? ጥዋት ቀዳሚ የልማዴን ከከወንኩ በኋላ ዓለም፤ ኢትዮጵያ አፍሪካ እንዴት እንዳደሩ ዜና ፈላልጌ አነባለሁኝ። እኔ የቴሌቪዥንም ፍቅረኛ አይደለሁም። አንድ ዓመት ሆነኝ TV ከሌለኝ። ከማድመጥ ማንበብ ይቀናኛል። #ጓድ ገዛህኝ ወርቄ ጎንደር ከተማን ከጦርነት #ዓውድማነት ታድገዋታል። ጓድ ገዛህኝ ወርቄ የጎንደር ክፍለ አገር የኢሠፓ ፩ኛ ጸሐፊ ነበሩ። ጎንደር ከሁለት ሲተረተር...