ልጥፎች

አቶ ዳውድ ኢብሳ የኢትዮጵያን መንግሥት እያስደገደጉት ነውን?

ምስል
አቶ ዳውድ ኢብሳ  የኢትዮጵያን መንግሥት እያስደገደጉት ነውን? „አንተን በፍራሃት ወደ ቅድስናህ መቅደስ እሰግዳለሁ።“ መዝሙር ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፯ ከሥርጉተ©ሥላሴ 14.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። አቶ ካሳሁን ጎፌ መግለጫን የገባኝን ያህል ስጥፈው ቆፍጠን ያለ ነው ድፍረቱ ከኖረ ብዬ ነበር። አቃለው አሳንሰው ሲዩትም ደግሞ አይደለም ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለመካከለኛው ምስራቅም አስጊ ነው ብዬ ነበር። የአፍ ወልምታ ለተባለውም ያልኩትን ብያለሁኝ። ሲጀመርም እኔ የአቶ ዳውድ ትምህክት መሰረት እንዳለው፤ በቀላል መታዬት እንደሌለበት ሞገደኛ እና ከባድ ውሳኔ ስለመሆኑ ገልጫለሁኝ። የ5ቱ የ ኦሮሞ ድርጅቶች ውሳኔም ከዚህ ጋር የሚዋደድ ነው። አሁን ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ በስኳር ፖለቲካ ኢትዮጵያ እንደ ገቡ አዳመጥኩኝ። ፍቅሩን ያሰንብትላቸው እንጂ እፍ ብለዋል። የጣሊያኑ መሪ ወደ ዛው አቅንተው እንደ ነበርም አድምጠን ነበር። እና ተመለሱ ይሆን ወይንስ ምጥዋ ላይ ተበለስ ጋር? ከዙፋን አስወርዶ በጥድፊያ ያሰመጣው የኤርትራን መንግሥት ምን ቢኖር ነው ብለን ማሰብ ግድ አለን። ደረታቸው ነፍተው ሲናገሩ የሰነበቱት አቶ ዳውድ ኢብሳ በሦስተኛ አገር ሽምግልና ከልሆና በጅ አልልም ያሉ ይመስላል። ሌላ ከሚመጣም ወዳጃቸው አገር ብትሆንላቸው ይሻላቸዋል። ነገም በ አገርነት እንቀጥላልን ባይም ናቸው። ወጣት መሪም ታች ካለ በቂ ነው ብለዋል። ምርጫው የሳቸው ነው። ማን ደፍሮ ይናገራል ጭጭ ረጭ ሆኗል። ከእትጌ ኤርትራ ቤት ዘው ከተባለ መውጫ የለም፤ ወይ መዋጥ ወይ አብሮ መስመጥ ነው … ግን ኢትዮጵያን ማን ነው እዬመራት ያለው? በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ኤርትራ ታጣዋለች ተብሎ የታሰበው ረጅም እጅ ይሁነኝ ተብሏል። ኦዴፓ

መቼ ነው የህወሃት መኳንነት ሃፍረት የሚባል የሚሰራላቸው?

ምስል
አለማፈረን ግባ በሉት ¡ „አህዛብ ለምን ያጉረመርማሉ?“ መዝሙር ፩ ቁጥር ፪ ከሥርጉተ ሥላሴ 13.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። የእንጀራ ልጆች ፍዳ! ጫጫታ በረከተ በማህበረ ተጋሩ ሠፈር። መቼም እኔ ከወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌሰቶ ጋር ተብጥብጦ የተጋቱ አለማፈር ብቻ መሆኑን እዬተረዳሁኝ ነው። እንዲያውም አያፍሩም አሁን አዬር መንገድ ላይ ባለው ገመና። የተጠናከረ የሎቢ ተግባር እንዳይካሄድ እኮ መቼም ኢትዮጵያ የሚል አንድ ተቋም ብቻ እሱ ስላለ ነው እንጂ የመብት ረገጣው እኮ የኦሽትዝ ግፍ ያዬለበት ነው። ሰብዕዊ መብት ይከበር የሚሉ አገሮች እኮ የ አዬር መንገዱን አሰራር እንደጸዬፉት ማድረግ ይቻላል። ግን ከ አዬሩ ላይ ያለው ንጹህ ብሄራዊ ሰንድቅ አላማ ቃልኪዳን ስለሚይዝ ነው ዝም የሚባለው።   አሁን እዛ ያሉ የተጋሩ ሃላፊዎች ሳር ቅጠሉ እሱ በእሱ ሲሆን ትንሽ ብጣቂ ነገር እንዴት ልብ አይሰራላቸውም? አያፈሩበትም፤ በር ስትከፍትም፤ ኮሪደርም፤ መጸዳጃ ቤትም፤ ካፍተሪያም፤ ሜዳውም ላይ ሁሉም ቤተ ተጋሩ ሲሆን አይቀፍም! ህሊና ያለው ጥፍር ላይ ነውን?  በሩ ራሱ እኮ ጠረኑ እነሱን እነሱን ነው የሚለው። ወለሉም እንዲሁ ነው። በእነሱ ዘመን እኮ ነው ሰው እያዬ እዬሰማ እግሩ የተቆረጠው ምክንያት ተፈልጎ። በእነሱ ዘመን ነው ወንድ ልጅ የተንኮላሸው፤ በእነሱ ዘመን ነው ዘራፋ እንዲህ ባህል የሆነው፤ ምን ያልታዬ መከራ አለና። ቃለ ምልልሱ ሲታይ ጠያቂውም ተጠያቂውም ዘገባ አቅራቢውም ዘገባውን አስተላላፊውም ያው ነው ቤተ ተጋሩ። እዛ አዬር መንገድ አንድ ነገር ሲፈጠር አንድ ሰው ለዬት ያለ ለማግኘት ይችግራል። በውነት ይቸግራል። በጣም ጸያፍ ነገር ነው። ዋ! ነው የሰማይ ጦሮ የታዘዘ ዕለት። አሁን

በለው! የአቦ ሌንጮ ለታ ፈረስትነት።

ምስል
የአቶ ሌንጮ ለታ የኦሮሞ ፈርስት ፈገግታ። „አቤቱ የሚያስጨንቁኝ ምንኛ በዙ፤ በእኔ ላይ የሚቆሙት ብዙ ናቸው።“ መዝሙር ፫ ምዕራፍ ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ 13.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ቢስ አይይብን ዶር ለማ መገርሳ እና ዶር አብይ አህመድን ብለናል። የአፍ ሳይሆን የውስጥ ወልምታ እንዳይኖርባቸው አብዝተን እንጸልያለን። ውዶቼ እንዴት ናችሁ ደህና ናችሁ ወይ። ባለፈው አንዲት ሴት በተፈጥሯዋ አንድ ጡት አብቅላ በህልሜ አዬሁኝ ብያችሁ ነበር አይደል? እህቴ ስተፈታልኝ ኢትዮጵያ መከራዋን ተሻግራ አንድ የምትሆንበት ዘመን ይመጣል አለችኝ። እኔም እንደ አፍሽ ያድርግልን አልኩኝ። ዛሬ ስለተፈሪው ማንነት ስለ ኢትዮጵያዊነት ትንሽ ማለት ፈለግሁኝ። አንድ የጠራ ነገረ ማወቅ ፈለግሁኝ። ፍራንከፈርት ከዶር አብይ አህመድ ጋር ሥብሰባ እንዳለ አዳምጫለሁኝ። ወደ ፍሬ ነገሩ ከመሄዴ በፊት ስለፍራንክፈረት የነፃነት ትግል ዓውራነት፤ ለዴሞክራሲያዊ ተጋድሎ አዕምድነት ትንሽ ማለትን እሻለሁኝ። እንግዲህ ፍራንከፈረት የፖለቲካ ጭንቅላት አባ ወራዎቹ ያሉበት ቦታ ነው። አባወራ ነው ያልኩኝ እማ ወራ ሴት ፖለቲከኞች በአላዛሯ ኢትዮጵያ ስለማይታሰብ ነው፤ አብሶ ውጪ አገር ያው መፈናፈኛ የለም። ይቀኑብናል ወንዶቹ። ለምን? ልባቸው ያውቀዋል።  ወደ ቀደመው ጉዳዬ ልሳን ስመለስ ፍራንክፈርት ውስጥ በግራሞት እስኪ ይሁኑበት ብለው፤ በተደሞ የባጁ ስንት የሚያውቁ፤ ስንት ለኢትዮጵያ የደከሙ ወገኖች ከቅንጅት ግርግር ጋራ በተያዬዘ አንገታቸውን ደፍተው የተቀመጡ እንዳሉ አውቃለሁኝ። ዛሬ አሜሬካን ዲሲ ነው የኢትዮጵያ ፖለቲካ አናት ሳይባል እንቅልፍ ላይ እነሱ በነበሩበት ጊዜ አውሮፓ በ90ዎቹ መጨረሻ በሳል የሆኑ፤ ሞጋች የሆኑ

አህዱ ራዲዮ እና ዕድምታው በጥቂቱ።

ምስል
አህዱ አሰገዱ። „ተግሳጹን ተቀበሉ ጌታ እንዳይቆጣ፤ እናንተም በመንገድ እንዳትጠፉ ቁጣው ፈጥና ትነዳለችና። መዝሙር ፪ ምዕራፍ ፲፪ ከሥርጉተ©ሥላሴ 12.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።                                               የላቀው ሊሂቅ! ·       ግ ራሞተ ሰሞናቱ።፡ አህዱ በሚባል ራዲዮ አቶ ሌንጮ ለታ እና አቶ በቀለ ገርባ ቃለ ምልልስ አድርገዋል። ትንሽ በትንሹ እንዬው እስቲ ብዬ አስባለሁኝ። በውይይቱ የተሻለ የመልስ መስጠት ጥበብ በአቶ ሌንጮ ለታ አይቻለሁኝ ስልታዊ እና ግልጻዊ ለመሆን ጥረዋል። የአቶ በቀለ ገርባ ደግሞ ወደ መንፈስ ለመቀረብ ማዶኛ ሆኗል - ለእኔ። ያልመድኩት ነገር የሳቸው ጉዳይ ነው። ጊዜ ያስፈልገኛል።  አድማጮች ሲጠይቁ ነበር። ጠያቂዎች እና አስተያዬት ሰጪዎች አቶ ሌንጮ ለታን ከፍ አድርገው „ክቡር“ እያሉ ማቅረባቸው አቶ በቀለ ገርባን አልተመቻቸውም የመረጋጋት ሁኔታ አላዬሁባቸውም። እኔ ሁለመናን ነው የምከተታለው።  ይህን ሳይ ሚሊዮኖች የሰገዱለት  የአብይ ለማ ፍቅረ አክብሮት እንዴት እንዳስተናገዱት ወፌን ጠይቅኳት። ይገባል አይደል። በሁለቱ ሊሂቃንም ብዙ ሰው ነው የሚጸፈው አክብሮ። ወዶ ናፍቆ አልቆ እና .... እናማ አቶ ሌንጮ ለታን አምስገነው አድማጮች ሲናገሩ ፊድባኩን ለኩት፤  ይህን ወስጠቱን ቪዲዮውን እያዬ መገመት ነው። https://www.youtube.com/watch?v=ifs2-94ibME አቶ በቀለ ገርባ አቶ ሌንጮ ለታ በአሐዱ ሬዲዮ bekele gerba lencho leta interview on ahadu radio አቶ በቀለ ገርባ ባላፈውም ጊዜ ሥሜ በክፉ ተነሳ፤ እን እከሌ አሳንሰው አዩኝ  ብለው እ