መቼ ነው የህወሃት መኳንነት ሃፍረት የሚባል የሚሰራላቸው?
አለማፈረን ግባ በሉት¡
„አህዛብ ለምን ያጉረመርማሉ?“
መዝሙር ፩ ቁጥር ፪
ከሥርጉተ ሥላሴ
13.10.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
የእንጀራ ልጆች ፍዳ!
ጫጫታ በረከተ በማህበረ ተጋሩ ሠፈር። መቼም እኔ ከወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌሰቶ ጋር ተብጥብጦ
የተጋቱ አለማፈር ብቻ መሆኑን እዬተረዳሁኝ ነው። እንዲያውም አያፍሩም አሁን አዬር መንገድ ላይ ባለው ገመና።
የተጠናከረ የሎቢ ተግባር እንዳይካሄድ እኮ መቼም ኢትዮጵያ የሚል አንድ ተቋም ብቻ እሱ ስላለ
ነው እንጂ የመብት ረገጣው እኮ የኦሽትዝ ግፍ ያዬለበት ነው። ሰብዕዊ መብት ይከበር የሚሉ አገሮች እኮ የ አዬር መንገዱን አሰራር
እንደጸዬፉት ማድረግ ይቻላል። ግን ከ አዬሩ ላይ ያለው ንጹህ ብሄራዊ ሰንድቅ አላማ ቃልኪዳን ስለሚይዝ ነው ዝም የሚባለው።
አሁን እዛ ያሉ የተጋሩ ሃላፊዎች ሳር ቅጠሉ እሱ በእሱ ሲሆን ትንሽ ብጣቂ ነገር እንዴት ልብ
አይሰራላቸውም? አያፈሩበትም፤ በር ስትከፍትም፤ ኮሪደርም፤ መጸዳጃ ቤትም፤ ካፍተሪያም፤ ሜዳውም ላይ ሁሉም ቤተ ተጋሩ ሲሆን አይቀፍም!
ህሊና ያለው ጥፍር ላይ ነውን?
በሩ ራሱ እኮ ጠረኑ እነሱን እነሱን
ነው የሚለው። ወለሉም እንዲሁ ነው። በእነሱ ዘመን እኮ ነው ሰው እያዬ እዬሰማ እግሩ የተቆረጠው ምክንያት ተፈልጎ። በእነሱ ዘመን
ነው ወንድ ልጅ የተንኮላሸው፤ በእነሱ ዘመን ነው ዘራፋ እንዲህ ባህል የሆነው፤ ምን ያልታዬ መከራ አለና።
ቃለ ምልልሱ ሲታይ ጠያቂውም ተጠያቂውም ዘገባ አቅራቢውም ዘገባውን አስተላላፊውም ያው ነው ቤተ
ተጋሩ። እዛ አዬር መንገድ አንድ ነገር ሲፈጠር አንድ ሰው ለዬት ያለ ለማግኘት ይችግራል። በውነት ይቸግራል። በጣም ጸያፍ ነገር
ነው። ዋ! ነው የሰማይ ጦሮ የታዘዘ ዕለት።
አሁን የዚህ ግፍ የወቃው መከረኛ ነፍስን ከእግሩ ሥር ወድቆ አዬር መንገዱ እራሱ ይቅርታ መጠዬቅ
ሲገባው አሁን ይፏልላል። ለነገሩ ከ700 ሺህ በላይ ያፈናቀለን፤ የ9 ያላኑሰ ቤተ እግዚአበሄርን ያቀጠለ፤ ሺዎችን ያሰደደ፤ ሺዎችን
ከእንሰሳ ጋር አስሮ ያንገላት አቶ አብዲ ኢሌ ሃኒ ሙን ላይ እንደነበሩም አዳመጥን።
ግፍ አይሆን ወይ? ምንድን ነው
ሰው ማለት ኢትዮጵያ ውስጥ? ምድነው ኤትኪስ ማለት ኢትዮጵያ ውስጥ? ምንድነው ሞራል ማለት ኢትዮጵያ ውስጥ?
በቃ ቃሉ ብቻ ነውን ኢትዮጵያ ወይንስ ህዝቡ? የትናት ላይበቃ ዛሬም ውሽት፤ ዛሬም ቅጥፈት፤
ዛሬም አላጠፋነም። ዝርዝሩን የሠራተኛውን አውጥቶ አዬር መንገድ ስለምን አያጠናውም።
ቀድሞ ነገር ኢትዮጵያ እስከ ልጆቿ አለችን እዛ ቤት? ሲከፋት የሚከፉ? ሰትጠቁር የሚጠቁሩ?
ስትጠቃ አለሁሽ የሚሏት ልጆቿ እዛ ቤት እኩል ይሰተናገዳሉን? አስተዳደር ተብዬው አያፍርም? ቢያንስ ለዛ ለሚኮፈሱበት ገበርዲን
እና ከራባት ክብር ሲሉ እንኳን አንደበታቸውን አይያዝም? እሚገርም እኮ ነው።
ለነገሩ አቤቱ ብአዴን አመራን ዘሩን እነቅላለሁ ብሎ ለተነሳ ማንፌሰቶ 27 ዓመት ሙሉ ሲያደገድግ
ይህው ዘሩ በተለያዬ ሁኔታ ተነቀለ። ያን ሁሉ አሳር ያላፉትም ይህው ነው ስድት ነው። የሚገርመው ብቃት አንሶት ነው ይላሉ። በደንቀዝ ጫማ ተግበቶ 4ኛ ክፍል ሳይደረስ ፈተናው እዬተሰራለት ሾመቱ አብራሪነቱ ኮከቡ ሲሰጥ እኮ እናውቃለን።
ዲግሪው ሁሉ እኮ የእንቦይ ካብ ነው። የተገዛ ድግሪ እኮ ነው ያለው። የተገዛ ሹመት እና ሽልማት ነው የለው። ቀን ሰጠን በሉ ይልቅ። "ቀን የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል" አይደል የሚባለው። ዓለም አበጥሮ አንጠርጥሮ ያውቃችኋዋል። ለመዳን እንኳን አትፈቅዱም። ይቅርታ ያደረገላችሁን ህዝብ ለማቁስል ፍጠናታችሁ ይገርመኛል። ያልታደላችሁ ናችሁ፤ ዕድለኝነትም ነበር እንዲህ በነበረው ሁኔታ ምናችሁም ሳይነካ መቀጠላችሁ... አማራን መፍራት ግን የተገባ ነው።
የትናንትም የዛሬም መሳፍንታት ስለ
አነሰው ነው ብቃቱ ወደ ቦይንግ የተዛወረው ይሉናል፤ ሌላው ተረት ደግሞ ስላልቻለ ነው ረዳት የሆነው አማራ ስለሆነ ቢባል አይሻልም፤ አሳዬ
እኮ ያ ቀንበጥ ያ አንበሳ የቀደሙትን ጀግንነት በተግባር ታሪክ የደገመው ረ/ አውሮፕላን አብራሪ ሃይለመድህን አበራ። ሰብዕዊነቱንም፤ ልቅናውንም፤ ጥበቡንም፤ ማስተዋሉም፤ ታጋሽነቱንም፤ የሞራሉም ልዕልናንም መቻሉንም በዝምታው ውስጥ አሳያችሁ እኮ።
አመለኞች። ጊዜ የማያስተምራችሁ። ምን አለ ፈጣሪ አምላክ ከእነ ቅጥፈት እና ትዕቢታችሁ ንቅል ቢያደርጋችሁ። በድለው ደግሞ ተበዳዩ ይቀርታ ይጠይቀን ይላሉ? ፈጣሪ እንዲህ የኢትዮጵያን እናቶች በሰርክ በተለያዬ መንገድ እንደምታስለቅሱት የእጃችሁን ይስጣችሁ።
እፍረት እኮ ነው ለአንድ አገር መንግሥት እንዲህ አንድ የቦይንግ አውሮፕላን አብራሪ እንዲህ
ትቶላችሁ ገጠር ገብቶ ገበሬ መሆን። ውርዴት እኮ ነው። ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/ እግዚብሄር ቢፏልሉ ምድር አይብቃኝ ቢሉ እኮ ይገባቸዋል። ይህ አፓርታይዳዊ አጋዛዝ ዘመን አላስተምረው ብሎ እንዲህ ሲዘባነን።
ከላይ እስከታች እነሱው ናቸው አራጊ ፈጣሪ። ማን እነሱን ደፍሮ? ማንስ እንሱን ነክቶ? ማንስ እንሱን ከሥልጣን አውርዶ? ማንስ
እነሱን ቀጥቶ?
የኢትዮጵያ መንግሥት ይፈርበት ለዚህ ውርዴ ድርጊት፤ የኢትዮጵያ መንግሥት አንገቱን ይድፋበት ለዚህ ሁሉ
በአማራ ላይ ለሚደርሰው ንብርብር ግፍ።
በዚህ ሚዲያው የ አማራ ሊሂቃንን ያዋክባል፤ በዚህ የመንግሥት አካላት አማራውን ይድጣሉ፤ በዚህ ሥርዓቱ አማራን ያሳድዳል፤ የት ይህድላችሁ አማራ?
በሌላ በኩል ግን ብራቦ የአማራ ማስ ሚዲያ! ጎበዞች ጎልጉሉት መከራውን፤ „ካልጎሼ አይጠራም።“ ይህች አገር ለአማራ እንጀራ እና ሆና የኖረችበት ዘመን ማክተም አለበት።
በቃችሁ ሊባል ይገባል ማንም ይሁን ማን።
Ethiopia:ካፕቴን ዮሴፍ ሃይሉ የበረራ ስልጠና ዋና ዳይሬክተር ምላሽ ሰጠ በረዳት አብራሪ ዮሐንስ
ደከም ያለ ስለሆነ ነው ቦይንግ ላይ የተመደበው።
Ethiopian
Top Mereja News _ የኢትዮጵያ አየር መንገድ መልስ ሰጠ መልሱ ይተነተናል
የድምጽ ማስረጃው ከቴሌ የመረጃ ቋት የተገኘ ነው..በፖለቲካ አመለካከቱ ብቻ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የተባረረው ..ከአቶ ተወልደ ጋር የተደረገ የስልክ ልውውጥ
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ