በለው! የአቦ ሌንጮ ለታ ፈረስትነት።

የአቶ ሌንጮ ለታ የኦሮሞ ፈርስት ፈገግታ።
„አቤቱ የሚያስጨንቁኝ ምንኛ በዙ፤ በእኔ ላይ የሚቆሙት ብዙ ናቸው።“
መዝሙር ፫ ምዕራፍ ፩
ከሥርጉተ©ሥላሴ
13.10.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።






ቢስ አይይብን ዶር ለማ መገርሳ እና ዶር አብይ አህመድን ብለናል። የአፍ ሳይሆን የውስጥ ወልምታ እንዳይኖርባቸው አብዝተን እንጸልያለን።

ውዶቼ እንዴት ናችሁ ደህና ናችሁ ወይ። ባለፈው አንዲት ሴት በተፈጥሯዋ አንድ ጡት አብቅላ በህልሜ አዬሁኝ ብያችሁ ነበር አይደል? እህቴ ስተፈታልኝ ኢትዮጵያ መከራዋን ተሻግራ አንድ የምትሆንበት ዘመን ይመጣል አለችኝ። እኔም እንደ አፍሽ ያድርግልን አልኩኝ። ዛሬ ስለተፈሪው ማንነት ስለ ኢትዮጵያዊነት ትንሽ ማለት ፈለግሁኝ።

አንድ የጠራ ነገረ ማወቅ ፈለግሁኝ። ፍራንከፈርት ከዶር አብይ አህመድ ጋር ሥብሰባ እንዳለ አዳምጫለሁኝ። ወደ ፍሬ ነገሩ ከመሄዴ በፊት ስለፍራንክፈረት የነፃነት ትግል ዓውራነት፤ ለዴሞክራሲያዊ ተጋድሎ አዕምድነት ትንሽ ማለትን እሻለሁኝ። እንግዲህ ፍራንከፈረት የፖለቲካ ጭንቅላት አባ ወራዎቹ ያሉበት ቦታ ነው። አባወራ ነው ያልኩኝ እማ ወራ ሴት ፖለቲከኞች በአላዛሯ ኢትዮጵያ ስለማይታሰብ ነው፤ አብሶ ውጪ አገር ያው መፈናፈኛ የለም። ይቀኑብናል ወንዶቹ። ለምን? ልባቸው ያውቀዋል። 

ወደ ቀደመው ጉዳዬ ልሳን ስመለስ ፍራንክፈርት ውስጥ በግራሞት እስኪ ይሁኑበት ብለው፤ በተደሞ የባጁ ስንት የሚያውቁ፤ ስንት ለኢትዮጵያ የደከሙ ወገኖች ከቅንጅት ግርግር ጋራ በተያዬዘ አንገታቸውን ደፍተው የተቀመጡ እንዳሉ አውቃለሁኝ። ዛሬ አሜሬካን ዲሲ ነው የኢትዮጵያ ፖለቲካ አናት ሳይባል እንቅልፍ ላይ እነሱ በነበሩበት ጊዜ አውሮፓ በ90ዎቹ መጨረሻ በሳል የሆኑ፤ ሞጋች የሆኑ የፖለቲካ ትኩሳት ትንፋሽ ነበር ፍራንክፈርት። እንደ ዛሬው የተገኘው ሰው ሁሉ የፖለቲካ ተንታኝ የሚሆንበት የለበለብ ጉዞ አይደለም የፍራንክፈረት የፖለቲካ ጠበብት አቅም።

በሌላ በኩል ደግሞ ሆላንድ ሁሉም ነገር ዛሬ ዛሬ ተቀዛቅዞ አያለሁኝ። የመጀመሪያ የተቀናጀ ቪዲዮ ቅንብር ተግባር በተሟላ ዝግጅት ይከውንበት ነበር። የአዕምሮ ጋዜጣ አዘጋጆች ነበሩ የሚመሩት። አዕምሮ ጋዜጣ ላይም እኔ አዝናኝ በሆኑ ጉዳዮች ላይ እጫጭር ስለነበር እነሱ መሆናቸውን አዋቃለሁ፤ ሆላንድ በፖለቲከ አቅም እኩል ከሌሎች የአውሮፓ አገሮች ጋር ተደማጭ እንዲሆን አድርገውት ነበር ለወቅቱ ማህበረ አዕምሮ። ኢህአፓም ጠንከር ያለ መሰረት ነበርው እዛ። ብዙ በቪዲዮ የተሰናዱ ሰነድም ይኖራቸዋል ብዬ አስባለሁኝ። አውሮፓ ላይ ሲዊዲን የሚኖሩ ኢትዮጵውያን ከጋዜጠኛ  አህመድም በፊት አንቱ የተባለ የኮሚኒቲ ራዲዮ ነበራቸው።

ጦቢያን መጽሄትን የሚወዳደር „ራዕይ“ የሚባል መጽሄት በፕሮፌሽናል ሙያተኛ የቦርድ አባላት የሚተዳደር መጽሄት ደግሞ ፍራንክፈረት ላይ ነበር። ስደተኛ ራሱ ባለቤት ነበረው። የማስተርጎም አገልግሎት የሚያሟሉ የኮሚኒቲ ድርጅቶች ነበሩ በዬአውሮፓ አገሮች፤ የልምድ ልውውጥም አደርጉም ነበር። አብዛኛውን የፖለቲካ ድርጅቶችን እንዲሰባሰቡ የተቀናጀ ትግል እንዲያደርጉ በማዕከላዊነት የሚመሩት ዩኢትዮጵያን ኮሚኒቲዎች ነበሩ። የዚህኛው የዚያኛው ድርጅት ሳይባል። 

የመንግሥትን ያህል የሚሞግት አቅም የነበረው ንጹህ የኢትዮጵያዊነት መንፈስ አውደ ምህረት ነበር ፍራንከፈርት። ሊሂቃኑንም ተንታኞችም ጋዜጠኞችም የማታፈሩባቸው ነበሩ። ምን ይሆናል ዕድሜ ለቅንጅት ሁሉንም አፈራርሶ፤ ድብዛውን ክው አድርጎ፤ ግንኙነቱን በትኖ፤ ዬዬግለሰቦችን ማህበራዊ ሰላማዊ ኑሮን ቀውስ ውስጥ ዱሎ ግድብ እና ወሰን ሰርቶ መራራ ሰንብት አደረገ፤ ጠንቁ ግን ዘመን ተሻጋሪ ነው …

ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ፍራንክፈርት ሲመጡ ግልጽ አድርገው እንዲገልጹ እምፈልገው ማን እንደሚበልጥባቸው ነው? ኦሮሞነት ወይንስ ኢትዮጵያዊነት? ከሳቸው ነጥዬ የማላያቸው ሚኒያ ላይ ባዬሁት ያልተለመደ ወኔ ትንሽ ትዝብት ጫር ቢያደርግብኝም፤ የሻሸመኔ እና የቡራዩ ታሪክ ይቅር የማይለው ጭካኔያዊ አፈጻጻም እሳቸው በሚያስተዳደሩት አንባ ማዬቴ ውስጤን ቢያስከፋውም ሁልጊዜም በቅንነት፤ በታማኝነት የማከብራቸው፤ የምሳሳላቸው ዶር ለማ መገርሳም ቢሆኑ ማን እንደሚበልጥባቸው ሊነገሩን ይገባል። 

ይህ የሽፍንፍን ጉዞ ብዙ ከባከንበት፤ ብዙ አቅም ከፈሰሰበት፤ ብዙ ሰው መስዋዕትነት ከከፈለበት በኋዋላ መና ነው እዬቀረ ያለው … ዕውነትም እንደ አነባች ነው። የዕውነት ቀን ናፋቄ ሆኛለሁኝ። ምኞትሽ ምንድን ነው ተብዬ ብጠዬቅ የአላዛሯ ኢትዮጵያ ሊሂቃን ዕውነት ውስጥ መኖርን ሲሳዩን ነው የምለው። ያደክማል አይደል የ አውነት ፍለጋ ፍዳ?

በሦስተኛ እማነሳቸው ለእኔ ከኦህዴድ / ከኦዴፓ ለመንፈሴ ቀረብ ያሉት አንድ ቀን ደግሞ አንገቴን እስኪያስደፉኝ ድረስ አቶ ካሳሁን ጎፌም ማን እንደሚቀድምባቸው እንዲነገሩን እሻለሁ። ምክንያቱም ከሌሎች የኦሮሞ ሊቀ - ሊቃውንት ጋር ድካም ማብዛት ከእንግዲህ አያስፈልግም። አዲስ ወጥተናል የሚሉ አክቲቢስቶችን አዳምጣለሁኝ እባብን ያዬ ነው፤ ብቻ ሰው ለማያተርፍበት ነገር መደከምን ሃራም ማለት አለበት። እኔ ለሚከስር ነገር አልደክምም ከእንግዲህ።

ለዚህም ነው እኔ አማራ ማጥናት ያለበት ተጨማሪ ቋንቋ ግዕዝ ስለመሆኑ አበክሬ መግለጽ የምሻው። ሚስጢር ያለው እዛ ስለሆነ … ነፃነት ማለት የሚበልጥበት ግዕዝ ሰለሆነ። ያለተቀዬጠ፤ ያልተደለዘ፤ ያልተበረዘ፤ ያልተለበጠ የኢትዮጵያ ሰበል ግዕዝ ስለሆነ። የእንግሊዘኛ ይሁን የላቲን ፊደላት ጥገኛም ያልሆነ ነው ግዕዝ። ግዕዝ ዘመን ጠገብ የፍለስፍና ዓውደ ምህረት ነው። 

 ልዕልተ ኢትዮጵያ ለቤተ እግዚአብሄር እንኳን የእኔ የምትለው የፍልስፍና ቋንቋ ያላት አገር ናት። ባጋጣሚው ካነሰሁት ዘንዳ በልቤ የሚመላለስ አንድ ጉዳይ አለ፤ ስለምን ዶር አብይ አህመድ ግዕዝን ለማጥናት እንዳልደፈሩት? በዚህ ልቅናቸው ላይ ግዕዝ ተምረው ቢሆኑ ኖሮ ወደ ዘረ ያዕቆብ ይጠጋጉ ነበር። 

ባጋጣሚው እማከብራቸው ዶር ምህረት ደበበም ይሁን ወጣት ቀጣይ ፈላስፋዎች ግዕዝን ቢጠጉ ዘመኑን ይዋጁታል። ብዙ ነገር ቀርቶብናል። ብዙ የኢትዮጵያ ሊቀ ሊቃናት እኮ መሰረታቸው ግዕዝ የመሆኑ ነው የልቅናቸው ሚስጢር። ኢትዮጵያ ሚስጢር ናት የሚባለውም በዚህ ጽላትነት ነው።  

ወደ ቀደመው ምልስት ሲሆን ቲም ለማ ማለትን እኔ አቁሜያለሁኝ። ሻሸመኔን ያዬ፤ ቡራዩን ያስተዋለ ቲም ለማ ማለት ማለጋጥ ይሆናል። እኔ ለማ እና አብይ ብቻ ነው የምለው። ሁለቱም ቢሆኑ ማን እንደሚቀድምባቸው ሊነግሩን ይገባል፤ የአፍሪካ አንበሳ ለመሆን ከመሰናዳታቸው በፊት ዋናውን መነሻ ማንነት ላይ ያላቸው አቋም በግልጸት ማወቅን ነፍሴ ትሻለች። ከበፊቱ በበለጠ አሁን። የተሰበሰበሰው እዬፈለሰ ስለሆነ ... 

እርግጥ ነው በዶር አብይ የቀደመ ሥነ ግጥም ውስጥ፤ እንዲሁም የቅንነት ጋዜጠኛው አቶ አንተነህ ከበደ መጻህፋቸውን መግቢያ እንዳነበበልን ኢትዮጵያዊነት ለጠ/ ሚር አብይ አህመድ ልጥፍ አለመሆኑን እረዳለሁኝ፤ ግን አሁን ያለው ይህ የኦሮሞ ኢንፓዬርን ከመዲናዋ ከአዲስ አባባ ጀምሮ የመመሥረት ዘመቻ ቅኝት ነፍሴ ይህን ጥያቄ እንዲያነሳ ይጎሰጉሰኛል። 

አብሶ የንጉሥ ታከለ ኡማ ግስጋሴ የት ላይ ሊያቆም እንደሚችል ልጓም አልተሠራለትም። ይህ ቤት ለድሆች ታደለ ምንትሶ ቅብጥርሶ ተቀባይነት እንዲያገኙ መላሾ ነው። እና ሚዲያም ዕውቅናቸውን እንዲያጎበት ሆን ተብሎ የሚከውን ተግባር ነው። ስንት ጊዜ እንሸወድ። አዲስ አባባ ላይ የኦሮሞ ወጣቶችን ብቻ የሰበሰበ የታሪክ ቅኝት ኑሮን አያውቅም። ታቦተ ሎሬት መንፈሱ ይህን ሲያድምጥ ምን ይጨንቀው እላለሁኝ እኔ ... ስለምን የአዳማ ከንቲባ አይሆኑም እሳቸው? 

አህዱ ራዲዮ ከአቶ ሌንጮ ለታ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ የተከታተሉ አንድ ጠያቂ ስለምን ሁልጊዜ „ኦሮሞ ኦሮሞ ትላላችሁ“ ብለው ጠይቀዋል፤ ከዚህ ጋር ሊያያዝ የሚችለውም  „ሲሞቅ በማንኬያ ሲቀዘቅዝ በሹካ አይሁንም ወይ" ተብሎ ለተጠዬቀው ጥያቄ ለሚፈልጉት ጉዳይ ብቻ ግልጽ የሚሆኑት ጮሌው አቶ ሌንጮ ለታ "ኦሮሞነትህን ትተህ ኢትዮጵያዊነትህን ተቀበል የሚለኝ ከመጣ እስከ ልጅ ልጆቼ ድረስ ኦሮሞ መገንጠል አለበት ብዬ አስተምራለሁ" ብለው እንቅጩን ነግረውናል። ይህ ማለት ኦሮሞ ፈርስት ማለት ነው።

ታዲያ ስለምን በወጣቶቹ እንዴት ልንፈርድ እንችላልን? ይህን መንፈስ አስተናግዳለሁ ብሎ አብሮ ለመሥራት የወሰነው ግንቦት 7 እና ኢሳት እነሱ መሥራቾቹ እንኳን የተነሱበትን ትተው እያሉ ልባችን ውልቅ ሲያደርጉት የከረሙበት ጉዳይ ጊዜ መስታውቱ እንዲህ አድርጎ አሳዬን። ዘጭ በዘመነ እንቦጭ!

 አሁን ግንቦት 7 ይህ አልሳከላት ሲል „አማራ ነኝ“ አትበል በማለት፤ የአማራ ድርጅት አዴፓ ባዘጋጀለት መድረክ ራሱን ድርጅቱን የሚያስተናግደውን ጨምሮ በአማራ መደራጀት ውርዴት ነው፤ ኋላ ቀርነት ነው፤ አለመሰልጠን ነው እያለ ያስተምራል። ኢትዮጵያዊነትን ፊደል መቁጠር ካለባቸው የግንቦት 7 ሊሂቃናት ናቸው። ዴሞክራሲንም እንዲሁ። 

የአማራ ተጋድሎ ሲቀጣጠል „የመረጣችሁት ጊዜ አሁን አይደለም“ ሲሉ እነሱ ኦሮሞ ወገኖቻችን አሰባበስበው ብራስልለስ ላይ የሠሩትን ያውቁታል። ብራስልስ የሚኖሮ ኢትዮጵውያን አልነበሩንም? አሁንም ይሄው ነው ድግምታቸው። ካለጋሬ ኮረቻ ላይ መውጣት አይቻልም እና።  

አማራማ ከኢትዮጵያዊነቱ በላይ ጌጥ የለውም። አሳያቸው እኮ በ27 ዓመት ያልተደፈረውን ኢትዮጵያዊነት ገላጩን የጥቁር ህዝብ የነፃነት ዓርማውን አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን ይዞ ፊት ለፊት ሲማገድ፤ 


እነሱ የኦሮሞ ሊሂቃን እና ዓርማቸውን አዝለው ተቀበሉልን እያሉ አውሮፓ አሜሪካ ላይ ሲያውጁ፤ 



አማራ ደግሞ ጀግና ኮ/ አብዲሳ አጋ፤ ዘራይ ደረስ፤ አብርሃም ደቦጭ፤ ሞገስ አስገደሞ፤ ሃይለማርያም ማሞ የተሰውሉትን ራሳቸውን የገበሩለትን የወደዱትን ያከበሩትን ያስከበሩትብ ብሄራዊ ሰንደቅዓላማውን ከፍ አድርጎ ሞቴን ከአንተ ጋር ብሏቸዋል። አሁን ይልቅ እነሱ ተመልሰው ተሟጋችን ነን ባዮች ደግሞ ሆነዋል። እንኳን ለዚህ አበቃቸው። ወደ እኛ ፈቃድ ለለምጣት።


የሆነ ሆኖ ከሰሞናቱ አማራ ነኝ አትበል በአማራ መደራጀት የለብህም ኡኡታን ጥቃት የሚመከት ፈንጁን አቶ ሌንጮ ለታ ልከውለታል ለራሱ አብረውት ለተሞሸሩት ለግንቦት 7። አይደለም በኦሮሞነት መደራጀት ኦሮሞነትህን ሳታስቀድም ኢትዮጵያዊነትን ተቀበል ከተባልኩ እምመርጠው ኦሮሞኔቴን ብለው ቁርጡን ገለጸዋል። ቁርፂ ማለትስ አሁን ነው።



አቶ በቀለ ገርባ አቶ ሌንጮ ለታ በአሐዱ ሬዲዮ bekele gerba lencho leta interview on ahadu radio


አቶ ጃዋር መሃመድም ውግዝ ከአርዮስ የተባለበት ይኸው ነው። የተከተለው አባቶቹን ነውና …. ማስቀጠል የሚፈልገው የአባቶቹን ሌጋሲ ነውና። እንግዲህ በሚሊዬነም አዳራሽ በነበረው የቅዱስ ዮሖንስ የዋዜማ ዝግጅት በጠ/ ሚሩ በክብር ሥማቸው ከተጠሩት አንዱ አቶ ሌንጮ ለታ ናቸው። ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚለው አገር የገባው የአማራ ሊሂቅ ግን አንዳቸውም ሥማቸው ሲጠሩ አልሰማነም። የአማራ ተጋድሎ አገር የገቡ አክቲቢስቶችም እንዲሁ።
  
አንዳንዶቹማ በእጥፍ ነው ሊቃናቶቻቸው ሥማቸው የተጠሩት ዕውቅና ማግኘት ስላለባቸው። ሚዲያውም እንዲሁ ነው በዛ ሰሞን ፋና ከወያያቸው ሦስት ሊሂቃን ውስጥ አንዱ ዶር አፈወርቅ ተሾመ ነበሩ። 

https://www.youtube.com/watch?v=q60AVb_1m9k&t=292s

በሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከውጭ ከተመለሱ የፖለቲካ ሃይሎች ጋር የተደረገ ቆይታ ክፍል 2

https://www.youtube.com/watch?v=XOtLNYr-sg4


በሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከውጭ ከተመለሱ የፖለቲካ ሃይሎች ጋር የተደረገ ቆይታ ክፍል 1

ፋና ቴሌቪዥን አወያይ ዱላ ይዞ ነበር ቃለ ምልልሱን ከአማራ ህዝብ መንፈስ ጋር ያደረገው። መቼም ጉደኛ አገር ናት ኢትዮጵያ አወያዩ ቀጥሎ ሊሆን ይችላል … ደሞዙ ላይ ሲሆን ማከያ ጉርሻም አግኝቶ ይሆናል … የአማራን ቅስም መሰበር በዬተገኘው አጋጣሚ ተልምዷልና። ባህልም ሆኗል አቋምም ተይዞበታል። ይህም ሆኖ ኢትዮጵያ የነፍሳችን ጉልላት ናት ለእኛ ለአማራዎች።

የፋናው አወያይ ኢትዮጵያን ጉልላት ማድረግ ስለተሳነው እዛው ኮዳው ላይ ሲዳክር ነበር የተመለከትኩት። አቤት የ እሱም ሥልጣን ሥልጣን ሆኖ ሲቆርጥ፤ ሲያፋጥጥ ሲገደብ፤  ለአማራ ግን ትናንትም ዛሬም ወደፊትም ኢትዮጵያ ከነፍስም በላይ ናት። ይህ እንዳይሰፈን ነው አማራ የሚገለልበት፤ የሚጨቆንበት፤ አደባባይ ልዩ ተጽዕኖ እንዲህ ባለማፈር የሚደረግበት። ኢትዮጵያዊነትን የሚፈራ ሁሉ ነው አማራን የሚፈራ።

የሆነ ሆኖ ኢትዮጵያ የምትፈለገው ለቅድመ ሁኔታ መተዳደሪያ ነው ወይ ነው የእኔ ጥያቄ? አሁን እኔን የትኛው ደፋር ጋዜጠኛ ነው ማን ይቀድምብሻል ብሎ ሊጠይቀኝ የሚችል? ድፈረት ነው።  ከኢትዮጵያዊነት በላይ ምን ክብር ምን ድንቅ ነገር ምን ዕጹብ ነገር ኖሮ ነው ከኢትዮጵያዊነት ጋር ሌላው ማንነቴ ተወዳዳሪ ሆኖ የሚቀርበው?

ስደት ላይ አኩል አይደለንም በሥነ - ልቦና ልዕልና ከአፍሪካ ሐገራት በላይ ነው ኢትዮጵያዊነት። ከአንዲት ኬኒያዊት አንስት ጋር ፈጽሞ አይገናኝም የመንፈስ ልዕልና አቅሙ የኢትዮጵያዊነት። ት/ ቤት የሚቸገሩበት ነገር የሌላ አፍሪካ አገር ይሁን የላቲን አሜሪካ ተማሪዎች የእኔ የሚሉት ባህል ማንነት ትውፊት ጊዜ እንኳን የላቸውም። 

ስለባህል አብራሩ ሲባሉ መምህራኖቻችን ይህም ከእኛም አለ ከእኛ የሌለውን ንገሩን ይሏቸዋል። ነፃነት ማጣት ሁለመናን ነው የሚቀማው። ዛሬ ኦሮሞ አለኝ የሚለው ነገር ሆኑ የቆዬው ኢትዮጵያ ነፃ አገር ስለሆነች ብቻ ነው። ነፍሱን ራሱ የብሄሩን ሥም ራሱ "ኦሮሞ" የሚለውን። በጣሊያን ቢገዛ ሮቤርቶ ሥሙ፤ ምግቡ ስፓጌቲ፤ ቋንቋ ጣሌንኛ ባህሉም  የአውሮፓ በሆነ ነበር። ኦሮሞነትን ያቆዬው ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው።  

ባላፈውም አጫውቻችሁዋለሁኝ ከሦስት ኪሎ በላይ የሆነ 100.00 የሲዊዝ ፍራንክ የሚሸጥ አንድ መጸሐፍ የ193 አገሮችን የፊት ገጽን ይዞ ታትሟል። ለ6ወራት ያህል ዙሪክ ባቡር ጣቢያ አካባቢ የፎቶዎች ኤግዚብሽን ነበር፤ ለዛ ኢትዮጵያን ወክዬ ተጋብዤ ለካስቲንግ ስሄድ ወደ ድርጅቱ ስገባ እና ተዘጋጅቼ የኢትዮጵያ ቀስተ ዳመንን ቲሸርት ለብሼ ለፎቶ ስዘጋጅ የነበረው አክብሮት ልክ አልነበረው። 

ራሱ ማናጀሩ ነበር ያነሳኝ፤ ወደ 45 ደቂቃም ካፍተሪያቸው ልዩ የቢአይፒ ሳሎን ውስጥ  አውግተናል። በዕለቱ ፎቶ ተነሺዎች እስከ 10 የሚደርሱ ነበሩ። አንዳቸውም ይህን ዕድል አላገኙም። የሰንደቃችን ክብሩ ልክ የለውም።

እያንዳንዷ የአካሌ ክፍል ስለ ኢትዮጵያዊነት እዬሰማሁ፤ እያዬሁኝ ቢቆራረጥ ቅጭጭ አይለኝም። ኢትዮጵያዊነት የሚገፋ፤ እንደ  አሮጌ ጨርቅ ተበጣጥቆ የሚጣል አይደለም። ኢትዮጵያዊነት ቢያደምቅ እንጂ የሚያደበዝ አይደለም። ኢትዮጵያዊነት የውስጥ ነፃነትን ቢያበለጽግ እንጂ አንገት የሚደፉበት ማንነት አይደለም። ኢትዮጵያዊነት ከእውቅት፤ ከጥበብ፤ ከአምክንዮም በላይ ነው። ሲኖሩበት ብቻ ይሆናል ሚስጢሩ ነፍስን የሚያለመልመው።

አማራነትን እኔ እማዬው ልክ እንደ ፆታዬ እንደ ሴትነቴ ነው። አማራ አይደለሁም አልልም። አማራ ነኝ። ወላጆቼ አማራዎች ናቸው። ከቤቴ ውስጥ እኔ ሳድግ አንድም ቀን „አማራ“ የሚባል ቃል አዳምጬ አላውቅም። በፍጹም! ድንግል ትመሰክራለች። ወላጆቼ እኔን ሲሳድጉኝ በአባቶቻቸው በእናቶቻቸው ሌጋሲ ነው።  እልህ ነው እኔን አማራ ያደረገኝ።

ይህም ሆኖ ቢደመር ቢቀነስ፤ ቢካፈል ቢባዛ አማራነት ከኢትዮጵያዊነት በላይ መሆን ቀርቶ መወዳደር አይችልም - ለእኔ ለሥርጉተ ሥላሴ። በፍጹም በፍጹም በፍጹም። ኢትዮጵያዊነቴ ነው አማራነቴን የሰጠኝ። ስለምን? አባቶቼ ኢትዮጵያ የምትባለውን አገር አበጀተውታል እና። በዛች አገር በደማቸው፤ በአጥንታቸው አጥንተው መኖር ስለቻሉ ነው ወላጆቼ እኔን መፍጠር የቻሉት። 

አሁን እኮ ይህ እንዳይሆን በዘመቻ በህግ በፖሊሲ ደረጃ 27 ዓመት የተሠራውን እያዬን ነው። ቅድመ አያቶቼ ፊደል ሲቀርጹ እኮ አገር ለማበጀት ነው፤ ለጠላት እጃችን አንሰጠም ብለው ራሳቸውን ሲሰው አገርን አላስደፈርም አላዋርድም ሲሉ አገር አቆይተው ለተተኪ ለማውረስ ነው። ቋሚ ቅርስ ውርስ ፈጥረው ለትወልድ የሚታይ የሚጨበጥ ሲያበረክቱ አገር አበጅተው ነው።

እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ይህ ፊክ የሆነው አንድነት ሳይሆን እውነተኛው አንድነት ከሆነ ከአማራነቴ በላይ በላይ በላይ በላይ ኢትዮጵያዊነቴ ይበልጥብኛል። ግን ፌክ ነው አንድነት የሚባለው ኦሮሞ ስታገኝ አሮሞ ነኝ እያልክ፤ ጉራጌን ስታገኝ ጉራጌ ነኝ እያልክ፤ ሁለቱንም ስታገኝ ኦሮሞ እና ጉራጌ ነኝ እያልክ፤ የራስህን ሰው ባገኘኸው ሁሉ እዬሰካህ በአንድነት ሥም እነግዳለሁ ስትል ግን አይቻልም እልሃለሁኝ። ሎሌህ አይደለሁም እልኃለሁኝ፤ ግርድና አልነበረም የአባቶቼ ሌጋሲ ብዬ ፊት ለፊት ወጥቼ እሞግትኃአለሁኝ። ከዚህም ባለፈ ህዝቤ የአንተ ጋሬ ተሸካሜ ሊሆን አይገባም ብዬ ሞግቼሃለሁ ወደፊትም አምግትኃለሁኝ።

አሁን እራሱ በዝምታ ውስጥ ነው ያለሁት፤ ፌስ ቡክ የጀመርኩ ዕለት ግን … ይከብዳል። በሁሉ ቦታ እምገለልበት ምክንያትም ሥርጉትሻ ዝቅ ብላ ማረግረግ፤ ለግልብጥ የለብ ለብ ፖለቲካ መናጆ መሆን ስለማትፈቅድ ስለሆነ ያን ጊዜ ፌስ ቡክ ላይ መታደምን ስፈቅድ … ህ። ህ ነው የሚሆነው።

አንድ የአማራ ሊሂቅ አቶ ሌንጮ ለታ የተናገሩትን ቢናገር ኖሮ ይህኔ አገር ይደባለቅ ነበር። ምድር ቀውጢ ይሆን ነበር። አንድ የአማራ ሊሂቅ አማራ ነኝ ሲል እንኳን በማህበራዊ ኑሮ ውግዝ ከአርዮስ ነው። 

የግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕ/ ብርሃኑ ነጋ ኦሮሞዎችን ብቻ ብራስልስ ላይ ሰብሰብበው እኔ የተወለድኩት ከዚህ ነው፤ ቋንቋውን አልቻልኩትም እንጂ እኔም ደሜ የኦሮሞ አለበኝ ብለው ሲናገሩ ውርደት አይደለም፤ ኋላቀርነት አይደለም፤ ዘረኝነት አይደለም፤ ጊዜውን ያልጠበቀ አይደለም፤ የአንዱ መራራ ነገር ቅብዕ ቅዱስ ነው የሌላው ዕውነት ደግሞ ግዞት ነው።

ሚዛን የተነፈገው የወጀብ ቁራኛው የኢትዮጵያ ፖለቲካ እንዲህ ነው ዘመን ከሰጠው ጋር ወክ እንዲህ ስለሚል … ተረበኛ በሉልኝ እንዲህ ዓይነቱን የጊዜ ቧልተኛ ሰሌዳ። ጊዜ ራሱ ቧልተኛ ነው። ራስ እግሩን አንተ በበላይነት በምትቆጣጠረው፤ የምታቀረብውን ብቻ እዬለህ የእኔ የምትለውን ወዝህን ዕውቅና እንዲያገኝ ሌት ተቀን እዬባተልክ ሞኖርህ እንደሆነ የአደባባይ ሚስጢር ሆኖ ግን እንዲህ እና እንዲያ፤ እንዲያ እና እንዲህ …. ለጎንደሮች ግጥማችን አይደለም። ጎንደሮች የግንባር ሥጋዎች ነን። „ዕውነትን ተናግሮ ከመሸበት ማደር“

በ50 ዓመት ውስጥ አንድ የአማራ ድርጅት ተፈጠረ ተብሎ ነው ይህ ሁሉ ፍዳ የሚታዬው። 6 የኦሮሞ ድርጅቶች እያሉ ሦስት አራት የትግራይ ድርጅቶች እያሉ፤ አፋሩም እንዲሁ…  ለሥሙ ግንባር በሚባለው ግራባው ብአዴን / አዴፓ እያለ ሥሙን „አማራን“ አስገብቶለት እንደ ሴሚ ካርድ ወያኔ ሃርነት ትግራይ አመራሩን ባሻው በፈለገው እያስመራ … 27 ዓመት ተቀለደ። አሁን እንኳን ተፎካከሪ ፓርቲዎች ዕድሉን አግኝተው ክብር ያገኙት አማራ መሬት ነው ተብሎ ከተሰጠው ሽራፊ መሬት ላይ ነው።

https://www.youtube.com/watch?v=q60AVb_1m9k&t=292s

በሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከውጭ ከተመለሱ የፖለቲካ ሃይሎች ጋር የተደረገ ቆይታ ክፍል 2

https://www.youtube.com/watch?v=XOtLNYr-sg4


በሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከውጭ ከተመለሱ የፖለቲካ ሃይሎች ጋር የተደረገ ቆይታ ክፍል 1


ይህም ሆኖ አብሮ ኮሮጆ ሊቀራመት የተሰለፈው ሁሉ ራሱን ችሎ አማራ በሊሂቃኑ ልጆቹ ሲደራጅ የውስጥ ቁስለት ሆነ ለሁሉም። ይሄ ነው እኔን ወደ አማራነት የሚገፋኝ እንጂ ኢትዮጵያዊ ከሚለው ክብር በላይ አማራነት በልጦብኝ፤ ልቆብኝ አይደለም። የማይወዳደር ነገር አይወዳደርም። ከነፍሴ በላይ ነው ለእኔ ኢትዮጵያዊነት። ትክ የለውም። ሰው ሰራሽ ከሆነው ከተቀዳጁ ማንፌስቶም በላይ ነው። ቀድሞ ነገር ከተቀዳጁ ማንፌስቶ በላይም ነው አማራነት። ነው እኮ!

ብቻ ብቻ ... ጨዋታው አማራን እስከ ወዲያው የመቅበር የጋራ የወል የኪዳን ምክር ስላለ ብቻ ነው የእኔ አማራነት። አማራ ኢትዮጵያን የመምራት፤ ጠ/ ሚር ይሁን ነገ ደግሞ ቅኝተ ፕሬዚዳንታዊ ይሆን ብቻ በተፈለገው ሁኔታ እንዳይወዳደር ለማድረግ የታጨ የመከራ ቁልቁለት ሁነኛ ፈቺ አልተገኘለትም። ስለዚህ ባለቤቶች አለንልህ ልንለው ግድ ይለናል።

አሁን ከሰሞናቱ የፌድራል ምክርቤት ስብሰባ እዬተካሄደ ነው፤ ዋናዋ ልስልስ ያሉ ወጣት የትግራይ ሰው ናቸው፤ አፈ ጉባኤዋ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብሪሂም፤ ከሥራቸው ያሉት ደግሞ ወ/ሮ ፍርህይወት ናቸው? በ27 ዓመት ውስጥ አንዲት አማራ ሴት እዛ ደረጃ መድረስ አልቻለችም? በዬመሥሪያ ቤቱ ወደ ኮርፕሬሽን ወረድ ስትሉ፤ የመምሪያ ሃላፊዎችን ስታዩ የለም። አይደለም አማራ ኦርቶዶክስ ድብዛው ጠፍቷል። ዘመን አብይ ስለሆነ ነው እንጂ አዲስ ሪቦሊሽን የሚያስፈልገው እኮ ነው። ዙሪያ ገባው ድርቀት ነው አማራንም ተዋህዶንም ስታተስቡት። 

ነገስ ነው ፍሬ ነገሩ? የ27 ዓመቱን ግብረ ምላሽ ጭዳዊ ጉዞ አባሪ እና ተባባሪ ሆኖ የኖረው አዴፓስ ነገስ እንዲህ ትውልዱን እዬቀበረ በፍርስራሹ ላይ የቀይ ስጋጃ አንጣፊ ሆኖ ይቀጥላል ወይንስ እንዳ አባቶቹ የሚተርፍ የሚወረስ ቅርስ ያበጃል? ወጣት ሊሂቃኑን አብቅሎ አንፆ ተፎካከሪ በማድረግ እረገድ ታጣፊ አልጋ ገዝቶ እንደለመደበት ለሽ ይላል ወይንስ ካፌውን ተቋድሶ ስለ ተሰዬመበት ዓላማ ይተጋል?፡የተቃጠለ ጊዜ ነው የነበረው ለምድር እንቦዩ ለቀድመው የኢህአፓ ቅርንጫፍ ለብአዴን።

የሚገረመው ታምራት ደግሞ ይህን ሁሉ እያዬን እዬሰማን የ27 የወያኔ ሃርነት ትግራይ እና አጋሮቹ እሾኽ አማራ ላይ፤ ኦርቶዶክስ ላይ አሜኬላ በቅሎ እንዲህ ወና ስለመሆኑ እያዬን ነው ኢትዮጵያ የነፍሳችን ማደሪያ እንደትሆን በድንግልና የምንፈቅደው። ያው አሁን መንግሥት አለ ብለን ስለምናሰብ ሁሉንም ሥራዬ ብለን ስለምንከታተለው ያለው ዕውነት አማራ የተሰረዘበት፤ የኦሮቶዶክስ ልጆች የተሰረዙበት ሁኔታ ነው የሚታዬው በፓርቲው ይሁን በመንግስት መዋቅር። ሲቢክስ ብለው ባምሳያቸው ባዋቀሩት እንኳን ሳይቀር። 

ሁለቱም በጣምራ አማራም ኦርቶዶክስም ምደረበዳ መሆናቸውን እያዬንም ነው። አሁን ባሉት የለውጥ መንፈሶች አሳታፊ ይሁን ሲባል አማራ ስለመከነ ሌላው ይተካበታል። ያበቀሉት የ24 ዓመት ወጣት ለትልቅ ሃላፊነት አጭተው ይመድባሉ። ይህም ሆኖ ነው እኛ ከኢትዮጵያዊነታችን በላይ ምንም የለም ነው የምንለው። ለእኛ ኢትዮጵያዊነትን መተው የማይደፈር አመክንዮ ነው። 

ከቶ ኢትዮጵያዊነት አልባ እንዴት መሽቶ ሊነጋ? እኔ መሬት ላይ ሲዊዘርላንድ የሠራሁት ሁሉ ነገር ለዛውም የዘመኑ አውራ ነኝ ባዮች፤ አጋፋው - ሰብስበው - ጠቅልለው ከማይጠግቡት የግራ ፖለቲካኛ ህልመኞች ዕጣ ነፍሴን እዬታገልኩኝ ድርጅት ነኝ ከሚለው ባላይ የተከወኑት ኢትዮጵያዊ ተግባርት ራሱ ከጫፌ ድርሽ አይልም።  

ቋንቋዬ ኢትዮጵያዊነት ነው። የፊደል ገበታዬ ኢትዮጵያዊነት ነው። እማገኛቸው ሰዎች ሁሉ አማራ ነኝ ብዬ ነግሬያቸው አላውቅም። አሁን እንኳን አልለውም እንኳን በቀደመው ጊዜ። አንድ ጊዜ በሰባዕዊ መብት ዙሪያ ከአንድ ድርጅት ጋር እሰራ ነበር፤ አለቃዬ የህግ ባለሙያ ነበረች። ቢሮዋ ውስጥ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ልሙጡ ሰንደቅዓላማ ነበር። ዛሬ ከአንድም የመንግሥት አካላት ቢሮ ኢትዮጵያ ውስጥ ያ ልሙጥ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ የለም። እንዲያውም ህገ መንግሥት ተጣሰ ኡኡታ ነው ለዚህ ነው መስቀል በፋቲክ እንዲከበር የተደረገው።

የእኔ መጻህፍቶቼ ላይ ቃሉ እራሱ አማራ የሚል አልተጻፈም። ክብር ሲባል፤ ማዕረግ ሲባል፤ ገድል ሲባል፤ መንፈስ ሲባል ከኢትዮጵያዊነት በላይ የለም። አማራ ለኢትዮጵያዊነት ትንፋሹ ነው። 

ልዕልት ቤቲ ታፈሰ ውሃ ልክነ ነን ትላላችሁ ብላ ነበር ዶር ደስአለኝ ጫኔን የሞገተችው፤ በውነቱ ለአማራ ህዝብ ውሃ ልክነት ያነሰዋል ትንፋሹ ነው ለኢትዮጵያዊነት። ዛሬስ ቢሆን? የት ላይ ነው ያለው ኢትዮጵያዊነት? እንጅባራ ሰማይ እኮ መስክሮታል። የምድሩን እማ ብለን ብለን ሰሚ ስናጣ እዮር ሥራውን ራሱ ሰራው።  


27 ዓመቱን እራሱን እያስጠፋ ያው አሁን አሁን አንደበት ላይ ብቻ ቢሆንም ኢትዮጵያዊነትን ለቀን ያደረስ መንፈሱን ያቆዬው እኮ እሱ ራሱ አማራ ተማግዶ  ነው።  ኢትዮጵያዊነት እኮ የሚተን አይደለም። በልባቸው ኢትዮጵያን የሚጠሉ ሰዎች ብቻ ናቸው አማራን የሚጠሉት። በልባቸው በኢትዮጵያዊነት ቂም የቋጠሩ ብቻ ናቸው አማራን የሚጠሉት።

ራሱ ከአማራ ጋር የሚደረገው ድርድር ያልታሸ ነው ያለው የእነ አቶ ሌንጮ ድርጅት፤ ሰማያዊ ፓርቲን የአማራ ድርጅት ነው ያሉትም እነሱው ናቸው። አሁን ኦሮሞ ፈርስት የሚሉን። ሰማያዊ ህብረ ብሄር ፓርቲ ነው።

የአቶ ሌንጮ ለታ ድርጅት ከግንቦት 7 ጋር ጋብቻ የፈጸሙት ሊቀመንበሩ አማራ ስላልሆኑ ብቻ ነው። ኤርትራም ከሌላው በተለዬ ለግንቦት 7 ያን ያህል ሙሉ የሎጅስቲከስ ድጋፍ ያደረገችው ሊቀመንበሩ አማራ ስላልሆኑ ነው። 


ኮ/ ታደስ ሙሉነህንማ እማ አዬን።  የኢትዮጵያ መንግሥት እራሱ አሁን ከሆነ አጉልቶ የሚቀድሰው ግንቦት 7  ሊቀመንበሩ አማራ ስላልሆኑ ነው። ይህ ዕውነት መደፈር አለበት። አንድም ተጋሩ በአንደበቱ የአማራ ሊሂቃን ሥም ደፍሮ መጥራት አይችልም። 

ስለምን ቢባል አማራ መሪ ከሆነ የኢትዮጵያ ክብር መመለሱ አይቀሬ መሆኑን ያውቁታል። ዘር ያለበት እንኳን አይፈልጉትም። ሌላው አማራ ለእናት አገሩ  ዋልታ እና ማገርነቱ የእውነት ነው። ኢትዮጵያዊነት የወረት ወይንም የታይታ አይደለም ለአማራ። ለአማራ ሁለመናችን ጠረናች ኢትዮጵያዊነት ነው። 

ሞገሳችን ኢትዮጵያዊነት ስለሆነ ነው ትምክህተኞች ነፍጠኞች የምንባለው። ነፍጥ እና አልገዛማም ባይነት ነው አገር ያቆዬው። ትምክህተኝነት አልገዛም ባይነት ነው በነፃነት ለመደራደር ነው። አማራነት ልክ እንደ ኢትዮጵያዊነት ባርነትን ባንዳነት ይጠዬፋል። 

ኢትዮጵያዊነትን አማራ ሲፈጠረብት ለመሸጋጋሪያ ድልድይነት አይደለም ወይንም ቀን ለማሳለፊያነት አይደለም ወይንም ተሸብልሎ ለመሸብለል አይደለም ጸሐዩ ለማድርግ ነው። ልዕናው ለማድረግ፤ እጬጌው ለማድረግ ነው። ሐቁ ይህ ነው። ቢገላብጥ ቢወላልቅ ፈርሶ ቢሰራ አማራ በውስጡ ኢትዮጵያዊነት ነው ያለው፤ በአማራ ህሊና፤ በአማራ መንፈስ፤ በአማራ አንጎል ውስጥ ያለችው ሐገረ ኢትዮጵያ ናት።

ይህ ሁሉ መገፋት፤ ይህ ሁሉ በረድ፤ ይህ ሁሉ እሳተ ጎመራ ባጅቶበትም አሁንም አማራ ኢትዮጵያ ብሎ ለመጣ መሪው ለዶር አብይ አህመድ በሚገርም ሁኔታ የውስጡ ልብ አድርጓቸዋል። ካለምንም ቅደመ ሁኔታ። ምናቸውንም ሳያይ። የኦነግ  የአቀባበል ዝግጅት ላይ ከቶ የአብዩ ፎቶ ነበርን? አይታሰብም። እኔ እምለው እንዲህ ነው …. በፌክ ኢትዮጵያዊነት ሊጀመር ይቻላል ሊቀጥል ግን አይቻልም፤ 

… ዶር ለማ መገርሳም „ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነው“ ሲሉን በቅጽበት ሆ! ብለን ከጎናቸው ነው የተሰለፍነው። አሁን ያለበትን ሁኔታ ልባቸው ነው የሚያውቀው፤ ይጽደቁበት ይፍለቁበት ይተከሉበት እኛ አናውቀውም። 
አማራ ኢትዮጵያዊነትን የሚመጥን አቅም ላለው ለማንኛውም ሊሂቅ ልቡ ክፍት ነው። ትናንትም ልቡን አልተዘጋም፤ ዛሬም ልቡ አልተዘጋም ወደፊትም አይዛጋም።

ይቅርታ እማልጠይቀበት አሁን እነ አቶ ሌንጮ ለታ እንዴት ብለው ነው በምንስ ሞራል ነው በብሄራዊ ደረጃ ካሉ መዋቅሮች ውስጥ የሚሠሩት? ኦሮምያ ላይ ይቻላሉ፤ በብሄራዊ ደረጃ ለዬትኛውም የኃላፊነት ደረጃ ግን ተረብ ነው። ቁርጡን ነግረውታል  ለኢትዮጵያ መንግሥት።

ይጠቃለል ---  ጎንደሪት ሥርጉትሻም በዛ ተገፊ ተጋፍታሪ ባጣ ቆዬኝ መንደር በጎንደሮች ብሂል ነገረ ዛሬ እስቲ ብሂሎች ይከውን „ቁርጥ ያጠግባል!“


ኢትዮጵያዊነት ተፈሪነት ነው!
ኢትዮጵያዊነት ከዕውቀት በላይ ነው!
ኢትዮጵያዊነት የጥበብ ነባቢት ነው!
ኢትዮጵያዊነት ዘመን አሻጋሪ ማንነት ነው!
ኢትዮጵያዊነት ዕጹብ ድንቅ ደማቅ ሥነ - ህይወት ነው! …  


የኔዎቹ የልቦቼ ኑሩልኝ።


መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።