አቶ ዳውድ ኢብሳ የኢትዮጵያን መንግሥት እያስደገደጉት ነውን?

አቶ ዳውድ ኢብሳ  የኢትዮጵያን መንግሥት እያስደገደጉት ነውን?

„አንተን በፍራሃት ወደ ቅድስናህ መቅደስ እሰግዳለሁ።“
መዝሙር ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፯
ከሥርጉተ©ሥላሴ
14.10.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።

አቶ ካሳሁን ጎፌ መግለጫን የገባኝን ያህል ስጥፈው ቆፍጠን ያለ ነው ድፍረቱ ከኖረ ብዬ ነበር። አቃለው አሳንሰው ሲዩትም ደግሞ አይደለም ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለመካከለኛው ምስራቅም አስጊ ነው ብዬ ነበር።
የአፍ ወልምታ ለተባለውም ያልኩትን ብያለሁኝ። ሲጀመርም እኔ የአቶ ዳውድ ትምህክት መሰረት እንዳለው፤ በቀላል መታዬት እንደሌለበት ሞገደኛ እና ከባድ ውሳኔ ስለመሆኑ ገልጫለሁኝ። የ5ቱ የ ኦሮሞ ድርጅቶች ውሳኔም ከዚህ ጋር የሚዋደድ ነው።

አሁን ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ በስኳር ፖለቲካ ኢትዮጵያ እንደ ገቡ አዳመጥኩኝ። ፍቅሩን ያሰንብትላቸው እንጂ እፍ ብለዋል። የጣሊያኑ መሪ ወደ ዛው አቅንተው እንደ ነበርም አድምጠን ነበር። እና ተመለሱ ይሆን ወይንስ ምጥዋ ላይ ተበለስ ጋር?

ከዙፋን አስወርዶ በጥድፊያ ያሰመጣው የኤርትራን መንግሥት ምን ቢኖር ነው ብለን ማሰብ ግድ አለን። ደረታቸው ነፍተው ሲናገሩ የሰነበቱት አቶ ዳውድ ኢብሳ በሦስተኛ አገር ሽምግልና ከልሆና በጅ አልልም ያሉ ይመስላል።

ሌላ ከሚመጣም ወዳጃቸው አገር ብትሆንላቸው ይሻላቸዋል። ነገም በ አገርነት እንቀጥላልን ባይም ናቸው። ወጣት መሪም ታች ካለ በቂ ነው ብለዋል። ምርጫው የሳቸው ነው። ማን ደፍሮ ይናገራል ጭጭ ረጭ ሆኗል። ከእትጌ ኤርትራ ቤት ዘው ከተባለ መውጫ የለም፤ ወይ መዋጥ ወይ አብሮ መስመጥ ነው …

ግን ኢትዮጵያን ማን ነው እዬመራት ያለው? በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ኤርትራ ታጣዋለች ተብሎ የታሰበው ረጅም እጅ ይሁነኝ ተብሏል። ኦዴፓ እንዲህ ሆኖ ይነጣፋል የሚል ግምት አልነበረኝም። ዕድሜ ለኢምሬት የዶራል አሞሌ።

እንደሚታዬው ኦሮምያ ክልል አቅም አንሶታል፤ ሦስት ም/ፕሬዚዳንት አስመርጧል። አሁን ደግሞ ሁለት ምክትል ጠ/ ሚር እንጠብቅ ይሆን በፌድራል ደረጃ?  ውጭ ጉዳይም የሰማነው ሰምተናል። ከዚያም ያለፈ ነገ እንደሚመጣ ይታሰባል። አብይ ብቻውን ፈትልክ ማለት ተስሜን አሜሪካ ጉዞ መልስ አይፈቀድለትም።

በነገራችን ላይ በተባበሩት መንግሥታት ጉባኤ ስረዛም ሚስጢሩ ይኸው ነው። ጀርመን ላይም ኦዴፓ ጠንካራ የደህንነቱ ጠባቂ መረጃ ሰጪ ካለገኝ ፈትለክ የለም። ውጭ ጉዳይ ሚ/ር ላይ መፈንቅለ መንፈስ አድራጊዎቹ ዶር ወርቅነህ ገበዬሁን አላመኗቸውም። ለሌላም የሽግግር ሁነት አይመችም።

ውዴቼ የት ሄዱ እነዚህ የፕለይ ጸሐፊዎች ድንገቴ ፖለቲካ እኮ እስከ አንገት ማሰሪያችን አጠገበን። ምን አለ ትንሽ ጫርጫር አድርገው ከጥበብ ጋር ቢያዋድዱት። ትናት ወታደራዊ አመጽ ነበር እንደ ሮብ ራዲዮን ዘጋባ። 

የታህሳሱ ግርግር ገጠመኝ ተበራከተ። ... የሰኔው፤ የሐምሌው፤ የመስከረሙ አሁን ደግሞ የጥቅምቱ ግርግር በዕለተ ሩቡ የድህንት ጾም ዕለት ነበር የተከሰተው። ለነገሩ አሁን የፈቃድ ፆም የእመቤቴ አለ። ጽጌ ፆም ይባላል።

ብቻ ድፍንፍን እድርገው እፍን አድርገው ቢይዙትም ውልብልቢቱ አልጠፋም … ከቶ ህዳር ላይ የመጨረሻውን የኩዴታ ሙከራ ስኬት እንሰበውን ይሆን?

ያው እኔ እደተለመደው ተግባሬን አብይን ፍለጋ ነኝ …

የኔዎቹ የጥበብ አምላክ ሚስጢር ይግለጥ።
ኑሩልኝ። መሸቢያ ግዜ።



አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።