አህዱ ራዲዮ እና ዕድምታው በጥቂቱ።

አህዱ አሰገዱ።
„ተግሳጹን ተቀበሉ ጌታ እንዳይቆጣ፤ እናንተም
በመንገድ እንዳትጠፉ ቁጣው ፈጥና ትነዳለችና።
መዝሙር ፪ ምዕራፍ ፲፪
ከሥርጉተ©ሥላሴ
12.10.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።

                                             የላቀው ሊሂቅ!
  • ·      ራሞተ ሰሞናቱ።፡

አህዱ በሚባል ራዲዮ አቶ ሌንጮ ለታ እና አቶ በቀለ ገርባ ቃለ ምልልስ አድርገዋል። ትንሽ በትንሹ እንዬው እስቲ ብዬ አስባለሁኝ። በውይይቱ የተሻለ የመልስ መስጠት ጥበብ በአቶ ሌንጮ ለታ አይቻለሁኝ ስልታዊ እና ግልጻዊ ለመሆን ጥረዋል። የአቶ በቀለ ገርባ ደግሞ ወደ መንፈስ ለመቀረብ ማዶኛ ሆኗል - ለእኔ። ያልመድኩት ነገር የሳቸው ጉዳይ ነው። ጊዜ ያስፈልገኛል። 

አድማጮች ሲጠይቁ ነበር። ጠያቂዎች እና አስተያዬት ሰጪዎች አቶ ሌንጮ ለታን ከፍ አድርገው „ክቡር“ እያሉ ማቅረባቸው አቶ በቀለ ገርባን አልተመቻቸውም የመረጋጋት ሁኔታ አላዬሁባቸውም። እኔ ሁለመናን ነው የምከተታለው። 

ይህን ሳይ ሚሊዮኖች የሰገዱለት  የአብይ ለማ ፍቅረ አክብሮት እንዴት እንዳስተናገዱት ወፌን ጠይቅኳት። ይገባል አይደል። በሁለቱ ሊሂቃንም ብዙ ሰው ነው የሚጸፈው አክብሮ። ወዶ ናፍቆ አልቆ እና .... እናማ አቶ ሌንጮ ለታን አምስገነው አድማጮች ሲናገሩ ፊድባኩን ለኩት፤ 

ይህን ወስጠቱን ቪዲዮውን እያዬ መገመት ነው።

አቶ በቀለ ገርባ አቶ ሌንጮ ለታ በአሐዱ ሬዲዮ bekele gerba lencho leta interview on ahadu radio


አቶ በቀለ ገርባ ባላፈውም ጊዜ ሥሜ በክፉ ተነሳ፤ እን እከሌ አሳንሰው አዩኝ  ብለው እንደ ነበርም አዳምጫለሁኝ። ይህን የፖለቲካ ሊሂቅ ከመሆን በፊት መወሰን ያለበት ነው።

የሆነ ሆኖ እስከ ተባበሩት መንግሥታት የመምራት የሞራል አቅም አላቸው ብለን እኮ ጽፈናል። ፈልጎ ማንበብ ነው በዬጊዜው የተሰጠውን የቅን ኢትዮጵያውያንን ሪኮመንዴሽን።

ይህም ብቻ አይደለም ጎንደር እኮ መሪዬ ብሎ ሞትን የፈቀደበት አመክንዮ አስበነው ለነበረው የብልህ መሪነት ክህሎት ልዩ ሽልማት ነበር። ጎንደር ለሳቸው የሰጠውን ለማንም አልሰጠም። 

ይልቅ አሁን በሁሉም ቤት አብዩ መንገሡን እያዳመጥኩኝ ነው። ክብርን አስጠብቆ መቀጠል የራስ ጉዳይ ነው። „ከአነጋጋር ይፈረዳል ከአያያዝ ይቀደዳል“ እንዲሉ … መቼም ዶር አብይ አህመድ እና ዶር ለማ መገርሳ ከዚህ ያውጣቸው ብለናል ... የጥበብ ትንፋሽ ትቅረባቸው፤ አፍቅሮተ ህዝብ ከሜዳ የሚታፈስ ከችርቻሮ የሚገዛ አይደለም።  

የሆነ ሆኖ ዘመን መስታውት ነው ያዬነውን አዬን ያዳመጥነውን አዳመጥን። በቅንነታችን ስለሚገጥመው እክል ቅንነትን የማስተናገድ አቅም ያነሰው ይጨነቅበት። ወገኖቼ አይደላችሁም ያለው ይባትልበት፤ ዕድሜ ልኩን መቆርቆር የቤት ሥራው ይሁን። እኛ ምን ሲገደን። መልካምነት የህሊና ስንቅ ነው። አክብሮትም የኢትዮጵያዊነት የማንነት ማርዳ ነው። ኢትዮጵያዊነት ከዕውቀትም ከማናቸውም አምክንዮም በላይ ነው።

የሆነ ሆኖ መሪነት በመቻል ወስጥ ነው። ሁለመናው ሊፈተሽ ያልፈቀደ ሊሂቅ ሰብሰብ ብሎ ቤቱን ከርችሞ መቀመጥ ነው። ወቃሳ ተፈርቶ፤ ነቀሳ ተሸሽቶ፤ ሙግት በሩቁ ሆኖ ህዝብ እምራለሁ ብሎ ማሰቡ ራሱ የተገባ አይደለም። መሪነት ድፈረትን ይጠይቃል። ወኔው በ እውነት ወስጥ ሆኖ ስለሆነ ነገር እንጂ ስለመሰለው ነገር ጉዳዩ አይደለም ለአንድ የህዝብ እረኛ ሙሴ። 

መቻል ነው ፊት ለፊት ወጥቶ የአደባባይ ሰው ከሆኑ በኋዋል። ሁልጊዜ ፋሲካ የለም። ሲኦልም እንዳለ ማሰብ ይበጃል። አቶ በቀለ ገርባን በሚመለከት የዓለም ሚዲያ የሰባዕዊ ድርጅቶች ሁሉ ሚዛናቸውን የሚያሰተካክሉበት ሁኔታ ተፈጥሯል።
  • ·      ኦነግ እና ሰሞናቱ።   

አቶ ሌንጮ ለታ በዚህ ዙሪያ ለቀረበላቸው ጥያቄ እነሱን ጠይቁ ብለዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦነግ ስምምነት አናውቀውም የሚለው ዕድምታ የሁለቱም የኦሮሞ ሊሂቃን ዕድምታ ነው። እኔም እንዲሁ ነው የጻፍኩት። እንኳንስ እኛ የኢህዴግ አጋር የሚባሉ ድርጅቶች በምን ሁኔታ ስምምነቱ እንደተካሄደ የሚያውቁት አይመስለኝም። እንዲያውም እኔ ስጽፍ ሽንቁር አለበት ብያለሁኝ። ከድኜ መተው ስላሰኘኝ።

በሌላ በኩል ግንጫ እና አንቦ ወጣቶች ባዶ እጃቸውን ሞት ጋር ሲጋፈጡ ታጣቂ ከነበረው ኦነግ ያን ግዜ የት ነበር በሚል የሚገርም አመክንዮ አንስተዋል አቶ ሌንጮ ለታ።  ያው የቄሮ እንቅስቃሴ ከከፊል ሽዋም ያለፈ አልነበረም። አቶ ልንጮ ለታ የት ነበር ኦነግ ወጣቶች ገዢውን መንግሥት በባዶ እጅ ሲጋፈጡ ሲሉ ይህ ለኦነግ ብቻ ሳይሆን ኤርትራ ነበር ለሚሉት የቧልት ማህበርተኞች ሁሉ ጥቃት ያወጣ አጽህኖታዊ አስተምህሮ ነው። ሌላም አለ ነገ ይመጣበታል። 
  
በሌላ በኩል ግን ሰላማዊ ትግል ምርጫዬ ነው ያለው ኦፌኮ ከኦነግ ጋር እስራለሁ ሲል በምን ሁኔታ ይሆን የተሰማማው? ይህን የኢትዮጵያ ህዝብ መጠዬቅ አለበት። ኦፌኮም ጫካው ጠማኝ ሊል ይሆን በቀጣዮቹ ጊዜያት? አሁን አሁን ደግሞ ምቾት ሰጊድ ለኪ ማለቱን እያስተዋልን ነው።

መቼም ኦፌኮ ለኦነግ ዓርማ ግንባር ቀደም ተሟጋች መሆኑ ብቻ ሳይሆን የ150 ዓመት ስትራቴጃዊ ትግላችን ለድል በቃ ሲል በአደባባይ በአቶ በቀለ ገርባ አማካኝነት አድምጠናል። ኦፌኮ ከዚህም አልፎ ርስት ቆጠራ ላይ ስለመሆኑም አደምጠናል። እና ኦፌኮ ከኦነግ ጋር ያለው ሁኔታ ምን ይሆን ሚስጢሩ? መመርመር፤ መጠናት ያለበት ይህው ነው። ነገም ይህን በዚህ ዙሪያ እቀጥልበታለሁኝ።

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ የመንፈስ ሚስጢር  ነው።

የእኔዎቹ ኑሩልኝ።

ማለፊያ ጊዜ።  

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።