ልጥፎች

To Toni Loba, Good Luck Wishes!

ምስል
·          Toni Loba የፍቅር ጠይም ዕንቁ!   ሌላው በሦስተኛ ደረጃ አሁን የፊታችን ሃሙስ እንደ አውሮፓወያኑ አቆጣጠር ግንቦት 24. 2018 ወደ 15ሺህ ተመልካች ታዳሚ በሚገኝበት የጀርመን የ2018 የሞድ አሸናፊ Germeny Next Topmodel 2018 (GNTM) ውድድር በደም ሐረግ ዘሯ አፍሪካዊ ናይጀሪያዊቷ በጀርመን ሽቶትጋርድ የምትኖረውን ቶኒ ትሆናለች ብዬ ነው እማስበው፤ ሦስት ተጨማሪ ተፈታኞችም አሉባት አንዷ እንደሷ ከጠይምነት ወደ ዳማነት ያደላች ናት። ለነገሩ ጥርጣሬም የለኝም ። ይህ ውድድር ለረጅም ጊዚያት ከቦታ ቦታ እዬተነቀሳቀሱ በጋራ በመኖር የሚካሄድ ሲሆን ወላጆች ሥራቸውን በአግባቡ ስለማይሰሩ ፕሮጀክቱን ለሚመረቱ ለዓለም አቀፍ ሞዴሏ፤ የቴሌቪዠን ሞደሬተሯ፤ ለዳኛዋ ለወይዘሮ ሃይዲ ክሉም እና ለአጋር ዳኞቻቸው እንዲሁም ለተሳታፊ የካሜራው ቲም ሁሉ ብዙ ፈተና በዬዘመኑ ይገጥማል። ሰብዕናቸው ያልጠኑ ተወዳዳሪዎች ከዘርኝነቱ ጋር ተዳምሮ ወይንም ከበታችነቱ ጋር ታክሎ ፈተናው በጣም ያዬለ ነው። ለዚህም ነው እኔ ወላጆች ልጆቻቸውን እንዴት ማሳደግ አለባቸው፤ የልጆቻቸውን ራዕይ ለማሰካት ምን ላይ ቢያተኩሩ መልካም ይሆናል የሚለውን „ የተስፋ በርን“ እንድጽፍ የተገደድኩበት አብዩ ምክንያት። ልጆች የማይገኘውን ዕድላቸውን በሥነ - ምግባር አቅም ማነስ፤ ወይንም ራስን ችሎ በመቆም አቅም መሳሳት፤ ወይንም በህሊና እንጻ ድህነት ምክንያት ወርቁን አጋጣሚ ያጡታል። እኔ ስለመጪው ነገረ ዓለም ያስጨንቀኛል። ትውልድ በአግባቡ ካልተገነባ አህጉርም፤ ዓለምም፤ አገርም እንዳለ አይቆጠርም። እኔ የማዬው ግድፈት በሠለጠነው አለም ይሁን ባልሰለጠነው ዓለም በትውልድ አገነባብ ላይ ያለው ትጋት አንድ አቅጣጫ ብቻ የተከተለ

Prinz Harry und Meghan. (Braun Diamond.)

ምስል
                                       የቡኒ ሚስጢር የብሌን ድምጽ ነው፤                           የጠይም ዕንቁ ቅኔም ነው!                                         ከሥርጉተ ሥላሴ 19.05.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ)                               „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤ እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“ (ምሳሌ ምዕራፍ ፲፮ ቁጥር ፱) ·                  መኖር ሲያምርበት። ዛሬን እጅግ ሐሤት ወደ አገኘሁበት ነጥብ አብረን ብያለሁኝ። የንጉሣውያን ታሪክ የምመሰጥበት ዋነኛ መስክ ነው። በዛ ውስጥ ያለው ሀገራዊ፤ ሃይማኖታዊ፤ ታሪካዊ፤ ትውፊታዊ ቅርስ ሰብዕናን በማነጽ ረገድ ያለው ሞራላዊ አመከንዮ ቀልቤን ይገዛዋል። አውሮፓ ላይ የሚኖሩ ንጉሣዊ ሥርዓቶችን፤ መሰናዶዎችን ሁሉ አቅጄ ፕሮግራም ይዤ እከታተላቸዋለሁኝ። በዚህ ዘርፍ ኢትዮጵያ ዲታ ነበረች ግን ፈቅደን አነደድነው። የ3 ሺህ ዘመናት ታሪክ አለን ስንል ያወራረድነው ኩራታችን በማንደድ ነው። ማንደዱም ብቻ አይደለም - አገለልነው። ማግለልም ብቻ አይደለም ተጸዬፍነው። ግን የክብር ክብር፤ የልዕና ልዕልና የዕንቁ ዕንቁ የቡኔ ዕንቁ ቅኔያዊ የሚስጥር ዕዮር ነበር። ብልሆች አይደለንም። ታላቁን ዓለም አቀፍ የመንፈስ የገብያ አዳራሸን ነው የደረመስነው - ፈቅደን። በአሁኑ የሥልጣን ሽግግር ትንሽ ወደ ራሳችን ተመልስን ግራማችን ሁንበት ያልነበት መንፈስ እና ምልክት ታይቷል። በዚህ ተጽናንቻለሁኝ። መልካሙ ነገር መልካምነት እንጂ ክፉነትን አይደለም የሚያሰረክበን። ብናውቅበት! ስስነታችን አሳስቶ ብቄተ ቢስ አደረገን። እንኳንስ ልንወዳደር ቀርቶ ጭንቅላታችን አንገታ

አቤ ጎቤ ህያው ነህ!

ምስል
                የጥቃት ማርከሻው                  አቤ   ጎቤ ህያው ነህ !                ( ሥርጉተ – ሥላሴ )                       ከሥርጉተ – ሥላሴ፤ ከጭምቷ – ሲዊዘርላንድ። (16.02.2018)           „ የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤ እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል። “  ( ምሳሌ ምዕራፍ ፲፮ ቁጥር ፱ ) የውስጥነት ማርዳ፤ የመሆን አንባነህ፤ ደመሙቅ ሳተና ውለታ ብዙነህ። አንተ የእኛ ቤዛ የክብር ቀለም፤ ቀስተዳመና ላይ ህላዊ ለምለም። ደምህ ተቆጥቶ ሲጠራህ ጫካው፤ ቃልን አዋውለህ በነፍስህ ጠለፍከው፤ ኪዳንን አድርሰህ ሰማዕትን ሸለምከው ። መከታ የሆንካት ለዛች የዕንባ ዕንክብል፤ አለሁልሽ - ም፤ ያልካት የችሎት አንበል። አንተ የእኔ ጌታ ! ያራራይ መዝሙር፤ አንተ የእኔ ጀግና ! የግዕዝ ገበር። ጥቃትን ያወጣህ የዕዝል ቀንዲል፤ ተምሳሌት አባት የተግባር ሰብል። የኔታ ልበልህ የደምጥሪኝ ግሥ፤ አባ ጎቤ ታጠቅ የአንበሳ ልሳን። በሥምህ ድል ይሁን ትውልድ ይቀስስ፤ ደምመላሽ ተፋሲል የኲራት ቆሞስ። እንደ ጠፋ አይቀርም፤ አንደ ጨለመባት፤ ጭምትነት ያጫት፤ የአብሮነት ፍቅር ናት። ቀኗ አይቀርምና ገስግሶ ይስማት፤ ገላድ ይቀድሳት ብሥራትን ያሰማት። የ 44 ቱ እናት የጥንት የጥዋቷ፤ የነብዮ ልሳን ግማደ – ሟተቷ። ሰለቷ ይሰምራል ምንታምር ትውፊቷ፤ የአንጀት መልዕክት ያላት ተደሞ ማሚቷ ። መታሰቢያነቱ፤ እንደ ተናፈቀ በሥጋ ለተለ

ጆሲ፤

ምስል
                  የቸርነት አንበል።            ከሥርጉተ ሥላሴ 09.04.2018 ( ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። )      „ አምላካችን መጠጊያችንና ሃይላችን፤ ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው። “  ( መዝሙር ፵፭ ቁጥር ፩ ) ·          መነሻ። https://www.youtube.com/watch?v=tg9U4fMMNfU „Ethiopia: ጆሲ በፋሲካ በዓል ከቤታቸው ተፈናቀሉ ዜጎች ያደረገላቸው “ ·          የቸርነት አንበሉ ወጣት ድምጽ፤ „ ተጣልተን ከኖርንበት ጊዜ በፍቅር የኖርንበት ጊዜ ይበልጣል። ኢትጵያዊነት መልካምነት። እኛ ኢትዮጵውያን ፈጣሪ ሰውን ሲፈጠር አብረን ተፈጥረናል። ለዚህ ምስክሩም ከአንድ አባት እናት ተወልደን እንኳን ቀለማችን ይለያያል። በፍቅር አብረን እንኖራለን ! “                    ·          እንዲህም ሆነ … ልክ በእኛ በሲዊዝ ሰዓት አቆጣጠር 22.18 ነው። ክምሽቱ 4 ሰዓት ከአስራ ስምንት ደቂቃ። „ እጬጌ ሂደትን “ ወግ ቢጤ ጹሑፍ ጨርሼ ለማከብረው ለሳተናው ቀድሜ ከተወሰነ ደቂቃ በፊት ልኬለታለሁኝ። ሰውነቴ ስለዛለ ለቅለቅ አልኩኝ። ሻማዬን አብርቼ የተለመደውን አደረስኩ። አንቅልፌን ለማባባል ጋዳም ብዬ ከመተኛቴ በፊትም እናት ሐገሬ ልዕልት ኢትዮጵያ እንዴት ዋልሽ፤ አመሸሽ ለማለት ቴሌቬዢኔን ከፍቼ ዩቱብ ሳይ መጀመሪያ ጅጅጋ ላይ ለብሄራዊ ሰንደቃችን የተሰጠውን ታላቅ ክብር በኢትጵያ የመወድስ የክብር ሙዚቃ ተቀነባባሮ አዳመጥኩኝ። „ ለቀላሃ የምናውለውን መዋለ ንዋይ