ሌላስ? ህም ተዚህ፤ ህም ተዚያ፤ ህም ተዚያ ማዶ!

 ጭላጭ ሳይስቀሩ … 
እም እንዳይሆን
ስለ ጸዮን ዝም አልልም፤ ስለ እየሩሳሌም ጸጥ አልልም፤ 
ጽድቅዋ እንደ ጸዳል፤ መዳናዋም እንደሚያበራ 
እስኪወጣ ድረስ። 
ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፷፪ ቁጥር ፩
ከሥርጉተ©ሥላሴ
07.09.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።

የሚገርሙኝ ነገሮች የበረከተበት ወር ነበር ነሃሴ። ብዙ ብርካታ የሚባሉ ጉዳዮችን አስተውያለሁኝ። ዛሬም እንደ ትናቱ የሞገድ ጉጉሱ እንደ ተጠበቀ ሆኖ። ትልቁ ጥያቄ ግን ወያኔ ሃርነት ትግራይ ተዳክሟል ወይ የሚለው ጉዳይ ነው ለእኔ ለህሊናዬ ቅርብ የሆነው፤ ዕውን ወያኔ ሃርነት ትግራይ ተዳክሟል ወይ ትልቁ አምክንዮ ነው - ልንዘናጋበት የማይገባው።

እርግጥ ነው ወያኔ ሃርነት ትግራይ አንድ ክንፉን ተመቷል ከሰሞናቱ። ችግሩን ከእርሱ ብዙ ማይልስ ርቆ መሬት ሲያስነጥስ፤ የራሱንም ህዝቤ የሚለውን ዕንቁውን ሳያስጨንቅ  በዕንባም ሳያሳጥብ "በሞኝ ክንድ" እንዲሉ መፈተኛው ሌላ ቦታ ነው፤ የምስራቅ ኢትዮጵያን ህዝብን ሲያስለቅስ የቆዬበት ሁኔታ የመፍትሄ አሰጣጥ ዘይቤን ብዙ ሰው አላስተዋለውም፤ ልብም አላለውም፤ አላደነቀውም፤ ዕውቅና ለመስጠት አልደፈረውም እንጂ የኢትዮ ሱማሌ ጉዳይን መስመር ለመሳያዝ የተሄደበት መንገድ እጅግ ዘመናዊ፤ ስልጡን ብቻ ሳይሆን እምነት የሚያስጥል ነው።

ዶር አብይ አህመድ የመጨረሻውን የእውቀት ደረጃ ያዋዋሉበት ሙያ የሰላም እና የደህንነት ነው፤ ጥበብ መሬት ላይ በውን በዳግሚያ ትንሳኤነት እንዲታይ የተደረገበት፤ ከተከናወኑት ግዙፍ አገራዊ ጉዳዮች እንደ አንዱ ሊታይ የሚገባው ነው በሥርጉተ ዕድምታ። ልክ እንደ ኢትዮ ኤርትራ።

እውነት ለመናገር በዚህ በአጭር ጊዜ ውስጥ ይህን መሰል የመንፈስ ተረገጥ ልዕልና ይገኛል ብዬ አስቤ አልነበረኩም እኔ በግሌ። ይህ ማለት ግን አሁን ችግር አይፈጠርም እያልኩኝ አይደለም። ብቻ በዚያ አካባቢ OMN ሳይቀር በርካታ የእሳት መጫሪያ ስብርባሪ ገሎችን አቅራቢ እንደ ነበረ አስተውል ነበር። ለቀውስ ፈጠራ እና ለውጡን ላማሳጠት ትልቁ የመንፈስ ማረፊያ እንደ ስለት ልጅም ይታይ የነበረው ይህው ክልል ነበር። "ቁጭ ብሎ አብይ ሥራውን ስለምን አይሠራም" የሚለው ስሞታ ሸማቃ ይህው አምክንዮ ነበር። 

ብቻ ኦብነግ እና ኦነግን ያህል ድርጅት ግባ በለው ብለህ ችግር አይኖርም ብሎ ለመደምደም ባይቻልም፤ የቀወሱ አፈታቱ ጥልቅታዊ ዘዴ ግን የልቤ የሚባልለት ነው። የአማራር ብቃት ከሥም በላይ ሃሳብን የመድረግ ክህሎት የታዬበት ዕጹብ ነበር ማለት እችላለሁኝ።

ችግርን በሚመለከት በሌላ በኩልም እሰከ አጥቢያ አድባር ድረስ የአመራር የጥራት ችግር፤ የመዋቅር ችግር፤ የአደረጃጃት ችግር ገና ብዙ ተጋድሎን ይጠይቃል። ዋናው እንብርት ጉዳይ ግን የኢትዮ ሱማሌ ክልል አዲሱ ተመራጭ መሪው የሰብዕዊ መብት ተሟጋች መሆናቸው፤ የኢትዮ ሱማሌ አክቲቢስቶች ከሥልጣን እና ከዝና ባሻገር ለወገኖቻቸው ችግር ሊሰሩ የቆረጡ መሆናቸው ነው ተስፋ ሰጪ የሚያደርገው። እነሱ የሚያስደስቱኝ ሌላው ጉዳይ የኮፒራይት ሰለባዎች አለመሆናቸውም ጭምር ነው።

የኢትዮ ሱማሌ አክቲቢስቶች በራስ የመተማመን አቅማቸው ላይ ያለወጣ ወይንም ታች ያለወረደ ነው። ይህ ማለት ወደ አንባገነንም ወይንም ወደ የበታችንት ስሜትም ያልወረደ ተመጣጣኝ የመንፈስ ቁመና ላይ መገኘታቸው እጅግ አበረታቹ ፍሬ ነገር ነው። ለኢትዮ ሱማሌ ወጣቶችም ይህ ጠቃሚ ተምሳሌነትም ነው። ለትውልድ ግንባታ አትራፊም ነው። 

እንዲያውም ለእኔ በመንፈስ ልዕልና ደረጃ በጥራት ተጀመረ አዲሱ ለውጥ የምለው አካባቢ ቢኖር ኢትዮ ሱማሌን ብቻ ነው። ሌሎቹ የለውጥ አራማጆች ቢሆኑም ኦህዴድ እና ብአዴን በለውጥ ፈላጊዎችም ዘንድ በጣም የጎሹ ጉዳዮች አሉባቸው እኔ በርቀት እንደማዬው ከሆነ።

በራሳቸው ውስጥ ነጥረው ለመውጣት ችግር አለባቸው። ኦህዴድ የማንን ተልዕኮ ሙሉ ለሙሉ ተሸከመ ወይንም በአንፃራዊነትም ለማን ያደላል፤ ዝንባሌው የት ላይ ነው ለሚለው፤ ብአዴንም ስለምን ተፈጠረ ለሚለው መልስ የሚጠብቁ ፈታኝ ጉዳዮች ናቸው።
ሰውም ደፍሮ አይሄድባቸውም። የእኛ ነገረ ለብለብ ነው። አናበስለውም - አናሸውም አናተረትረውም  - እንፈትገውም በጥቅሉ መንሹ የለም በመዳፋችን።

እርግጥ ነው ኦህዴድ ላይ ያለው ችግር እንደ ብአዴኑ አይደለም። ቢያንስ ኦህዴድ ላይ ሥልጣናቸውን ለማስቀጠል የሚያስችል ሥራቸውን እዬሠሩ ነው፤ ራሱ ከድርጅቱ ውጪ ያሉ የኦሮሞ ልጆችን ከማዕከል ጀምሮ የተከፈተላቸው ዕድል ድንቅ ነው።

 ኦህዴድ ለኦሮሞ ልጆች ተቆርቋሪነቱም እጅ የሚያስቆረጥም ጣዕም አለው። ከሆኑም እንዲህ ጠቅልሎ መሆን፤ ከተውትም እርግፍ አድርጎ። ይህ የግብር ይውጣ ጉዳይ ነው ተንጠባጣቢ የሚያደርገውና።  

ብአዴኖች ግን በቀደመው የዥንጉርጉር መንፈስ ላይ ናቸው ያሉት። አይሏቸው ፌድራል መንግሥት ባህርዳር ላይ ናቸው ያሉት፤ በክልላቸው እራሱ ወሳኝም አይደሉም አቅማቸውም ይህን ያህል ነው። አይሞግቱም። የወያኔ ሃርነት ትግራይን ሩብ ያህል ጉልበት የላቸውም የእሺ ወታደሮች እንጂ የአይ ባለደረቦች አይደሉም።

ብቻ ብአዴኖች አይሏቸው የአማራ ክልላው መሪዎች፤ ብቻ ራሳቸውን የሚሸረሽር ተግባራትን ተግተው ልክ እንደ ዛሬ 43 ዓመቱ እዬሠሩ ነው። ብህዴን ነው የሚባለው ያ የሻገተው ድርጅታቸው፤ ምንም አልተጠመቁም እኮ ከዛው ላይ ነው ያሉትም። ዛሬም አቶ ታደስ ካሳ የሚነግሩንን ነው የሚነግሩን። „ከዬት መጣ አትበሉ ብቃት ብቻ እዩ“ አደንቋሪ የአሮጌ ቆርቆሮ ጮኽት ... ኮሽኮሼ፤ 

ብቻ ብሄራዊ መንግሥት ነን፤ አሳታፊ ነን፤ አቃፊ ነን ከሚል አጉል ትምክህት ጋር ተወጣጥረው አማራ የሚለውን ሥሙን ለላንቲካ ብቻ እንደ ንግድ ፈቃድ ሰርትፊኬት ይዘው የሄሮድስ መለስ ዜናው ሥነ-ልቦናው እንጂ ዘሩ ምን ያደርጋል ሊሂቃን ባዮችን እዬጋበዙ ልብ አውልቅ ተግባር ይከውናሉ።

ገራሚው ነገር ይህ ለአማራ ብቻ ነው የሚሰራ ፍልሰፍና ነው። መንገዱም አማራ ብቁ ልጆቹ ነጥረው የአገር መሪ የመሆን ዕድላቸው ተንኮላሽቶ እስከ ወዲኛው እስከማይታወቀው ዘመን ድርስ አምክኖ እንዲቀር የማድረግ። 

አማራ ተዋዳዳሪ፤ ተፎካካሪ እና ተመራጭ አቅም እንዳይኖረው ማክሳት።  ዋናውን የአማራ ድርጅት የሚባለውን ሥሙን፤ ዓርማውን ቢቀይሩትም የሚሠራ አይሆንም። ጭንቅላት ውስጥ ያለው ጣዖት ለማፍረስም፤ ላመስፈረስም ፈቃዱም የለም። አሁን ከዛው አይዲዮሎጆ ውስጥ እንደ ሰመጡ ሲለናቆጡ ነው የሚታዩት። አሁንም ፈሪዎች ናቸው። የተሰጣቸውን ብቻ ነው የሚጎርሱት።

ህብረ ብሄር ፓርቲ ነን በሚል ተግባሩን የፌድራሉን ሃላፊነት እንወጣለን ብለው አላቅማቸው ተንጠራርተው ነው የማያቸው። ስለ 13 መቶ ክ/ ዘመን ትምህርት ይዘህ መጥተህ አማራን በአራቱ ማዕዘን ለታዘዘበት የመንፈስ ጦርነት አድናለሁ ማለት ዘበት ነው። ስለሆነም ብአዴን ቁልፉ ጠፍቶበታል። የሌላ ብሄረሰቦችን ተወካይ ተሸክሞ ውክልናውንም ለእነሱ ለፌድራል እዬቀለበ እዬሰጠ፤ ራሱንም ሳይድን አብሮ ይወድቃታል። የመንታ እናት አይነት ነው የማዬው የጉድ ክምር …. 

ብአዴን ወይን ነጥሮ በአማራነቱ አልወጣ ወይ ነጥሮ አልበቃ! ወይ አላበቃ። ዝም ብሎ መትበስበስ ብቻ...

ወደ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ምልሰት ሳደርግ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ታላቁ ክንፉ ኢትዮ ሱማሌ ላይ ቢመታም እራሱን አጠናክሮ በማውጣት እረገድ አዳዲስ ምላጮችን ብቻ ሳይሆን ሺህ ሚሊዮን ሞረዶቹን ሸማምቶ አሁንም ማን ደፍሮኝ ብሎ በቀደመው የብሄራዊ ገዢነቱ ልክ ሥልጣኑ፤ አቅሙ ላይ በሁለተኛዋ ርዕሰ መዲና መቀሌ ላይ በሁሉም መስክ መንፈሱን አብቅቶ እና አደረጃቶ ህዝቡን በተጠንቀቅ ላይ አስቀምጦ የልቡን እዬሠራ ነው የሚገኘው። ትናንት „መቀሌ“ ተብላ የተሰዬመችው መርከብም ሥራ መጀመሯ ተበስሯል። ጎሽ ብለናል አይዋ ለውጥ። „መቀሌ>ኢትዮጵያ“

በሌላ በኩል አንድም ሰው ንክች ማደረግ አይችልም ፌድራሉ መንግሥቱ። የፈለገ ወንጀለኛ እዛ ሄዶ ይመሽጋል ነኪ ጠያቂ የለውም። ከትግራይ ክልል በሚሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ማናቸው ኢ-ሰባዕዊ ድርጊት ቢፊጸም ማዕከላዊ መንግሥት ትንፍሽ የለም። አቅሙ በአቅሙ ልክ ሙሉዑ እንደ ሆነ ነው የወያኔ ሃርነት ትግራይ።

ከሱዳን ጋርም ቢሆን በቀደመው ልዕለ አገርነት ልክ ግንኙነቱ አለ። ይህ ስጋት አይደለም ለማዕከላዊ መንግሥት ይሁን ለተፎካካሪ ፓርቲዎች፤ ስጋቱ የአማራ መደራጀት እና አማራ ነኝ ማለት ነው መከራ ሸክም ግማድ ሆኖ ያለው። ተገንጣይነትን የልቤ ያሉት ድርጅቶችም ሆኑ አክቲቢስቶችም ስጋት አይደሉም። አማራ ብቻ ነው ስጋቱ። 

በዚህ ሁኔታ ነው አንድም ሰው ለዘር ሳይበቃ ልቅምቅም ብሎ ሁሉም አገር እዬገባ ነው ያለው። ከዛ ያሉት ምንዱባኖች የለመዱት ነው። ውጪ አገር ያሉት ግን ሌላው ቀርቶ ገዳይ ስኳዶችን እንኳን ከምንም አልቆጠሯቸውም።

ገራሚው ነገር ስለምርጫ፤ ስለ አቀባባል እና ወዘተ ሸር ጉድ ሰዉ ይጨነቃል። እኔ ደግሞ የሚያስጨንቀኝ ሌላ ነው። የነፍስ ጉዳይ። ወያኔ ሃርነት ትግራይ ቤተ - መንግሥትም ቢሆን ስለነሱ ሰፊ ጥብቅና የቆሙ መዋቅሮች፤ ለእነሱ መረጃ የሚሰጡ ሙሉ አቅም ያላቸው ሃይሎች አሉት።

ሌላው ቀርቶ ወንጀላቸው በዚህ አጋጣሚ እንዲሰረዝ ተግተው የሚሠሩ የሌላ ብሄረሰብ አባለት ሁሉ ሰዎች አሉላቸው። እነኝህ ሰዎች ለህይወታቸው ምሽግ ጥበቃ ያሰናዱ፤ ባይሳካስ ቢቀለብስ የሚል መሰናዶ ያሟሉ ናቸው።

እኔ እንደማስበው ነፃነቱ አንጻራዊ እንጂ ፍጹማዊ አይደለም። ለውጡ ጥገናዊ እንጂ  ሥርነቀል መሆኑም የታወቀ ነው። ቢያንስ ይህን ለመቀበል አለመፈቀዱ ነው ነገስ ስለሚለው አጀንዳ ቢስ ሆነን የምንገኘው። በድሉ መጠቀም መልካምነት ቢሆን አንድ ነገር ቢፈጠርስ ብሎ ህሊናን ማሳናዳት ግን ዋናው ጉዳይ ነው።

በፍጹማዊነት ወያኔ ሃርነት ትግራይ ከግድፈቶቹ ታርሞ፤ ይቅርታ ጠይቆ፤ ለውጡ የእኔም ነው ብሎ፤ ከውስጡ የተቀዬረበትን እርምጃ መውሰድ ሲችል ነው ልብ ጣል ሊደረግ የሚገባው። አሁን በዬሰዓቱ የሚደመጠው ያው የለመድነው ትዕቢት ነው። የፈለገ አዲስ ወጣት ቢመጣ ምላጩ ያው ነው። በ አዲስ ጉልበት እና አቅም ተራራ ላይ የተከፈስ የጉድ ክምርነት። 

በሌላ በኩል አቶ ጃዋር መሃመድ አዲስ አባባ ላይ ሆኖ በድፍረት የሚሰጣቸው መግለጫዎች መንግሥት ነኝ ዓይነት ነው፤ ዶር/ ደብረጽዮን ገብረሚኬኤል የሚመሩት ጋንታ ደግሞ መቀሌ ላይ ሆኖ ሁሉ በእጄ ብሏል።

ወትሮውንም ኢትዮጵያ ሁለት ርዕሰ መዲና ነው ያላት። ለዚህ ነው ቢኦኤም ዶቼሌም መቀሌ ላይ ልዩ ተወካዮች ያሏቸው። አሁን ማዕከላዊ መንግሥታት ወደ ሦስትም እዬተሻገረ ነው። የማዕከላዊ መንግሥት ጠ/ ሚር አብይ አህመድን አክሎ።

አስጊ ችግሮችን ለመፍታት፤ ለመቆጣጠር የሚኬድበት መንገድ ዘገምተኛ፤ የበዛ ትእግስት ያሸነፈው፤ እያወቀ እንደማያውቅ ሆኖ የሚቀርብ፤ ያዬውን እንዳላዬ አድርጎ የሚያይ ለሰስ - ለዘዝ - ልስልስ - ዘገም ያሉ ነገሮች ናቸው ያሉት። አለመቀደም በሚቻልባቸው ጉዳዮች ነገ ከተቀጠረ በችግር መነከረም ይመጣል። 

50 ዓመት በሴራ - በሸር - በተንኮል - ፖለቲካ አሳሯን ስትከፍል ለቆዬችው ለአላዛሯ ኢትዮጵያ መንገዱን ይሁነን ብለው፤ እራሳቸውን ለማረም ስንቶቹ ይሰናዳሉ ቢባል እንደማዬው ከውጪ ወደ አገር ውስጥ ገባ የሚባለው፤ ሆነ ሊገባ የተሰናዳው እንኳን አሁንም ቀዝቃዛው ጦርነት ውስጥ ነው ያለው። በቃ! ሲደባደብ ከትንሹም ከትልቁም ጋር። ሊሂቅነት ማለት ተለጣፊ ታርጋ ብቻ ሆኖ እዬታዬኝ ነው።

አሁን ለሁሉም የማስታገሻ ክኒን የሆነው ልክ እንደ 69 ታሪክ ያው አማራ ክልል ነው። የአማራ ወጣቶች ደግሞ የዛሬዎቹ የክትም የዘወትርም የህሊና አቅም አላቸው። ብልህ እና አስተዋዮች ስለሆኑ መንፈሳቸውን ለማውረስ፤ ክብራቸውን አሳልፈው ለመስጠት፤ ልቅናቸውን ለሌላ ሥመኛ እንደ ታቦት ለመከብከብ ፈቃደኞች አይደሉም። „በቀድሞ በሬ አርሶ የከበረ የለም“ ሙከራውን ሁሉ ከንቱ እያደረጉት ነው … በጋብቻ፤ ባምቻ፤ በዝምድና፤ በሽልንግም ሁሉም ዘመቻ ያለው አማራ በአማራነቱ እንዳያስብ የማሰናክል ሩጫ ሽቅድድም ዘመቻ መሬት ላይ ያለው ትርኢት … ይኸው ነው።

የአማራ ወጣቶች ግን በችግሩ ውስጥ ስላደጉ አስተርጓሚም፤ አመሳጣሪም፤ ፕሮፖጋንዲስትም አይሹም። ፕሮፖጋንዲስታቸው መከራቸው ስለሆነ የእነ ጮሌ የሞገድ ዋና ሆነ ስልት እንዲሁም ስትራቴጅ ባሊህ ሊሉት የቻሉ አይመስልም።

ለሁሉም ዋስተናው የአማራ መደራጀት፤ የአማራ ራሱን ችሎ መቆም ሆኖ ሳለ በዚህ አበጃችሁ ሊባሉ ሲገባ ጎማ ብቻ ሁንልኝ አይነቱ አካሄድ ለኢትዮጵያም አይጠቅማትም። ለውጡ ለድል የበቃው አማራ በቃኝ ብሎ በተነሳ በማግሥቱ ነው። 43 ዓመት የተካሄደው ተጋድሎ በሁለት ዓመት የአማራ የማንነት የህለውና ተጋድሎ ለተስፋ ታጨ ትግሉንም አሳምሮ ቋጨው፤ ከተስፋ ጋርም አዋዋለው።

ይህ እርምጃ ለሁሉም ሚዛን የሚስጠብቅ ሰፊ ጠቀሜታ ያለው ሆኖ ሳለ ነገር ግን ዘመቻው በአማራ ወጣቶች መንፈስ ላይ ሥነ- ልቦናዊ ጫና በመፍጠር ነው ጦርነት የተከፈተው። ቀደም ባለው ጊዜ ተው ቄሮ ብቻ አትበሉ ስንል አልተሰማም ነበር።

 አሁን ከሚገባው በላይ የተለጠጠ የበላይነት እዬተፈጠረ በመንፈስ እያዬሁኝ ነው። ይህ ደግሞ ወደ አንባገነንት የሚወስድ ነው የሚሆነው። የትግራይ ልጆችን አጠፊውም ይኸው ጉዳይ ነው። ደረጃውን ያልጠበቀ የራስ መተማመን ስሜት።

 ሁልጊዜም ሚዛን የሚያስጠብቅ ሃይል ያስፈልጋል። ይህ ብልህነት ራሱ የጠቅላይ ሚ/ር ቢሮ አልገባውም። ጠ/ ሚሩን እኮ ሆ! ብሎ የደገፈው አማራ ነው። አዎና። ይህን ሃይል አጠናክሮ ማውጣት ሲገባ ኩርኩሙ ራስን ማፈረስ ነው የሚሆነው። ከአማራ ጋር የተዋለደውም የነገ የአማራ ልጆቹን ጉዳይ ማሰብ ተስኖት አብሮ ይደልቃል። መጪው ጊዜ ሁሉም ወደራሱ ተመልሶ በውነት ውስጥ ባሉ መፍትሄዎች ዙሪያ ማሰብ ካልቻለ፤ ለዛ ካልተጋ አስጊነቱ ሰፊ ነው። 

አማራ ተመታ መለትም ታይቷል የ27 ዓመቱ መከራ። ከዛ የባሰ መከራ ይገጥማል። አሁን እኔ በምን ሂሳብ አተ ንጉሡ ጥላሁን እና አቶ ጃዋር መሃመድ ገጠሙ የሚለውን ፍቺ ያለገኘሁለት ጉዳይ ነበር፤ በጣም አቅርቦ ለጠ/ ሚር ቦታ ሁሉ ከ አብይ የተሻለ ይል ነበር። ያኦ ኦቦ አዲሱ ረጋስን አክሎ፤ በሰሞኑ በአቶ ንጉሡ ጥላሁን ገለጣ እራሳቸውን እንደ ማስረጃ ሲያቀርቡ አርሲ እንደ ተወለዱ ነበር ያዳመጥኩት። ላካንስ ግንኙነቱ አርሲኛ ነበር አሰኜኝ። ሁለም ጎጆውን ረስቶ አይደለም እታገላለሁ የሚለው። 
  • ·       ላስ? ህም ተዚህ፤ ህም ተዚያ፤ ህም ተዚያ ማዶ!

ብቻ ለውጡ ሳይሳከለት ቢቀርስ ብሎ በህሊና መሰናዳት ያስፈልጋል። ለውጡ ባይሳካ ፕላን ቢ // ፕላን ቢ ባይሳካ // ፕላን ሲ አማራጮችን መያዝ ያስፈልጋል። ለዚህ ነው አማራ በብሄሩ መደራጀቱ አስፈላጊ የሚያደርገው።

አንዱ ሲከሽፍ ወደ ሌላው መሸጋገር እንዲቻል። ራሱ ለገዱ መንፈስ የአማራ መደረጃት ብቻ ነው ጥሪቱ - ጋሻ እና መከታው አጥሩም። የፈለገ ቢሆን አብን በገዱ መንፈስ ላይ አይደራደርበትም። በፍጹም! የገዱ ክንዱ የአማራ ወጣት ራሱን ሆኖ መደራጀቱ ብቻ ነው። ሌላው የቀን ጉዳይ ነው።

ሁሉም ወደዬ ጎጆው ነው የሚያማትበው። ጥሪት አልባ የነበሩት ድርጅቶች እኮ እዬታዩ ነው፤ ብትን መቆሚያ መሬት ጠፍቶ ለጊዜው ተለጠፉ ነገ ደግሞ ይታያል አስለጣፊው ተውጦ ወይንም ከስሞ ወይንም ተከፍሎ ታሪክ ብቻ ሆኖ መራራ ስንብት ሲያደረግ።
  
አርቆ ማሰብ ያስፈልጋል። ባይቻል፤ ባይሳካ፤ ባይሆን፤ ቢከሽፍ፤ መንገድ ላይ ቢቀር ብሎ ማሰብ እራስን ከአደጋ ብቻ ሳይሆን ህዝብንም ከመንፈስ ውድቀት ይታደጋል። መሰናዳት ካለ በሞቀው ላይ ለብ ቢልም ለብ ያለውን ወደ ሞቀው ማሸጋገር ይቻላል፤ በረዶ ላይ ያለውን ቀስቅሰህ ለማሞቅ ግን ሌላ መከራ ነው።

አብሶ በድንገተኛ ፍልስፍና ለሚታመሱ የፖለቲካ ድርጅቶች ሲወድቁ ሲነሱ ያኖራቸው ምክንያት ይኸው ነው። አርቀው መሳብም፤ መተንበይም አይችሉም። ሌላው ቀርቶ ባልነበሩት የታሪክ ፈርጅ ሄደው ሲማገዱ እንኳን አያስተዋሉትም። አንዲት ቀን ብዙ ናት እንኳንስ ዓመታት ለፖለቲካ አቋም ሆነ ተቋም።

ማጥናት የለም ዝም ብሎ የሆነ ነገር … ትልቅነትን ተሸከመህ ትናንት እንዴት ታለፈ የለም … የዛሬ መገኛ በምን ታልፎ ነው የለም፤ ማን ድልድዩን በምን ፈተና አሰናዳው የለም … በቃ በጥሬው መጭ ነው … ስለሆነም ጥሪታቸውን እያጡ ነው። 

የፖለቲካ ሊሂቆቹ ሁልጊዜ በሌላ ነገር ላይ ርግጠኛ የሆነ ፕላን እና ተስፋ ዘርግተው የህዝብን መንፈስ በራዕይ መረብ ላይ ስለሚዘረጉ፤ ጎል የለም፤ ተጫዋች የለም፤ አጫዋች የለም፤ ሜዳ የለም፤ የሚኖረው አራጋቢው እና ማህል ዳኛው ብቻ ነው። ስለዚህ ከአንዱ ውድቀት ወደሌላ በአልተሸነፍኩም ጀብዱ ብቻ ግፋ በል ነው። ድክመትህን ጠንክሬያለሁ እያልክ ብቻ ራስህን ሸርድደህ መዳከር።

ወደፊትም ስልት እና ስትራቴጃቸው ሰውን ማንገሥ ስለሆነ ከተለመደው የሚያልፍ አይሆንም። አሳዛኙ ይሆናል ብሎ የሚገበረው የደሃው ነፍስ መሆኑ ብቻ ነው። አሁን ለመጪው ምርጫ ዕድሉ ከተገኜ ተሰባሰብን፤ ተደራደርን፤ ተዋህድን ተቀላቀልን ይሰማና፤ ከምርጫ በኋዋላ ደግሞ ተሰነጠቅን ሳይባል ግን ተገምሶ ይታያል። ሲዋህዱ ሲቀላለቀሉ አውራ ዜና ነው፤ ሲፈርሱ ደግሞ ውሹን ማንሳት ወንጀል ነው። ለምን ተብሎ አይጠይቅም እእ … ያም ሃጢያት ነው … ደጋፊውም ያው መተርትር ነው። ዝም ብሎ ሁሉንም ማዬት ነው የሚገባው... መማገድ አያስፍልግም። አቅምም ማፍሰስ .. እነሱ ሲታረቁ ሌላው ማህል ቤት ተጎልቶ ይቀራል። 

ብቻ በአንድ ነገር ልጽናና የዶር አብይ ካቢኔ ሙሉ የሃሳብ መሰናዶ አያጣም የሚል ግምት አለኝ። ምክንያቱም እንደ መሪ በእኔ ዕድሜ ለዚህ ቦታ ውሃ ያልነካው ሃሳብ በማፍለቅ ያዬኋዋቸው የመጀመሪያ ሊሂቅ መሪም ስለሆኑ።

ይህን ታህሳስ ላይ ሁሉ ጽፌዋለሁኝ። የሃሳብ ተዋሽ አይደሉም። ሰው ባቀደው ላይ ዘው ባይም አይደሉም። በልካቸው ያቅዳሉ በልካቸው ይንቀሳቀሳሉ። እንደ ገና የተሰናዱ ናቸው በሃሳብ ደረጃ። ስለዚህ ፕላን ቢ ይኖራቸዋል ብዬ እገምታሉሁኝ። ባይሳካ፤ ወይንም ቢቀለበስ፤ ወይንም መንገድ ላይ ቢሰናከል፤ ሴረኞች አይተኙለትም። ለዚህ እከሌ ተከሌ የለም።

ነፃነት እፈልጋለሁኝ ብሎ ሲታገል የነበረው ግን ተለዋጭ አማራጭ አዲስ ሃሳብ የማፍለቅ ችግር አለበት። ሁልጊዜ ሰው ባቀደው ላይ ነው ቤት ለእንግዳ በሉኝ ሲጠወር እማዬው። ወይንም በኖረው እሳቤው። እሱ ብቻ ሳይሆን የሚደንቀኝ እንጥፍጣፊ እርሾ ሳይተው ነው አሁን እዬተንቀሳቀሰ ያለው … ለዘር፤ ቤት ጠባቂ እንኳን የለም። አንድ ነገር ቢፈጠር አቤት የሚል …

  • ጥቂት መረጃ አውሮፓውያን ምን ይላሉ ምንስ ተስፋ አሰሉ።


ሲዊዝ በዶር አብይ አህመድ ተቀባይነት እና እርምጃ ተስፋማ ትላለች። ለዛውም ሲዊዞች በሁሉም የፖለቲካ ጉዳይ ጥልቆዎች አይደሉም። ሲዊዞች ሲበዛ ገለልተኞች ናቸው። በግል ህይወትም እንዲሁ። አሁን ከ7ቀን በፊት በዶር አብይ አህመድ ተቀባይነት ላይ እና በወያኔ ሃርነት ትግራይ የ27 ዓመት የጨለማ አገዛዝ ዘመን ጥልቅ የሆነ ጥናታዊ እንደ ዶከምንተሪ ሊታይ የሚችል የራዲዮ ዝግጅት ነበራቸው። ስጋቱንም ቀውሱንም በሎሳሳ ገልጠውታል።

ዘገባው ለዛውም የአገሬው ተወዳጁ ራዲዮ SRF ፕሮግራም የሠራው። አብሶ ኦስትርያ፤ ጀርመን፤ እና ሲዊዝ ጀርመንም ላላችሁት ጥሩ መረጃ ይሰጣችሁዋል ብዬ ስለሰብኩኝ ለጥፌዋላሁኝ። 

ግርም ብሎኛል ድንቅ ብሎኛል። ጸሐፊዋ የቄሮን መንፈሶች ብቻ ስላነጋገሩ የተጋድሎ ዝበት አለበት። አንባቢዋ ደግሞ ወርቅ አድርገው አቅርበውታል። የሆነ ሆኖ ሲዊዝ ይህን ያህል የወያኔ ሃርነት የ27 ዓመት የሰቆቃ ዘመን በዚህ መልኩ ታቀርባለች ብዬ አላስብም ነበር። ምክንያቱም እዚህ የፖለቲካ ጥገኝነት ለማግኘት ውሃ ያዘለ ተራራ ስለሆነ።
  • ·       ጥቂት ጥሪት… እንዲያው ለአመል ታህል እንኳን ….

ወደ ቀደመው እንደ አበው፣---- የኔዎቹ በህይወት ውስጥ ትንሽ ተቀማጭ ነገር ማስቀመጥ ያስፈልጋል። የመንፈስ ጥሪት ለክፉ ቀን የሚሆን። ደስታም ሲመጣ ሃዘንም ሊኖርበት ይችላል ብሎ ማስብ። ትርፍም ሲመጣ ሊያከስርም ይችላል ብሎ ማስላት። ድጋፍም ሲመጣ ተቃዋሚም ይኖራል ብሎ ማስላት። መኖርም ሲመጣ ሞትም ይመጣል ብሎ ተሰናድቶ መቀመጥ ይገባል። ስንዱነት ቢጠቅም እንጂ አያከስርም። ደግሞ ወጪ የለውም በህሊና መሰናዳት።

የሰው ልጅ ሁልጊዜ እኩል ማሰብ ይኖርበታል 50% ላይ መቆም አለበት። ሊሳካም ላይሳካም ይችላል። ባይሳካ በዬትኛው በር እወጣለሁኝ? በሩ ቢዘጋ በዬት መስኮት እወጣለሁኝ? መስኮቱ ቢዘጋ የትኛው ጣሪያ ምቹ ይሆንልኛል? ብሎ ማሰብ ይገባል። አዬሩ ቢታፍን መተንፈሻዬን የት ላይ ቀዳዳ ይኖረዋል ማለት?

 የማዬው ግን ልብን ጣል ያደረገ መዘነጋት ነው። ይህ አይበጅም። አይደለም ለፖለቲካ ሊሂቃን ለግል ኑሮም በማይሳኩ የኑሮ ፈተናዎች ውስጥ እንዴት ብዬ እሻገረዋለሁኝ፤ በምን ዓይነት ቁጥብነት የሚለው ካልታሰበ ህይወት የድንገቴ ሰለባ ትሆንና ሚዛን ያጠ ትንፋሽ ገዢ ይሆናል። „ልብ ያለው ሸብ“ እንደ ጎንደሬዎቹ ….
  • ·       ጨዋታን ጨዋታ እስቲ ያንሳውል ይላሉ ስለ ጎንደሬዎች ተተነሳ ዘንድ …  

ጎንደሬዎች ሚዛናዊ ናቸው። ዛሬ ሚዲያ ሥሙ የተጸዬፈውን ልጃቸውን አርቲስት አበበ በለውን እና የጥበብ እናትን አርቲስት አለመጸሐይ ወዳጆን በክብር ተቀብሏል። አንደዚህ መሆን ጥሩ ነው። ለጎንደር ሆነ ለኢትዮጵያ አርቲስት አቶ ታማኝ በዬነም ሆነ አርቲስት አቶ አበበ በለው ከጎንደር የባህል ኪነት አብረው ነው የጀመሩት።

 የመክፈቻ ዝግጅት በነበረበት ጊዜ በሲኒማ ባር ያን ጊዜ አንባሳደር ወንደወስን ሃይሉ ነበር ያደራጀቸው። እና እኔም ታዳሚ ነበርኩኝ። ከዚያም በኋዋላ አገር ውስጥ በነበረው ማናቸውም ኪነ ጥበባዊ ጉዞ አብረው ነበሩ።

ውጪ አገርም እስከ ኢሳት ምስረታ ድርስ አብረው ነበሩ። በኢሳት የምሥረታ ሂደትም አርቲስ አቶ አበበ ባለው የጎላ የበኩሉን ድርሻ እንደተወጣ አውቃለሁኝ። ተምሳሌነታቸው ለልጆች ይባጃል ብዬ በልጆች መጸሐፍ ላይ ተመክሮዎን ጽፌያቸዋለሁኝ - እኔ። ስለ አብሮ አደግ ጓደኛ ስጽፍ። 

ከልጅነት እስከ አውቀት ድርጊታቸውን ብቻ በማዬት ስለማውቃቸው። የግል ግንኙነት ከማናቸውም ጋር የለኝም። ሰላምታም የለኝም። አሁን ተዚህ ወደ 5 ጊዜ አቶ ታማኝ በዬነ መጥቷል። ሦስት ጊዜ ሄጃለሁኝ እሱ በተገኘበት ስብሰባ የ ኢትዮጵውያን ተሳትፎ ለመዘገብ ነገር ግን ሰላም አንባባልም። እንደ አንድ አገር ልጅም አንተያይም። 

ወደ ቀደመው፤ --- ነገር ግን አሁን ያለው የማዕካላዊ ሆነ የክልል መንግሥቱ ተባደግ አያያዝ ግን አላዝንበትም ግን ይገርመኛል። ለዚህ ነው እኔ በገደምዳሜ ስጽፍ የሰነበትኩት። ለነፃነት ትግሉ ሁለቱም በሚያምኑበት መስክ ተግተዋል - እኩል። የሚበላላጥ ነገር የላቸውም። 

ሁለቱም ተመሳሳይ ዕድሜ ላይ በአንድ የጥብብ ማዕዶት የሰከኑ ነበሩ። ሁለቱም ጎንደሬዎች ናቸው። ሁለቱም አማራ ነን አይሉም። ሁለቱም ኢትዮጵያዊ ነን ባዮች ናቸው። ስለምን አንዱን የሚዲያና የአብይ ካቢኔ  ንጉሥ ሌላው ባይታወር እንደ ሆኑ ጠ/ ሚር አብይን ባገኛቸው የምጠይቃቸው በኽረ ጉዳይ ነው። የእኔ ጉዳዬ በድምጽ አላባዎቹ ኢትዮጵያዊ እናቶች የውስጥ ቁስለት ምግለት ላይ ነው።

የሁለቱም እናቶች በሰቀቀን እንደኖሩ ነው የማስበው። የጎንደር እናት መከራ ውስጥ የእኔዋ እብዬም- እትዬም፤ እናትዬም፤ እትዬ አማራችም አሉበት። እኔ ባለ ሦስት አራት እናት ነኝ እና። ጎረቤቶቻችን፤ ያሰደጉኝን ሁሉ ፍዳቸውን አስከፍያቸዋለሁኝ። 

ስስለዚህ የአርቲስት አቶ ታማኝ ውድ መነኩሲት እናት // ክብርት እህት ልዕልት የአርቲስት አቶ አበባ በለው እናት ደግሞ አልባሌ ሆኖ መታዬቱ ለእኔ አይመቸኝም። እኔ ስሞግት የባጀሁት ስለ ኢትዮጵያ እናቶች ዕንባ ነውና። ዕንባ ወደ ፍሰሃ ሲቀዬር ደግሞ ማበላላጥ እኩል ደረጃ ላይ ላሉ ልጆች ለእናት ግማዱ ሰፊ ነው። የመከራ ቀን ነው -  ለእኔ። አንዱ የአገር ኩራት ሌላው ደግሞ ለመክሰሰም ያልበቃ …

ወይ ሁለቱንም ማንገሥ ወይ ሁለቱንም በልክ መያዝ። የሆነ ሆኖ  የአብይ ካቢኔም የአያያዝ ዝበት እንዳለበት እያስተዋልኩኝ ነው ለስልትም መሆኑን አሳምሬ አውቃለሁኝ፤ እኔ ግን ቀደም ብዬ እማውቀውን፤ እንደ ሌሰን ያጠናሁትን የአብይን መንፈስ እንዲህ አልጠብቅም ነበር - በፍጹም። ሥርጉተ ሥላሴ ይህን ደፍራ የምትጽፈው አሁን ውጪ አገር ስላለች ነው። እርሾ ስላለ … እርሾ ሳታስቀር ሙጥጥ አድርገህ ጨልጠህ ከጋገርከው ግን ልሳንህን ዘግተኸዋል ማለት ነው፤ ማናሻ የለህምና።

 … ደግሞ በአብይ ካቢኔ ላይ ያሻኝንም መጻፍ መብቴ ነው። ግዴታዬን አሳምሬ ስለተወጣሁኝ። እንደ እኔ የጻፈም የሞገተም የለም። ወደፊትም በመልካም ነገሮች እተጋለሁኝ። ውስጤ እንዲህ ቁስል የሚልበትን ነገርም ሲገጥመኝ አልመረውም እንዲህ እዘረግፈዋለሁኝ። አቤት ስልበት ከነበረው ቦታ አሁን ምን ዕይታ አለሽ በእናቶች አያያዝ ብባል በዚህ ዘርፍ ዳሽ እንዳይሆንብኝ እዬሰጋሁኝ ነው ... 

የሆነ ሆኖ ባለመብትነቴ ማንም ባልነበረበት ጊዜ በስንት ማስጠንቀቂያ ውስጥ ራሴን ማግጄ ተማግጀለታለሁኝ ለአብዩ መንፈስ እና ነፍስ፤ ለራሱ ለድርጅቱ ለኦህዴድም ሆነ ለብአዴንም ለገዱ መንፈስ። የተገባውን በእንቡጥነቱን - አሳምሬ አድርጌላሁኝ። ነገር ግን ሥርጉትሻ የድል አጥቢያ አርበኛ ሁና አታውቅም። ሲያልፍም አይነካትም። አልተፈጠረችበትም። እንዲያውም ሰው መድመቅ ሲጀምር ሸሻ ነው የምትለው …

ስለ ጎንደር ሚዛናዊነት እና ከማዕከላዊ መንግሥት ያስናቀ ተግባርን ስለመከወኑ ይህ መረጃ ይገልጣል። ጎንደር ሁልጊዜም ኩራት ነው። ሚዛን። አብሶ አርቲስት አቶ አበበ በለው  ከአለምዬ ጋር በተዳራቢነት የእሱ ሥም ቤለበት ሁኔታ ኬክ ሲቆርሰ ብዙም አልተመቸኝም ነበር። 

የራሱ የሆነ ማንነት፤ የራሱ የሆነ የትግል ታሪክ፤ የራሱ የሆነ የትጋት መስክ ስላለው መጠለል አስፈላጊ አልነበረም። እኔ ብሆን አላደርገውም። ሞገደኛም እቴጌም ነኝ። ተጥርቼም ጋዳ ነው እንኳስን ተደራቢ ልሆን ቀርቶ … ክብሬን አስደፍሬ አላውቅም፤ ትርፍ ተናገሪ ሰዎች በማህበራዊ ኑሮ ከገጠሙኝ እንኳን አስጠግቼ አላውቅም። ቁጥብ የሆነ እምሳሳለት የእኔ ማንነት አለ፤ ቤተሰቦቼ አሉ፤ ማህበረሰቡ አለ ያሳደገኝ፤ በሁለመና ሰብዕናዬን የቀረጹት እጅግም የደከሙ ደግሞ አሉ። 

የጎንደሩ አቀባባል ብቻ የውስጥነት ነው። ንጹህ ነው። አርቲፊሻል አይደለም። እነዚህ ነፍሶች ተከፍሏቸው ወይንም በድርጅታዊ ሥራ ውስጥ ለውስጥ ስብከተ ዝና ተደርጎላቸው አይደለም። 

በራሳቸው ፈቃድ እና ጊዜ፤ በራሳቸው ወጪ ነው ይህ የሚሆነው። ይህ ደግሞ ለማግሥታዊነት መሰረት ነው። ጊዜ ሰጠውም አልሰጠውም ለሁሉም እኩል መሆን። የህሊና እርሾ ማለት ይሄው ነው። እትብት መንደሬ ሁልጊዜም ጎንደርዬ ያኮረኛል። ጎንደር ማለት ይኸው ነው። ጣዕሜ ለእኔ እንደዚህ ያለ አኩል የማዬት ማዕድ ነው። የፕርፖጋንዳ ሰለባ ያልሆነ ተቀባይነት እና ተወዳጅነት ነጥሮ ሲወጣ ጠረኑ ይስበኛል= ይመስጠኛልም፤ ብቻ ጎንደርሻ ባለ ማርዳ ሚዛን!

በሌላ በኩል አዲስ ድምጽ ራዲዮንም ተግባሩን አልረሳም ብጹዕን አባቶቼን አግኝቶልኛል። ይህም ሌላው ፍሬ ነገር ነው። በዚህ ደግሞ አቤን ተባርክልኝ የእኔ ጌታ ብያለሁኝ። አይቼ የማልጠግባቸውን አባቶቼን ስላሳዬኝ ደስም ብሎኛል። ገለልተኛ በሆነ ሚዲያ ዕውነቱን ማወቅ በእጅጉ ያስፈልገኝ ነበር።  

Gonder Welcomes Alemtsehay Wodajo, Abebe Belew, and Dawit Tegegn
Addis Dimts Radio Host Abebe Belew Interview with Abune Merkorios

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።
የኔዎቹ ኑሩልኝ መሸብያ ጊዜ።



አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።