ዴሞግራፊ የዴሞክራሲ ውደቀት እንጂ የተሰፋ ልቅና አይደለም። {ክፍል አንድ}
ዴሞግራፊ የዴሞክራሲ
ውደቀት እንጂ
የተስፋ ልቀና
የተስፋ ልቀና
አይደለም።
ክፍል አንድ።
„የደከሙትን
እጆች አበርቱ፤
የላሉትንም ጒልበቶች አጽኑ።“
ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፴፭ ቁጥር ፫
ዝግጅት ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
06.06.2019
ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ።
v ተስፋ ይራመዳል።
v ተስፋ ያራምዳል።
v ተስፋ ያጓጉዛል።
v ምን ያህል እንደተጓዝኩኝ አላውቀውም?
v ምን ያህል እንደሚቀረኝም አላውቀውም?
v አለማወቄን ስጠይቀው አለማወቁን ገለጸልኝ።
v ተስፋን እጠብቃለሁኝ { የመጀመሪያው ተስፋ መጸሐፌ ላይ የመጨረሻ ሽፋኑ ላይ ላይ የጻፍኩት ነው} የትውስት
አይደለም እንደማለት።
· እፍታ
እጅግ የምትናፍቁኝ የአገሬ ልጆች፣ የኔታዎቼ እንዴት አላችሁልኝ? ደህና ናችሁ ወይ? የአብይወለማ
መንግሥት ስለ ዴሞክራሲ በቀን የሚናገርበት ዝክረ ቋት ቢሰናዳ ሞልቶ ይፋሳል። ዴሞክራሲ በዚህ በቀን ስንት ጊዜ የመግለጫ አክሮባት
በሚሰራበት፣ እንዲሁም ዴሞግራፊ አውራ መርህ በሆነበት ድርጅት ፍትልክ ሊል ከቶውንም አይችልም። አለበደምና@ፈጽሞ።
መሬት ያለካስማ አይቆም፤ ዴሞክራሲም በዴሞግራፊ ፍልስፍና አይቆምም። ሁለቱ የተለያዩ መነገደች
ናቸውና። ጨላማ ከብርሃን ጋር ግጥም የለውም። ዴሞግራፊ ለዴሞክራሲ ፍልስፍና ቀራንዮ ነው።
· የአገር ጭንቅላት።
ዴሞክራሲ የመሰረቱ አገሮች ስከነቱ ያለው ከሥርዓቱ ጭንቅላት ነው። አውቆ - አበድም፤ እብድም፤ መንፈሱ ያልተረጋጋም፤ የኢጎ አርበኛም፤ የዝና ዘመናይም፤ ጨዋ ምራቁን
የዋጠም፤ እርጉውንም፤ ክልፍልፍም፤ ንፋስም፤ ናጂም፤ አናቋሪም አቅም አዳኙም፤ አቅም ዋጩም፤ አሰተዋዩም፤ ታጋሹም የፈለገ
ይምጣ ሥርዓቱ በዴሞክራሲ አግባብ ከተገነባ በፈለገው አቅጣጫ ቀውስ ይምጣ ሃንድል ማድረግ ይቻለዋል።
ዴሞክራሲን የገነቡ አገሮች ህገ መንግሥቱን ራሱ ቀጥ አድርጎ ህልው የሚያደርገው የዴሞክራሲ ሥርዓት
ባላ እና ወጋግራ ሆኖ የቆመው ሥርዓቱ ነው። የሥርዓት አልበኛ ዘመንኛን
ቀጪው የሥርዓት አገናባቡ ሥህናዊ ጥበብ ነው።
... እኛ ደግሞ ይህ ነበረን ከ60 ዓመት በፊት። ግን በራሳችን ጊዜ በማሌ ፍልስፍና በትውስት
ማንነት አፈራርሰን አሁን እኛም እራሳችን እዬፈራራስን ነው። እንደ ሰው
ለመቀጠል እራሱ ግማዱ ቻለኝ ብሎ መጥቷል። አጀንዳችን ሊሆን የሚገባውም የሃቅ ቋት ነው።
የቀድሞውን ፕ/ ባራክ ኦባማ ለሁለት ጊዜ ለስልጣን ያበቃው ሥርዓቱ ነው። አሁንም ፕ / ትራንፕን
ለሥልጣን ያበቃው ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በመገንባቱ ነው።
v መንገዱ።
ዴሞክራሲያው ሥርዓት ለመገንባት ከራስ መጀመር ይጠይቃል። ከራስ ከተጀመረ ወንዝ መንገዱን ተከትሎ
እንደሚሄደውም ማንኛው መሰናከል በራሱ ጊዜ እዬፈታ የመጓዝ አቅም ይኖረዋል፤ አንድ በዴሞክራሲ ፍስልፍና ራሱን ለማስገዛት የቆረጠ ነፍስ፤ ተቋም
እና አገር ቢኖረን። የእፉኝቱ የአላዛሯ ኢትዮጵያ ፖለቲካ መከራ ይኸው ድርቅ የመታው መሆኑ ነው። ችግኝ እንጂ ማስበል አያውቅበትም።
የአላዛሯ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ተባይ ነው የሚያፈራው ገና ከመፈጠሩ። ተባዩ ደግሞ ሌላውን አዳርሷ መጨረሻ ራሱንም በመራራ ስንብት ይሸኛዋል።
ዴሞክራሲ የአፍ ማሟሻ ብቻ ነው ለኢትዮጵያ ፖለቲካ። የድርጅቶች አለመበርከትም፤ አለመዝለቅም፤ የመጨንገፍም መከራው
ከዚህ ላይ ነው። ሲፍርሱ እንኳን አያምርባቸውም፤ መቼም ከመፍረስ ቁንጅና ባይታሰብም፤ ተፈጥሯዊ ትውፊት እና ትሩፋቱ እንኳን ቅንጣቢ መከባበር
ድርቀት ይመታዋል።
አቋቋምን፤ አደራጀን፤ አሰፋን፤ ፈጠርን፤ መሰረትን ያሉት ድርጅት ወይንም ተቋም፤ በላያቸው ላይ
ዘመኑ አልቆ ይተናል። በቃ ትንታ በትንታ ይሆናል። በራሱ ጊዜ? ለምን ሲባል ባጎረፈ ወቅት ነው ምሰረታው፤ ውህደቱ፤ ቅልቅሉ የሚከወነው። ዴሞክራሲን ሥሙን በፍሬም
ለተሸከሙት ሩቃቸው ነው። ስለሆነም ሁልጊዜ ሲፈርሱ፤ ሲሰሩ ሲፈርሱ፤ ሲዋህዱ ሲበተኑ፤ ሲቀላቀሉ ሲፋቱ በቃ የፍርሰት ትዕይንቱ ትውልዱን ለማባከን በገበርዲን እና በከረባት
ቂቅታ ህቅታን ከስኖ መተመም ነው ... በአታሞ።
ስለምን ቢባል በዴሞክራሲ ፍልስፍና ውስጥ ሳይሆን በሴራ ፖለቲካ የተቃኘ ድርጅት ወይንም ተቋም
ስለሚገነባ። አመሰራረት ነው የተቋምን ህልውና ዝልቀት የሚመሰክረው። የሚያስከበረውም።
ዴሞክራሲን በራስ ላይ ቢጀመር እዬጠራ፤ ወልጋዳውን እዬገራ፤ ጠማማውን እያቃና፤ የዛለውን እያበረታት፤
አቅም ፈጥሮ፤ አቅም ሆኖ፤ አቅም በመሸለም ለቀጣይ ተጋድሎ በቅጡ የሚያሳናዳ ፍልስፍና ነበር ዴሞክራሲ። ዲሞክራሲ በራሱ የሰከነ እና የተደራጀ ፍልስፍና ነው። ችግሮችን ያጠና ብቻ ሳይሆን ለችግሮችም መፍትሄ አመንጪ ፍልስፍና ነው።
ለትውልድም ተሰራ የሚባል ታሪክ ቢኖር ይኸው በሆነ ነበር። ራሳችን አፍርሰን፤ ውስጣችን ተጻረን
ጀመርነው 60 ዓመት ሙሉ ይሄው መዳከር። ትውልድን ለብክነት ስንቅ በማድረግ። ለጥሪት ዕንባን በማስቀጥ።
የዴሞክራሲ ነፍሱ የብዙኃንን ሃሳብ ፈቅዶ፤ ወዶ የማስተናገድ አቅም ነው። ያ አቅም ደግሞ ተፈቅዶ፤
ተወዶ፤ ተከብክቦ ሲሆን ፈጠራ ይሰፋል፤ አስተሳብ ይበለጽጋል፤ አቅም ይጠራል። ሁሉ ያለውን ያዋጣል ስለዚህም ህብራዊ እሳቤ ሞተር
ይሆናል ወደፊት ለመቀጠል።
ዴሞክራሲ የተለዬን ሃሳብ በተጨማሪ ሃይልነት በእንክብካቤ እንዲያዝ የሚያደርግ እንጂ ያን ለማጥፋት፤
ያን ለማክሰም የሚደረግ ግብግብ አይደለም፤ የዴሞክራሲ ፈለግ የሚፈቅደው። ፍልስፍናውን ለማራመድ ራስን መግራት ይጠይቃል። ራስን ማሸነፍ
ይጠይቃል። ራሳቸውን ያላሸነፉ መሪዎች ናቸው በዬዘመኑ ትውልዱን በዴሞክራሲ ስም ሲያባክኑት የኖሩት።
አሁን ዘመኑ ጥሩ ነው። ማንዘርዘሪያ ገዝቷል። እንዲያውም እጬጌውን ዘመን ባገኘው የወርቅ ዙፋን
ነበር እማቀዳጀው እኔው ሥርጉተ ሥላሴ። ስለምን? የጎሼውን ስላጠራው፤ ሰውና ሰው መሳይ በሸንጎን አንዘርዝሮ ስለለዬው። ስለሆነም ይህን ዘመን ሰጥ የጥራት ንጥር ስጦታ ተግ ብሎ፤ አደብ ገዝቶ ግን ዳ ሳይሉ ራስን
መመርመር፤ ራስን መጠዬቅ፤ የቆሙበትን መሬት መፈተሽ ይገባል። ሌላ ምህንድስናንም ይጠይቃል ...
· ፍንጋጣ …
ከዴሞክራሲ ያፈነገጡ ነፍሶች ሁልጊዜ ራሳቸውን ብቻ የሚያዳምጡ ሲሆን፤ ሌላ አድህኖተ ሃሳብ ሊቀበሉ
ፈጽሞ የማይፈቅዱ ናቸው። ሁሉነገር እነሱ እናውቃለን ባዮችም ናቸው። ሳይንቲስት፤ ፈላስፋ፤ ተመራማሪ፤ ማህንዲስ፤ ባለቅኔ፤ ማናጀር፤ ፈርማሲስት፤
የኤሌትሪክ ባለሙያ፤ የመንገድ ጠጋኝ፤ የግድብ ሰሪ ማሃንዲስ ባለሙያ ወዘተ …
ይህም ባልከፋ ያን አድህኖተ ሃሳብ አፍላቂውን ነፍስ ከምንጩ ለማድረቅ እስከ ማስወገድ ድርስ
የሚሄዱ መሆኑ ነው ጠናናው እና ጠንባራው ጉዟቸው። ነፍስ ለማጥፋት
እጅግ ደፋሮች ናቸው። በግርዶሽ ስለሚከወን ግን ማንም ይህን ሊያሰተውለው
እና ከእነሱ ተነጥሎ ለመቆም ለመወሰን አይችልም። ስልቱ ረቂቅ ነው።
በዚህ እሳቤ ስንሄድ ከይፋዊው የኦህዴድ የዲሞግራፊ ፍልስፍና በፊት በዴሞክራሲ ሥም የተመሰረቱት
ተቋማትም ይኽንኑ ሲከውኑ ኖራዋል። ጥቃቱ በነፍስ ወከፍ ነው የነበረው።
የሚያሳዝነው የጥቃቱ ሰላባዎች ሰብሰብ ብለው፣ እራሳቸውን ከጥቃት ለመታገድ አሰበውበት አያውቁም
እንጂ ድርጅት ሃይል ነበር።
የተገፉ፤ የተገለሉ፤ ዘመቻ የሚካሄድባቸው ቢደራጁ፤ ቢሰባሰቡ ኖሮ ስንት አቅም ተቀብሮ ባልቀረ ነበር። በሌላ በኩል አመለኞችም የዘመን አክተርነታቸው በውጥኑ ገርቶ መስመር ውስጥ ማስገባት ይቻል ነበር።
የሰው ልጅ በጣት በሚቆጠሩ
ነፍሶች ዕድሜ ዘመኑን መታመስ አይኖርበትምና።
አሁን ልዩነቱ አገራዊ መልክ መያዙ ነው እንጂ ታውቆም፣ ሳይታወቅም ብዙ ነፍስ ልብ ተገጥሞለት
ስለመኖሩ አያውቀውም። ዛሬ ሲባንን አልነበርኩም ማለት አይቻለውም። መተንፈሻ ቧንቧ ተገጥሞለት በዛ ሲተነፍስ መኖሩን አምኖ መቀበል
ግድ ይለዋል። የራሳቸው ወሰን አልበቃ ብሎ በስንት እርቀት ንጸሃንን ሲያሳድዱ እንደኖሩ የደረሰብን አሳምረን እናውቀዋልን።
· ሰይጣናዊነት።
የዴሞግራፊ ፍልስፍና ሰይጣናዊ ነው። የቀውስ መቅድም እና መዳራሻም ነው። ቀውሱ ሲጀመር ሱማሌ
ላይ ነበር። ያ ታቅዶ ለሁለገብ ግብ የተከወነ ስለመሆኑ ዘግይቶም ቢሆን ተነግሮናል። ዛሬ አዲስ አባባ ላይ ብቻ ሳይሆን ጌዲኦ፤ ኬሜሴ ሲዳሞን እንደሰደደ እሳት አገር ምድሩን እያዳረሰ ነው።
የዴሞግራፊ ፍልስፍና የራስህን አውልቀህ ጥለህ የሰውን ድሪቶ በመረከብ ትውስታዊ ህልውናን ወደህም ሆነ ተገደህ ማጽደቅ ነው። የመንፈስ ቀዶ ጥገና እንበለው።
መንፈስህ ነው ተቀዶ ያለው ሁሉ የእኔ የምትለው የመንፈስህ ተፈጥሯዊ ትውፊት፤ የቤተሰብ
ትውፊት ሳይቀር ተዘርግፎ ይጸዳ እና የሌላውን ፍላጎት እርክክብ መፈጸም ይሆናል ቀጣዩ ዕጣ ፈንታ።
ይህን ያልተቀበለ ነፍስ ወይንም ተቋም ደምስሰው፤ አጥፋው፤ አስወግደው አይቀሬ ነው። ይህ እንግዲህ
በፖለቲካ ሊሂቃኑ፤ በተጽዕኖ ፈጣሪዎች ያለው ወልቆ የመገጣጣም ጋራጃዊ ሂደት ነው። አብሶ የኪነ ጥበብ ሰዎች እና ተጽዕኖ ፈጣሪዎች
ሳይታወቃቸው በራሳቸው ማንነት ፈቅደው ያልኖሩትን ኑሮ ኖር የሚሉት። በዚህ ውስጥ ተቋም ሆነ ሚዲያ ነገር የፈጠሩትም የዚህ ሰለባ ናቸው።
በተሰጠኝ ሰማያዊ ጸገዬ ውስጥ ነበርኩ ሲሉ እስቃለሁኝ እኔ። በተገጠመ ልብ ኖረህ ነበርኩኝ፤
ህልው ነኝ ማለት አይቻልም። ያ ብቻ አይደለም ልብ የተገጠመለት ደግሞ ሺዎችን አሰልፎ ደግሞ ለዳግም ሞት ይዳርጋቸዋል። ቀፎ ማንነት
ተሸክሞ አልባሳት? እም@
ቅኖች ሳይቀሩ ላባቸውን ጠብ አድርገው በሰሩት በራሳቸው ቤት ሌላ አዛዥና ናዛዥ በሞፈር ዘመት
ይፈቅዳሉ፤ ሌላ ጫኝ እና ተጫኝ መንፈስ ይፈቅዳሉ። እነሱ የሚያዩት የእናት አገርን ጉዳዬ ነው፤ ግን ያ ግርዶሽ ነው፤ መንፈስን አውልቆ
የመግጠም ጉዳይ ነው።
የራሱ ያለው ያ አልበቃ ብሎ ነው ደግሞ ከሌላ ተሻግሮ በሌላ ላይ ጫና እንዲካሄድ መሳሪያ ፈልጎ
የድርጅቱ አባል በማድረግ የለመደበትን ሰይጣናዊ ተልዕኮ የሚፈጽመው …
በዚህ ፍልስፍና ቅኖች፤ ደጎች፤ ታታሪዎች፤ የእውነት አርበኞች፤ ቀጥተኞች፤ ሃሳብ አፍላቂዎች፤
የፈጠራ ሰዎች ለአገር ንጹህ ተቆርቋሪዎች ተቀብረው በአንጻሩ የዚህ ተቃራኒ የሆኑ ነፍሶች ዓውዱን ሙሉ ለሙሉ ይቆጣጠሩታል። አሁን
ባለው ሁኔታ የአማራ ወጣቶች ያለባቸው ፍዳም ይኸው ነው …
የዴሞግራፊ ፍልስፍና ሰውን እንደ ሰው ሳይሆን እንደ ሮቦት ስለሚያው ማብሪያና ማጥፊያው በአንድ
ሰብዕ ሰብዕና ዙሪያ የሚሸከረከር
ይሆናል። ትቀበላለህ ተቀበል፤ አልቀበልም ካልክ ደግሞ ትወገዳልህ።
ይህ ደግሞ ሰውኛም ተፈጥሮኛም አይደለም። ግድያው የመንፈስ ነው የባሩድ አይደለም። ሰው
መሆንን መግደል ነው የዴሞግራፊ ፍልስፍና። ይቀጥላል …
መረጃ ሳይኖረን የማንንም ስም አላጠፋንም፦ ትርጉም በአብርሃም ዓለሙ (ዶ/ር)
ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል
ፍቅርም ሲያልቅ ትእግስት ይሰዳዳል።
የኔዎቹ ማለፊያ ጊዜ።
ኑሩልኝ ለእኔም ለአላዛሯ ኢትዮጵያም።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ