አሉታዊ የዴሞግራፊ ንድፍ የበታችነት ስሜት የሚያበቅለው ሙጃ ነው። {የወግ ገበታ}



እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በደህና መጡልኝ
አሉታዊ የዴሞግራፊ
   ንድፍ የበታችነት
             ስሜት
 የሚያበቅለው
ሙጃ ነው።

ክፍል አራት።

የደከሙት እጆች አበርቱ፤
 የላሉትን ጉልበቶች አጽኑ።
ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፴፭ ቁጥር 

ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
06.06.2019
ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ።





·       እፍታ።

እንዴት ናችሁ የቀንበጥ ሚዲያ የኔታዎች? ደህና ናችሁ ወይ? ዛሬ በጥምረት የሁለት ኢ - ሰብዐዊ፤ ኢ - ተፈጥሯዊ በሆኑ ወጥ መንፈሶች ዙሪያ ትንሽ እላለሁኝ። መነሻዬ እነዚሕ ትውልድን አጥፊ  የሆኑ የክፉ ህሊና እዳሪዎችን አሰመልክቶ ትንሽ ማለት ፈለግሁኝ። ሌላው ሁሉ ነገር ቅርንጫፍ ነውና።

ወሳኙ የኦሮሞ ሊሂቃን የሚያራምዱት ፖለቲካ መሰረታዊ ፍልስፍና መነሻው ሆነ መድረሻው በውስጣቸው እራሳቸውን ሆነው የመኖር አቅም ማነስ ይመስለኛል። 

ይኽ ራስን አሳንሶ፣ በራስ ውስጥ ያሉ ንጥረ ነገሮችን አግልሎ የመነሳት ፍልስፍና ደግሞ ኢትዮጵያ ላይ መነሻ ቀዬና የሥልጣን መንበር ይኑረው እንጂ ቀስ እያለ አፍሪካ ቀንድን፤ መካከለኛው አፍሪካን፤ ቀጥሎ ወደ ሙሉውን አፍሪካን ሊያጠቃልል በሚችል መልኩ የታቀደ ነው። ለዚህም ነበር የመስከረሙ የኦህዴድ ጉባኤ ወደ ኦዴፓ ሲሸጋገር መርኃችን ኦርሙማ ነው ያለው።

ለዚህ የማስፈጸሚያ ስንዱ ልል ዝልብ ሰሌዳው ደግሞ ብአዴን ነው። ሊጋባው ድልድዩ የአርሲው የጢቾ ባላባት ጃዋራዊው አቶ ንጉሥ ጥላሁን ናቸው። ለዚህም ነው ከሊቀ ሊቃውነታቱ አባት እና እናቶቹ ተነጥሎ ሥሙ ብቻ "የአማራ" የሚባለው ብአዴን የሥም ትውስት አሰኝቶ፤ ራሱን ያልቻለ ጥንዙል ስለሆነ ባለ ኦሩሙማ ባለራዕዮችን ተከትሎ አዴፓ ሲል  የኦሮሙማ ማሳ ለመሆን ስንዱነቱን በፊርማው በራሱ በጉባኤው ያጸደቀው። ዝለትም ፍዘትም አለበት ድርጅቱ አቤቱ ቅጥሎ ብአዴን። 

የሆነ ሆኖ ዛሬ ኢትዮጵያ ላይ ያለው ሁለገብ መፈናቀል ነገም ለእማማ አፍሪካም አይቀርላትም። ለዚህም ነበር ኦኤምኤን በኬኒያ ስትዲዮ ለመክፈት ሲያቅድ ቋንቋውን በኦሮምኛ፣ በሱማልኛ እና በስዋኽልኛም ለማድረግ መሰናዳቱን በቅንጡው የደም ወርኃ ባደረጉት በመስከረም ላይ የተገለጠው። ይቀጥሉ አይቀጥሉ አላውቅም።  

ስለሆነም የመከራውን ጥልቅ ፍላጎት የአፍሪካ ህብረትም ጉዳዩን በባለቤትነት ሊመለከተው፤ የዓለም ማህበረሰብም ሁኔታውን በጥሞና ሊዬው፤ ኢትዮጵውያንም በቅጡ እና በወጉ ሂደቱን ሊከታተሉት እና አሻም ብለው የወል ድምጻቸውን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ያሰሙ ዘንድ ይህን ጉዳይ ውስጡን፤ መንፈሱን፤ ሆድ ዕቃውን አብጠልጥለን ልናዬው ስለሚገባ በዚህ አጀንዳ ዙሪያ ሰፊ ጊዜዬን ለመስጠት የፈቀድኩት።

በመፍረስ ላይ ያለ ሰብዕና፤ በመፍረስ ላይ ያለ አገር፤ ለእርስ በእርስ ዕልቂት የተሰናዳ ህዝብ ይዘህ ስለ ዴሞክራሲ? ስለምርጫ? ስለ ቀጣይ የመንግሥት ፍኖተ ካርታ፤ ስለ ቀይ ምንጣፍ የዕውቅና ልዕልና ከማሰቡ በፊት ለምልዕቱ ህልናውን ዋስተና ያሰጥ ዓራት አይናማ መንገዳችን ሊሆን ይገባል!

ማንኛውም በውጭም በአገርም፤ በውስጥም የሚኖር ዜጋ ቅድሚያ መኖሩን ማስከበር ስለሚገባው፤ ስለ ህልውናው ግድ ሊለው ስለሚገባ፤ በበዛ የሚዲያ ወጀብ፤ በበዛ ሴሪሙኒያው የድግስ ውቂ ድብልቂ ኢትዮጵያዊው ዜጋ ሳይዘናጋ መኖርን ለማኖር መንፈሰን፤ አቅምን፤ ክህሎትን አማክሎ በስንዱና በነቃ ህሊና መሞገት ስለሚገባ ነው እኔ አትኩሮቴን በዚህ ዙሪያ ላይ ማድረግን የወደድኩት።

ከዋንኛው አክሳይ ማንፌሰቶ አናት ተነስተን በዛ ላይ በበቂ ግንዛቤ የተመሰረተ የጠራ ተግባር ካልከውን ኢትዮጵያና ልጆቿ መከነው ይቀራሉየሚገርመው ሊያስፈራሩን ይሻሉ። አያስፈራሩን! እኛ ሁሉ ያለን ህዝቦች ነን። ሁሉ ያለን በመሆናችንም መንፈሳችን ሙሉዕ ነው። ብድር፤ ትውስት የሚያስኬደን ምንም ነገር የለም። የሌላው ለትውስት ላይ ታች ይበል። የህሊና ስንቃችን በደረበብ ሳይሆን ቲፍ ብሎ የሞላ ነው።   

·       የመነሻዬ ሰቅ።

„መረጃ ሳይኖረን የማንንም ስም አላጠፋንም፦ ትርጉም በአብርሃም ዓለሙ (/)“

April 1, 2019 | Filed under: ነፃ አስተያየቶች | Posted by: -ሐበሻ
„ነጋዴ በኦሮምኛ ካልሸጠ አትግዙ – አቶ በቀለ ገርባ“
March 23, 2019

·       የበታችንት ስሜት ስውር ደዌ ነው።

ሰው ሆኖ የመፈጠሩ ሚስጢር ዕድምታ ያልገባው የሥነ- ፍጥረት ቤተሰብ የበታችነት ሁልጊዜም ይሰማዋል። የፈለገ ነገር ቢሟላለት፤ ቢኖረው፤ ዙፋን ቢጭን፤ እጬጌነት ቢታከልለት ከራሱ ርቆ ስለሚኖር ርጋታ የነሳው ነው።

ከፍጥረት ተለይቶ የፍጥረት ገዢ የበላይ ሆኖ የተፈጠረው የሰው ልጅ የፈጣሪ የየአላህ ቤተ መቅደሱ ሆኖ ሳለ ነገር ግን ሚስጢሩ ለተሰወረበት ነፍስ እረፍተ ቢስ ነው። ሰው ታላቅ ከሁሉም የላቀ የፈጣሪ የአላህ ፍጡር ነው። ከፈጣሪ በታች ሰው ሆኖ መፈጠር በራሱ ድንቅነትም፤ ቅኔነትም ነው።

·       ቀደምትነት በውነት አንጡራነት!

ቀደምቱ የኢትዮጵያ የአገራችን የሊቃውንተ - ሊቃናት፤ የነባዬተ - ነብያት ግን ከሰው ተፈጥሮ አልፈውና ተርፈው የሰው ፍጥረት መገኛ ሚስጢርና የድንቅነሽን የህልውናውን አንጓና ሰቅን በዕድምታ ተደመው፤ ለዓለም በሳይንስ፤ በሥነ - ፈለግ፤ በምርምር፤ በፍልስፍና ዘርፍ የቀደመ ፍጹም የቀደመ ትንታግ ተግባር ከውነውበታል።

አልፈው ተርፈው የህዋን ክዋክብት ሥያሜ እስከ መስጠት፤ ህዋው ውስጥ ሥማቸውን እሰከማስመዝገብ የደረስ የበቃ፤ የነጠረ፤ የጠራ ልቅና፣ ብጡልና፣ ልዕልና አሰመዝገበዋል የኛዎቹ ፈርጦች!የኛዎቹ ተክሊሎች፤ የኛዎቹ ዘውዶች። 

በበታችነት ድዌ የሚማስኑት ነፍሶች ናሳን ጎብኘት ቢያደርጉት ሊያገኙት ይችላሉ። በበታችን ደዌ እንዲህ ከሚባዝኑና ከሚሰቃዩ ...።

እንደ ሥርጉተ ዕይታ ጠበሉ ያለው ለእነሱ ናሳ ውስጥ ስለሆነ እዛ ሄደው ይጠመቁ፤ ጎንዳቸው ናሳ ይሁን ትላለች ሥርጉትሻ ተዚህ ከተደሞ መንደር ከሲዊዚና።

በሌላ በኩል „መጸሐፈ ፈውስ“ ጀርመንን እንዴት የዓለም መዳህኒት ፍልስፍና አከርካሪ እንዳደረጋትም ወደ ሃንቡርግ ጎራ ብለው ፈዋሽ ጸበል ይረጫጩ … ሌላም ሌላም …

ጀርመኖች ልጆቻቸውን እጬጌውን ግዕዝን በተጋ ሁኔታ ያሰተምራሉ። በበርሊን ፍሪ ዩንቨርስቲ፤ በሃንቡርግ ዩንቨርሰቲ፤ በሃይድልበርግ ዩንቨርስቲ። ሚስጢር ያለበትን ተፈላስፈውበታል። እነሱም አውሮፓም አሉ የሚባሉ የቀደምቱ ሊቃናቶቹ ብዙውን የቀለም ትምህርት ልቅና ያገኙት በዚኸው መስክ ባደረጉት ምርምር ነው። ስሜን ኢትዮጵያ አንጎል ነው ለኢትዮጵያዊነት ሆነ ለጥልቅ ሥነ ህይወታዊ ተፈጥሮ። 

ኢትዮጵያ የሉላዊው ዓለም የምርምር ህሊና ናትኢትዮጵያዊነት የጆግራፊ /የመልክዕምድራዊ/ ትምህርትን የመፍቀድ ያለመፍቀድ ሳይሆን የነቃው ህሊና የተባ ለምለም የዳበረ አንባ የመሆን አቅም የፈጠረ ባዕት ነው። ኢትዮጵያዊነት ከወገብ በላይ እና በታች አይደለም። ኢትዮጵያዊነት የሙሉ ሰው ጭንቅላት የብጡልነት ሥህን ነው። ኪነ ነው።

ኢትዮጵያዊነት ምስባክም ነው። ኢትዮጵያዊነት የሥነ - ተፈጥሮ በጥልቀት በእድምታ የተጠበበት የተደሞ ማህለቅም ነው።  ኢትዮጵያዊነት ሲሞላና ሲጎድል የሚንሻፈፉበት የጨዋታ ሟሟያ ማንነት አይደለም። ኢትዮጵያዊነት የስላቅ፤ የተረብ፤ የፖለቲካ ሸቀጥ መመቀጫ ሳይሆን ኢትዮጵያዊነት ዩንቨርስቲ ገብተወ ሊማሩት የሚገባ ሳይንስ ነው።

ይህን የምለው ሰሞኑን በዲስ የኢዜማ ጉባኤ ላይ ለተነሳ ጥያቄ የተሰጠው መልስ ለአቅመ አዳም ሆነ ለአቅም ህይዋን ያልደረስ ስለመሆኑ እገረ መንገዴን ለማጠዬቅም ነው። ይህን ጥያቄ ሳይመልሱ ኢትዮጵያን እመራለሁ ብሎ መታሰቡም ነው ዳጥና ምጥ የሆነው። ጋብቻው ከኦሮሙማ ጋር ስምረቱም የደዌ ተዋራርሽነት ስለሆነ ነው።   

በነገራችን ላይ ወደ ቀደመው ነገረ አትኩረተ ጀርመን ስመለስ አማርኛ ቋንቋ ጥልቀቱ፤ ለዛው፤ ውበት፤ የሚቀዳው ወዙ ላሂው እና ቅኔነቱ ጋር የጀርመንኛ ቋንቋ አቻው ነው ማለት እችላለሁኝ። ዓለም የተላላፈው ቋንቋ ነው ጀርመንኛ። ባይሆን የስዋሰው ክብደቱ አይደፈረም እንጂ ጣዕሙ፤ የትርጉም አሰጣጥ ዘይቤ ቅዬሳው ነፍስን ይገዛል።

በሌላ በኩል ደግሞ በበታችነት ደዌ የሚሰቃዩት ወገኖቻችን ስለ ድንቅነሽ ዓለም የደረሰበትንም የፍልስፍና ጭብጥ ገባ እያሉ በዬሐገሮች በሚገኙ ቤተ መጻህፍት በዬመምሪያው እዛም አደቡ ከኖራቸው ይሂዱና ይቀሰሙ - በትህትና። የሾለከባቸውን፤ ያጡትን፤ በራሳቸው ፈቅደው ነጡበትን ፍቀት እንዲያገግም ለማድረግ። በውነቱ በበታችነት ደዌ ለሚሰቃዩት የ አላዛሯ ኢትዮጵያ የፖለቲካ ሊሂቃን የማገገሚያ ጊዜ ያስፈልጋቸዋል። እዚህ አገር በሽታ ለጠናባቸው የማገገሚያ ሆስፒታል ራሱን የቻለ አለ።

ኢትዮጵያዊነት የነጠረ ፍልስፍና ነውኢትዮጵያዊነት የሰው ልጅ መኖርን ለማኗኗር በብዙ ሁለገብ ሁነቶች የቀደመበት ዩንቨርስቲ ነው። እና የበታችነት ህሙማን በሽታው እንዲህ የጠናባቸው በዬአገሩ እዬሄዱ ስለ ድንቅነሽ ይጎብኙ አዲስ አሉታዊ የፍልሰት የዴሞግራፊያዊ ልብጥ ሰኔል ከሙጃ ለመስራት እንዴህ አቅል ነስቷቸው ከሚንደፋደፉ፤ ፋታ አጥተው ከሚጣዳደፉ  ...አዬሩንም በጭንቀት አውሎ እረፍት ከሚነሱት … ሰብጋት ጥፊም ከሚያጮሉት ...

·       የበታችነት በሽታ ነው ወደ እብደት መንገድ ይቀይሳል

ከበሸታው ሁሉ የከፈው በሸት የበታችነት ነው። የበታችነት የሥልጣኔ ድርቀትም ነው። ኋላቀርነት በሥልጣኔ ኤኮኖሚያዊ ዕድገት አለመመጣጠን ነው። የአደጉ፤ ያላደጉ፤ በማደግ ላይ ያሉ አገሮች የሚባሉት።

እንደ ሥርጉትሻ ደግሞ ኋላቀርነት የአስተሳስብ ድህነትም ነውና የበታችነ ስሜት ወላጁ የአሰተሳሰብ ዕድገት አለመመጣጠን የሚያመጣው ቀውስ ዑደትም ነው ብላ ታምናለች። የበታችነት ንጹሕ ደዌ ነው። እያሉም ሞቶም፤ ሲሞቱሙ ሞተውም ሞትን በድርብ እዬሰለቀጡ እንደ ክኒን የሚያኖር ሥምአልቦሽ በሸታ ነው። በቁም ነፍስ ይማር ሊባል የሚገባው።

የበታችነት በሽታ ተጠቂዎች እራሳቸውን የሚያጽናኑበት በዕብለት በተሸበለለ ሽንገላ ነው። እውነትን በጣም ሲበዛ በጣም ፈሪዎች ናቸውደፋሮች አይደሉምለውሳኔም ቁርጠኛ አይደሉም። ከሃቅ ጋር ከመተያየት እንጦርጦስን ይመርጣሉ።

የበታችንት ስሜት ያለባቸው ሰዎች ጥላቸውን ሳያምኑ እንደባተቱ ይኖራሉ። በጣም ተጠራጣሪዎችን እና አፋኞች እና ጠቅልሎ የመያዝ በሽታም ያለባቸው ናቸው። ይህን ለማስታገስ ደግሞ ቀውስን የሙጥኝ ይላሉ። ቀውስ ሲፈጠር ድንጋጤያቸው ማሰታገሻ ፔኒስሊን ያገኛል።

ሁልጊዜም የበታችንት በሽታ ያለባቸው ነፍሶች ተለዋዋጭ ሰብዕና እጅግ በርካታ ገጸ ባህሬ ነው ያላቸው። ሲያሰኛቸው ኮሜዲ፤ ሲያሰኛቸው ትራጂዲ፤ ሲያሰኛቸው ደግሞ የሲቃ ተውኔት ተዋናይ ናቸው። የሰብዕናቸው መደብም ግራጫማ ነው። ስለ ግራጫማ ሰብዕና ብዙ ጊዜ ብጽፈውም ራሱን አስችዬ ግን በቀጣዩ የምናዬው ይሆናል። መኖሩ ከተገኜ። ስለነገ ቀርቶ ስለቀጣዮዋ ሰከነድ እውቀቱ የባለቤቱ ነውና። 
 
የበታችነት በሽታ በመማር፤ አገር በመልቀቅ፤ ሥልጣን በማግኘት፤ ቤተሰብ በመመሰረት፤ በሹመት እና በሽልማት አይለቅም በፍጹም። እንዲያውም ሹመት እና ሽልማት ሲያገኙም በጣም በበዛ ሁኔታ ደንጋጣ እና ተርበትባች ይሆናሉ። ኮሽ ባለ ቁጥር ይደናበራሉ ይባንናሉ።

የበታችነት ስሜት ያለባቸው ሁልጊዜም ድፍን ቅል ናቸው። ግልጽነት ትውር አይልባቸውም። ሰው ባወቃቸው ጊዜ ነው በሰጨኝ የሚሉት። ምክንያቱም ብዙ ዓይነት ገጸ ባህሪ ስላላቸው አደናገሬ ናቸው። ድንብልብልም ናቸው። ምክንያቱም ግልጽነቱ በዙር ተመለስ ውስጣቸውን ገልጦ እንደሚያንጠባጥባቸው ስለሚያውቁት ሁልጊዜ ንድፋቸው በቀጠሮ ነው። ቀጠሮኛ ናቸው ... 

ሌላው የበታችነት በሽታ የጭንቀት በሽታም ነው። የጭንቀት በሽታ ደግሞ ራስንም ሆኖ ለመኖር የሚፈትን በራስ ውስጥ ባለ መስተዋት ትርታን እዬቀለበ የሚያሳድድ፤ በራስ ዙሪያ ብቻ እዬተሽከረከረ ፋታ የሚነሳ የሚያሰምጥ በሽታ ይመሰለኛል። ይመስለኛል ነው ያልኩት ባለሙያ ስላልሆንኩኝ። 

አላዛሯ ኢትዮጵያ መከራዋ የሚፈለፈለው ተዚህ ነው። በራሱ መተማመን {ኮንፊንደንስ} ያለው ነፍስ ፈጣሪ እስኪሰጣት ድረስ ተግቶ መጸለዬ ይገባል። ከሁሉ በላይ በዚህ በሽታ የተለከፉ ነፍሶችን አቅል አቅም ሰብዕና ከመገንባት መቆጠብም በእጅጉ ያስፈልጋል። ምክንያቱም ተያይዞ ገደል ስለሆነ። እሷንም አያድኗትም እነሱም አይድኑምና

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነው!

ውቦቹ የቀንበጥ ሚዲያ ታዳሚዎች ኑሩልኝ። 
መሸቢያ ጊዜ። 
መሸቢያ ጊዜ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።