አሉታዊው የዴሞግራፊ ፍልስፍና የበቀል ፍልስፍና ነው። {የወግ ገበታ}
እንኳን
ወደ ቀንበጥ ብሎግ በደህና መጡልኝ
የውጥንቅጥወጥ
ውጥን።
አሉታዊው የዴሞግራፊ ፍልስፍና
የበቀል ፍልስፍና ነው። ኢትዮጵያ
ውስጥ የተወጠነው፤ ተወጥኖም
ተግባር ላይ እዬዋለ የሚገኘው
ጸረ ሰው፤ ጸረ -ሥነ -መኖርም ነው
ጸረ ሥነ አዕምሮም ነው።
ክፍል ሁለት።
„የደከሙትን እጆች አበርቱ፤
የላሉትንም ጒልበቶች አጽኑ።“
ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፴፭ ቁጥር ፫
ዝግጅት ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
06.06.2019
ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ።
ተስፋ ሂደት፣
ተስፋ ዘመን፣
ተስፋ አድዮ ነው።
·
እፍታ።
የተከበራችሁ የቀንበጥ ብሎግ ታዳሚዎቼ እንዴት ናችሁ? ዛሬ
ቪንቲ ፏ ፍንትው ብላለች። በእለቱ አሉታዊውን የኦዴፓን የዴሞግራፊ ፍልስፍና በቀጣይነት እናያለን …
እርግጥ በሁለት እርእስ
ነው የመጣሁት። አውራው እርሰ ጉዳይ ከማጠናከሪያው እርስ ጋር የተዋደደ ነው። መስተጋብራዊ ውህደቱ በሚስጢር ሳይሆን በይፋዊ ጉባኤ ነው።
አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ እንደምናዬው አውራው ድርጅት ኦዴፓ
እና የዴያስፖራው አውራ ድርጅት የቀሰተደመና ወራሽ ግንቦት 7 አብረው በትብብር እንደሚሰሩት። ትብብር ነው ያለኩት ቅኔዎቼ?ተቀናቃኝ/ ተቃዋሚ/ ተፎካካሪ አልወጣኝም።
ያ ክስመት ነው ትንት እንበለው ይሆን። ትንት ይሻላል ... ትናት አሰኝቶት መጪ ብሏል ... እቴ እነሱ ግጥግጡን እያስነኩት ነው ስላችሁ ...፧
አሁንማ የጫጉላ ጉዞውም አንድ ላይ ሆኗል። ሁለቱም
ሁለተኛ ርዕሰ መዲናቸውን ዲሲን አድርገው ዘንከትክት እያሉ ሰነባብተዋል። ሦስተኛዋ ከተማ ደግሞ ብራስልስስ ናፍቆትዬስ ስለምን ይቅርባት?ሰኔሻ ትዝታን ድገመኝ፤ ሀምሌዬ ሽውታን ድገመኝ ... ኩትኩቱን በዘንጣፌ ...
·
የወግ ገበታ።
የኦዴፓው አሉታዊው የዲሞግራፊ የሂደት ቁንጮ መሰረታዊ ውስጡን የጸነሰው
በቀልን ነው የሚል እምነት ነው ያለኝ። በጦርነት አትራፊ ወገን፤ አሸናፊ ወገን የለም ከበቀል በስተቀር። በበቀል ሥነ - ልቦናም
አትራፊም የለም። አትራፊው በቀል ነው። በቀልን አቅዶ መከወን ደግሞ መጨረሻው አሟሟቱ የከፋ ነው የሚሆነው። ከበቀል ትርፍ ተገኜ
ቢባል የሃሳብ አመድ ብቻ ነው።
ኢትዮጵያ ውስጥ የዲሞግራፊ ፍልስፍናውን የህዝብን የአኗኗር
ስብጥር ለመበወዝ ወይንም ለመቀዬጥ የተሄደበት የመንፈስ የቅይሳ ምህንድስና አሉታዊ በሆነ መንገድ ነው የተጀመረው፤
ውጥኑ ራሱ ቀጅቃጃና ቦጅቦጃ ነው።
ሲያቅዱትም ሲፈጽሙት የደፈሩትን ያህል እምቅ አቅም አልበራቸውም ማህንዲሶቻችን ገመናው በሰማዕቱ ዶር አብርሃም አለሙ ሲወጣ። አቅለቢስነት፤ ትግሰት አልባነት፤ ብስጩነት ነግሶ፤ እልህና ቁጭት አጎፍሮ ነበር የተመለከትነው።
አቅደህ
ለከውነከው ድንጋጤን ምን አመጣው? ኮሽ ባለ ቁጥር ምንስ ያደናብራል?ምንስ ያባንናል? ባልደራስ መከራን ተንበርክኮ እንዲዝቅ የተበዬነበት መከራው እኮ ያ ሲኦላዊ ምህንድስና ይነቃነቃል መሬት ሳይዝ ነው። ሌላ ነገር የለውም። መንፈስ ላይ ያለውን የተቀባይነት ማሳ ደግሞ አላዩትም እንዲት እንዳቃረው ...
መጀመሪያ አገር እንመራለን ብለህ እንዲህ መሰል ድንብዝ ውሎ ጉዞ የሌለው ከይሲ ተግባር አለመወጠን የዲሞክራሲ አሻጋሪ መንገድ እና ህይወት እኔ ነኝ ካልክ ዘንዳ።
ነገሩ ግን "አንቺው ታመጪው አንቺው ታሮጪው" ነው የሆነው። በወንጀል መጠዬቅ ሲገባ ሹመትና ሽልማት አዬን፤ እሱም ይሁን ሲባል አብራችሁ አጨብጭቡ ለመፈረሳቸው ወረብ አሳዩ፤ ማህሌት ቁሙ ግን በውነቱ ገምድልነት ነው። ከቶ የገዢዎቻችን ህሊና ለሌላ ተልዕኮ ለመፎር ዘመት ተሰደደ ይሆን?
ውይ ረስቼው ... ከሰሞናቱ ደግሞ ወግ አይቀርምአንድም ህግ ጣሽ ተጠርጣሪ በህግ አግባብ ሳይታይ ማህበረ ህግ ዕድምታ በገናናው አምዬ አጤ ሚኒሊክ ቤተ መንግሥት አሰተዋልን። መላ ጠፋ ...
ዴሞግራፊ በቀና ቢሆን ኖሮ ሰዎች በጦርነት፤ በራህብ፤ በተለያዩ የተፈጥሮ
አደጋዎች፤ ለምሳሌ በውሃ ሙላት፤ በድርቅ ቢሆን እነሱኑ መልሶ ለማቋቋም በወል ጥረት ማድረጉ ቢያስመሰግን እንጂ የሚያስወቅስም፤ ለማግስትም የሚያስፈራም
አይሆንም ነበር። ነገር ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ፖለቲካ ሴራ ብቻ አይደለም፤ በቀልንም የጸነሰ መሆኑ ነው ክፋቱ።
ባለፈው ጊዜ በአገራችን የተከወነው የአንድ ሚሊዮን ዜጎቻችን
ፍንቀላ በራሳቸው በፈጻሚዎች በኳስ
አጫዋቾች አንበል ከተሰጠን መረጃ
ጋር ሲገናዘብ ግን ዴሞግራፊ ፍልስፍናው ለጥነት ተግባር በቀጥታም ለበቀል ተልዕኮ ስለመሆኑ ገልጦልናል።
ምስቅልቅልን፤ ህውከትን፤ ቀወስን አቅዶ መከወን? ግን እኛ
ምንድን ነን? ሰው ነን ወይንስ ልብ የለበስን እንሰሶች?
ይህ የጥነት ውጥን ውጥንቅጥ የዝልቦ መከራ ተግባር ዛሬ
አይደለም ሌላውን አሳርሮ ወይንም አጎሳቁሎ የሚገኘው፤ የነገ የትውልዱ ተስፋ በቆዬ ነባር፤ የእኔ በሚለው ባህሉ፤ ሥነ - ልቦናው፤
ሃይማኖቱ፤ የአኗኗር ዘይቤው ላይ ሊያመጣ የሚችለው ተጽዕኖ በርቀት ሊታሰብበት ይገባል።
ጉዳዩ የሰሞናት ህውካታ የሚፈታው አይደለም።
በጥልቀት እና በጥንቃቄ ሊታይ የሚገባው ጉዳይ ነው። ማቆሚያም ማለቂያም የለውምና … በቀለኛ መንፈስ ሲሄድ ውሎ ሲሄድ ማደረ፤ ሲሄድ
ውሎ ሲሄድ ማደር ነው … ራሱ ቀዳዳውን ለመወተፍ የሚጓጓዝበት አስፓልቱ ራስ በራሱ ነው የሚዋራርድው በቀል X በቀል= በቀል።
ችግር ጭራውን ሳይሆን ሆድ ዕቃውን ማዬት የሚችለው እጬጌው
ሂደት ፈቅዶ ትንፋሽ ሰጥቶት ሲያጎለምሰው ይሆናል። አሁን የምናዬው የእግሩ እጭ ነው። ነገ ችግሩ ወደ ፑፓ ተሸጋግሮ አዳልት ሲሆን ፈጽሞ ኢትዮጵያ ልትወጣው ከማትችለው አርንቋ ውስጥ ትገባለች።
ከዚህ ጋር በተያያዘ ጋንቤላ ላይ ያለው የደቡብ ሱዳን ስደተኞችን፤
የኢሳ እና የአፋር ግጭትንም አስመልክቶም ያው የችግር እጮኛሞች ከዚህ ጉዳይ ጋር በጽኑ የተሳሰረ ነው። ባለቤት አልባ በነበረችው አላዛሯ ኢትዮጵያ የተጎረጎረን፤ ውስጥን ለመቦርቦር በዬአቅጣጫው ያለው የፈተና ማጫ
እና ግጥግጥ ከልብ ሆኖ ሊታሰብበት ይገባል። ግን ብአዴን ለግንቦት 7 ሥጦታ አበረከተለትን አቤቶ ኦዴፓ? አጀንዳው ወጥ ሆኗልና።
በሱማሌ የቀደመው ወንጀል እራሱ የአንድ ሚሊዮን ዜጎችን አቅደህ፤ የራስህን ወገን አፈናቅለህ በስተጀርባ ያለውን ፖለቲካዊ ፍላጎትህን ለማሟላት ስትነሳ በራሱ በቀል ነው።
የእኔ እናት፣ አባት፣ እህት፣ ወንድም ቢሆኑ
ብሎ ማሰብ ምንኛ ሰውኛ እና ተፈጥሮኛ በሆነ ነበር።
አኗኗራቸው ለራፊ ያልበቁ ነበሩ። ያም ኑሯቸውም ተቀንቶበት ማለት ነው
ያን ሰቆቃ የተቀበሉት። መቼም የኢትዮጵያ ህዝብ ኑሮ አሁን ከሆን ሚዲያውን ስልምንከታተለው እዬተመለከትነው ነው። ያው የዛሬ 27 ዓመት የነበረው ጭቃ ቤት 27 ዓመት ሲቆይ እርጅናው ተጫጭኖት ጉስቁልናውንም በከዘራ እያስኬደው እንደ ሆነ እያየን ነው።
ቤቶች ሁሉ አዛውንትነታቸው በተጎንብሶ መሄድ ሲያስከንዱት
እያስተዋልንም ነው። የግል ቤቶች ብቻ አይደሉም ቢሮዎችም። የከተሞች እድገት የሚባለው ቧልት እዬቃኘነው ነው። እኔ ከ27 ዓመት
በፊት የማውቀው የስሜን አውራጃ ከተማ የደባርቅ ፖሊስ ቢሮ ተጎንብሶ ነው የሚገባባበት ነው። አቶ ንጉሱ ጥላሁን የከተሞች እድገት
ያሉትን በፎርፌ ዜሮ የሚያሰገባ ሃቁ ይኸው ነው። ለነገሩ እሳቸው እራሳቸው የዘመን ምጥ እና ዳጥም ናቸው።
·
ምልሰት።
በምልሰት ያ ሁሉ ህዝብ እዬተፈናቀለ በ2017 መጨረሻ እንደ
ፈረንጆች አቋጠጠር ያን ጊዜ ኦህዴድ በዝምታው
ውስጥ ሆኖ ይተጋ የነበረው ህወሃትን ከቤተ መንግሥት መንበሩን ለመቆጣጠር፤ በሚዲያው OBN ዛሬ የማያድርገውን ያን ጊዜ ግን የተጋበት
የቀደሙ የትውልዱን ታሪኮችን፤ የማይደፈሩ አገራዊ ፋይዳዎችን አግዝፎ ዶክመንተሪ በመስራት እና በማውጣት፤ በዚያ ዙሪያ ሙሁራን በማውያዬት፤ „ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነው እና መደምር ሥነ - ቃል“
ዘመቻን ሥነ - ልቦናን የመግዛት ቀልብ ነበረው። ሙሉ አትኩሮቱ እዛ ላይ ነበር።
በተፈናቃዮች ላይ የነበረው አትኩሮት ደግሞ እርዳታ አሰባስቦ
ቤት የመገንባት ተግባር ነበረው። ያ በውነቱ እንደ ቅዱስ ተግባር የታዬ ነበር ለእኔ መሰል ጅሎች።
ቀልባችንም ልባችንም ሸልመን „ለማውያን“ ያሰኘን ትዕይንትም
ነበር። እኛ ጉዳያችን የማናውቀው የዘመን ጅሎች የህዝባችን መጠለያ ማግኘት ብቻ ነበር የተመለከትነው።
ስለምን አዲስ አባባ እና አካባቢው ተፈለገ የሚለውን ከጉዳይ
ያስገባው ቀርቶ እኔ ለራሴ ትዝም አላለኝም ነበር። የእኔ ትትርና እና ጥያቄ የነበረው ወላጅ አልባ ህጻናት አሰባስቦ አንድ ተቋም
ፈጣሮ የትውልዱ ተስፋ እንዲሆኑ በጽኑ አሳስቤም ጽፌም ነበር።
እጬጌው ሂደት ግን ገመናውን በራሳቸው አንደበት ዘረገፈው
እና የቀደመውን መፈናቀል ከአሁነ አሰፋፈር እና የወደፊት ትልም ጋር ስናመሳጥረው ከበቀል የተነሳ ስለመሆኑ ቁልጭ ብሎ ይተዬናል።
የኦሮሞ ልጆች በአገራቸው መሬት የትም ቦታ ይመቸናል ባሉበት
ባድማ የመቀመጥ መብት ሲኖራቸው ግን ከዛ ተፈናቅለው ወደ ሌላ ወደ ማያውቁበት ቦት ለፖለቲካ ትርፍ ሲባል ማምጣት ግን በራሱ ወንጀል ነው። ግን "ልጁ ዳኛ
አባቱ ቀመኛ" የሆነበት ጉድ ሆነና ህግም በዘመኗ ጠና አቤት ትላለች ወደ እዮር።
ቤት ገመና ከታች ነው። በቤት ውስጥ ስንት ነገር አለ?
በድንገት ደራሽ መከራ ፍንቀላ? እንደ ሰው ሆኖ ለመሰብ ከልተቻለ ማግስት ከመምጣቱ በፊት ይደርቃል ይበናልም?
ሌላው አቶ ለማ መገርሳ እንደተናገሩ „ቢቸገሩ ቢቸገሩ ሁለት አመት ብቻ ነው፤ ከሁለት ዓመት
በሆላ እግራቸው መሬት ስለረገጠ ሰው ይሆናሉ“ ሲሉ ያስ አገራቸው አልነበረንም? ከሁለት ዓመት በኋዋላስ ምን ታቀደ ብሎ
ማሰብ ይገባል?
ይህን ማንም የልቤ ብሎ አላሰበብትም። እነዚህ ምንዱባን በቀጣይ ደግሞ „ዘመቻ ምንትሶ“ በሚል ለዬትኛው ተግባር እንደሚሰማሩ?
ለማን? ለምንስ ፍላጎት ተደራጀተው እንደሚመጡ የሚታወቅ ነገር የለም?
·
የመከራ ሽልማት።
በሌላ በኩል ተፈናቃይ ወገኖቻችን የአዱገቡት ሰፈር ሲለቁም
ብዙም ነገር ነው የሚፈናቀለው። ቂሙ እዛ ሲኖሩ ሱማልኛ ቋንቋን፤ ባህል፤ ሥነ - ልቦና ጋር ተዋደዋል ነው አንዱ መሞገቻ። ይህ ዕሳቤ ጌዲዮ ላይ ደግሞ የማጥራት ዘመቻ ነው የተካሄደው።
ይህ
ዕሳቤ ጨፍላልቆ ወጥ ማህበርሰብን {ሆሞጂኒዬስ} ለመፍጠር የታለመ ብቻ ሳይሆን የአዲስ አባባን ፖለቲካ ለመቀዬር መታለሙ ደግሞ ነገ
የዛሬው አዲስገብ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ያሰፈሩት ወዝጠገብ ሲሆን በእነሱ እንጀራ የሚተዳደር ወገን ምን ሊያመጣ እንደሚችል አይታወቅም።
ስምሪቱ የሚከወነው በኦዴፓ ጠቅላይ አዛዥነት እና የጦር መሪነት ነውና።
ይህ ፍንቁል ህዝብ ና ሲባል የሚመጣ፤ ሂድ ሲባል የሚሄድ የኦዴፓ
የተጠንቀቅ ተጠባባቂ ሠራዊት ነው ማለት ነው። የራሱን
ማንንት በራሱ ጊዜ ያስረከበ። መቼም የሰው ማንነት በቋንቋ ብቻ የሚገለጽ አይደለም፤ ይህ በቁንጽል ለሚያስቡት ብቻ ነው።
በቀጣይ ጹሑፎቼ በዝርዝር እመጣበታለሁኝ። ይህ የሥነ - ህዝብ አሰፋፈርን ስብጥር ብወዛ ሲከወን ቂምን ቋጥሮ መሆኑ እያንዳንዷ ሥንኘን
በሚገባ ማጥናት ይጠይቃል።
መረጃ ሳይኖረን የማንንም ስም አላጠፋንም፦ ትርጉም በአብርሃም ዓለሙ (ዶ/ር)
ስለዚህ በቀሉ ጥምር ነው ማለት ነው። ተፈናቃዮች ሲፈናቀሉም፤
ሲሰፍሩም የበቀል ማወራራጃ
ሆነዋል ማለት ነው። አዲስ አባባ እና አካባቢው የሚኖረው ህዝብ
መለያው ኢትዮጵያዊነት ነው።
ከዚህ ውስጥ አንዱን ማህበረሰብ አውጥተህ ደግሞ ከተፈናቀሉት
ሥነ - ልቦና ጋር ወጥ አድርጎ የመቀመር ሌላም መሰሪ ስልት አለበት ማለት ነው። ኢንጂነር ታከለ ኡማ በሹመታቸው መባቻ ያደረጉት ይህን ነበር።
የኦሮሞ ወጣቶችን ነጥሎ ስብስቦ ማወያዬት። ቢሮ አደረጃጀቱም ይኸውን የተከተለ ነው።
በሌላ በኩል አዲስ አባባ የሚኖረው 79 ብሄር ብሄረሰብ
አባላት ደግሞ በዚህ ሂደት ግለት፤ ጫና እና ጭቆና ተቃዶ ተፈጽሞበታል። ምክንያቱም እነሱ ፕሮጀክታቸው ኦሮማዊነት ነውና።
የኦሮሞ ፖለቲካ ደግሞ ዓለም የሚያውቀው እኛም ከመስማት
አልፈን እያዬነው ያለው ሃቅ ነውና። ጠረኑ ቀውስ ጠማኝ ነው። የተሰበሰበ ፍላጎትም የለውም። እልቀት ቢስ ፍላጎት አዝሎ ነው ተሰልፎ
ያለው። ግን እያሳካ ነው። ህግ እንኳን እንዳይጠይቀው በይፋ ነው ድጋፉ እና እንክብካቤው።
በዚህም በዚያም ሰብዕና ሲገነባ በዝምታ የተከታተልኳቸው፤
በቁጥብነት ማስተዋልን ህሊናዬን መግቤ ሳደምጥ የባጀሁት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ሲዳሞ ላይ እንደዛ ኤጆቶን ሲያነግሱ ምን ተብሎ ሊተረጎም
እንሚችል አላውቅም። አንቦ ላይ በምን ሁኔታ፤ ሲዳሞ ላይ በምን ሁኔታ ..
ስንት መልክ፤ ስንት ይዘት፤ ስንት ቅርጽ ይዘን አገርን ያህል
ነገር ለመምራት እንደተሰናዳን ማዬት ይቻላል። ሚገርመው ይህን ለማጠፋፋት ደግሞ ሌላ ትዕይንት ተከውኗል ከሰሞናቱ። የምክትል ፕሬዚዳናቷ ወደ ቤተመንግሥት መግባት እንደ ጥሩ አጋጣሚ ታይቶ ... ህም ነው። እናስተውል እባካችሁን ...
አገር የሚመራው መንፈስ ራሱ ጃዋራዊ እኮ ነው። ለምን ይህን እናባጭለበታልን ... ፍኖተ ካርታ ማውጣት የተሰናው የ አብይወለማ ካቢኔ በዚህ መክንያት ነው።
ቀደም ብለው አቶ ሌንጮ ለታም ከዛው ነበሩ በኩሽኛ ዘይቤ።
ሲዳማዎች ግን ማሰብ እና ማሰተዋል የሚገባው ነግ ለእኔም የማለቱን ብቻ ሳይሆን የመዳኛ መንገዱን ዓይናቸውን ገልጠው ሊመለከቱት
ይገባል። ጌዲዮ ላይ የደረሰው መከራ እነሱንም ይለፈኝ ስለማለቱ ዋስትና የላቸውም። በቃኝን የማያውቀው አሉታዊው የዴሞግራፊ ሂደት ሱናሜ ነው፤ ርህራሄም የለውም የጊዜ ጉዳይ ነው … ውስጥህን ሰጥተህ ከመለመን
ውስጥን ቆጥቦ መቆዬት የተከደነ ሲሳይ ባለቤት ያደርጋል።
Ethiopia : ጀዋር እና ሽመልስ ፍቼ የመገኘታቸው ሚስጥር |ጨምበላላን እንደ ኢሬቻ
| ሙሉ ቪዲዮ | Jawar Mohammed | Shimelis Abdisa |
·
ሽብርን ስጋትን አቅደህ ዴሞክራሲ…?
የሆነ ሆኖ ለታላቋ ኦሮምያ ጠቃሚ የሚባሉ ነገሮች ሁሉ ቀውስን፣ ሽብርን፣ አለመረጋጋት አክሎ ቀጣይ ነው። እኛ ትጥቅ እስከፈታን ድረስ። ትጥቅ አስፈቺ ደግሞ የራሳችን የነጻነት ትግሉ ቤተኞች መሆናቸው
ደግሞ ተጋድሎውን መራራ፤ ጎምዛዛ እና ጥቁር ያደርገዋል።
በዚህ ዙሪያ ነው ፖለቲካቸው እያጠነጠነ የሚገኘው። ይህ
ደግሞ ለኢንዲት ገናና አገር አንዲት በታሪክ፤ በትውፊት፤ በትሩፋት በህብራዊነት ለበለጸገች አገር የሚመጥን አይሆንም፤ ሂደቱም ሙሉ ለሙሉ የበቀል
እርምጃ ነው።
ይህን ተጻሮ ነው የቆመው። አሁን የቤተ መንግሥቱ እደሳ ፕሮግራም ጥድፊያው ስለምን ብቻ ሳይሆን ሃላፊነት ያለውን ድርጅት ሳያማክሩ ርምጃ መውሰድ ራሱ ጠ/ሚሩን የሚያስጠይቅ ሆኖ ነገር ግን አቶ ዮናስ ደስታ ናቸው ከሥራ የተሰናበቱት ... ለዚህም ነው እኔ ይህ አሉታዊ ዴሞግራፊ ፍልስፍና የመንፈስ ቀዶ ጥገና ምህንድስና ነው የምለው።
አጥብቀው የሚጠሉት፤ የሚጸዬፉት ባህል፤ ቋንቋ፤ ሥነ -
ልቦና፤ ታሪክዊ ትውፊት፤ ወግ፤ ልማድ አለ፤ ያን አስሎ፤ እንደ እንሶስላም ሰልስሎ የማስወገድ
ተግባር አህዱነቱ በቁጥር አንድ ሳይሆን በግማሽ ሚሊዮን ህዝብ ነው የተከወነው። አንድ በጥባጭ ስንት ነገር ሊያጣፋ ይችላል እንኳንስ ግማሽ ሚሊዮን ህዝብ? ሰባዕዊነት ከሆነ አማራስ ገዲኦስ ሰዎች ዜጎች አይደሉምን?!
ከዚህ ጋር በተያያዥነት የሚታዬው „የእኛ ሰዎች ወደ ስልጣን
ከመምጣታቸው በፊት ሁሉም ቦታ ቦታ ገው ገው“ ነበር ያሉት የአቶ በቀለ ገርባ ራሲስታዊ በቀል ጠገብ ማንፌስቶም
ከዚህ ጋር ተቀናጅቶ፤ ተዋዶ ሊታይ የሚጋባው ይሆናል።
ነጋዴ በኦሮምኛ ካልሸጠ አትግዙ – አቶ በቀለ ገርባ
March 23, 2019
ስለሆነም ዛሬ ባለው ሁኔታ የኢህዴግ አውራ ፓርቲ ኦዴፓ
ለውጡን አሻጋሪነት ለማሳካት አሉታዊውን የዴሞግራፊ ፍልስፍናን ጸንሰህ ዴሞክራሲን ወደ ተግባር ለማሸጋገር መተለም ቀርቶ ቃሉን ለመናገር
ሞራሉ የለውም ባይ ነኝ እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
በአሉታዊ የተወጠነው የዴሞግራፊ ፍልስፍና ለዴሞክራሲ አዋላጅ ነው ብሎ ማሰብ ሰማይ እና መሬት ተገናኝተው አንድ ይሆናሉ እንደማለት ይሆናል።
ፍልስፍናው ወደ ድርጊት ለመለወጥ ኦዴፓ የሄደበት መንገድ ለበቀል ነው ብዬ ነው እኔ እማምነው። በውስጡ አብዝቶ የተጠዬፈው የጠላው ነገር አለው። ይህ የጠላው ንጥረ ነገርን በውዞ በአዲስ ስልት እና ቅዬሳ፤ በአዲስ የህዝብን የአሰፋፈር ስርጭት ለመቀዬር ለመቀዬስ ታልሞ የተከወነ ነው።
የዲሞግራፊ ፍልስፋና አመዛኙ ሰዋዊ ነው። ጥቃቱም ሰለባነቱም ሰዋዊ ሆኖ ነው። ነገር ግን ሰዎች የሚኖሩት እንሰሳትንም አላመደው ስለሆነ እነሱም የዚህ ሰላባ ተጠቂዎች ናቸው። እራሱን አሱን
ያጣ ቤተሰብ አይደለም ለማዳውን እንሰሳውን ልጁንም መርሳቱ የግድ ይሆናል። ሰቲት ሁመራ ሲለቀቅ በዚህ ዙሪያ የከፋ ነገር መከሰቱን አውቃለሁኝ። አራስ ልጅ እናት እንዴት እንደተለያዩ ...
·
የምስቅልልቅ ሸመታ።
ይህ ሁሉ ምስቅልቅል በቀልን ጸንሶ፤ በቀልን ለማዋለድ በመሆኑ
በሰማይም በምድርም ሊወገዝ ይገባል። ልንጠዬፈውም ይገባም ነበር። የሰሞናት አጅንዳም ብቻ ሊሆን አይገባም ነበር።
ለፖለቲካ ትርፍ ከቀውስ ምስቅልቅል ሸመታ አድነኝ ብሎ ህሊና
ያለው ጤነኛ ሰውም ሊጸልይ ይገባል፤ እነሱም ሱባኤ ሊይዙ ይገባል። መጋቢት አንድ ቀን የታዬው አደጋም ይኸው ነው።
ለነገሩ ጠ/ሚር
አብይ አህመድ ወደ ሹመት ሲመጡ ከዋዜማው ዕለት ጀምሮ ያልተለመዱ ብዙ ሰማያዊ ማስጠንቃቂያዎች ነበሩ። የመሬት መራድ፤ የመሬት መገመስ፤
ያልተለመደ ድምጽ ከሰማይ መውረድ፤ ከሰማይ እሳት መዝነብ፤ ብሄራዊ ሰንደቅ ሰማይ ላይ መታዬት ወዘተ …
·
ሰውኛነት።
ጥንቃቄ መደረግ ያለበት ግን ተገደው መጥተው አዲስ አበባ
እና በአካባባዊ የሰፈሩ ወገኖች ግን ካለ ሳሃቸው መውቀስ፤
በከፋ ዓይን መመልከት፤ ማግለል እና አንዳች ነገር በእነሱ ላይ ጥቃት መፈጸም እንሰሳነት ይሆናል። ለነገሩ ሚዛናች እኮ ሰውኛነት
ቁልቁል ሆኗል። ሰው መገደሉ አልበቃ ብሎ ተቀጠቀጠ፤ ተቃጠለ ነው የሚደመጠው። ተሳህለነ!
የሆነ ሆኖ በግፍ ፍንቀላ የተካሄደባቸው እነሱ በራሳቸው ላይ የመወሰን ቅንጣት መብት የላቸውም። ለእነሱ ከዚህ የአፓርትመንት ኑሮ ይልቅ ሱማሌ አካባቢ ከእባቱ አረንቋ አቅራቢያ ከምትገኘው
ግርግም ጎጆ የበለጠ ሐሤታቸው ነው።
ራሱ የቆላ ሰው ግልጽ እና ቀጥተኛ ነው። ባህሪውም ድብ ያለ ሳይሆን ፍንትው ያለ ነው ለዛውም ሀረርጌ። በአኗኗርም ዘይቤው
ከደጋው ጋር በብዙ የሚለይ ስለሆነ ለእነሱ
የፈተና ዘመናት ነው።
በእነሱ የተወሰደው እርምጃ አብሯቸው ያደገውን ቅይጥ ሥነ ልቦና እና ሱማልኛ ቋንቋን እንዲፋቱ
በሌላ በኩል ደግሞ አዲስ አባባ ላይ ለሚገኘው አማርኛ ቋንቋም ላይ ተጨማሪ ጫናዊ ተጽዕኖ እንዲያሳድሩ እነሱ ባልመከሩበት ሁኔታ፤
በተደራጀ መንገድ የበቀል ጦር ማስፈጸሚያ መሆናቸው እንድ ዜጋ ያንገበግባል፤ ይመረምራል፤ ያማልም …
ወላጅ አልባ የቀሩ ልጆች፤ ትዳር አልባ የቀሩ ሚስቶች፤
እና ባሎች፤ ጠዋሪ አልባ የቀሩ ህሙማን፤ አዛውንታት፤ አራሶች፤ በግፍ የተደፈሩ እህቶች የደቂቃ ሰቃይ ሲታሰብ ይኮሰኩሳል እንኳንስ
ለወራትማ ከቶ የኢትዮጵያ ህዝብ ከብረት ቁርጥራጭ የተሰራ ነው ያሰኛል? ነገስ? ነገ ደግሞ ባለተራው ይቀጥላል …
ከዚህ ጋር በዬትም ቦታ የሚገደለው የሚፈናቀለው ወገን ጋር
ሲነጻጸር ግን ከሱማሌ የተፈናቀሉት ወገኖች የተሻለ ዕድል አላቸው ማለት ይቻላል፤ ሦስተኛ እና አራተኛ መፈናቀል አይገጥማቸውም፤ ሁነኛ
ባለቤት መንግሥትም ስለአላቸው።
·
መከወኛ።
ውዶቼ የቀንበጥ ሚዲያ ታዳሚዎች ቅኖቹ ቅኔዎቹ በዚህ ዙሪያ ይቀጥላል።
ይህን ጉዳይ እንደገብስ ግምድል ሊጥ ሸብልለን፤ እንደ ሪሚጦ ሸፋፍነን ረምጠን መተው የለብን። የቅንጅት ፍርሰት በወቅቱ ፍርጥርጥ ብሎ ወጥቶ ቢሆን ኖሮ፤ ችግሩ ለዛሬም ተሻጋሪ ባልሆነም
ነበር።
ችግርን በወቅቱ ሳይከድኑ ወይንም ሳያባብሉ ወይንም ሳያቆላምጡ
አፍረጥርጦ ከነጠረው እውነት ጋር የማገናኘት ተልዕኮን አዲሱ ትውልድ እንደ መርህ ሊወስደው ይገባል። ግልጽ በሆነ መስመር ላይ ነው
ወጣቱ አቅሙን ማፈሰስ የሚገባው።
ወጣቱ ራሱን ማበከን አይኖርበትም። ማግባት ባለበት ወቅት
ማግባት፤ መማር ባለበት ወቅት መማር፤ መሳተፍ ባለበት ጉዳይም በቀጥተኛ አቋም እና ውሳኔ ሊሆን ይገባል።
የትናንቶቹ የ60ዎቹ የፖለቲካ ሊሂቃን ናቸው አሁን በአከተርነት
ተሰልፈው፤ ዕድሜውን ሳይቀር እዬቀሙት የሚገኙት። አሁንም ወጣቱ በዘመኑ በራሱ ጊዜና ወቅት ከፖለቲካ ተገሎ ዕድሜውን እንዲሾልከው የሚያደርጉት።
የአብን ፍዳም ይኸው ነው። አመራሩ በሙሉ ወጣት ነው የአብን። ስለዚህ
በቀደሙት ድንጋጤ አመጣ። ምክንያቱም እንሱ በ70 // 80 ዓመታቸውም ተንታኝ ናቸው፤ ቀያሽ ናቸው፤ አራጊ ፈጣሪ ናቸው በዛው በኩሬ ውሃ ዕይታቸው እና ግንዛቤያቸው።
እነሱ የመዳህ ፖለቲካ ነው የሚያራምዱት። አንድ ቀን እግረ ተከል ሆነ የማያውቅ። ዕድሜያቸው ሄዷል የሥልጣኑ ፍላጎት ግን
„ፍቅር እሰከ መቃብር“ መርህን ተከተል ብሏል። ጊዜ ቆሞ የሚጠብቀው እንሱን ብቻ ነው። እነሱ ወደ ምድር
ሲመጡ የነበረው ሰዓት ሳይዞር እዛው ላይ እንደቆመ ነው¡ ሰ ዓቱ ተፈጥሯዊ ሂደቱን ክዶ በእነሱ ፍቃድ ነው የተሰራው¡
ልምዱ ተመክሮው አውንታዊ ቅናዊ ቢሆን የአመራር ተከታታይነት
ያፈልቃል፤ የእነሱ ግን ሙጭጭ ነው … ቡቃያን መቀንበጥ … መዘንጠል … ማሳረር … ማምከን …
ይህ ሂደት በእኛ ዘመን ማብቃት አለበት። አማካሪዎቹ እነሱው መሆናቸውን „ልብ ያለውን
ሸብ“ እንደ ጎንደሮች መርሁን ወጣቱ ማድረግ ይጠበቅበታል።
በሌላ በኩል ግን … ወጣቱ ሴረኛም በቀልኛም መሆን የለበትም። እነዚህን ጸረ ሰብ ባህሪያትን
በጽኑ መጠዬፍ ይኖርበታል። ሰውን ገድለህ፤ ሰውን አፈናቅለህ፤ ሰውን ጠልተህ፤ ሰውን አግለህ ዕድሜህ የሐሤት ሊሆን ከቶውንም አይችልም።
ፈጽሞ! ፈጽሞ!ህሊናን ማሰደድ ስለማይቻል ...
በቀል የጥፋት ጽንስ ነው።
በቀል የጥላቻ ውላጅ ነው።
ጌጦቼ .... አብረን ቆዬን በሞጋች መጣጥፍ።
ህሊናችን የተሰራ ሁሉንም ነገር እንደ ወረደ እንዳለ ለመቀበል ሳይሆን ለሙገታም ነውና ለማድመጥ በመፍቀዳችሁ እንሆ ደስ አለኝ፤
ኑሩልኝ ለእኔም ለአላዛሯም ኢትዮጵያ። መሸቢያ ጊዜ።
ፍቅር ሲያልቅ ትዕግስት ይሰደዳል።
ትእግስትም ሲያልቅ ፍቅር
ይሰዳዳል።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ