አሉታዊ ዴሞግራፊ የቂም ደም ነው።
እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በደህና መጡልኝ
አሉታዊ ዴሞግራፊ የቂም ደም ነው።
ቂመኝነት መርዛማ የህሊና ብል ነው።
ክፍል ሦስት
„የደከሙትን እጆች አበርቱ፤
የላሉትንም ጒልበቶች አጽኑ።“
ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፴፭ ቁጥር ፫
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
11.06.2019
ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ።
ተስፋ
ፈታሽ
ተስፋ
ጠያቂ
ተስፋ
ሞጋችም ነው።
ተስፋን በዝም ብሎ ማስኬድ
አይቻልም። ተስፋ ራሱ ተስፋ ሰጪውን ይፈትሻል። ተስፋ ለጋሺውን ይሞግታል። ተስፋህ ነኝ ያለውን የፈታትሻል። „ለእናት አገራችን
ሲባል ሥልጣን በአናቱ ይዘቅዘቅ“ ያሉት የዛሬው የመከላከያ ሚ/ሩ አቶ ለማ መገርሳ ዛሬ ላይ መልኩ፤ ይዘቱ፤ ፎርሙ እና ቅንብሩን የራስን ህሊና ሳይቀር አሳምሮ ይሞግታል
የተናጋሪውን መንፈስ አካል፤ ህሊና፤ ሩኽ ጭምር ረፍት ነሺ አመክንዮ ነው። የሚሞግተው አርስ በእርሱ ነው።
እንዲህ ካለው ክህደት ጋር …
መረጃ ሳይኖረን የማንንም ስም አላጠፋንም፦ ትርጉም በአብርሃም ዓለሙ (ዶ/ር)
በኢትዮጵያ ፖለቲካ ያለው
ተጨባጭ ሁኔታ የሚያሳዬን አክሮባቲስትነት ይኽውን ነው መገላበጥ እንደ ሽንብራ ቂጣ። ተፎካካሪ/ ተቃዋሚ/ ተቀናቃኝ/ የተፎካካሪ ተደማሪ ሁሉም በተስፋ ውቅያኑስ ህዝብን ከ50 ዓመት ላላነስ ምን በመሰለ ኦፔል መርከብ ቂምን ሰንቆ ግን
ተመስጥሮ ሲቀዝፉ ... ሲያስቀዝፉም ኖረዋል። ከእንግዲህ ግን የሚችሉ አይመሰለኝም፤ አብሶ ህሊናው ከራሱ ጋር ላለ ፍጥረት። ኢትዮጵያን ያቄመ ነፍስ መቼውንም ከርደት አይድንም።
ዘመኑ ባለኪዳን ነው። እጬጌው ዘመን የትውልዱን
ብክነት አይቶ መዳህኒታዓለም አባቴ ማንዘርዘሪያውን ይዞ ከች ብሎ ቀረ የሚባል የፖለቲካ ሊሂቅ እስኪጠፋ ድረስ ሁሉንም በተመሰጠረበት
አሉታዊ የቂም ንጥፍ
የተግባር ድርቀት ላይ አስቀምጦ ወና አስቀርቶታል።
የአብዛኞቹ ችግር በውስጣቸው
ያለው የቂመኝነት ስንቅ ነው ገመናቸውን እንዲህ እብድ እንደ ዘራው ምንትሶ እዬዘከዘከው የሚገኘው። ግልጽነቱም ህመሙ እኮ ያ ተመስጥሮ ተቀምሞ የተከዘነው የቂም ኩትኩት ስንቅነት ነው። ሁልጊዜ ተሸብልሎ ተሸፋፍኖ መቅረብ ግድ የሆነባቸው።
የፖለቲካ ሊሂቃኑ ቀጥተኛም ግልጾችም አይደሉም። እሚነግሩን ቅርፊቱን ነው። ስለምን? ተቃርኗቸው ከእናት እትብት ጋር ነውና። እሷን አቂሞ በክብር መዝለቅ ደግሞ አይቻልም። ስለምን ቢሉ የፈጠራት አምላክ ስለማይረሳት። ስለማይተዋት። ስለማይዘናጋት። አላዛሯ ኢትዮጵያ የፈጣሪ፤ የቅዱሳን፤ የሰማዕታት፤ የደናግላን የንጹሓን ትምክህት መጠጊያ ናትና።
የተፈጠረ አዲስ ድርጅት፤
ማህበር፤ ተቋም፤ ሹመት፣ ሽልማት የተስፋ ነጋሪት ቢጎሰም ጽንሱ ቂም ከሆነ መንጠባጣቡ አይቀሬ ነው። አሁን እምናዬው መከራም
ይኸው ነው። እራሱ ገፃቸው በነበረው ላሂው ስለመቀጠሉ እንሱ ባያውቁትም አድባር እዬራቃቸው ተላምጦ የተጣለ አገዳ መምሰላቸውን
ግን እያዬን ነው። ያ እንደልባቸው ይፈነጥዙበት የነበረው የምልዕት መንፈስ ዛሬ አራግፏቸዋል። አገር ውስጥም ውጭ አገርም። አድባሩ ሁሉ ውሃ ውሃ ነው የሚሸተው። ጠረኑም ድንብዝ።
ወደ ቀደመው ጉዳዬ ምልሰት ሳደርግ ያ ልስልል መቼ ጠግበነው
ይባል የነበረው የመከላከያ ሚነስተሩ የአቶ ለማ መገርሳ ድምጽ ተመልሶ ለእርድ ሲያዘጋጀን ሰውና ዴያቢሎስን ለመለዬት በውነቱ
አቅም አጣን። እንደ አድህኖ እናዬው የነበረው ምስል ራሱን አብዝተን በእጅጉ ፈራነው።
ቂመኝነት ክፉ ነው። ቂመኝነት
የሰውን ጸጋ መክሊት እና ተፈጥሮ ወደ አውሬነት የሚቀይር ክፉ ድዌ ነው። የመስከረሙ የቡራዩ ሰማዕታን፤ የአዲስ አበባ ሰማዕታን የዚህ ሁሉ ገመና ሰለባዎች ናቸው።
በቂመኝነት የተሰላው
ምህንድስና በራሱ በምንወደው ብሄራዊነት መርዙ ተቀምሞ መቅረቡ ሌላው ጣምራዊ ገማና ነው። ራሱን ችሎ ቂመኝነቱ
ከነጥሬ ምርቱ ቢቀርብ እንደ አመጣጡ አቅም አሰባስቦ መሞገት ወይንም መከላከል ይቻል ነበር። ግን ሰለበን። ተሰልስለን ተሰለብን። የሆነው የሆሊውድ ፊልም ነው
የተሠራው። በህሊናችን ላይ ተረገጥው ፈነጠዙበት፤ እግዚአብሄር ይይላቸው እንጂ …
ሰው ለራሱ ህልፈት እና ለራሱ
ንደት ተነብርክኮ መሬት ተደፍቶ የጸጋ ስግደት እንደ ሰማዕታተቱ ሰግዶ እንዲቀበል ማድረግ በራሱ የወንጀል ቁንጮ ነው። ያ
ለብሄራዊነት ፍቅር ሲባል የረበበው የመንፈስ አቅም በግፍ ተዳፋ፤ በግፍ ተቀጠቀጠ፤ በግፍ ተረገጠ። ዛሬ ሌላ ጥቁር ቀን ላይ
ነን። በጀርመንኛ አንድ ጥበብ የጨለመበት { Eine Art Dunklheit!}የሚል ከእውነተኛ የራሴ ታሪክ የተሰራ ታሪክ ነበር።
ከአንዲት ጀርመናዊት የራዲዮ ጋዜጠኛ ጋር አብረን ነበር የሠራነው። ዛሬ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ሊሂቃን እከሌ ተከሌ ሳይባል ሁነታቸውን ሳዬው እንደዛ ሆነው ነው ያገኘኋዋቸው ጥብብ ነው ብለው የሄደበት መንገድ ጨለማዊ ጥብብ ነው። ድቅድቅ። ከወደዳችሁ አዳምጡት ...
ጥቁሩ ቀን ለእኛ ብቻ
አይደለም ለዬትኛውም የፖለቲካ ሊሂቃን ጭምር እንጂ። ተስፋ በተደረገበት ልክ ቀርቶ ተስፋን በፈጠረው አምላኩ ፊት ለመቆም ሁሉም የፖለቲካ ሊሂቃኑ አቅም የለውም። ቂመኝነት ጸንሶ ዕድሜ ዘመን የቅኖችን፤ የንጹሃናን፤ የደናግላንን አቅም እንደ ቅንቅን ሲመጥ፤ ሲመዘምዝ የኖረው
የኢጎ አርበኛ ሁሉ እንደዚህ ዘመን መለመላውን ቀርቶ፤ እርቃኑን ሆኖ የቀረበት ዘመን ከቶውን ታሪክ አላስተናገደም።
ዘመን ራሱ ፊቱን አዙሮባቸዋል። ቤተ መንግሥት እና መጋቢት አንድን በምልሰት እሰቡት። ይመራል ግን ህሊና ላላቸው ልጓም ነው፡፤ ራሳቸውን ቀጥተው እና ገርተው ሱባኤ የሚገቡበት፡፤ በዬዘመኑ የሰው ልኳንዳ አዘጋጇ እናት ዕንባ ...
አሉታዊው የዴሞግራፊ ፍልስፍና
ለመከወን የተመረጠው አጀንዳ ኢትዮጵያዊነት ነው። ለዛ ደግሞ ስስ ብልቱ ከዬት
እንደሚገኝ የተሰላ ንድፍ ነበር። ግን ፈጣሪ ደግ አምላክ ነውና ገዳይን ሳያውቁ ለመገደል ፈቅዶ ከመሰናዳት፤ አውቆ መሰናዳት
የተሻለ ነውና ይህን ስለሰጠን አምላካችን እናመሰግነዋለን። ሥልጣኔው በ እውነት አተገባበር ላይ ቢሆን እንጂ በሸቀጥ ቅርሚያ ተኮር ባይሆን ነው የሃሳቤ መድፊያ።
„አባቶቻችንም ቂም ይዞ ጸሎት
ሳል ይዞ ስርቆት“ የሚሉትም ለዚህም ነው። አሁንም ለምታባራው አገር ትልም ሳይሆን ለምታጠፋው አገር መሰናዶ አቅምን በብዙ ማባከኑ የሚገባ
አይመሰለኘም።
ባለፈም እሰጣ ገባ ውስጥ
ገብቶ መፏገትም አይገባም። ሊሆን የሚችለው ነገር ተስፋን በእግዚአብሄር ላይ ማድረግ ብቻ ነው። አቅምን መቆጠብ፤ በብዙ ጉዳዮች
ላይ ዘሎ ዘው ከማለት በተዕቅቦ እና በርጋታ ነገሮችን ማዬት፤ መመርመር የሚገባ ይመሰለኛል። የትኛው እርምጃ ጥቅሙ ሊለካ፣ ሊሰፈር የሚገባው ከኢትዮጵያዊነት አቅም ጋር መሆን አለበት። ትግሉ እሱን ከመስበር ጋር ስለሆነ።
አብሶ ቂምን የሰነቀ አሉታዊ
ዴሞግራፊ ምህረት የለሽ ነውና ሱናሜውን ለመከላከል ቢያንስ ህሊናዊ መሰናዶን አደራጅቶ፤ በነቃ ህሊና ለመፋለም መሰናዳት
ከእያንዳንዱ በግል ከሁሉም በጋራ የሚጠበቅ ግዴታ ይመሰለኛል። ይህ ማለት ምን ማለት ነው ትችቱም፤ ሙግቱም ከጥላቻ የጸዳ መሆን አለበት ነው።
መፋለም ስል እንደ ቤተ መንግሥቱ „ጦርነትን“ ማወጅ አይደለም።
እውነት እኮ ልዩ አቅም ነው። እውነት ያለው መሳሪያ ግምጃ ቤት የሚያስኬደው ምንም ነገር የለም። እውነትን ሰንቆ በእውነት ማህለቅ ዕብለትን፤ ክህደትን፤ ማስመሰልን፤ ፌክን ማራገፍ ይቻላል። ግን
ድፈረትን ይጠይቃል።
ቂም ያለበት ሰው መዳኛም
የለውም - ፈጽሞ። ቂሙን የሚፈጥረው ደግሞ የበታችነት ስሜቱ ነው። ይህን በቀጣዩ የምናዬው ይሆናል። የዚህ የአሉታዊው የዴሞግራፊ ፍልስፍና ሥሩም ይኸው ነውና። የበታችንት፤ ራስን አሳንሶ፤ ዝቅ አድርጎ መገመት፤ ተበልጫለሁኝ ብሎ ማሰብ፤ ከተፈጠሩበት የአቅም እርካብ መንሸራተት ወዘተ ... የሚገርመው ሰው ከ እንሰሳ ተልይቶ ሰው ሆኖ መፈጠር በራሱ እኮ ከበቂ በላይ ነበር። ሰው ሆኖ የተፈጠረ ሰው ስለምን ከሰው አንሼ ነበርኩኝ ብሎ ያስባል?
የሆነ ሆኖ አሁን ኢትዮጵያ ላይ ያለው
ያደባ የደባ ቂም ባለ ፓወር ነው። መዋቅሩን እያሰላሰለ ዘርግቷል። በሁሉም ዘርፍ መንበረ ሥልጣኑን የተቆጣጠረ ስለሆነ ጥበብን
ከአባቶቻችን ብልህነትን ከእናቶቻችን በመቀሰም በጥንቃቄ፤ በርጋታ፤ በስክነት መራመድ ይጠበቅብናል።
ተራ ጥላቻ፤ ተራ ዘለፋ፤ ተራ
ቂመኝነት ከሰማይ እሳት አውርዶ መጋቢት አንድ ቀን አሳይቶናል እና ከዛ ራስን ማረም እና ራስን መቆጠብ ይገባል። ያ ለቤተ መንግሥቱ የተላከ ብቻ አይደለም፤ ማስተዋል ለጎደለን ሁሉ ነው። ፉክክር፤ ውድድር ከፈጣሪ ጸጋ ጋር ሲሆን ጋዳ ነው። ቤተ መንግሥት ይዘህ አንድ ቀንጣ ነፍስ ጋር ግብግብ ስትገጥም እዮር ቁጣውን ላከ ... በማይገደብ፤ በማይለካ ስልጣኑ ...
ስለሆነም ተመክሮ፤ ልምድ
ከእውነት አንባ እንጂ ከቂመኝነት ባለመሆኑ ራስን ከቂም በጸዳ መልኩ ማትጋት ይጠበቅብናል። በደሉ ድርብ ነው። ግን ድርቡን
በደል ታግሶ ማሳለፍ ደግሞ የሰው ልጆች ግዴታ ነው። ቂመኝነት የተበከለ ደም መርዝ ነው።
ስለዚህም ይህ አስቀንቶን፤ ይህ
አስጎምጅቶን አብረን ወደ ገደሉ እንዳንገባ ራስን ከሁሉ ነገር በፊት ከቂመኝነት ማጽዳት ቀዳሚው ተግባር ሊሆን ይገባል።
ሁሉም ራሱን
ያሻንፍ። ሁሉም ስለ ኢትዮጵውያኑ የፖለቲካ ሊሂቃኑ ኢጎ አክሮባቲስትነት ሳይሆን ስለራሱ ኢጎ ተራራነት አስቦ ከተራራ ወርዶ ሰውነትን፣ ተፈጥሯዊነትን መላበስ ይገባዋል። የቂም
ፉክክር የኃጢያት እንጂ የጽድቅ መንገድ አይደለምና።
ፍቅር ሲያልቅ ትእግስት
ይሰደዳል
ትእግስትም ሲያልቅ ፍቅር
ይሰዳዳል።
ቂመኝነት መርዛማ የህሊና ብል
ነው!
የኔዎቹ የኢትዮጵያ ቅኔዎች የእኔም የኔታዎች ኑሩልኝ። መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ