19.11.2019 የድንጋይ ጫጉላዊ ሽርሽር።

 

የድንጋይ ጫጉላዊ ሽርሽር።
 
 No photo description available.
 
ብር
ትር
የድንጋይ ሽርሽር።
ስንድድ ተሰራለት
ጨሌ ዘነበለት
በጭካኔ ዜማ ጫጉላው ከበረለት።
ሸማ ቀረበለት
ገዳ ሰገደለት
በዕንባ ቅልቅል ሜጫ ፈነጨበት።
ድንጋይ እና ሜጫ
ውሉ የእርግጫ
ህሊናው ግራጫ
ዘመኑን ገደሉት እንዲህ በፍጥጫ።
ቀርቶ እንደ ዋዛ፣ የጥንት የጥዋቱ
ሰውነት ማጣቱ
እርስቱ ሆነለት መታበይ ስባቱ።
ያ የድንጋይ ዘመን ተመልሶ መቶ፣ እንዲህ ዘመነበት
በድንጋይ ሽርሽር፣ መኖርን ፈጨበት።
ህይወት ቀጠፈበት
ቤት ንብረት ጠፋበት
ስጋት ሰፈነበት
ዋይታ ነገሠበት።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።