19.11.2019 ድንጋይ ቀን ወጥቶለት።

 

ድንጋይ ቀን ወጥቶለት። 
 
 No photo description available.
ድንጋይ ቀን ወጥቶለት
ቄሮ ተፈጥሮለት
የጭካኔ ሃውልት በሥምረት ቆመለት
የአረማዊ ድርሳን ዘሞ ቀረበለት።
ድንጋይ ቀን ወጥቶለት
ድንኳን ተጥሎለት
የሰው እርድ ቀርቦለት
ዕንባ ጎረፈለት።
ድንጋይ ቀን ወጥቶለት
መንገድም አልፎለት
እርፍት አግኝቶበት ሃኒ ሙን ሁኖለት
ተጓዥ አልቅሶበት
ቄሮን አንግሦለት
ማህፀን መክኖበት።
ድንጋይ ቀን ወጥቶለት
መውገሪያ ሰምሮለት
ኦዳ ተቀብሎት
በጥቁራማ ዘመን ይሁንታ ቅብነት።
የትውልዱ ሞራል ዝቅዝቅ ተጉዞበት
የማረጉ ኩራት በኵረት በቅሎበት
በስጋት ዳመና አገር ታመሰበት
በሰቆቃ ስቃይ ፍጥረት አረረበት
ድንጋይ ቀን ወጥቶለት።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።