19.11.2019 የሞት ጠረን ለሴራ ፖለቲካ ቀመር በኦዳ ኢንፓዬር።

 

የሞት ጠረን ለሴራ ፖለቲካ ቀመር በኦዳ ኢንፓዬር።
 
 No photo description available.
እንዴት ናችሁ ጤና አዳሞቼ? ደህና ናችሁ ወይ? ኦዳና ጃራ ግብግባቸው በጉልህ እስኪወጣ ቀዳሚው የአህድዮሽ ጉዞ በፀረ ኢትዮጵያዊ መንፈስ ይቀጥላል። 
 
ከዚህ መከራ የሚድነው አሁን ባለው ሁኔታ የአድዋ ሥርዕዎ መንግሥት ብቻ ይሆናል። 18 ወራት የኢትዮጵያን መከራ ያልወቀጠው እሱ ብቻ ነው ማለት ይቻላል። የቀረበት የማህል አገር ዘመናይነት ብቻ ነው። እርግጥ ነው በራሱ መስመር አገርን አምሷል። ሰፊ ስለሆነ እሱን አቁሜ ወደ ዋናው እርእሴ ልሂድ።
 
በዚህ 18 ወራት የበቀል ማወራረጃ፣ የጭካኔ የመሞከሪያ ጣቢያ የነፍስ ይማር ባዕት ያልሆነ አዬር ባዕት አልነበረም።
ቁንጥንጡ፣ ዝርክርኩ፣ መሰሪው፣ ሸፍጠኛው የአብይወለማ ሌጋሲ ተጭኖ በያዘው የአማራ ህዝብ እና መንግሥት ከቀደሙው ዘመን ባላነሰ ፍላጎቱን ለማስፈፀም የመሞከሪያ ጥንቸል አድርጎት ባጅቷል።
 
አሁን ግዙፋን ኦፕሬሽን በእንደልቡ አቶ ዮኋንስ ቧያለው እና በአቶ መላኩ ፈንታ የስሜን አሜሪካ እና የለንደን ጉዞ ሀ ብሎ ይጀምራል። ሲመለሱ የእራሱ እግር የእግሩ ራስ ሆኖ ይጠበቃቸዋል።
 
በዚህ ማህል ሁለት አውራ ጉዳዮችን እንይ።
ሃሳብን የማስተናገድ አቅም።
ጥያቄ መጠዬቅ በህግ ያስቀጣል በዴሞክራሲ አሻጋሪው ጠቅላይ ሚኒስተር የህሊና አቅም። ሽብሽብ።
የተገደሉት ሊሂቃን በሙሉ የሞገቱ ስለመሆናቸው እኔ በግሌ አልጠራጠርም። የታሠሩትም ቂሙ የሚመነጨው ሞገታችሁኝ ነው። ጠቅሚሩ ቶለራንሳቸው ዜሮ ነው። ፈሪም ናቸው።
 
መናገር መናገር መናገር ጥሪያቸው ይህ ነው። ማድመጥ አቻችሎ መጓዝ አልተፈጠረባቸውም። ስለዚህ ዴሞክራሲ ሞቶ የተቀበረው እሳቸው በህይወት የተፈጠሩበት ዕለት ነበር። እኔ ዴሞክራሲን በሳቸው ዘመን አልጠብቅም እንደ ማለት። እሱ ቀርቶ ተጨቁኖ መኖርን ለሚያሰቃዩት ህዝብ ቢፈቅዱ መታደል በሆነ ነበር።
የሚበልጥን ሰብዕና የመቀበል አቅም አረመኔነት።
 
በዬትኛውም መሥፈርት፣ በዬትኛውም ሙያ፣ በዬትኛውም ክህሎት ከኦዳው አሻጋሪ በላይ ፈቅ የሚል፣ ብቅ ለግለግ ብሎ የሚወጣ መሪ መንፈስ አይፈለግም። ዶክተሮች ጄኒራሎች አይፈለጉም። በዓለም ዐቀፍ ማህበረሰቡም የሚታወቁ፣ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ወረፋ ጠባቂዎች ናቸው ለሞት።
በዙሪያ የሚፈለጉት ለኩርኩም እራሳቸውን ያመቻቹ ናቸው። አማራጭ ሃሳብም ሰብዕናም የተከለከለ መንገድ ነው በዶር አብይ አህመድ የእጬጌነት ህልም። እኔ ይህን እርቃነ መንፈስ ሰብዕና ብዬ እገልጠዋለሁ። ዘመናቸውንም የመቃብር ሥፍራ እለዋለሁ።
 
ያው እርግማን እንደሚያወርዱቡኝ አውቃለሁኝ። ያከበርኳቸውን ያህል አሁን ላይ እንዴት መለመላቸውን እንደ አውሮፓ የክረምት ግንድ እንደሚታዩኝ ሳልደብቅ ልነግራቸው እወዳለሁ። ቀለሙ ያለቀ እስክርቢቶ። እኔ እንደ ሰው እንጂ እንደ ጃርት፣ እንደ እስስት፣ እንደ እርኩም ሆኜ ስላልተፈጠረ ሥነ ምግባሬ እውነቱን በልቤ ያለውን በድፍረት እገልጣለሁ።
 
በዚህ ስሌት ስሄድ ከሥር ፎቷቸውን የምለጥፈው እነዚህ ነፍሶች የሞት ተቀጣሪ እንደሚሆኑ አስባለሁ። በነገራችን ላይ በጥቅምቱ የጃዋራዊ እንቅስቃሴ የመነሻ ምክንያታዊ ጉዳይ የሰኔው የባህርዳር እና የአዲስ አበባ ኦፕሬሽን አካል አድርጌ እወስደዋለሁ።
 
በዚህ ኦፕሬሽን ሞት የታጨለት ነፍስ እንደነበር ነፍሴ ትነግረኛለች። ከዛ በኋላ የሆነው የሐረር፣ የአንቦ ጉዞ የመግለጫ ጋጋታ እና ሁካታ ያን ኦፕሬሽን ክሽፈት ድንጋጤን ለማስተባበል የተጣደ ነበር። 
 
ይህ የሚያሳዬን የተደራጀ የመንፈስ ኃብት ምን ያህል በድንጋይ ጉልላት ገዢዎችን እንደሚያንቀጠቅጥ ነው። ሃሳቡን ፍጥረተ ነገሩን ስለምንጠላው አቶ ጃዋር መሃመድን የአገር መታመስ እና በስበቡ ስላለቁት ነፍሶች፣ ስለወደመው ንብረት፣ ስለተፈናቀሉ ዜጎች ስናስብ በሰኔው የባህርዳር ግርግር የአማራ ህዝብ በሰለጠነ አርምሞ ባያስተናግደው ኖሮ ለመሰል ተጨማሪ የበቀል የእልቂት ዋይታ የተሰናዳም ነበር።
 
በዚህ በጥቅምቱ ግርግር ሴረኛው አካል ሙሉ ለሙሉ የባህርዳሩን መሰል ያቀደውን ነፍስ መቅሰፍ ባይችልም ተቀናቃኙን መንፈስ የሚቀናቀን ሌላ አዲስ የኃይል አሰላለፍ ፈጥሯል አትርፎበታልም። 
 
ለጃዋርውያን መሬት ላለው ደጋፊ ግን አለርም ፈጥሮለት መሰሪውን ኦፕሬሽን አጣብቂኝ ውስጥ ስለከተተው ይቅርታውን ለማሳመን በነበረው ሂደት ኢትዮጵያ እና ህዝቧ የታማኝ መሪ ናፍቆቷ ምን ላይ እንዳለ አሳይቷል። " ባዕድ ህዝብ እና አገር፣ ክህደት " ባዶነት፣ ጭድነት።
 
ዬቀጣዩ ጊዜ ሌላ የሞት ስዋሰዎች።
 
ዋናው እርእሴ ይሄ ነው። የሱማሌ አክቲቢስቶች፣ ጋዜጠኞች፣ ሙሁራኖች ህዝቡ በታሪኩ እንዲህ ዓይነት ሰዋዊ፣ ፍቅራዊ፣ የኢትዮጵያ መሪ አግኝቶ ስለማያውቅ የመጀመሪያ ሥራው አቶ ሙስጡፌ ዑመርን መጠበቅ ይሁን። ለ27 ዓመት የምስራቁ ፖለቲካ የመኃል አገር ግለት እና ዕድምታው ለኦዳ ሥርዕዎ መንግሥት የመንፈስ ድሎት መጓጓዣ አቅም ማጠራቀሚያ እንዳይሆን ተጠንቅቆ ይራመድ።
 
በክፋ ቀን ቀዳሚው የግንባር ሥጋ የሆነው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና የባለ አደራው ንቅናቄ የመንፈስ ጥበቃ ህብረ ብሄራዊ ሆኖ የራሱን የተደራጀ የመንፈስ ሰላማዊ ሠራዊት መፍጠር ይገባል። የእሱ ጉዳይ የፈረንሳይ ጀግኖች ብቻ መሆን አይኖርበትም።
 
በዚህ ውስጥ የሞት ጠረን በአቶ ክርስትያን ታደለ እና በአቶ መላኩ ፈንታም ሊኖር ስለሚችል አማራዊው መንፈስም ጉዳዩን ለሚመለከተው አካል ከማሳወቅ ጀምሮ መንፈሱን አንቴናውን አንቅቶ መጠበቅ ይገባዋል።
 
ብቸኛው።
ብቸኛው ተጠቂ ምንም መጠለያ የሌለው የምዕት የዕውነት አርበኛው የእመት ፋናዬ ልጅ የብራናው ብሌን ጋዜጠኛ ተመስገን ደስአለኝ ነው። እሱ በጣም ያሳዝነኛል። እንደ እኔ ጥግ አልባ ብቻውን ስለሚባትል አንጀቴን ይበላዋል።
 
በፍጥነት ቲም ተመስገንም የመንፈስ ጋርድ ያስፈልገዋል። ስለዚህ ቢያንስ የጥበብ ዓውድ ታዳሚዎች በዙሪያው ሊሰባሰቡ ይገባል። ያን ሁሉ ደክሞ ለአንዲት የብዕር ሽልማት ያልበቃ ግን ዕንቁ።
 
በገዳዩ መንፈስ የተራ ጉዳይ ካልሆነ የሚቀር ብቁ አቅም ይኖራል ብዬ አላስብም። ስለዚህ ሁሉም ለራሱ ዘብ መቆም ይኖርበታል። ዘመነ ኦዳ ዬአቅም አራጅን ተቋቁሞ የትውልዱን ተስፋ እንዲበቅል ለማድረግ ሁሉም አቅም ላላቸው የሰብአዊነት ጀግኖች መመገብ ይገባዋል።
ጉዳዩ በኃይማኖት በብሄረሰብ ጨዋታ የሚወራረድ አይደለም። 666። ለዚህ ነው እኔ ከፈረቃም ከተረኝነትም በላይ ነው የምለው።
 
ማከያ።
ለግድያ ኦፕሬሽን ሲወጠን ንፁኃን ለማሳሳቻ ለግብር ይቀርባሉ። ይህ የተለመደው የአራት ኪሎው የሴራ ግንብ ተጨማሪ የአደናግሬ መሰሪ ገፀ ባህሪ ነው።
ሁለተኛው ጉዳይ የትኛውም የዚህ ዘመን የግድያ ኦፕሬሽን ቁንጫን መውጫ የአማራ እና የጋሞ ህዝብ፣ እንዲሁም የኔታዋ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ናቸው።
የገዳዩ መንፈስ ትክሻ።
እንደ ድርጅት ግንቦት ሰባት።
እንደ ግለሰብ ወ/ ሮ ሙፍርያት ካሜል እና አቶ ደመቀ መኮንን ናቸው። በታሪክም ተጠያቂዎች ናቸው።
የህወሃት ጉዳይ ዬራሱ ተደሞ እና የዘመቻ መስመር ስላለው ከዚህ ጉዳይ ጋር ማለካለክ አልፈልግም።
ዘመነ ኦዳ ለምህረት የመጣ አይደለም።
ዘመነ ኦዳ የአራጅነት ተውኔት ኢንፓዬር ነው።
ፍቅር ሲያልቅ ትዕግሥት ይሰደዳል።
ትዕግሥትም ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።