ቡና እና ልብ የልብ ጓደኛሞች። "በጥዋቱ ቡና መጠጣት የልብ በሽታ ተጋላጭነትን እንደሚቀንስ ጥናት ጠቆመ" BBC

https://www.bbc.com/amharic/articles/cwyxygk1z18o

"በጥዋቱ ቡና መጠጣት የልብ በሽታ ተጋላጭነትን እንደሚቀንስ ጥናት ጠቆመ"

"በጥዋቱ ቡና የሚጠጡ ሰዎች ከልብ በሽታ ጋር በተያያዘ የመሞት ዕድላቸው ዝቅተኛ መሆኑን አንድ ጥናት ጠቁሟል።

ቀኑን ሙሉ ቡና ከሚጠጡ ሰዎች ይልቅ በጥዋት የሚጠጡት ከልብ በሽታ አደጋ ከመራቃቸው በተጨማሪ ረዥም ዕድሜ ይኖራቸዋል ይላል ጥናቱ።

ነገር ግን ከልብ በሽታ ለመራቅና ረዥም ዕድሜ ለመኖር ቡና ብቻ በቂ ነው ወይ የሚለውን ጥናቱ አይመልስም።

በቱሌን ዩኒቨርሲቲ ኦቢሲቲ ሴንተር ተመራማሪ እና ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ሉ ኪ እንደሚሉት ምንም እንኳ ቡና ለምን የልብ በሽታ አደጋን እንደሚቀንስ ባይታወቅም ቀኑ ሲገባደድ ቡና የሚጠጡ ሰዎች የሰውነታቸው ዑደት ስለሚረብሹት ሳይሆን አይቀርም።

ይህ ጥናት ረቡዕ ጥር 1/2017 ዩሮፒያን ኸርት ጆርናል በተባለው መፅሔት በኩል ነው ይፋ የተደረገው።

ዶ/ር ኪ አክለው "ቡና የምንጠጣበት ሰዓት ምንም ያክል ለውጥ እንደሚያመጣ ለማወቅ ተግባራዊ ሙከራ ማድረግ አለብን" ብለዋል።

"ይህ ጥናት በጥዋቱ ቡና መጠጣት ለምን ከልብ በሽታ አደጋ እንደሚታደግ የሚያስረዳው ነገር የለም" ሲሉ ይተነትናሉ።

"ምናልባት የተሻለው ማብራሪያ ከሰዓት አሊያም አመሻሹን ቡና የሚጠጡ ሰዎች የሰውነታቸውን ዑደት [ሰውነታችን የ24 ሰዓታት አካላዊ፣ አእምሯዊ እና የባሕሪ መለዋወጥ ዑደት አለው] ስለሚያውኩት ይሆናል።"

"ይህ ደግሞ የልብ በሽታ ሊያመጡ የሚችሉ እንደ እብጠት [ኢንፍላሜሽን] እና የደም ግፊት ያሉ አደጋዎች ሊጥለን ይችላል" ሲሉ ያብራራሉ።

ኒው ኦርሊየንስ የሚገኘው ቱሌን ዩኒቨርሲቲ አጥኚዎች ከአውሮፓውያኑ 1999-2018 ባለው ጊዜ በብሔራዊ የጤና እና አመጋገብ ጥናት ውስጥ የተካተቱ 40 ሺህ 725 አዋቂ ሰዎችን ሂደት ተመልክተዋል።

ሰዎቹ በየቀኑ ስለሚበሉት ምግብ እና መጠጥ እንዲሁም ቡና ይጠጡ እንደሁ፤ የሚጠጡ ከሆነ ደግሞ መች የተባሉ ጥያቄዎች ተጠይቀዋል።

ምንም እንኳ ከዚህ ቀደም የወጡ ጥናቶች ቡና ለጤናችን የተወሰነ ጥቅም እንዳለው ቢገለፅም ቡና መች ብንጠጣ ነው ጥቅም ያለው የሚለው ሲጠና ይህ የመጀመሪያው ነው።

ዶ/ር ኪ እንደሚሉት በጥናቱ ከተካተቱ መካከል 36 በመቶው በጥዋቱ ቡና የሚጠጡ ሲሆኑ የተቀሩት ደግሞ ቀኑን ሙሉ የሚጠጡ ናቸው።

አጥኚዎቹ ላለፉት 10 ዓመታት ሰዎቹን የተከታተሉ ሲሆን በዚህ ወቅት የሞቱ ሰዎችን የሞታቸውን መንስኤም ሲመዘግቡ ነበር ተብሏል።

ጥናቱ እንደሚጠቁመው ቡና በጥዋቱ የሚጠጡ ሰዎች 16 በመቶ የመሞት ዕድላቸው የቀነሰ ሲሆን ከልብ በሽታ የመሞት ዕድላቸው ደግሞ 31 በመቶ ዝቅ ያለ ነው።"

በጥዋቱ ቡና የሚጠጡ ሰዎች ከልብ በሽታ ጋር በተያያዘ የመሞት ዕድላቸው ዝቅተኛ መሆኑን አንድ ጥናት ጠቁሟል።

ቀኑን ሙሉ ቡና ከሚጠጡ ሰዎች ይልቅ በጥዋት የሚጠጡት ከልብ በሽታ አደጋ ከመራቃቸው በተጨማሪ ረዥም ዕድሜ ይኖራቸዋል ይላል ጥናቱ።

ነገር ግን ከልብ በሽታ ለመራቅና ረዥም ዕድሜ ለመኖር ቡና ብቻ በቂ ነው ወይ የሚለውን ጥናቱ አይመልስም።

በቱሌን ዩኒቨርሲቲ ኦቢሲቲ ሴንተር ተመራማሪ እና ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ሉ ኪ እንደሚሉት ምንም እንኳ ቡና ለምን የልብ በሽታ አደጋን እንደሚቀንስ ባይታወቅም ቀኑ ሲገባደድ ቡና የሚጠጡ ሰዎች የሰውነታቸው ዑደት ስለሚረብሹት ሳይሆን አይቀርም።

ይህ ጥናት ረቡዕ ጥር 1/2017 ዩሮፒያን ኸርት ጆርናል በተባለው መፅሔት በኩል ነው ይፋ የተደረገው።

ዶ/ር ኪ አክለው "ቡና የምንጠጣበት ሰዓት ምንም ያክል ለውጥ እንደሚያመጣ ለማወቅ ተግባራዊ ሙከራ ማድረግ አለብን" ብለዋል።

"ይህ ጥናት በጥዋቱ ቡና መጠጣት ለምን ከልብ በሽታ አደጋ እንደሚታደግ የሚያስረዳው ነገር የለም" ሲሉ ይተነትናሉ።

"ምናልባት የተሻለው ማብራሪያ ከሰዓት አሊያም አመሻሹን ቡና የሚጠጡ ሰዎች የሰውነታቸውን ዑደት [ሰውነታችን የ24 ሰዓታት አካላዊ፣ አእምሯዊ እና የባሕሪ መለዋወጥ ዑደት አለው] ስለሚያውኩት ይሆናል።"

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።