"አሜን!"
አሜኑ!
„ፍቅርህ ከወይን ጠጅ ይልቅ መልካም ነውና። ዘይትህ መልካም ማዕዛ አለው፤
ሥምህ እንደሚፈስ ዘይት
ነው፤ ስለዚህ ደናግል ወደዱህ።“
(መኃልዬ መኃልዬ ዘሰሎመን ምዕራፍ ፩ ቁጥር ከ፩ እስከ ፫)
ሕይወት ነፍሷን ጠርታ፤ ተጣርታ መንፈሷን
ንብ በዓውራው ሆኖ አስከፈተ በሩን።
ውለላ ከማሩ ጥንግ ድርብ ለግሶ
ተስፋ እዬዘመረ በጃኖ ቆምሶ
እርገቱ ወረደ ማዕረጉን ተላብሶ።
ማግሥት ተስልፎ አቋቋሙ አምሮ
ነፍስ አባት ሆነለት ሥርዬትን አዳምሮ።
ዝግ ባለው መንበር የውቅያኖስ
እርገት
ዝቅ ብለው ሲበሩ በዝማሬ
እዕዋፋት
ትውፊት ትሩፋቱ ዳርእስከዳር ስምረት።
ጥጆች ሲቧርቁ በግርግሙ ብሥራት
ሽምጥ ሲጋልቡ ታማኞች በአኃቲት
በድብባ ስትመርቅ ወላድ የወግ ደርሷት
ዛሬን ተነገላይ የሉላዊ
ቅምረት።
ዝልቅቱ በፍጥነት ርምጃን ጨምሮ
ምጥቀት በብልሃት በጥበብ ተቃኝቶ
„መደመር“ አበራ ራዕይን አጉልቶ!
„ቃል“ ቀን ለገሰው በቅኔ ዘቃና ጉባኤ
ውልደቱ ተሟልቶ ሁለንትና - ዛጉኤ፤
እቅፍቅፍ በሐመር፤ ጥላቻ በሰኔል
ፍቅርም በሞገሱ፤ ክስመት ➳ ለሳጥናኤል።
ርትህ ባባንዱ ሚዛን በህሊና
በህብርነት ፈክቶ የሰንደቅ ደመራ
ቀደምቱ በዕድምታ የአብይ ጎመራ!
አይዞህ! የእናቴ ልጅ ደም መላሽ ታናሼ፤
አይዞህ! የእምዬ ልጅ የቁርጥ ቀን ዋሴ፤
የድንቅነሽ
ጠሐይ የእውነት እጬጌ።
ቀን ከሌት ስትባትል ከነባቢትህ ጋር
ቀን ከሌትም ስትሮጥ ከውስጥህ ዘብአደር
እማማን አፍሪካን በሰላም ልትቀምር።
ከቶ ማን ልበልህ? አንደማን ልበልህ?
ተመሰጠርክብኝ ሎሬቱን አክለኽ።
ሌላም ልከልልኽ „ሃሌሉያ“ ብዬ
„አሜኑ“ ልበልህ ምርቃት አክዬ።
ተባርክ ብልህስ ከቶ ያንስብኝ?
ኑርልኝ ብልህስ ድፈርት ይሆንብኝ?
ብቻ …ብቻ፤ ሆድ ይቻለው ድርጊትህ ባረከኝ።
የፍቅርን አርበኞች በፍቅር ሲቃኙ
የፍቅርን ተፈጥሮ ኖሮበት ሲዳኙ
የፍቅር ሰማዕታት እንዲህም ሲናኙ
ተመስገን ጌታዬ አንተ የሁሉ ጌታ
„ቃል“ በቃሉ ጸንቶ ዲያቢሎስ ተመታ!
ምህርት በይቅርታ እልፍኙ ተሠርቶ
ትውልዱ ፈቀደ አንድ መሆን በርቶ!
· ሥጦታ … ለፍቅራዊነት ዓለምአቀፍ ሙሴ፤
ለጠ/ ሚር አብይ አህመድ እና ለሚያግዟቸው አካሎቻቸው፤ በሃሳብ ለሚደግፏቸው ቅኖች፤ ለፍቅር
ሲሉ ለተሰዉ ሰምዕታት የፍቅራዊነት ንዑዳን፤ ነፍሳቸውን አርያመ ገነት ያግባልኝ። ለፍቅር ተፈጥሮ መርህ፤ ልዕልና ሲሉ ለቆሰሉ፤
አካላቸውን ላጡ ቅዱስንም ሁሉ ይሁንልኝ።
- · ተጣፈ።
ሰኔ 17 ቀን 2010/ ሰኔ 24 ቀን 2018 ሲዊዘርላንድ።
- · ማከያ።
ይህን የፍቅር ዓለም አቀፍ ቀን እንዲወሰን በፍቅር ተፈጥሮ መርሆዎች ዙሪያ ዓለም የሥርዓት ትምህርት
ነድፋ ተግባር እንድትጀምር፤ የፍቅር ተፈጥሮ መርህ መምህር፤ ሳይንቲስት፤ ተማራማሪ፤ ፈላስፋ፤ ኤክስፐርት፤ ልዩ ልዩ ተቋማት ዩንበቨርስቲዎች
እንዲኖሯት፤ ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከመግባታቸው በፊት ሰብዕናቸው እንደ አንድ የመግብያ መሥፈርት እንዲወሰድ
የአጭር እና የረጅም ጊዜ ትልሙን፤ አጠቃላይ መንፈሱን የያዘ አቤቱታ ለቀድሞው የተባባሩት መንግሥትት ጸሐፊ፤ ለአውሮፓው ህብርት
እና ለመሰል ሰውኛ እና ተፈጥሯዊኛ ድርጅቶች አቅርቤ ነበር። መልስ አክብረው ቢልኩልኝም።
ነገር ግንተግባር ስላልተጀመረ በ2017 መጋቢት ላይ የቃላት የፖስተር ቻናል ጀመርኩኝ። እኔ ባልፍም ሃሳቡን ወራሽ እንዲኖረው ለማድረግ።
ነገር ግንተግባር ስላልተጀመረ በ2017 መጋቢት ላይ የቃላት የፖስተር ቻናል ጀመርኩኝ። እኔ ባልፍም ሃሳቡን ወራሽ እንዲኖረው ለማድረግ።
በ2015 የነበሩት ለተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ ባን ኪሙን Ban ki-Moon ለጻፍኩላቸው መሰረተ ሃሳብ መልስ ሲጽፉልኝ እስኪ የአገርሽን
መንግሥት አማክሪ ብለውኝ ነበር። አንድ ቅን ሰው ለማግኘት በማይቻልበት ሁኔታ መሞከሩ አግባብ ስላልነበረ የራሴን ሙከራ ሳደርግ
ቆዬሁኝ።
ትናንት እንደ ኢትዮጰያ ቀን አቆጣጠር ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓመተ ምህረት ጥንስሱ ተጀመረ።
ይህ ለእኔ የህልሜ ዋዜማ ነው ለዛውም በእትብቴ።
በቃላት ፖስተራዊ ቻናሌ ራዕዩን በዚህም መልክ ሰርቼው ነበር፤ ዓለም ዓቀፍ የፍቅር ቀን እንደሚያስፍለግ።
የተለያዩ መምሪያዎች የተካተቱበት ሳመሪ ላይም ተጨማሪ ሃሳቦች በዝርዝር አሉበት።
LoveIsm’s
Dream Seven.
Published
on May 6, 2017
- · ክወና።
ናፍቀሽኝ አገሬ።
አፈሬ ነው መስመሬ(23 06 2018)
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።
ፍቅራዊነት አዲስ የህይወት መስመር!
የኔዎቹ ለነበረን ዘንጣፋ ጊዜ እግዚብሄር ይስጥልኝ - ኑሩልኝ።
ሥርጉተ ©ሥላሴ 24.06.2018
(ከመንኩሲያዋ ሲዊዘርላንድ።)
ሥርጉተ ©ሥላሴ 24.06.2018
(ከመንኩሲያዋ ሲዊዘርላንድ።)
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ