ልጥፎች

ከኖቬምበር 23, 2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ

#ዝርግ

  #ዝርግ #ትርትር #ፍትልትል #ዝልግልግ #ዝልዝል #ትብስብስ መርጣችሁ የፈለጋችሁትን ሰይሙለት።   "ጠማማ ሰው ጥልን ይዘራል፤ ጆሮ ጠቢ ሰው የተማመኑትን ወዳጆች ይለያያል።"   (ምሳሌ ምዕራፍ ፲፮ ቁጥር ፳፰) #ምዕራፍ ፳።   እንዴት አመሻችሁ ውቦቹ ቅኖቹ።    #ኦላ እራሱን #ከሶ ፤ ቃሉንም #ክዶ መግለጫ አውጥቷል። ትንሽ ረብ እስኪል መጠበቅ ስላለብኝ ነው የዘገየሁት። ሁለተኛውን መግለጫ ከBBC ነው ያገኜሁት፤ ከሥር አያይዘዋለሁኝ።    እኔ እንኳን ብናኝ የኢትዮጵያ መንፈስ የለለበት ድርጅት ጋር አቅም ማዋጣት አልሻም። አትራፊ ስላልሆነ። የመጀመሪያውን ስለፃፍኩበት ግድ ስለሆነ ነው ለማያያዝ። እርግጥ ነው ሰሞኑን ዝበት ከዛም ከዚህም ስላለ የማቃናት ተግባር ግድ ይለናል። በተለይ በትውልድ ጉዳይ ለምንሰራ ባተሌወች። ያለመመጣጠን፤ የመክበድ፤ የክህሎት መራራቅ፤ ሚስጢር የማመሳጠር አቅም ስስነት ብቻ ……… ብቻ ኢትዮጵያ ዕዳ ተሸከሚ ስትባል #ኦነግ የሚባል ድርጅት በታሪኳ ተፈጠረባት። ምን እንደሚፈልግ? ምን #እንዳሳካ የሚታወቅ ነገር የለም? ያው ፕሮጀክቱ ዱር ቤቴ ይቀናዋል፤ የሰው ልጅን ማስጨነቅ፤ ማሳደድ፤ መሰረዝ፤ ማፈናቀል፤ መረበሽ ተልዕኮው ነው። ይህን ተሸከም ሁለት ትውልድ አልፎ ሦስተኛ ተተካ። መሃከነ። ዕውነት ለመናገር ጃል መሮ እዩኝ እዩኝ የማይሉ ዝምተኛ ናቸው። አይናገሩም። ስለዚህም አይሞገቱም። ምን ጎድሎባቸው ጫካ ገቡ ቢባል #ጫና ለመፍጠር፤ እንደ ማስፈራሪያ፤ እንደ መቀጣጫ፤ ለ፬ኪሎው ስኬት #ሽፋን ለመስጠት ነው። እኔን የሚገባኝ ይህ ነው። የሆነ ሆኖ #ኦላ ሰሞኑን ያለወትሯቸው #ጭካኔያቸውን አመኑ። ጭካኔው ሲታመን በምክክር ነው። ዘርዘር አድርጌ ጽፌበታለሁ...