ልጥፎች

ከኖቬምበር 25, 2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ

#እነኝህን አበባወችን ለአፈር?

    #እነኝህን አበባወችን ለአፈር?    "እግዚአብሄርን መፍራት ወደ ህይወት ያመራል።"   (ምሳሌ ፲፱ ቁጥር፳፫)   #ምዕራፍ ፳።   ከሰሞናቱ ጦርነቱ በፊት #የዘውዴ ንቅናቄ ነበር። " #ፍትህ #ለዘውዴ የሚል" የጦርነት መከራው ይሁን ስኬቱ #አናርኪዝምን መሸለሙ ነው። #አናርኪዝም ብዙ ባህሪያቱ ተፈጥሯዊ ሆነ የህግ - ጥሰት ላይ ያተኮሩ ናቸው።   ጦርነት ሲታሰብ ተጓዳኝ #ድቀቶች ፤ ተጓዳኝ አሰቃቂ ገጠመኞች ሁሉ ሊታሰቡ ብቻ ሳይሆን ጥፋቶቹ በሙሉ ተዘርዝረው ኪሳራው #ሊመዘን ይገባ ነበር።    አስደንጋጩ ሁነት አሁንማ የጦርነቱ አየሩ #ቀጠናዊ መልኩ በፍጥነት "ከእርምጃ ወደ ሩጫ ሆኗል።" የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚ/ር ሳሉ የጠቅላዩ ሞቶ ነበር። ያን ጊዜ ለአወንታዊ ነው። ዛሬ የሚነግረን ግን ለመጠነ ሰፊ ጥፋት እና ኪሳራ ነው።   በጦርነት ህፃናት፤ ሴቶች፤ አዛውንታት፤ ህሙማን ተከላካይ ስለማይኖራቸው፤ ህግም ስለሚጣስ በስፋት #ይጠቃሉ ። ከሁሉ የሚከፋው አውጥቶ መናገር የማይቻለው ይህን መሰል ጥቃት ለእኛ ባህል #ንብርብር ጉዳት አለው።   እነኝህ #አበባወቻችን አበባነታቸው ለአፈር ሆነ። ይህም ሆኖ አጥፊን፤ ወንጀለኛን ወይንም #ታማሚን ከስር መልቀቅ ቀሪወችን #ቅጣልኝም ነው። የሆነው ይሄው ነው።   ለነገሩ አሁንም ህወሃት ዱር ቤቴን ሲመርጥ መቀሌ ከተማ #ደረቅ ወንጀለኞችን ከእስር ለቆ ችግርም እንደ ነበር ሰምቻለሁኝ። በቀል እራስ እግሩ የሆነ ዘመን።    #የተጋሩ እናቶች በስንቱ ይቀጡ?    #አሁን እራሱ ጭንቅ ላይ ናት ትግራይ። ሱባኤ ነው። በንጽህና ፈጣሪን // አላህን እባካችሁ እንጠይቅ። ...

ሃሳቡ አወንታዊ ነው። አወንታዊነት ...

  ሃሳቡ አወንታዊ ነው። አወንታዊነት #ካርቱም ላይ ሳይሆን ፬ኪሎ ላይ ፊደል መቁጠር #መጀመር አለበት። አወንታዊነቱ "ራስ ሳይጠና ጉተና " ካልሆነስ?   ልጅ እናቷቱ ታማ፤ ቃሬዛ ላይ ሆና እያዬ እማ ምንሽን ሳይል ሱዳንን ቢመለከት ፈጣሪ ምን ይለዋል?   "እግዚአብሄር ግን መንፈስን ይመዝናል።" "መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፲፭ ቁጥር ፲፮።"   #ምዕራፍ ፳።   #ሰላምታ #በዕድምታ ።   እንዴት ነንን? ሙያሌ እንዴት አድሮ ይሆን? ባድመስ? ውልቂጤስ? ማዕከላዊ ጎንደርስ? አላማጣ ቆቦስ?   #ጠብታ ።   «ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች ውይይትን ለማስተናገድ ጥሪ አቀረቡ» https://www.bbc.com/amharic/live/c50mdr1p8907t   "የዓለሙ የሰላም አባት፤" የኢትዮጵያ የጦር አዛዥ፤ የብልጽግና ፓርቲ #ፕሬዚዳንት ፤ የኢትዮጵያ #ጠቅላይ ሚር፤ "የዓለሙ የሰላም #ሎሬት " የመጀመሪያው የኖቤል አሸናፊ እና ተሸላሚ ስለ ጎረቤት አገር ሱዳን የእርስ በርስ ሰላም የተመኙትን ከዓለም ዓቀፋ ሚዲያ፤ ከዘወትር ደንበኛዬከBBC ፔጅ ትናንት አየሁት።   ቢሠሩበት አይደለም የአፍሪካ ግጭቶች ግዙፋን የእስራኤል እና ጋዛ፤ የራሺያ እና የዩክሬን መከራን ለመቋጨት "የዓለም የሰላም አባት፤ ሎሬት" የሚል ግሎባል ዕውቅና አግኝተዋል እኮ። ነበር - በነበር ተወራረደ እንጂ።   #ሰሞናቱ ።   1) ዜናውን አይቼ የዘገየሁበትን እግረ መንገዴን ላብራራ። " #ቁሞ " ቀር የሚል ስድብ የተሳደበን ሰብዕና መልካም እንዳደረገ ፔጃችን ላይ ተለጥፎ ነበር። እንዲያስተካክሉት ስማጸን ትናንትም፤ ከትናንትም በስቲያ ስለነበር ያን መልክ ማስያዝ ነበረብኝ።...