ሃሳቡ አወንታዊ ነው። አወንታዊነት ...
ልጅ እናቷቱ ታማ፤ ቃሬዛ ላይ ሆና እያዬ እማ ምንሽን ሳይል ሱዳንን ቢመለከት ፈጣሪ ምን ይለዋል?
"እግዚአብሄር ግን መንፈስን ይመዝናል።"
"መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፲፭ ቁጥር ፲፮።"
#ምዕራፍ ፳።
እንዴት ነንን? ሙያሌ እንዴት አድሮ ይሆን?
ባድመስ?
ውልቂጤስ?
ማዕከላዊ ጎንደርስ?
አላማጣ ቆቦስ?
#ጠብታ።
"የዓለሙ የሰላም አባት፤" የኢትዮጵያ የጦር አዛዥ፤ የብልጽግና ፓርቲ #ፕሬዚዳንት፤ የኢትዮጵያ #ጠቅላይ ሚር፤ "የዓለሙ የሰላም #ሎሬት" የመጀመሪያው የኖቤል አሸናፊ እና ተሸላሚ ስለ ጎረቤት አገር ሱዳን የእርስ በርስ ሰላም የተመኙትን ከዓለም ዓቀፋ ሚዲያ፤ ከዘወትር ደንበኛዬከBBC ፔጅ ትናንት አየሁት።
ቢሠሩበት አይደለም የአፍሪካ ግጭቶች ግዙፋን የእስራኤል እና ጋዛ፤ የራሺያ እና የዩክሬን መከራን ለመቋጨት "የዓለም የሰላም አባት፤ ሎሬት" የሚል ግሎባል ዕውቅና አግኝተዋል እኮ። ነበር - በነበር ተወራረደ እንጂ።
1) ዜናውን አይቼ የዘገየሁበትን እግረ መንገዴን ላብራራ። "#ቁሞ" ቀር የሚል ስድብ የተሳደበን ሰብዕና መልካም እንዳደረገ ፔጃችን ላይ ተለጥፎ ነበር። እንዲያስተካክሉት ስማጸን ትናንትም፤ ከትናንትም በስቲያ ስለነበር ያን መልክ ማስያዝ ነበረብኝ።
ያ ጸያፍ አገላለጽ ለማንም ሊሆን አይገባም። ፔጃችን #ያቆሽሻል ነበር ሙግቱ። በጥንቸልም፤ በድንቢጥም ስም እየተመጣ ሲያውክ የነበረን ክፋ ሃሳብ ስሞግት ዋልኩኝ አደርኩኝ።
ጉዳዩ ሁለት የሥምረት ፓርቲ አካላት ጋር ነው። ጉዳዩ ለፔጃችን "#ቁሞ ቀር" የሚል ቃል ስላለበት አይመጥንም ነበር ሙግቱ። በሌላ በኩል ፔጁ ትጉህ ስለነበር ፔጃችን ሊያጣው ስለማይገባም ነበር በበዛ የታገስኩ፤ የፈለገ ሃሳብ ያራምድ። የሚስማማኝም ይሁን የማይስማማኝ ግን በፔጃችን ዲስፕሊን ልክ መሆን ግዴታ ነው።
ዘለፋ፤ ስድብ፤ ፈጣሪ በፈጠረው ፍጡር ላይ የኤክስ ምልክት፤ ተፈጥረው ግን (ነውረኛ የሆኑ ቃላት፤ ስንኛት፤ ሐረጋት፤ ፆታዊ ጉዳዮች ያልተገቡ ከሆኑ ) ፔጃችን አይፈቅድም። እኔ ከደከምኩኝ በሚጠቅም ለትውልድ ሊሆን በሚችል በታረመ አንደበት ሊሆን ይገባል።
የሚገርማችሁ ዘመኑ የወጣቶች ይመስላል። ከዚህም ባለፈ #የታዳጊወች ሆኖም እያዬሁ ነው። አዛውንቱም እንደ አዛውንት፤ ጎልማሳውም እንደ ጎልማሳ መሆን ሲገባ ፋክክሩ ከታዳጊወች ጋር ሆኗል። አክሰሱ ላላቸው ታዳጊወች አብዝተን ልንጠነቅ ይገባል።
ስለሆነም ያን የማከብረውን ትጉህ ፔጂ ከቻሉ "ቁመቀር" ማስተጋባት ተገቢ ስላልሆነ፤ እንዲሰርዙት በስተቀር ፈቅደው ፔጁን እንዲሰናበቱ ለመንኩ። አልሆነም መራራ ስንብት ሆነ።
2) በሌላ በኩል አንድ ሚዲያ ላይ ኮንፓክት የሆነ መሰናዶ አዳምጬም ስለነበር አጋዥ መረጃወችን ለማሰባሰብ ጊዜ ያስፈልገኝ ነበር። በሁለቱ ምክንያት የዶር. አብይ አህመድ አሊን አወንታዊ ግን #ከራስ ጋር ያልተመከረበት፤ የራስን የአገርን ተጠያቂነት እና ኃላፊነት ጣራ እና ግድግዳ ያልፈተሸ፤ የውሳኔ ሃሳብን ለመሞገት ጊዜ ወሰደበኝ።
#ዛሬ በስሱ ይሞካከር።
«የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሱዳን ጦር፣ የፖለቲካ እና የሲቪል ፓርቲዎች አካታች በሆነ አገራዊ ውይይት ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረቡ።" ዘገባው የBBC ነው።
ሸጋ ነው። ሌላው ዓለም ውስጣችን እንደምን #እንኩሮ እንደ ሆነ ስለማያውቅ ሊደንቀው ይችላል። ድንቅነት፤ ውብነት ቅርጽ አይደለም። የውስጥ ይዘት እንጂ። ቅርፊት ተልጦ ይጣላል። አይበላም።
የውስጥ ይዘት ደግሞ ሰው የሆነ ሰው የሚመራው፤ የሚያስተዳድረው፤ ተስፋ ያደረገው የእንሰሳት ማህበር ሳይሆን ህሊና ያለው ረቂቅ የእግዚአብሄር የአላህ ፍጡር ሰው ነው። የሰው ልጅ በተፈጠረበት መሬት በድህነት፤ በጉስቁልና ለመኖር እንኳን ፍርሃት ታውጆ፤ ስጋት ቀስሶ፤ መፈናቀል ነግሶ፤ ሞት ሰርክ እንደ ጤፍ ነዶ በአዳዲስ ማጭድ እያጨደ እራስ ሳይጠና ጉተና የሆነ ሃሳብ ቋት አይገፋም።
#የአብይዝም ሹማምንት።
ኢትዮጵያ ያሉ አዳዲሶቹ የፓርላማ አባላት? ኢትዮጵያ ያሉ አዳዲሶቹ የካቢኔ አባላት? ኢትዮጵያ ያሉ ሚኒስተራት ይሁኑ፤ አንባሳደራት ይሁኑ፤ ኮሚሽነር ምክትል ኮሚሽነር፤ ይሁን ምክትል ሚር ልብሳቸው፤ ሞገሳቸው፤ ግርማቸው ለሰው ልጅ ለዛውም ለወገናቸው #ከርህርህና ጋር ሊታረቁ ይገባል መጀመሪያ። ከአጽናኝነት ጋር ሊተዋወቁ ይገባል። ከአይዟችሁ ተፈጥሮ ጋር ቁጭ ብለው ሊመክሩ ሊዘክሩ እራሳቸውንም ሊወቅሱ ይገባል።
45 የእግዚአብሄር ፍጡር በአንድ ጉድጓድ መኖራቸው ሲያከትም መሃያ ለሚሰጠው ኢትዮጵያዊ ሹም ክብር ኩራት ሊሆን አይገባም። ነገ በፓርላማ እንዴት ሠርግ እንደተጠሩ ለብሰው እንደሚመጡ የላይኛው ይመዝነዋል። ከርታቶቹ የሙያሌ ምንዱባንስ? የአላማጣው ጉዳይስ?
የሆነ ሆኖ ውስጥን ሸሽቶ ውጭ ወጩን አያነጋም። ቢሆን ግን የራስግ እምታ ላይ አብሮ አምጦ ቢሆን ኖሮ ከዛ አልፈው ስለ አፍሪካ፤ ስለ ዓለም ተቆርቋሪ መሆን አማረኝ ቢሉ ዶር አብይ ይሁን አምላኪወቻቸው ያምርባቸውል። በስተቀር ግንጥል ጌጥ ነው።
ጠቅላይ ሚር አብይ ብቻ ሳይሆኑ ፓን አፍሪካኒስት ለመሆን የሚሹ ሹማምንቶቻቸው በአገራቸው፤ በወንዛቸው የተፈናቀለውን ከጎርፍ ጋር እየተጋፋ ሙለ ፰ ዓመት የሚንገላታውን ወገናቸው ለመጠለያ፤ ለእህል ውሃ ሳያበቁ ለራፊ ሳያበቁ ለዓለም የጤና ድርጅት WHO ምክትሉ አፍሪካዊ መሆን አለበት ቢሉ ጠብ አይልም። እስኩ እስር ቤቱን ሄደው ይዩ። ይህ ሳይሆን የውብ ቃል ፍሰት ዲስኩሩም፤ ሞዱም #የእንቧይ ካብ ነው። የላይኛው መስፈሪያ አለውና።
ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ የኃላፊነት ደረጃቸው ብልጫ ቢኖረውም ሁሉን እሺ ስለሚባሉ የሚታረም ግድፈት ሳይሆን የሚራባ ግድፈት ተበራከተ። የስሜን ኢትዮጵያ ችግር መልክ ሳይዝ የምስራቁ ችግር ተመረተ። በዓለም አደባባይ ሁልጊዜ እራስን መምራት ተስኖ በአገር ውስጥ መፈናቀል አልበቃ ብሎ ደጓን ኬንያን በስደተኛ ማጥለቅለቅ ሊታፈርበት የሚገባ ገመና ነው።
የጋንቤላው፤ የጉሙዙ፤ የኮሬ፤ የውልቄጤ፤ የአፋሩ፤ የትግራዩ፤ የአማራው፤ የኦሮሞው ክልል ትርምስን ለማን ተሰጠ? ለመቼስ - ተቀጠረ? እራስን ማሸነፍ ይቅደም። የሰውን ልጅ ማጣጣል፤ ማቃለል አያስፈልግም። የሰው ልጅ የፈጣሪ ፍጡር ነው። ፒኮክ በነገሳባት ኢትዮጵያ ዜጋዋስ?
ጠቅላይ ሚር አብይ ፓን አፍሪካኒስት ናቸው ብዬ አለምንም። ውጫቸውን፤ ውስጣቸውን ፓን #አረቢክ መሆናቸው፤ #ፕሮ እስያዊ መሆናቸው ከውስጤ ስለምከታተላቸው የማምንበት የራሴ ሃቅ ነው። በኢትዮጵያ የዘመናዊ መሪነት ታሪክ ውስጥ ፓን አረቢክ መሪ አላዳመጥኩም። ከሎሬት አብይ አህመድ በስተቀር።
የሚያስቀናቸው፤ የሚማርካቸው፤ የሚፈልጉት ኢትዮጵያን የአረብ ሥልጣኔ አሻራ ወራሽ የማድረግ ነው። የራሧ በቂ ያላት አገር። ትናንት ከተፈጠረ አገር በታች አድርጎ ማየቱ በራሱ ውስጥን ያቆስላል።
እራሳቸውን እንደ ኦብጀክት ወስደው ዶክተር አብይ አህመድ አሊ አለኝ የሚሉትን ጸጋ፤ አለኝ የሚሉትን የትጋት አቅም ቢመረምሩት፤ ቢፈትሹት ከራዲዮ ኦፕሬተር - ሎሬት የዓለሙ ያደረገች አገር ኢ-- ት--- ዮ ---ጵ--- ያ ካለ መፈንቅለ መንግሥት ፈቅዳ ምራኝ --- ንዳኝ ያለች የላቀች፤ ያስቻላት፤ #የተሰጣት፤ የበቃች ስለመሆኗ ዩንቨርስቲ በሆነላቸው ነበር። አይፈልጉትም። አይጠነቀቁለትምም።
ከእኔ ጀምሮ በነፍስ ወከፍ የተጋንላቸው፤ የተማገድንላቸው ምስክርነት የሰጠናቸው፤ የተማገድንላቸው ሚሊዮን ኢትዮጵውያን የመቻላችን አቅም የተቀዳው ከዊዝደሟ ኢትዮጵያ፤ ከብልኋ አፍሪካ ነበር። እሳቸው ልጥፍ ፓን - አፍሪካኒስትነትን አድርገው ማዶ - ማዶውን ሲዩ በዛ ሲራመዱ አያቸዋለሁኝ። አይጠቅማቸውም። ሲጠቅማቸውም - አላየሁም። ቀደምት አገር ቻይና፤ ራሺያ፤ ጃፓን ወደ ቀደመ ክብራቸው መመለሳቸው ነው ያተረፋቸው። የእኔ ብለው ውስጣቸውን በፍቅር ስለተቀበሉት አንቱ ሆኑ።
እርግጥ ነው ኢትዮጵያ ባላት ድንቅነት ብዙ አገሮች ሊወዷት፤ ሊቀርቧት ይሻሉ የአረብ ዓለሙን ጨምሮ። ግን የራስን አቃሎ፤ ጥሎ ሊሆን አይገባም ነበር። ከአንደበት ጀምሮ እራስን አቅሎ "ለማኝ ነነን፤ ለማኝ ሉዓላዊነት የለውም" እያሉ ለዘወትር ጠላቶቻችን ለማህበረ - ግብጽ ሊቃናት ልብ ማሞቂያ አልሚ ንጥረ ነገር መመገብ የተገባ አልነበረም። ከዚህ ወጥቶ እኛ እንዲህ ነን ልቅና ና ቢሉት በጅ አይልም። ኢትዮጵያ እኮ የሁሉም ነገር የምርምር አገር ናት። ከእሷ የሚነሳ ንፋስ እንኳን ይፈራል። እንኳን ትንፋሿ ጠረኗ።
የውስጥነት ጥያቄ ነው። ቱርክ ላይ በነበረው COP31ኛ ጉባኤ ከስጦታው ጀምሮ ሁሉንም የሚዲያ ሽፋን ተከታትያለሁኝ። ከውስጥ ለውስጥ የሆነ ተፈጥሯዊነት ይቀደም እያልኩ ነው። የራስን መሰጠት አርቆ፤ አንቋሾ፤ ኢትዮጵያን ዘላፊ ሹሞ ሸልሞ፤ ሚኒስተር አድርጎ እያንጎባለለ ያለ መንግሥት እንደምን ለጎረቤት አገር ተቆርቋሪ ይሁን? ፰ ዓመት ብዙ በጣም ብዙ ነው። ሁለት የምርጫ ዘመን ነው በሌሎች አገሮች። ህዝብ ተኮር ካልሆነ #ቁጥር ብቻ ነው።
ፕሮጀክቶች ተወጥነው እንደሚጠናቀቁ አያለሁኝ። ግን ሰዋዊነት፤ ተፈጥሯዊነትን #ተጭኖ እና ተረግጦ ሊሆን አይገባም። ህዝብ ለመቀነስ ፕሮጀክትም አለ። የሚቀነሰው አገር ያበጀችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተወሃዶ እና አሳረኛው የአማራ ህዝብ ነው። ሙሉ ፰ ዓመት ሞት እና ማፈናቀል? ማንን ለማስደሰት ይሆን?
በአገራችን በኢትዮጵያ ብዙው ነገር የተዛባ ነው። መኖርን #በፕሮፖጋንዳ ድርድር መመራት አይቻልም።
"#ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ በአረብኛ ቋንቋ ባጋሩት መግለጫ በሱዳን ያለውን ጦርነት ለመቋጨት እና ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ውይይቱን ለማዘጋጀት እና ለማስተባበር እንደሚሹ አስታውቀዋል።" BBC።
ከራሳቸው አገር ፖለቲከኞች ጋርስ ነው ግዙፋ ጥያቄ። በዛ ዲስፕሊን ውስጥ ማለፍን ይጠይቃል። ቤት ሳሎን፤ ኩሽና፤ በረንዳ፤ አስፓልት ሳይጸዳ ባህር ማዶ? ቋንቋውን ባልጠቀምበት ወደድኩኝ። አማርኛ አቅም ያለው #ቋንቋ ነው።
የራስን ገመና ስጦ አድርጎ የሌላን ገመና ልጋራ?????? ከውስጤ ያልገባ አቋም ነው። እሰይ፤ ጎሽ፤ አሸወይና ልለው አልችልም። ከውስጣቸው ካዘኑባቸው ኢትዮጵያዊ ዜጎች አንዷ ነኝ። ብዙ ተደክሞላቸዋል። ግን የአማራ ልጅ ለሳቸው እንደ ፓኪስታን ህዝብ እንኳን ሊዩት የማይፈቅዱት ፈተና ነው። ለሁለት ሰዓት ለፓርላማ ቆይታ ትዕግስት የሌላቸው መሆኑን ባለፈው የፓርላማ ዘመናቸው ታዝቤያለሁኝ።
አሁን ወዳጆቻቸውን በፖለቲካ ድርጅት #ምደባ ፓርላማ አስገብተዋል። ነገ ሃሙስ ፏ ፍንትው ብለው የልቦቻቸው ይገኛሉ። ተዘጋጅቶ የተሰጣቸውን አስተያዬት ጥያቄ እና መልስ ሴሪሞኒ እናያለን። ከረባቱም - ገበርዲኑም፤ ሙሉወርዱም ፋሽኑም። ሙያሌ፤ ሃይቅ፤ ደባርቅ፤ ደብረብርሃን ላይ ያለው የራስ ወገን ሰቆቃ ግን ማን አለው? ምንስ አለው?
#ክወና።
ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ቢሮ አይወዱም። መስክ ነፍሳቸው ነው። ስጦታ ትርታቸው ነው። ሴሪሞኒ ትንፋቸው ነው። ኢቬንት ፕሮጀክታቸው ነው። የመንግሥት ሚዲያወች ማህበራዊ ሚዲያቸው የሚጥለቀለቀው በአንድ መሪ ሁነት ብቻ ነው። በዓለም በአገር ውስጥ መፈናቀል ፩ኛ በወጣች አገር።
የሱዳን ህዝብ ስቃይ ቀርቶ፤ የጋዛ ጦርነት ስቃይ አብሶ የህፃናቱ ፎቶ በገፍ አለኝ። ሰላማቸው ይናፍቀኛል። ጎንደር ከተማ እንደ መወለዴ ቅርብ ያለ ስሜት አለኝ ለሱዳን ህዝብ። ግን "ራስ ሳይጠና ጉተና አይናፍቀኝም።"
ክቡር ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ሆይ! ላም እረኛ ምን አለን ቢያዳምጡ ይበጃል። ድርጅትም ፓርቲም እማናመልከው፤ ይህ መሪዬ ነው የምንለው ፖለቲከኛም የለለን የኢትዮጵያን ዜጎች ቢያንስ ቢያደምጡ ጥሩ ነው። ከእኛ ይልቅ ግን የላይኛውን ይፍሩ። ሁሉ ያልፋል። ሁሉ ይቀራል። ዕንባ ማህተም፤ መለያ ሌጋሲ ባይሆን ያተርፋሉ ለ50በ60 ዘመነወት።
ውዶቹ የBBC ዘገባ አጭር ነው አያይዠዋለሆኝ።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
ፍቅር ሲያልቅ ትዕግሥት ይሰደዳል።
ትዕግሥት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
25/11/026.
"ኢትዮጵያ መድረኩን ለማዘጋጀት እና ግልፅ ውይይት እንዲካሄድ ለማስቻል ዝግጁ መሆኗን የገለፁት ዐቢይ፤ የሱዳን የተለያዩ ኃይሎች ልዩነታቸውን ፈትተው የፖለቲካ ስምምነት ላይ እንዲደርሱ እንደሚመኙ ገልፀዋል።"
"ዐቢይ ያቀረቡት ዕቅድ በሱዳን ያለውን የእርስ በርስ ጦርነት ለመቋጨት፣ በሱዳን ተዋጊ ኃይሎች መካከል ያለውን ልዩነት ለመፍታት እና ፖለቲካዊ ሽግግር ለማምጣት ያለመ መሆኑን መግለጫቸው ያትታል።"
"ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰላም ዕቅዱ በፖለቲካ አጀንዳ የተመራ አለመሆኑን አስምረው ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ታሪካዊ ወዳጅነት መሠረት በማድረግ የአገሪቱ አንድነት፣ ሉዓላዊነት እና መረጋጋት ላይ ያተኮረ መሆኑን ተናግረዋል።"
"የሱዳን የወደፊት ዕጣ ፈንታ በሱዳናውያን ብቻ ነው የሚወሰነው ያሉት ዐቢይ፤ ሁሉን ያሳተፈ ውይይት ብቸኛው የሰላም አማራጭ መሆኑን በመግለጫቸው ጠቁመዋል።"
"ከዚህ ቀደም በሱዳን ወታደራዊ እና ሲቪል አመራሮች መካከል የነበረውን ልዩነት ለመፍታት ኢትዮጵያ ያደረገችውን ጥረት አውስተው አዲስ አበባ ለኻርቱም ሰላም እና መረጋጋት ድጋፍ እንደምታደርግ ተናግረዋል።"
"አራት ዓመታት ሊሞላው ጥቂት ወራት የቀሩት የሱዳን ጦርነት በሱዳን ጦር እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይል መካከል የሚደረግ ነው።"
"በጄኔራል አብድል ፋታህ አል-ቡርሐን የሚመራው የሱዳን ጦር ኢትዮጵያ ለፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ድጋፍ ታደርጋለች ሲል ይከሳል። አዲስ አአባ ግን ይህንን ውንጀላ አትቀበለውም።»
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ