ህሊና።
ህሊና።
ከሥርጉተ - ሥላሴ (Sergute©Sselassie)
10.01.2018 (ከጭምቷ - ሲዊዘርላንድ።)
10.01.2018 (ከጭምቷ - ሲዊዘርላንድ።)
„ትሁት ልብ የሥጋ ሕይወት ነው፤ ቅንዓት ግን አጥንትን ያነቅዛል።“
(መጸሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፲፬ ቁጥር ፴)
(መጸሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፲፬ ቁጥር ፴)
·
እንደ መነሻ
ESAT Efeta 5 Jan 2107 (2018)
„ይድረስ ለአቢይ አህመድ (ዶ/ር (ለኦህዴድ ፅህፈት ቤት ሀላፊ በኤርሚያስ ለገሰ)
- ቆንጽሎ ማዬት የጭንቀት በሽታ ነው።
ዛሬ ትንሽ ከፖለቲካ ተንታኙ ጋዜጠኛ ኤርምያስ
ስጋትን ማነሳሳት እንዲህ አሰኘኝ። ይሳሳ - ይባዘት - ይቀንደብ፤
የማከብርህ ወንድሜ ጋዜጠኛ ኤርምያስ ለገሰ እንዴት
ሰነበትክ? ምነው እንዲህ ብትክትክ አደረገህ? አንድ ጊዜ ከእነከሌ ጋር ጎን ለጎን መቀመጥ የለባቸውም ትላልህ፤ ከተጨባጭ ውጪ የሆነ
ነገር። አሁን ደግሞ ኦፌኮን ምህረት ይጠይቁ ትላለህ? ግራው ገባህ።
እንደዚህ ከሆነ አትደራጁም ብላችሁ ጦር የሰበቃችሁባቸውን የአማራ ድርጅቶችን ይቅርታ ጠይቁ - እናንተም። የአማራን ተጋድሎ „የነፃነት ሃይል እያላችሁ“ ሥነ - ልቦናችን ባልተወለደ አንጀታችሁ ያረሳችሁትን ሁሉ ቁስሉ እንዲሽር ይቅርታ ጠይቁ። ከገዳይ ጋር የጎንደር ፋሲል ግንብን የዜና ሽፋን በማድረግ ጎንደሬ በሙሉ በገዳይ ስዕል ውስጥ የተቀረጸውን መንፈስ ይቅርታ ጠይቁ።
ለነገሩ ፋሲል ግንብ እኮ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያለው ቅርስ ነው። በዚህ ቢኬድ ጦሱ የሚገፋ አልነበርም። መንገዱ ጠፍቶን እንዳይመስልህ፤ ሳናውቅ ቀርተንም አይደለም። እስቲ ይሁንላቸው ብለን ነው። የሆነ ሆኖ እኔ ከቅድመ ሁኔታህ ብዛት በስተቀር አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ። ይልቅ አንተ ተስንት ዘመን በኋዋላ አዲሱ የኦፌኮን አክቲቢስት በመሆንህም እንኳን ደስ አለህ።
ኢሳት ላይ እፍታ ላይ የነሳሃቸውን ነጥቦች ሲገርሙኝ አሁን ደግሞ ነፍሱን በዬትኛው መስመር አንደ ተቃኜ ቅጥ አንበሩ ጥፍት ያለው ጹሑፍ በበላይ መሪነት እና በተመክሮ ዝቀሽነት ትዕዛዝ ቢጤ አቅርበሃል። ያ አልጠግብህ ስላለ ደግሞ ወደ ዶር አብይ ዞር ብለሃል። ቅንነትም ትህትናም የነጠፈበትን ብቻ ሳይሆን በአጻጻፍ ሥርዐቱም በፍጹም ሁኔታ የአንተ ጠረን የለበትም።
ለመሆኑ አንተ እዛ በወያኔ ሃርነት ትግራይ አራጊ ፈጣሪ በነበርክበት ስልጣን ላይ ኦፌኮን በሚመለከት የሠራኸው ስራ ይኖር ይሆን? ማለት በህዝብ አደባባይ፤ በሰላማዊ ሰልፋቸውም፤ በስብሰባቸውም የተገኘህበት ዓውድ ከኖረ እሱን ብትዘረዝረው ምናለ? ሌላው እቅድ አውጪም ሆነሃል፤ በሌላ ፓርቲ የውስጥ ህይወት ገብቶ እቅድ ማውጣት ይቻላልን? ከቻልክ ፓርቲህን ቋሚ የሆነ ሃሳብ አንዲኖረው እገዘው በልምድ የዳበርክ አይደለህ። የተመክሮ ማቅኛ መደብር እንደ ከፍትክ ነው ይህ ጹሑፍህ ያሳረዳኝ።
እራሰህንም ውስጥህን እያሳዬህን ነው። ስለምን ዶር. አብይ አህመድ እስከ ዛሬ ድረስ ትዝ ብለውህ አያውቁም? አሁን እንዴት ትዝ አሉህ? ምነው እንዲህና እንዲያ ያደርገሃል? አታውቀውም እንጂ አንተን አክብረን የተቀበልንበት እኮ ስለቀሰቀስከን አይደለም። አልነበረም? በራሳችን ውስጥ አድርገን ልናይህ የፈቀድንበት እንደ ሰው ግንዛቤ ቢለያዬም፤ ግልጽነትህን ከምንም በላይ በውስጣችን ስለዬነው ነበር። አንተም እዛው ውስጥ ማህበርተኛ ነበርክ።

በሌላ በኩል አንተንም ቁጭ ብሎ የሚያዳምጥህ ሰው
ስላከበርህ እንጂ ካለከበርህ አያዳምጥህም፤ የጻፍከውንም አያነበውም።
የእነኝህ የፖለቲካ ሊሂቃን ጎልቶ መውጣት ከዋናወቹ የፖለቲካ ሊሂቃን በላይ አንተን ሥርህን አንድዶታል፤ ለምን? ብቸኛው
ተናጋሪ ስለሆንክ? አይምሰለህ እጅግ የሚበልጡህ ዓራት ዓይናማ ተናጋሪዎች አሉ።
ዕድሉን አላገኙም፤ ምክንያቱም ከቅንጅት በኋዋላ ውጭ ሀገር አንተው በምታመልከው ማንፌሰቶ አፈና ስላለ። እንዲህ ተቆርቋሪ ከሆንክ ዶር. መራራ ጉዲና ስለምን አልታሰሩም እሰተ ዛሬ ድረስ ተብለው ሟርት ሲደመጥ አቻህን እንዲህ አደባባይ ወጥተህ ለምን አልሞገትክም? ለመሆኑ ስለምን እንደታሰሩ? ማን እንዲታሠሩ ሁኔታውን እንዳመቻቸ የእኔ ብለህ በጥልቀት የመረመርከው ጉዳይ አለን? ማለቴ በብሄራዊ ፖለቲካ ተንታኝነትህ ብቸኛው ነህና፤ ጸሐፊነትህ ሲታከል ደግሞ የበለጸገ ስብዕና አለ ማለት ነው። እኔ አኮ ያነሳሃቸውን ነጥቦች በሚመለከት የራሴን ዕይታ ልጽፍ ነበር ግን፤ የፋክት ጸሐፊው ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና እዛው ላይ በሚገባህ ቋንቋ ነግሮሃል ብዬ ነው።
አንድም ያልመለሰው ሃሳብ ስላልነበረ ነበር ዝም ያልኩት እንጂ ተመችቶኝ አልነበረም። ሁለት ጊዜ አዳምጨዋለሁ። ያው ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ከኖረ ሁለት ጊዜ ማድመጥ ልማዴ ነው። የሆነ ሆኖ „እንደ አለቃህ ቀደህ ስትጥል ማዬት እፈልጋለሁ¡“ ከአንተ አይጠበቅም። ያቺ ቅድስት በዜና ያስተዋወቅከን ልጅህ ይህን ብታውቅ ትወቅስሃለች። ስለ ንግግር ጥበብ ስላነሳህ ዶር አብይ አህመድን በሚመለከት ጥበቡን ስለተማርኩት መነሻ አድርገው የተነሱበት እና የመሰጠኝ ሙሉውን አንባቢዎችህም ያገናዘቡት ዘንድ አቀርበዋለሁ - ዛሬ።

ለመሆኑ „ስብሰባ
አያስፈልግም፤ ውይይት አያስፈልግም“ ለሚል መሪስ መልዕክትህ ምን ይሆን? ዶር አብይ አህመድ የስብሰባ እና የንግግር ወሳኝነትን
ለአንድ ማህበረሰብ የእውቅት መተላለፊያ መንገድ ስለመሆኑ የተጠበቡበትን ፍልስፍና ድንቅ ነበር። አንድ ፕሮግራም አዘጋጅታችኋዋል
አላዳመጥኩትም እርሱን ብቻ ነው ያዬሁት። „ዕለታዊ“ ጥሩ ሥም ነው ተመችቶኛል። የሚበጀው በራስ ውስጥ የሆነ፤ ነገን ያደማጠ ሃሳብ
መኖሩ ነው። ተጠዋሪ ያልሆነ።
አቃጁ ሲሸበሽበው የማይሸበሸብ ሲዘረጋውም የማይዘረጋ።
አቃጁ ሲሸበሽበው የማይሸበሸብ ሲዘረጋውም የማይዘረጋ።
ሌላው ዶር አብይ አህመድ ለማለት ቀፎሃል። ተዎው
„ጃኬታችን አውልቅን መሬት እንርገጥ፤ ከዲግረው በላይ ሰውነታችን ይበልጣል“
ያሉትን ጽፌልህ ነበር። አቶ ቀርቶ አብይ አህመድ በላቸው። ጉዳያቸው አይደለም። ፕሮ ፋይላቸውን እዬው በምን በምን ሙያ እንደተማሩ።
እርግጥ መማር በራሱ ግብ አይደለም።
ውስጥን እስከ አለወጠ ድረስ፤ ለመማርማ/ ለመማርማ እኮ ጠ/ሚር ሃይለማርያምም እኮ የተማሩ ሊሂቅ ናቸው። የሠሩባቸውም የሃላፊነት ቦታዎች ወዘተረፈ ነው። እኔን ያልገባኝ እንዲህ የተቃጠልክበት ነገር ምንድን ነው? ያብሰለሰለህ ጉዳይ ምንድን ነው? ታመስክ እኮ? የማናውቅህ ሰው ነው የሆንከው። የሚበልጥ አቅም ለመቀበል ውሱኑነትህን ገለጥክልን። ይህን ያለስተዋልኩት ነበር በአንተ ሰብዕና ውስጥ። ተዚህ ላይስ ተመስገን ብያለሁ።

እኔ እንደማስበው ችግርህ በውስጥህ ካስቀመጥከው
መንፈስ ጋር ይሄ አዲስ ወጥና ድንቅ መንፈስ ሊጣጣምልህ አልቻለም። ምክንያቱም ምንም ሳታስቀር ሙሉውን ለአመንከው መንፈስ ቦታውን
መርተህዋል። ልቦናህ ቦታ የለውም ሌላ አዲስ ሁሉን ጥሶ የሚወጣ ቡቃያ ሃሳብን ለመቀበል። ግን በዬሰከንዱ አዲስ ሰው መፈጠሩ፤ ከዚህ
አዲስ ሰው አዲስ ሃሳብ መፍለቁን አለመቀበል ሰማይና መሬት አልተሠራም የማለት ያህል ነው። ጊዜ እኮ ሂያጅ ነው ተጓዥ፤ ዛሬን ደግመህ
አታገኘውም።
ዛሬ አልፎ ነገ ሲማጣ ነገ ዛሬ ይሆናል፤ እሱም ሲሄድ ሌላ ነገ ይመጣል፤ ሌላው ነገ ደግሞ ስታገኛው ዛሬ ይሆናል እሱም ይሄዳል … በሌላ በኩል አንተን የሚያስከነዳ ሳይንስን የተመራመረ በማህበረሰብ ውስጥ የሰከነ ብቃት ያለው ወጣት ከች ሲል ደንግጠሃል - የእውነት። ተበልጥክ። ያለውማ አልደነገጠም። ይልቁንም ከፖለቲካ ሊሂቃናት መሪዎች ሁሉ ልቆ እና ጎልቶ፤ „አናስደንግጣቸው!“ ብሏል።
የሚያስከብር ሰብዕና ከሙሉ ብቃት ጋር የሰጠው፤ ከኢጎ የወጣ አቅሙ ነው እሱ እያለ እንዴት እንዲህ ይሆናል ብለን በህሊናችን ከድንነ በሌለበት እምንሟግተው። እንዲህ መመባል ቀላል ነገር አይደለም። ይሄ ታማኝነት ገብያ ተሄዶ አይሸመትም። ወገን የእኔ ብሎ በህሊናው መቀበል በመንፈስም ከእርሱ ጋር በአውንታዊነት መምከር። ልክ አንደማከብራቸው እንደ ዶር. ኮንቴ ሙሳ።

- · የቅንነት ጥፊ።
የሚበልጥ ሃይል ሲመጣ ደረጃ እዬሰጠህ፤ በፕርሰንት
እዬሸነሸንክ ከምትቸገር፤ ቅደም ተከተሉን በዕምሮህ ማደራጀት ያለብህ ይመስለኛል እንደ ፖለቲካ ተንታኝ ጋዜጠኝነትህ። ይህን ማደረግ
ከተሳነህ እዬጣለህ ይሄዳል አዲሱ ዕሳቤ፤ እሽቅድድሙ ከጊዜ ጋር ነውና። በምድር ቆሞ የሚጠብቅ ምንም አይነት አምክንዮ የለም።
በዚህ እርእስ ጉዳይ ባለፈውም ዓምት አንድ ጹሑፍ ጽፌ ነበር። በለፈው የአሜሪካኖች ምርጫ ላይ CNN ጎላ ያለውን ዕይታ ያጎናጸፈው ሃይል ነበር። ግን ሆነ? አልሆነም። ጊዜ የሚሰጥህ የራሱ አማራጭ አለው። አማራጩን የመጠቀም ወይንም ያለመጠቀም የራስ ጉዳይ ነው። በዚህ ውስብስብ፤ በታመቀ፤ ትብትብ ችግር ውስጥ ሱሪ በአንገት ብሎ ነገር አይሠራም።
ይህ የቅንነት ጥፊ ነው - ለእኔ። አሁን የተበተነን ህሊና እያሰባሰቡ ነው እነኝህ ወጣቶች። በዚህ ማህል የውጪ ጠላት ቢነሳ በዓራቱም ማዕዘን በሩ ክፍት ነው። ይህን እንደ ፖለቲካ ተንታኝነትህ ሊያሳስብህ ይገባ ነበር፤ በላይ በላይ በጫና ከምታዋክባቸው። ከምታብጠለጥላቸው። ሰላማቸውንም ከምትቀናቀነው። ሰብዕዊነት በሚደርሱ አደጋዎች ሁሉ ወገኖቻችን ተጎጂ ስለሚሆኑ በሩቁ ማሰብን ይጠይቃል። ካለ ሰው ሃይማኖትም፤ መስጊድም፤ ቤተ ክርስትያንም፤ ታቦትም፤ ፖለቲካም ወና ነው። አንተ እቴ አጅግ ዘመናይ ነህ …

ስለዚህ ይህን ወቅት አድምጦ መፍትሄውን በሚያቃልለው
መንገድ ላይ አቅምን ማጥፋት፤ ቅንነትን መለገስ ያስፈልጋል። በቁንጽል ጉዳዮች ዘርፍ፣ ጅራትና ቀንድ እያወጡ ሳይሆን ተያያዥና ተወራራሽ
የሆኑ ነገሮችን በተደሞ ማዬት፤ በጥልቀት የእኔ ብሎ መመርመርን ይጠይቃል - በስክነት። ከውስጥ ማጥናት። ዶር. አብይ አህመድ እኮ
የዛሬ ሰው አይደሉም። ዛሬ የተፈጠሩም አይደሉም።
ከስሜታዊነትም ተግ ማለት ያስፈልጋል። መከራ ላይ ያለ ሰው ትንፋሹን የሚሰበስብበት እራፊ የነፍሱ ማደሪያ ናት። አንተን የሚያስጨንቅህ የቅደመ ሁኔታ ጉዳይ ነው። በዚህም የተሰበሰበ ሃሳብን መበተን - መፈርቀቅ። ይህ ለባለቤት አልቦሹ ሰፊ የኢትዮጵያ ህዝብ እምብዛም ነው። በተፍረከረከ፤ በሽርክት፤ እና በግርድፍ ጉዞ ዘመን ተገፋ፤ ትውልድም ታጨደ፤ አሁን ግን ዘመኑ በራሱ ዘመኑን በአዲስ ቅኝት በለውጥ ሐዋርያት አቀለመው።
ቢያንስ ቅን የሆነ መንፈስ አለን ማለት ተችሏል። ቅን መሆን ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ሊሂቅ ፈጽሞ የማይታሰብ ነው አንተን ጨምሮ። አንተ አልኩ ለማለት ነው አሁን እቅድ አውጥተህ ዲሲ ላይ ሆነህ ማዘዝ ያሰኘህ፤ ይህ በኦህዲድ በኩል ላነሳህው ነጥብ ሁሉ ይመልስልሃል። መካች አቅም ስለሆነ ነው በአጭር ጊዜ የሁሉንም መንፈስ የመግዛት አቅሙ አንቱ የሆነው። የመንፈስ አቅም የህሊና ማድረግ የችርቻሮና የጀምላ ሸቀጥ አይደለም። በተሟላ ሰብዕና በቅሎ የሚያጸደቅ ረቂቅ የህሊና መስኖ ነው።

„Dr. Abiy Mohammed ሕዝብን የሚያረጋጋ ንግግር ተናገሩ“
„ኦህዲድ በእድገት ውስጥ ያለ ድርጅት ነው። በርካታ ቻሌንጆች እዬገጠሙት ያነን እዬፈታ የመጣ ድርጅት ነው። ችግር ባይኖር
ኖሮ መሰብሰብ ባላስፈለገ ነበር። ኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግር ባይኖራት ኖሮ 60/ 70 የፖለቲካ ፓርቲ ባላስፈለገ ነበር። መደማመጥ
ስሌለ፤ መስማማት ስሌለ ነው እንጂ 60 ፓርቲ አያስፈልገንም ነበር። ይሄ ችግር ደግሞ የሚፈታው በማኩረፍ አይደለም። የእኔ ሃሳብ
ካልተደመጠ ብቻ በማለት አይደለም። በመቀራረብ ነው። ማስተዋል የሚገባን ኦሮምያ 300 ሚሊዮን ህዝብ ማስተናገድ የሚያስችል ፖቴንሻያል
አለው። የኢትዮጵያ ህዝብ 100 ሚሊዮን አይሞላም። እንኳን ብሄር ብሄረሰቦች ጁቡቲም፤ ኤርትራም ሱዳንም ቢመጡ በህግ፤ በሥርዓት እሰከ ሰሩ ድረስ አብሮ መኖር፤ አብሮ ማደግ አስፈላጊ ነገር ነው።
ዱባይ ያደገችው ውሃ ኢንፖርት አድርጋ፤ አፈር ኢንፖርት አድርጋ፤ ድንጋይ ኢንፖርት አድርጋ፤ ሰውም ኢንፖርት አድርጋ ነው።“
ስለሆነም ከአንተ ቅልውጥ ወይንም ሞፈር ዘመት የሚያስመጣ የሃሳብ ድርቀት የለባቸውም።
የሃሳብ ተጠማኝ አይደሉም። ዲታ ናቸው። ተርፎም ይናኛል።
- · ወደ ውስጥ
ስለዚህም በዘመንህ ውስጥ ለመሆን መጀመሪያ ፍቀድ። ስለምን ተጠራጣሪ ትሆናለህ? ተጠራጣሪነት እና ተፋላጭነት የሶሻሊዝም ሰቁ ነው። የሆነ ሆኖ ባነሳሃቸው ነጥቦች ላይ በተወሰኑት ላይ ብቻ ዕይታዬን ልግለጽልህ። ከራስህ፤ ከተፈቀደልህ ዕንቁ ዘመንህ ውጪ ስለሆንክ። ጹሁፍህ ሆነ መንፈስህ ጠብ አጫሪ ነው ወይንም ሃሳብን ከፋይ። እጅግም ተጋፊ ነው።
- · ኦህዲድና የተፎካካሪ ፓርቲዎች ስጋት።
በመጀመሪያ ነገር መሬት ላይ በሁለቱም ብሄረሰቦች
ማለት በኢትዮጵያ ሱማሌ እና በኦሮሞ ከ600 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች አሉ። ከዚህ ውስጥ የምግብ ዕጥረት ያለባቸው፤ ነፍስጡር ሴቶች፤
ካለፍቃዳቸው የተደፈሩ ሴቶች፤ ከወላጆቻቸው የተለዩ ህጻናት፤ ከትምህርት ገበታቸው የተለዩ ወጣቶች፤ አዛውንታት፤ ጤናቸው የተጓደሉ
ስንት ወገን አንደ ሆን እስበው። ይሄ ይጎርብጥህ መጀመሪያ ነገር፤ ከፕሮፖጋንዳን ከቅስቀሳ የሌላ ፓርቲ ተጠማኝ ንድፍ አዘጋጅነትን
ከመመኘት።
የትኛው ይቀደም? ገና የኦፌኮን መሪዎች ተመርጠው ያሸንፉናል እና አይፈቱ ወይንስ መከራውን የሚጋራ አቅም መሬት ላይ መገኘት ለእነኝህ ሊሂቃን የቱ የሚቀድም ይመስልሃል? ዶር ነገሶ ጊዳዳን እኮ በክብር ስበሰባ አሳተፈዋቸዋል።
አንተ ከዛ ከ66ቱ ዘመን ውስጥ ነው ያለኸው፤ እነሱ ደግሞ ከዛ ዘመን ውጪ ናቸው። የጥላቻ ፖለቲካ ቤተሰቦች አይደሉም። እነሱ እለታዊ አይደሉም። ነገን ያደመጡ ናቸው። አንተ እንደምትለው አንደኛው የኦፌኮ ከፍተኛ መሪዎች መፈታት የሥልጣን ተፎካካሪነት ኦህዲድን እንደሚያሰጋውና በዚህም የተነሳ መፈታታቸውን በቀና ኦህዲዶች ስለሚመለከታቸው ጥርጣሬ ገብቶሃል። አበስኩ ገብርኩ።
አንዲህ ዓይነት ሰዎች አይደሉም። አንተም ለእነሱ አሰበህ አይደለም፤ መሬት ላይ ያለውን የተሰባሰበ መንፈስ በጥርጣሬ ወጥረህ አቅምን ለማባከን ነው። የእነሱ ንጹህ መንፈስ ከተለመደው የጨበራ ተዝካር ጉዞ ውጪ ነው - ስክነቱ - እርጋታው - ማድመጡን ካልፈቀድከው ውስጠህ ሊሆን ከቶውንም አይችልም።

„ኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግር ባይኖራት ኖሮ 60/ 70 የፖለቲካ
ፓርቲ ባላስፈለገ ነበር። መደማመጥ ስሌለ፤ መስማማት ስሌለ ነው እንጂ 60 ፓርቲ አያስፈልገንም ነበር። ይሄ ችግር ደግሞ የሚፈታው
በማኩረፍ አይደለም። የእኔ ሃሳብ ካልተደመጠ ብቻ በማለት አይደለም። በመቀራረብ ነው።“
ይሄንን የአንተ ማንፌስቶ ይፈቅዳልን? አንዳትዋሽ። ጽድቁ ቀርቶ በወጉ በኮነነኝ ነው።
የድርጅት ማህበርተኛ ያልሆነውን የውስጥ ሰላማችን ቢጠበቅ ምንኛ ዕድለኞች በሆን ነበር።
ሌላው ደግሞ አሁን ትእዛዝ ቢጤም አስተላልፈሃል
… ግን ይቻልሃል? እስቲ ጓዳህን መርመር አድርግ፤ እንኳንስ ኢትዮጵያ ከዚህ አማረ ተደራጀ ብላችሁ አልነበረም ያዙኝ ልቀቁኝ ስትሉ
የነበረው? ከዚህ ሲዊዝ የነበረውን የአንድነት ፓርቲ ደጋፊ አካል ማን ያፈረሰው ይመስልሃል? አባላቱን ዘርፎ ከጥቅም ውጪ ያደረገው
የግንቦት 7 ቅ/ ጽህፈት ቤት ነው። ለመሆኑ ግንቦት 7 ከተፈጠረ ጀምሮ የትኛው ፓርቲ ነው ደፍሮ ከግንቦት 7 ዕውቅና ውጪ በአንድ
አውሮፓ ሀገር ስብሰባ የሚጠራው? ይቻላል? ከግንቦት 7 በፊት አውሮፓ እንዲህ አልነበረም።
አንጋፋው ኢህአፓ እንኳን ይህን አያደርግም ነበር። መድህን፤ መኢሶን፤ ኢህአፓ፤ አርዱፍ፤ መአህድ፤ ኢተፖድህ፤ አማራጭ ሃይሎች ደጋፊዎች፤ ኢዲዩ ሁሉም በህብረት የዶር አረጋይ በርሄ ፓርቲን ጨምሮ ስበሰባዎችን ሞቅ ደመቅ አድርገው ነበር በጋራ የሚያሳልፉት።
ያ መድረክ ትምህርት ቤት ነበር። የተለያዩ የፖለቲካ ሊሂቃንን የምንሞግትበት ፊት - ለፊት። እነሱም ተመክሯቸውን የሚያዘምሩበት ነበር። ዝም ብንል ምን አለበት ብትተውን? እዚህ አኮ ኮምኒቲም አይፈቀድም፤ አንዲት ትንሽዬ ስበስብ መፍጠር አይቻልም። እንኳንስ ሌላ? እናንተ ሰው ሰብስቦ ማናገር ነውር ከሆነባችሁ ስለምን ይሆን ሌላው ሰው ሰብስቦ እንዲያናግር እንቅፋት የምትሆኑት? ስበስባ ንግግር እኮ ት/ ቤት ነው። ሙያም ነው የምትሰለጥነበት። አዶልፍ ሂትለር ሆነ ሙሶሎኒ ያን ያህል ሠራዊት ማሰለፍ የቻሉት እኮ በንግግር የጥበብ ክህሎት አቅም ነበር።

ዓለም እራሷ ስብሰባ
ናት። ትውልዱ ታፍኗል። ከቻልክ ይህን ታገልና አሸንፍ። ሚዲያህስ ኢትዮጵያዊ ሊሂቃኑን በሙሉና በእኩልነት ያሳትፋልን? የክትና የዘወትር
ነው የምናዬው። ከቻልክ ይህን ድፈረው? ቤትህን አስተካክል መጀመሪያ። ሁሉን
በእኩል ዓይን እይ። በዬዓመቱ ስለምን ይሆን ከዬድርጅቶች ጋር ግጭት የሚኖረው? ችግሩ የት ላይ ነው? አጥነተኸዋልን?
አቅሙም አለህ ችሎታውም አለህ። ተዘጋጅተህም ነው ውይይት እምትገባው።
ይህ መቼም አሊ አይባልም። አንተ ነህ ያለህን ቀለም ማወቅ ተስኖህ አንዲህና እንዲያ የምትሆነው … እንጂ እኛማ አክብረን እናዳምጥሃለን። እማዳምጠው እፍታን ብቻ ነው እኔ። ስለምማርበት። ለምንድን ነው አንዳከበርነህ እንድንኖር አማትፈቅደው? ስለምን ትፈታተነን አለህ? አጅግ ነው እኔ ያዘንኩብህ።
ይህ መቼም አሊ አይባልም። አንተ ነህ ያለህን ቀለም ማወቅ ተስኖህ አንዲህና እንዲያ የምትሆነው … እንጂ እኛማ አክብረን እናዳምጥሃለን። እማዳምጠው እፍታን ብቻ ነው እኔ። ስለምማርበት። ለምንድን ነው አንዳከበርነህ እንድንኖር አማትፈቅደው? ስለምን ትፈታተነን አለህ? አጅግ ነው እኔ ያዘንኩብህ።
አቦ ለማ መግርሳን እና ዶር አብይ አህመድን በሚመለከት
ልታውቃቸው ስላልፈቀድክ ልታውቃቸው አልቻልክም። እንዲያውም እንደ በፖለቲካ ህይወት አንደ መሥራትህ፤ እንደ መኖርህም ለእነሱ ያለህ
ክብርና የምትሰጠው ዕወቅና የደበዘዘ ሆኖ ነው ያገኘሁት። ጠፍቶህ አይመስለኝም። ልተቀበልበት ያልቻልክበት የራስህ ምክንያት ይኖራል።
መቀበልም ግዴታ የለብህም።
ግን የምታነሳቸው ነጥቦች ሁሉ አንተንም ድርጅትህንም ያስገምታሉ። ፍሬ ፈርስኪዎች እና ተራ ምቀኝነት ወይንም ኢጎ ነው ሆኖ ያገኘሁት። ሌላው የምታቀርበው የአምክንዮ አቅም እዚህ ላይ መቅኖው ተንኮላሸ። የኦህዲድ አዲስ አመራር መለኪያው በሥልጣን ሽኩቻ የመለካት ሂደት መመዘናቸው ራሱ ግርም የሚያደርግ ነው። በመጀመሪያ ነገር መርሃቸው ተፈጥሯዊነት ነው።
በተፈጥሯዊነት ውስጥ ሰው እንጂ ወንበር ወይንም ሥልጣን በእነሱ ቤት ቦታ የለውም። ወይንም ቀጣዩ የኢትዮጵያ መንግሥት ፕሬዚዳንታዊ ወይንስ ጠቅላይ ሚኒስትራዊ፤ ፌድራላዊ ወይንም አህታዊ ይሁን አይደለም። ይህ የሚያብሰለስልህ አንተኑ ነው። ይህ ከ40 ዓመት በላይ የተኖረበት ዘመን ተለውጧል። ጥለውህ ሄደዋል።
የዘመኑን ባህሪ የለወጡት ደግሞ ሁለቱ ወጣት የኦህዲድ መሪዎች ናቸው። ከዚህ አለፍ ያለው ምልከታ ደግሞ ባለፈው ዓመት በሳቢያ ተዘቅዝቆ የተሰቀለው የጎንደር የአማራ ማንነት ተጋድሎ አብዮት ይዞት የተነሳው „በቀለ ገርባ መሪዬ ነው“ ብሎ ነው። በዚህ ስሌት ስትሄድ ኦህዲድ አይደለም ኦሮሞ መሬት ሌላም ቦታ የበቃ የመንፈስ ሃብት አለው። ዲታ ነው። መንፈሳችን እኮ ገዛ።
በሥነ - ሥርዓት ቃለ ምልልሶችን ሁሉ አንከታተላለን። እኔ እኮ ንግግሮችን የምጠቅሰው ስለተደምምኩበት ነው። ሌላ አንድ ነገር ልንገርህ አንድም ኦሮምያ በሚባል ቦታ „ዓጼ በካፋ“ የሚል ት/ቤት አልነበረም፤ ጎንደር ግን ከአንደኛ እስከ 8ኛ ነበር። እንግዲህ ይህ ት/ቤት እኔ ተማሪ እያለሁ ነበር የግል ነበር። ሥሙ የሚሰጥህ ትርጉም አለው - ቅኔ።

ሁለቱም ወጣት ሊሂቃን አቶ ለማ መግርሳና ዶር.
አብይ አህመድ በታሪክ አማራን አግሎና ተጸይፎ በኖረው የ40 ዓመት የሶሻሊዝም ፖለቲካ አፈር ድሜ ያስጋጡ ጀግኖች ናቸው - ለእኔ
እንደ አማራ። እንዲህ አማራ እንደ አማራነቱ ከልቡና ከውስጡ በንጽህና የተቀበለ ድርጅት ቢኖር ኦህዲድ የመጀመሪያው ምንአልባትም
የመጨረሻው ይሆናል። ወደፊትም ይኖራል ብዬ እኔ በፍጹም አላስብም። በጥብጦ አይጋት ነገር። እራሱ የኢህአፓ ዝንጣፊ ብአህዴን በሥሙ
ተጎልቶ አማራዊ ጠረን የለውም። እንዳይኖረው ተደርጎ ያልተወለዱት ሲፈነጩበት የነበረ ድርጅት ነው።
አቶ ደመቀ መኮነን እኮ ኦሮሞ ናቸው። አማራ መሬት ያደጉ ግን በዘገጠው ፖለቲካ የሰመጡ - ዝገት። ሌሎቹንም ታውቃቸዋለህ አብርህ ነበርክና። አንድ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ብቻቸውን ምን ሊፈይዱ ይችላሉ። አሁንም በመግለጫው አንዴት እንደ ተገፈተሩ ተመልክተሃል። ከአራቱ ወኪሎች ውስጥ አማራ ወኪል አልባ ነበር።
አንደበታችንም፤ ልሳናችንም፤ ሥነ - ልቦናችንም ተከርችሟል። ውጪ ሀገር ደግሞ ከገዳዮች፤ ከአሳሪዎች፤ ከደብዳቢወች፤ ከልዑልኑ ጋር እንዲሁም ከዘራፊዎች ከወያኔ ሃርነት ትግራይ ጋር አማራ ነው ተብሏል። ስለምን? ይህን መንፈስ ሰብዕዊነት ከቆረቆረህና ካንገላትህ አትሞግተውም? አዬህ ይህ ነው የአንተን የፖለቲካ ብቸኛው ብሄራዊ ተንታኝነትህ ፊት ለፊትህ የሚገጥም የሃቅ እንክብል ነው። ታሪክህ ነው በአውንታዊም ይሁን በአሉታዊ።

- · ኢትዮጵያ የወልዮሽ አጀንዳ ትንሳኤ።
በሌላ በኩል ብዙ ጊዜ ሀገር ውስጥ ያሉት ይባላል በውስጥም በውጭም ኢትዮጵያን ከነሙሉ ተፈጥሯዋ የተቀበለ ድርጅትም ቢኖር ኦህዲድ ብቻ ነው። ኢትዮጵያ ፍቅሯ በውስጣቸው ከነጣዕሟ አለች።
አንድ የማህበራዊ ሚዲያ ታታሪዎችን የጋራ አጀንዳ የላችሁም ብሎ የሞገተ አንድ ወጣት ፎረም 65 የሚባል የመወያያ መድረክ አዘጋጅ አሁን የጋራ አጀንዳ ሆና ኢትዮጵያ ስትመጣ ደግሞ „የዓመቱ ድንቅ ሰው አቶ ለማ መገርሳ“ ሊባሉ አይገባም እዬአለ ሲሟገት ሰምቻለሁ። ኢትዮጵያ ከመሬት በታች ትቢያ ለብሳ ተቀብራ ስለመኗሯ እራሱ የማያዋቅ ሆኖ ነው የቀረበው።
ፍላጎታችን ምን እንደሆን አይታወቅም። እግዚአብሄር ይመስገን ሰሞኑን ከሁለት ንጥር ኢትዮጵያዊ ታላላቅ ሊቃናት ጋር SBS ውይይት አካሄዶ ቅን፤ ግልጽ እና አስተዋይ ሊቃናት ይገባቸዋል ሲሉ አፋቸውን ሞልተው ተነጋርዋል። ዶር አብርሃም አለሙ እና ዶር ደረሰ ጌታቸው ይባላሉ። የፖለቲካ ትንተናቸውም ወላድ በድባብ ትሂድ ያሰኛል። ኮረቸባቸዋለሁ በወገኖቼ።
« Hopes and Concerns:- What is to be done? - SBS Amharic“
ከዚህ በላይ የሚያስደስት የሚመስጥ ከቶም ምን
ዓይነት አጀንዳ ሊኖር እንደ ተፈለገ ሁሉ ግራ ያጋባል። በአጋጣሚውም ለሁለቱም ሊሂቃን ማለትም ለዶር. አብርሃም አለሙ እና ለዶር
ደረሰ ጌታቸው ያለኝን አክብሮትና አድናቆት ብቻ ሳይሆን ለፍጹማዊ ሙሁራዊ ቅንነታቸው ያለኝን ፍቅር ልገልጽላችሁ እወዳለሁ።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አንተም ጤነኛ መንፈስ ነበርህ ስለ ልጅህ ቅድስና የጻፍከው እኔ እንደ ድርሳን ነበር የደጋገምኩት። አትሜ አስቀምጨውማለሁ። እርግጥ በጎንደሬ ላይ ያለህ ምልከታ ዘባ ያለ ቢሆንም። ለዚህም አትገደድም አንተ ወደድከን ወይንም ጠላህን እምታመጣው ለውጥ የለም። አለመሰልጠናችን ለውሽክታ ሆነህ፤ አልሆነህ ጉዳያችን አይደለም። እንዲያውም ለምታበረክተው አስተዋፆ የተለዬ አክብሮት ነው እኔ በግሌ ያለኝ። ስለምትስቅብን እሚቀርብን ነገር ስሌለ። … ምን እንዳለን፤ ምን እንደምንችል አሳምረን እናውቀዋለን እና - ጎንደሬዎች። …

ሌላው ላነሳልህ እምሻው አብዝተው ጸሐፊ አቶ ግርማ
ካሳ ሆኑም ሌሎቹም ጸሐፍት የኦሮሞ መንፈስ አህታዊነት በሚመለከት እምብዛም አለመሆኑን ሲጽፉ እዬተከታተልኩኝ አነብ ነበር። የቄሮም
የረጅም ጊዜ ትግል የተወሰነ አካባቢ ብቻ ነበር። አሁን እነሱ የሰሩት ድንቅ ነገር አህታዊነቱን በአጭር ጊዜ በሥነ - ልቦና አቅም
አጎልብተው ጭምር አስተሳስረውታል። የአርሲ፤ የወለጋ፤ የሽዋ፤ የኢሊባቡር፤ የባሌ፤ የከፋ የሀረር እንዲህ የሚል ነገር ነው የነበረው።
አሁን ግን ቃለ ምልልሶችን ሳዳምጥ ግርም የሚሉ የጥንካሬ ውህደት ይታያል። ይህም 40 ዓመት ያልነበረ አሁን መሬት ላይ የታዬ፤ ግርማ ሞገስ ያለው የተግባር ማሳ ነው። አዬህ ሰው ሰብስቦ ማናገር እና አለማናገር ጠቀሜታውን በዚህ መለካት ትችላልህ፤ …
አሁን ግን ቃለ ምልልሶችን ሳዳምጥ ግርም የሚሉ የጥንካሬ ውህደት ይታያል። ይህም 40 ዓመት ያልነበረ አሁን መሬት ላይ የታዬ፤ ግርማ ሞገስ ያለው የተግባር ማሳ ነው። አዬህ ሰው ሰብስቦ ማናገር እና አለማናገር ጠቀሜታውን በዚህ መለካት ትችላልህ፤ …
„Ethiopia:
ክቡር ፕሬዝዳንት አቶ. ለማ መገርሳ በሚሊየም አዳራሽ ወገን ለወገን ደራሽ“
ሌላው ስለ አቦ ለማ መገርሳ ወጣቱ ምን ያህል
አክብሮት እንዳለው እዬው፤ ይህ እንግዲህ አዲስ አባባ ነው። አዲስ አባባ የሁሉም ለሁሉም ከተማ ናት፤
- · ተደማጭነት ስለመቀነስ - ሌላ ስጋት።
እርግጥ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ብዙ ፈተናዎችን ሊያዘጋጅ ይችላል፤ አሁን ነጥሎ እሳቸውን ብቻ አንዲቀርቡ ያደረገበትም ሌላ መሰሪ ነገር ሊኖርበት ይችላል። ግን ለእኛ ለቅን ኢትዮጵውያን „ከኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ በላይ ሌላ ኦክስጅን አያስፈልገንም። ተልዕኳቸውን በተስማሚው ጊዜና ወቅት ለዛውም አማራ መሬት ላይ የልባችን አድርሰውልናል። ቦታው ራሱ የጣና ገዳማት ቅዱሳን ጸሎት የፈጸመው ድንቅ ታምር ነው። የግዮን ገደል።
ለቅኖች እንደ መንፈስ ቅዱስ ጸበል አድርገን ቆጥረነዋል። ስንት ጥቃት እና ስንት መስቃ በሰማው ጆሯችን በአባቶቻችን እና እናቶቻችን መሃከል ተገኝተው ራህባችን ጥማችን ፈውሰውታል። ወያኔ ሃርነት ትግራይ ካልደከመው የፈለገውን ያሲር፤ ማንም ምንም ሃይል ከአቦ ለማና ማተባችን የሚለዬን የለም - ለቅኖች። የ40 ዓመቱ የፖለቲካ ድብብቆሽ ጨዋታ እኮ ከሞቱ አሟሟቱ ነው የሆነው። ድቅቅቅቅቅ ነው ያለው።
ከዚህ በላይ ሌላ የምሥራች ቀን አንጠብቅም እኛ - የልደት ቀናችን ነው። አሁንም እኮ ሚዲያውን የተቆጣጠረው የእሳቸው አድናቂ ነው። ሰውም ጋር ስትነጋገር ይሄው ነው አጀንዳው። ስታነብ ይሄው ነው። ዘመን ጥሩ ነው አማራን የሚወድና የሚያከብር ሊሂቅ እኛ በህይወት እዬለን ተፈጠረ። ይገርማል። ተመስገን እንጂ ሌላ ከቶ ምን ይባላል። ምንስ ይከፈለዋል ለሰማዩና ለምድሩ ንጉሥ።
- · የእስረኛ አፈታት ላይ የአማራ ተጋድሎ ቀርተው ኦሮሞዎች ቢፈቱ …
ደስ ይለናል። አንድም ልጅ ደስ ብሎት ይደር።
አንዲት አንስት ደስ ብሏት ትደር። እንዲት እናት ጎንበስ ብላ እንደ ዕምነቷ አምላኳን ታመስግን - ትሳቅልን። የፊት የፊቱን ይላል
ጓያ ነቃይ። ዛሬ ኑሮው ውድ ነው።
ትራንስፖርቱ ችግር ነው። የአንድ ነፍስ ቤተሰብ ከዚህ ከወጣ ለእኔ በግሌ ትርፍ ነው። ያው ከወያኔ ሃርነት ትግራይ የሚጠበቅ ብዙም የልብ የሚያደርስ ነገር አይኖርም - ተኖረበት እኮ።
በሌላ በኩል ምን ኢትዮጵያ እስረኛ እኮ ናት። አንተም እራስህ እስረኛ ነህ። እዛ እያለህ ትንፍሽ አትልም ነበር። አሁን ኢትዮጵያ ብትናፍቅህ ብድግ ብለህ ተነስተህ መሄድ አትችልም። ውጪ ሀገር ስበስሰባ ሲካሄድ የተሳታፊው ጀርባው ነው የሚነሳው። ስለምን? እስረኛ ስለሆን። አሁን የወያኔ ሃርነት ትግራይ እስረኛን ቢፈታ በእጥፍ ሌላ እስረኛ ያስገባል። በዬቤቱ እኮ እስር ቤት አለ። የቀድሞ የገበሬዎች አገልግሎት ህብረት ሥራ ማህበራት ሁሉ እስር ቤቶች ናቸው።
ስለዚህ አቶ ለማ መገርሳ የራሳቸውን ብሄረሰቦች አስፈትተው የእኛን አስቀሩ የሚል ዕሳቤ ይኖራል ብለህ አትሰብ። ይሄ የልጆች ጨዋታ ነው። ሁላችንም እስረኞች ስለሆን። የአቶ ለማ ኢትዮጵያዊነት ለቅኖች ቅደመ ሁኔታም፤ በፐርስንት በመደርደር የቁጥርም ተማሪ መሆንን አንፈቅደውም። ስለምን? ቀናተኞች ስላልሆን። የቅናት ቅንቅን ስላልበላን። ወንበርም ህልማችን ስላልሆን - ውስጣችን ናቸው። ጸሎታችንም ናቸው።

- · ኮ/ደመቀ ዘውዴ መፈታት መደራደሪያነት መላመት።
ከዚህም አልፎ ብሄራዊ ጉዳይ፤ ብሄራዊም አጀንዳም ነው። አልሰማህምን ሲዳሞ ተወልደው ያደጉት ፕ/ ዶር. ዳንኤል ተፈራ አጀንዳቸው ነው። ከዚህ ሌላ የትኛውም መንግሥት ይፈራረቅ ቦንብ ነው። ይህ ጥያቄ ሳይመለስ ሰላም በኢትዮጵያ ይስፍናል ተብሎ አይታሰብም። አፈር ነፍስ፤ አፈር ደም፤ አፈር ህይወት፤ አፈር ኑሮ ነው።
የአርበኛ የፊታውራሪ መለሰ ሃይሉን አደራ በልቶ የሚተኛ አንድም የአማራ ልጅ አይኖርም። ማን በዚህ ይደራደራል። ጎንደሬ በጋሻውን አንብብ ከቻልክ … ስንት የደም ግብር አርበኛ ሴቶች ሳይቀሩ አንደተከፈለበት።
ስለዚህ የወልቃይትና የጠገዴ የአማራ ማንነት የኮሜቴ አባላት በወልቃይትና በጠገዴ ጉዳይ የመወሰን
ስልጣኑ የላቸውም። መብታቸውም አይደለም። የሚደራደሩበትም አይደለም። በደም ድርድር የለም። በማንነት ድርድር የለም። እስከ ዕድሜ
ልክ ጦርነቱ ይቀጥላል። ረመጥ ነው። አይበርድም። ይህን ስለማታውቁ ነው „የነፃነት ሃይል“ እያላችሁ ባለፈው ዓመት ጥያቄውን መረጋጋጫ
ያደረጋችሁት።
ትግሉ እንዲደናገጥ አድርጋችሁታል። እንቅፋትም ሆናችሁታል። የወያኔ ሃርነት ትግራይ የልብ ልብ አግኝቶ የሰላም ኮንፈረንስ አንዲያጋዘጅ ያደረገውም መሰረታዊ ምክንያት አሱ በጠመንጃ እናንተ ደግሞ በፕሮፖጋንዳ ስለታገላችሁት ነው። ግን ቀጣይነቱን በእርግጠኝነት ነው የምነግርህ … ሁለት ትውልድ አልቆ ሦስተኛው ትውልድ ተተክቷል … ይቀጥላል … እዬፋመ …
እዬጋመ የሚሄድ ነበልባል ነው … ማንነት አይሸመትም ወይንም አይቀናም። አዬህ በዛ ዘመን ትምርት ቤት ሳንገባ ነበር ጉልማ መሬት የነበረን። ሰሊጡ ተሽጦ ባንክ ይቀመጥልን ነበር ገንዘባችን። ዘመናይ ኑሮ ነበር። መሬት ቢሉህ ዝም ብሎ መሬት አይደለም። የነጭ ወርቅ መሬት ነው። ሥራ ባህሉ ብቻ ሳይሆን እጅግ ስልጡን ማህበረሰብም ነው። ትንሽ ስታሾፍበት ሳይህ ገርመህኛል። ታሪኩን አታውቀውም። ቤተሰቡንም እንዲሁ። አንድ ወጥ ዘር ነው። ፍቅሩም መሬት ላይ ሳይሆን የሰማይ ጸጋ ነው። ቤተሰቡ በሙሉ ርጥብ ነው - አዱኛማ ነው።

- · የጥምረት ዕሴት።
እስረኞችን በሚመለከት የወያኔ ሃርነት ትግራይ
ፈታም አልፈታም የአቶ ለማ መግርሳ ብቻ ግዴታ አይደለም። የሚችሉትን ሁሉ አድርገዋል። አቶ ለማ መገርሳ፤ ዶር. አብይ አህመድ፤
አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና ዶር. አንባቸው መኮነን። በአጋጣሚ ከዛ የተፋለሙትን ሁሉ እከሌ ተከሌ ሳይባል አመሰግናቸዋለሁ። ምን ያህል ጦርነት
እንደ ነበር መግለጫውን ማደመጥ ይቻላል። ተቆራርጦ በቀረበው ውስጥም አቶ ለማ መገርሳ የሚሰጡትን የወያኔው መሪ ይጥሱታል እዛው
ላይ። ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ።
ከድንጋይ ላይ ውሃ ማፍሰስ ነው። „ተማመን“ የሚለው አልተማመኑም። „ጥገኞችን ድራሻቸውን እናጠፋቸዋለን ነው“ የሚሉት ዶር. ደብረጽዮን ገብረሚኬኤል። እራሱ ቃለ ምልልሱ የደምሂቱን አቶ ሞላ አስገዶም እንዴት ተምልሶ መጣ ያሰኛል። እሚያያዝ ነገር አኮ ነው የጣፋው የተበተከ ጉድ። የሆነ ሆኖ ከነዚህ ሰዎች ጋር መቼውንም መግባባት የሚቻል አይመስለኝም። አሁንም ጫካና ጉድጓድ ውስጥ ነው ያሉት።
ዘመን ጥሏቸው አልፏል፤ እንሱ እንኳንስ አብረው ሊጓዙ ዘመን ጥሏቸው ማለፉን እራሱ አላወቁትም። ሥነ- - ዐዕምሯቸው የመቀበል አቅሙ ብሎኑ ወልቋል። አሁንም ጉባኤቸው ሲደናቆሩ ከርመው ነው የሚወጡት። እርግጥ ኦህዲድን ለመፎካከር አዳዲስ ምላጭ የትግራይ ወጣቶችን ይዘው ብቅ ሊሉ ይችላሉ።
ግን ተፈጥሯዊነት በፋደሰበት ሰብዕና የሚጨመርም፤ የሚቀድም፤ የሚልቅም መንፈስ ማግኘት አይቻልም። የተጨማተረ ጉዞ ነው። የተመረዘ መንፈስ ነው። መንገዱም መንፈሱም ብኩል ነው የነፈሰበት። ይልቅ የእስረኞች ጉዳይም የሚጠበቀውም እነ ጌቶቹ ጉዳያቸውን እስኪከውኑ ይሆናል። ካልተስማሙ ይሆናል፤ ከተስማሙ ግን እጥፍ መከራ ይጠብቃል።

ሌላው የአቶ ለማ መገርሳና የዶር. አብይ አህመድ
ማድመጥ፤ መመራመር የሚገባው አብሯቸው ያለውን ቅዱስ መንፈስ ጭምርም ነው። ይህ ቅዱስ መንፈስ መጠነ ሰፊ አቅም አለው። ይህ አቅም
በአንድ ጀንበር የተፈጠረ ሳይሆን በክህሎት የበፀገ ነው። ይህ አቅም ሰሞናት ያበቀለው የጌሾ ቅጠል አይደለም፤ እንዲህ ማንም እንዳሻው
የሚሸመጥጠው። ወይንም በትውስት ማንነት የበቀለ አይደለም። በታመነ ብቃት ሂደቱን ጠብቆ ዳብሮና ጎልምሶ የሰበለ ነው ተከድኖ የቆዬ
ሲሳይ ነው። ቅብዕም አለ ይህን አትርሳ።
- · አንኳር የተጋድሎ መድረክ።
„ልብ የሚነካ አስገራሚ ንግግር Dr abiy ahmed # mind set“
- እጅግ የማከብራችሁ የሀገሬ ልጆች ቅኖቹ -
አሁን ዶር አብይ አህመድ ንግግር እና የጋዜጠኛ ኤርምያስ የእፍታ ሙግት፤ አንዲሁም ጹሑፍን ፕሪንት አድርጋችሁ ከቻላችሁ ፊት ለፊት እስቀምጣችሁ ትሟገቱበት ዘንድ ሙሉውን ጽፌዋለሁ። ሁለቱንም ቁጭ አድርጉና መዝኑት። ሚዛን ለራስ ነው ይላሉ ጎንደሮች ሲተርቱ … ከእነሱ እራስ ሊወርድ አልተቻለውም። በዬተራ ይደስቃቸዋል። አሁንማ በፈረቃም ሆኗል።
ወያኔ ሃርነት ትግራይ በተደራጀ ሁኔታ ከሚታገላቸው በላይ እጅግ በከፋ ሁኔታ ማህበራዊ ሰላማቸው እና ሥነ - ልቦናቸውን እያጨናነቋቸው ነው። ወያኔ ሃርነት ትግራይ አንዚህን የተስፋ ማህደሮች ልቅምቅም አድርጎ የካቴና እራት ቢያደርግላቸው ይወዳሉ። ያን ጊዜ ስለት ያስቋጥራል።
ለዛውም ሚዛኑን በድፍረት እና በፋክት አስደግፎ የሚሞግተው የፋክት አከርካሪ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና አቋምን በሚፈትን መልኩ። የትኛው ቅን ጋዜጠኛ የትኛው ደግሞ የምቀኝነት ፊታዋራሪ እንደሆነ ለኩት። ይግርማል ትንፋሽ ተገኘ ተብሎ ይህን ያክል ያዙኝ ልቀቁኝ ማለት … ትዝብት ነው። ምን አለ ትንሽ ነፍሳችን ቢገባ።
የሚገርመው ሆኖ በማያውቅ ሁኔታ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ደጋፊዎች ሳይቀሩ በዶር አብይ አህመድ ጎን በመቆማቸው ምክንያት ከሁለት መከፈላቸው ምን ያህል የዶር አብይ አህመድ የርቀት ምናባዊ ጉዞ ጥልቀቱ እንደ መሰጣቸው ምልክት አይደለም የቅንነት ዋዜማ ነው ለነገ የፍቅር ትውልድ…
- · ቃል እና ጉልበቱ። ከንግግር ጥበብ አንጻር በዶር አብይ አህመድ እይታ።
- ይህንን አባባል ዶር አብይ አህመድ እንዲህ ይሞግቱታል …
„ ሃሳብ መሆኑ የሚታወቀው በቃል ሲገለጽ ነው። ቃል ካልወጣ በአእምሮ ውስጥ ብቻውን ቢብሰለሰል ሃሳብ ሊሆን አይችልም፤
ቢሆንም ለባለቤቱ ብቻ ነው የሚሆነው። ቃል ጉልበት አለው። ይተክላል፣ ይነቅላል። ትውልድ ይፈጥራል፤ ትውልድ ያጠፋል።ፍቅር ይዘራል
ጥላቻን ይዘራል። በቃል ውስጥ ብዙ መማር ብቻ ሳይሆን፤ ሐገርንም መሥራት ይቻላል።
ኢትዮጵያ የፈረሰችውም የተሠራቸውም በቃል ስለሆነ። ሁለቱንም ነገር ለመለማመድ እንደዚህ ዓይነት ፓብሊክ ስፒች ሰዎች ሃሳባቸውን ኦርጋናይዝድ አድርገው ለብዙሃን ሸር የሚያደርጉበት መድረክ ማግኘት ለእኛ ትልቅ ዕድል ነው።
ምዕራባውያን ከጥቂት ምዕተ ዓመታት በፊት ከፍ ያለ ቦታ ላይ ሆኖ በርከት ላለ ሰው ሃሳብን ማከፈል፤ የዕምነትም፤ የፖለቲካም ሌላም ፍልስፍና ሊሆን ይችላል ከፍ ያለ ቦታ ሆኖ በሚያምር ድምጽ ለብዙሃን ሃሳብን ማካፈል የተለመደ ልማድ ነበር።
ያ ልማድ ጠቅሟቸዋል። ዛሬ ምዕራብውያን በዬትኛውም መድረክ ሳይቸገሩ ሃሳባቸውን ያካፍላሉ፤ እኛ ደግሞ ሳንቸገር እናማለን። ሃሳብን እንደፈለግን ለመናገር ማህበረሰቡ ልምምዱ እንብዛም ስለሆነ። „

ከንግግር ጥበብ ሥርዓተ ትምህርት ዋና አናቱ ላይ
ነው የተነሱት። ለምሳሌ በፊውዳሊዝም ንግግር የጨለማ ጊዜ ይባል ነበር። ስለምን? ብዙሃኑ ታዳፍኖ ጥቂቶች ብቻ ጎልተው እንዲወጡ
ስለሚፍቅድና ያም የታፈነ ስለነበር። ካፒታሊዘም ማቆጥቆጥ ሲጀምር ደግሞ የንግግር የብርሃን ዘመን ይባላል። በደርግ ጊዜ በዬካቲት
66 የፖለቲካ ኢንስቲቲዩት ለ40 ሰዓት ለ20 ፔሬድ ትምህርቱ እንደ አንድ መደበኛ ትምህርት ይሰጥ ነበር። መፈተኛውም ከባድ ነበር።
- · እውቀትና ሥልጣኔ በዶር. አብይ አህመድ እድምታ፤
ለዚህ ነው ሰው ኢትዮጵያን ሸሽቶ ሊቢያ ላይ የሚሞተው። ያለንብትን ነገር ገሃነም የሚያደርገው የምናይበት ዕይታ ብቻ ሳይሆን የሰውን ዕይታ ለማድመጥ፤ ለመካፈል የምናደርገው ዝግጁነትም ጭምር ነው። ሰይፍ መቅላት የሚችለው ሥራውን ማከናውን የሚቻለው/ የሚችለው በሸካራ ሞረድ የተሳለ እንደሆነ ነው።
ሸከራ ሞረድ ከሌለ ሰይፍ የሚል ሥም አለ ግን መቅላት አይችልም። ሰውም አመለካክቱ የማያ መነጸሩ የሚስተካከለው በእውቀት ነው። በየዕለቱ በሚያገኘው ዕወቀት ሰው አመለካከቱን እዬተገራ፤ እዬተቀረጽ ሙሉዑ ሰብዕና እንዲላበስ ያስችላል። ስለዚህ ዕውቅትን ሳንሸሽ፣ ሳንፈራ፣ ሳንጠዬፍ ለመፈለግ የምናደርገው ጥረት መሳኪያው መንገድ አካዳሚያ ብቻ ሳይሆን ፓብሊክ ስፒችም ጭምር ነው።
ይህን ጉዳይ ደግምን ዳጋግመን ማሰብና መነጋገር ብቻ ሳይሆን አስፈላጊነቱን ማስፋት የሚያስፈልገው ከፍተኛው ችግር የእውቀት ባላቤቶች ብቻ ሳይሆን ዕወቀትን የሚያሰራጩበት ዓውድ አለመኖርም ጭምር ነው።
እንግዲህ ዕውቀት በወጣትነት ዘመናችን አቅጣጫ የሚያመላክት፤ ተስፋ እንድንሰንቅ የሚያደርግ ነው። ዕውቅት ያላቸው ሰዎች ነገን ለመሥራት ዛሬ ይተጋሉ። በጉልምስና ወራት ደግሞ ራሳችነን ቤተሰቦቻችነን እንድናስተዳደር ገንዘብ ጄነሬት ማደረግ አንድንችል ያግዘናል። በሽምግልና ወራትም ምርኩዝ ይሆናል። የማያዋቁ ሰወች ላይፋቸው ሚዘረቭል የሚሆነው ሲጨርሱ ብቻ አይደለም፤ ሲጀምሩም ጭምር ነው። መጀመሪያም በወጣትንት ዘመን ለጫት የምናጠፋው ጊዜ እና ለመጸሐፍ የምናጠፋው ጊዜ ባላንሱን ከሳተ፣ ከዛ የጀመረ ብልሽት ይዘልቅና መጨረሻችንም አደገኛ እንዲሆን ያደርገዋል።“
ይህ ነገን ያደመጠ የትውልድን ችግር የእኔ ያለ
ጥልቅ ንጥረ ነገር ነው ጋዜጠኛ አርምያስ ለገሰ ከአቶ ለማ መገርሳ ራስ ወርዶ ወደ ዶር አብይ አህመድ ዞሮ ደግሞ አዲስ ዘመቻ የከፈተው።
„ዕውቀት መስጠት ማካፈል ብቻ ሳይሆን በወጉ መደራጀት አለበት። ዕውቀት በወጉ የሚደራጅበት
በርካታ መንገዶች አሉ። እነሱን አልዘረዝርም። ነገር ግን እነሱ ሲሟሉ ስልጣኔ የሚባለው ነገር ይመጣል። ኢትዮጵያ ጨዋ አገር እንደሆነች
በተደጋጋሚ ይነገራል። ኢትዮጵያ ግን መኪና ውጪ ማሳደር አይቻልም። ከጨዋነታችን ብዛት መኪና ውጪ ረስተን የገባን እንደሆነ ስንመለስ
ስኮፕዮስ ስለማናገኝ ማለት ነው። ስልጣኔ ማለት ከዚህ ይጀምራል። ያለፋህበትን፤ ያልደከምክበትን ነገር አለመፈለግ። ስልጣኔ ያለፋህበትን
ካለመፈለግ ይጀምራል።“
አዬህ በዚህ ውስጥ የአማራን የተጋድሎ ታሪክ ብታዬው ደስ ይለኛል ጋዜጠኛ ኤርምያስ ለገሰ። በዕውነት እና በሸፍጥ መካከል ያለውን ልዩነት ለማተብህ ብለኽ አስተውለው። የሰው መንፈስ በትእዛዝ አይገዛም፤ በዘረፋም አይወረርም። ትርፉ ከባህር የወጣ አሳ ነው የሚያደርገው። የገንዘብ ጉዳይ አይደለም፤ ይህ የሥነ - ልቦና ጉዳይ ነው። በዚህ ውስጥ የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር መቅኖ አጥቶ መቅረትም እንደ ፖለቲካ ተንታይነትህ ራስህን ሞግተው። „ስልጣኔ ማለት ከዚህ ይጀምራል። ያልፋህበትን፤ ያልደከምክበትን ነገር አለመፈለግ።“
በዚህ ቃጠሎ በሽታ ላይ ስንት ሰው ወድቆ ይሆን? ወገኑን የገበረ ሁሉ። ትዳሩን የፈታ ሁሉ። ሞፈር ቀንበሩን የሰቀለ ሁሉ። ልጁን የትሜና የጣለ ሁሉ … እህህህህ …

- · ሥነ - ሰላም ለዶር አብይ አህመድ ዕሴቱ …
ይህን ቅንነት፤ ይህን አርቆ አሳቢነት ከቶ ምን ትለው ይሆን? ስላቅ ታሸከመው ይሆን? ወይንስ በጀመርከው ሰላምን የማወክና የማጨናነቅ ተግበርህ ትቀጥል ይሆን? ዘመቻው በዛ እጅግ በዛ … ፋታ ነሳሃቸው።
- · ዕውቀት እንደ ላም ናት። ጡትም ቀንድም አላት።“ ከዶር አብይ አህመድ።
ከእውቀት በስተቀረ። ለእውቀት በቂ ኢንበስትሜንት ማውጣት ዝግጁ ስላልሆን በመሃይምንት ለእነሱ ባርያ ለመሆን እንገደዳለን ማለት ነው። ስለዚህ በማወቅ ውስጥ ያለውን መልካም ነገር ማጨት አስፈላጊ ነው። ዕውቀት እንደ ላም ናት። ጡትም ቀንድም አላት። E = MC² ሄሮሽማ ላይ ሲወድቅ ቀንድ ነው። መብራት ሲያመነጭ እና ለኢነርጂ ሲውል ደግሞ ጡት ነው። እንዴት ነው የቀንድን አደጋ ተከላክለን እያለብን መጠቀም የምንችለው የሚለው ጉዳይ እንደ ግለሰብ እንደ ማህበረሰብ፤ የምናስበብት፤ የምንደክምበት ጉዳይ መሆን አለበት። ያወቀ ሁሉ ያለማል ማለት ስላልሆነ።
ዕውቀት ለልማት፤ ዕውቀት ለውጤት የሚቀዬርበትን ነገር መፍጠር በእጅጉ ያስፈልጋል። አሁን ባለንበት የኖሌየጅ ኤጅ ዕውቀት ተሎ ተሎ ያረጃል። ዛሬ ይፈጠራል ነገ ያረጃል። የሚያረጀው ግን ለማያወቁት ነው። ለሚያውቁት መሠረት ነው የሚሆነው። የትናንትና ዕውቀት አዲስ ዕውቀት ሲጨመር ለዛሬው መሠረት ሆኖ ነው የሚያገለግለው። ለሚያውቁ ሰዎች።
ለማያውቁ ግን ሊያረጅባቸው ይችላል። በዬዕለቱ ማወቅ የሚያስፈልገው ባቡሩ ፈጣን ስለሆነ ነው። አሁን ባለው በኖሌጅ ኤጅ ለመጓዝ በዬዕለቱ መድከም በዬዕለቱ መልፋት እና ዕውቀትን ማደርጀት የማይችል ግለሰብም ይሁን ማህበረሰብ ባቡሩ ፌርማታ አይጠብቅም። እንቅስቃሴ ላይ እያለ እያወጣ ይጥላል። ልክ አሁን ኢትዮጵያን ከዓለም ጉዞ በከፍተኛ እርቀት አስፈንጥሮ እንደ ጣላት። ማለት ነው።“
ከዬትኛውም ወገን ለመማር ዝግጁ መሆን የቅንነት
ጉዳይ ነው። ማድነቁ ማክበሩ ቀርቶ። ይሄን ልቅና ነው በሽታሽቶ እዬተፋለሙት ያለው። አለመሳጠጋት መብት ነው። ግን የሃሳቡን የቅንነት
የውስጥ ሰላማዊ መንፈስ ማወክ ከቅናት ውጪ ሌላ ሊባል ከቶም አይችልም። በኢትዮጵያዊነት ውስጥን የረጋና የሰከነ መንፈስን ነው እዬተፋለሙት
የሚገኙት። ከቶ ከምን ይመደቡ?
- · ትንፋሽና ዕውቀት በዶር አብይ አህመድ ህሊና።
በትምሀርት ወይንም በህይወት ይፈተናል። በትምህርት ስንፈትን ቢያንስ 50% ሰኪዩር ነው። ቴክስት ቡኩን እናውቀዋለን፤ ያነን ያነበበ ሰው 100 እንኳን ማምጣት ባይችል፤ 50 ሊያመጣ ይችላል። በህይወት ስንፈተን ግን ያልተዘጋጀን እንደሆነ አንዳንዴ ዜሮ የመሆን ዕድል አለው። ያ ፈተና የማያመልጥ መሆኑን አውቀን እራሳችን ማዘጋጀት እና ከችግር በላይ ለመሆን የሚያስችለን ደግሞ እንደዚህ ዓይነት መድረክ ሲዘጋጅ መጀመር ብቻ ሳይሆን በመጨረስ የዕውቀትን ዋጋ በማሳደግ ነው።“
ይገርማል። ለዚህ ብልህነት ነው ጋዜጠኛ ኤርሜአስ
ለገሰ ዲሲ ላይ ሆኖ መርሃ ግብር የሚነድፈው።
„… መንጠባጠብ ካለ ዕውቀት አይደረጅም ማለት ነው። ይጀመራል ግን አይደረጅም። ካልደረጀ ደግሞ የሚጠበቅበትን ግብ አያሳካም።
ንስር አሞራ በሰማይ ካሉ አሞራ ሁሉ የተለዬ ባህሪው፤ ዝናብ ሲመጣ ሁሉም የዐዕዋፋት ዘር መጠለያ ይፈልጋሉ። ይደበቃሉ። ንስር አሞራ
ግን ዝናብ ሲይ ከደማና በላይ ጥሶ ያልፋል።
የዝናብን ምንጭ ወደ ታች ነው የሚያው። የችግርን ምንጭ ወደ ታች ማዬት እስካልቻልን ድረስ ማህበረሰብ አይሸጋገርም። ማንኛውም ችግር ሲነሳ ከችግሩ በላይ ሆነን ወደታች ችግሩን ማዬት፤ አንደሚያልፍ ማወቅ፤ ያን ለማሳለፍ የሚያስችለውን ድልድይ ደግሞ ዕውቀት አንደሆነ ማሰብ በእጅጉ ያስፈልጋል።
ከእውቅት ጋር በቀጥታ የሚያያዘው ጉዳይ አቲቲዩድ ነው፤ አመለካካት ነው። ይህን መድረክ እያንዳንዱ የመጣ ሰው እንዴት ነው የሚያው? ከዚህ በኋዋላ የሚኖረው ሌክቸር ሚዲያዎች አንዴት ይገለገሉበታል? የምናይበት መነጸር ትከክለኛ የሆነ እንደሆነ ዕወቀት እና በጎ አመለካከት ሲደመሩ ማህብረሰብ መቀዬር ይቻላል፤ ጨለማን ብቻውን መተቸት ግን ብርሃንን አያመጣም፤ ክፋትን መኮነን ደግነትን ሊሆን አይችልም። ኋላቀርነትን ማጥላላትም ሥልጣኔን ሊያመጣ አይችልም።
ጦርነትን መፍራትም ሰላም ሊሆን አይችልም። ራህብን አለመፈለግ፤ መጠዬፍ ጥጋብ ሊያመጣ አይችልም። ችግሩን መዋቅ አልትሜቴሊ መዳህኒት ነው ማለት አይደለም። ችግሩን በአወቀ አዕምሮ መፍትሄ ማፈላለግ በእጅጉ ያስፈልጋል።“

ሃሳቡ ጥልቅ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ተቋምም ነው።
የኖርንበትን የችግር አረንቋ ከውስጡ እያላሰለሰ የተካነ። የመፍትሄውንም ኣቅጣጫ ያመለከተ ብቻ ሳይሆን ጉልበት የፈጠረ ነው። ይህ
እንግዲህ ከአንድ ዓመት በፊት የሳይንስና የቴክኖሎጂ ሚ/ር በነበሩበት ጊዜ ዶር አብይ አህመድ ወደ 1000 ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን
መንፈስ በቅናዊ ሃዲድ ለማስተሳሰር ያደረጉት ንግግር ነበር።
የሃሰብ ፍሰት እና ትሩፋቱ ወቄቱ በዶር አብይ
አህመድ ተደሞ፤ „ሃሳብ ይፈስስ! ሃሳብ ይለምልም!“
„አመለካከታችን የተስተካከለ እንደሆነ፤ ለዕወቅት ቦታ የምንሰጥ እንደሆነ፤ እራሳችና አክብረን፤
ሰው የምናከብር ከሆነ ይህ ጅማሮ፤ ይህ አቲቲዩድ ብቻ ሳይሆን፤ ፖለቲካም የምንናገርበት፤ ኢኮኖሚም የሚነገርበት፤ የብሄር ጉዳይ
የሚነገርበት፤ ሃሳብ የማይፈራበት ግን ደግሞ ድንጋይ የማይወረወርበት ይሆናል። ለእኛም ባይሆን ለልጆቻችን መልካም ኢትዮጵያን እንድንተው
መሠረት ይሆናል። እንደዚህ ዓይነት ነገር ሲጀመር መዝለቁን እና ውጤቱን ብዙ ሰዎች ይጠራጠራሉ።
ዛሬ ልናገር የምፈልገው ሃሳብ በቆሎ በሳይንስ ከጤፍ ገዘፍ ትላለች፤ ወፍራም ናት፤ እረዘምም ትላለች፤ እና ጤፍን ወደ ታች እያዬች አሁን ሰው በከንቱ ይደክማል እንጂ ከጤፍ ማህጸን እንዴት ዱቄት ይወጣል ብሎ ይደክማል ትላለች። ያው ኢጎ እና አብሪት ዕወቀት በሌለበት ሁሉ ስላለ ማለት ነው። ነገረ ግን አንድ ኩንታል ጤፍ ወፍጮ ቤት ስትወስዱት የተሻለ ዱቄት የሚገኘው በጤፍ ውስጥ ነው።

ዛሬ በጣም ጥቂት ሰው የሚመስል
1000 አንደ ሽህ ሰው በጣም ትንሽ ነው ጅማሮ ነው። ይህ ጅማሮ ግን ዘልቆ የኢትዮጵያን መጻኢ ሁኔታን አዳዲስ ሃሳብ የሚፈልቅበት፤
መነጋገር የማይፈራበት፤ በንግግር ውስጥ ማማር አንዳለ፤ እውቀት የሚገበይበት፤ ለመከራከር ለዲቤት ሳይሆን አርጊው ለማድረግ፤ ሰጥቶ
ለመቀበል የምንዘጋጅ ትውልድ እንደንሆን ያስችላልና። ይህ ጅማሮ እንዲቀጥል ሁላችሁንም ዛሬ ያሳዬነውን ኮሚትሜንት ማስቀጠል አለብን።
ምንአልባት አንዳንዶቻችሁ ጠቀሜታው ዛሬ ይገባችሁ ይሆናል። አንዳንዶቻችሁ ሁለት ሦስት ሳምንት ሊወስድባችሁ ይችል ይሆናል። ግዴለም ዋጋ የተከፈለበት፤ የተደከመበት ነገር ውጤት ሊያመጣ ስለሚችል አብረን በመዝለቅ እንደዚህ ዓይነት መድረክ አስፈለጊ መሆኑን ለእኛ ቢቀር ለልጆቻችን፤ ለምንተዋት ኢትዮጵያ ለብዙዎች ትምህርት ስለሚሆን የሚዲያ ሰዎችም ከማስታወቂያ ባሻገር ሃሳብ የሚፈስበት፤ የማይገደብበት ልምምድ ዓውድ መሆኑን አስባችሁበት ከዚያ አንጻር አንድትሰሩ፤ የተገኛችሁትም ሰዎች ፈረንጆች እንደሚሉት እያንዳንዳችሁ አንዳንድ ሰው ኢንፍሎዬንስ በማድረግ እንደዚህ ዓይነት መድረክ ከተማችን ውስጥ አንዲሰፋ፤ እንዲያድግ ያ ሲሆን አሁን ያለው ውጥረት ሊረግብ እንደሚችል ነው የምገምተው። ጅማሯችሁ ያመረ ይሁን! ሃሳብ ይፈስስ! ሃሳብ ይለምልም! ከእያንዳንዳችን ትምህርት ይገኛል። በቆይታችሁ እንደምትደሰቱ ተስፋ አደርጋለሁ አመሰግናለሁ።“

አዬህ „ዕለታዊ“ አይደሉም የምልህ ለዚህ ነው
ጋዜጠኛ ኤርምያስ ለገሰ። እሳቸው የሚደክሙበት በማግስታዊነት ላይ ነው። በተለይም በሃሳብ ነፃነት፤ አንተ ይህን መንፈስ የመምራት
አቅምህ ምን ያህል ይሆን ወቄቱ እስቲ ለካው? ከራስህ ጋር ምክር? „ለልጆቻችን
ለምንተዋት ኢትዮጵያ ለብዙዎች ትምህርት ስለሚሆን“
- · ብቁነት።
ዬኦሮሞ እናት አንዲህ ዓይነት ብቁ ልጆችን መቼውንም
አትወልድም ዓይነት ነው ትግሉ። ይገርማል። ለሰብዕዊ መብት እምታዝን ቢሆን ኖሮ 26 ህጻናት በሱዳን ወታደር አንባ ጊዮርጊስ ላይ
የታጨዱበት፤ በአንድ አጋዚ 50 ነፍስ ባርዳር ላይ የጠፋበት፤ 20 ሺህ ወጣቶች በርሃ ላይ በእስር የተንገላቱበትን የአማራ ተጋድሎ
አብዮት የእኔ ተብሎ በግንቦት 7 ዘራፍ ሲባል ትሞግተው ነበር።
ያ ህዝብ ጦርነት የታወጀበት አማራነቴ ይከበር ብሎ ነበር። ይህ ነበር ሃቀኝነት፤ ይህ ነበር ዕውነተኝነት፤ „የነጻነት ሃይሉ“ እያልክ ልባችን፤ መንፈሳችን ከማቁስል ትቆጠብም ነበር። አዘኔታ ይኖርህ ነበር። በል መባልህን ሰምተናል። የወያኔ ማዕክላዊነት አውጋዢ አይደለህምን? ታዲያ ያን የመሰለ የአማራ ተጋድሎ በግፍ እና በማንአለበኝነት ሲዘረፍ ምነው አፍህን ሞልተህ የአማራ ተጋድሎ አላልከውም ነበር? ማዕከላዊነት ተጠያፊ ከሆንክ? አሻም በማምንበት ሃቅ ውስጥ ሞቴን ያድርገው ስለምን አላልክም?

- · ቂሎች አይደለንም። እንታዘበለን።
ከዛ በኋዋላ ሁለተኛ ጊዜ አልተደመጠችም። የውሃ ሽታ ሆና ቀረች። ቄሮ ለአምስት ቀን አስደማሚ የሥራ ማቆም አድማ መታ። ማህል ላይ ተንስታችሁ ለኢትዮጵያ ሠራዊት ጥሪ አቀረባችሁ። የሥራ ማቆም አድማው ቢቀጥል አዲስ አባባ ሊደርስ ይችል ነበር፤ ግን ማህል ላይ እናንተ ተሰነቀራችሁ፤ በሦስተኛ ቀኑ ቆመ። አሁን የኦሮምያ ጸጥታ አስከባሪ ሃይል ቄርወችን ሰላማዊ እስከ ሆኑ ድረስ ማዋከቡን አቆመ።
በሌላ በኩልም ጥቃት ሲፈጸምበት ደጀኑ ሆነ። ይህ ሲታይ ደግሞ ሠራዊቱን በሚስጢር እያደራጀነው ነው ተባለ። ባለፈው ዓመት ታዩናላችሁ በሽዋ፤ በጎጃም፤ በወሎ፤ በጎንደር ትግሉ ይቀጥላል ተባለ፤ ፉክክር ነው መቼም ከተያዘ ከተረዘዘው ጋር። ያው የአማራ ተጋድሎ እቅዱን ይሸበሽባል ተብሎ ስላልተገመተ፤ አሁንም ጸጥ ረጭ ሆነ። ቆመ። አሁን ይሄ ማንን ነው የሚጠቅመው? እስቲ ቁጭ ብለህ እንደ አንድ ብቸኛ ብሄራዊ ፖለቲካ ተንታኝነተህ ሒደቱን አዳምጠው። ሁሉንም ዝም የምንለው አክብሮቱም ስለነበረ ነው እንጂ ጠፍቶን አይደለም።
እንደ አንተ እኔም መሬት ላይ የፖለቲካ ድርጅት ቋሚ ሠራተኛ ነበርኩኝ። በሁሉም ዘርፍ ጣልቃ ባይገባበት የህዝብ ተጋድሎ ምንአልባትም ዛሬ የተሸለ ደረጃ መገኘት ይቻል ነበር። ግን አልሆነም። ሲነግራችሁ አታዳምጡም።
አጋድመንም፤ ጫፍጫፉን ነካክተንም ተናገርን፤ ጻፍን ግን አልሆነም … ቢደመጥ ቢያንስ በመንፈስ መቃረራብ ይቻል ነበር … አልሆነም። አሁን ደግሞ ገና ኦህዲድ በህሊና ብቃት ኦርጅናል ሆኖ ሲወጣ የሥልጣን ተፎካካሪ ሆኖ ይወጣል ብለህ አንዳሻህ ባለሚዲያ ነህ ትደቃዋለህ። ብአዴን የሚባለው አስጊ አይደለም። ከዚህ አንጻር ነው የምታነሳቸው ነጥቦች የመነሻህን ሆድ ዕቃ የሚያሳዬን። ለማንም አይጠቅምም።
መከባበሩ ቢቀር መላ ቤተሰባቸው ሰላሙን አጥቷል፤ አንተ ደግሞ ተጨማሪ ጫና ፈጣሪ እና ወጣሪ አትሁን። እግዜሩም አይወደውም። እስር ውስጥ በዓይነ ቁራኛ እዬታዩ ነው ያሉት። ሰብዕዊነት ከዚህ ይጀምራል። ሰው አንዲህ ቅንነቱ ሲነጥፍ የነገ ነገር ከምንም ነገር በላይ ያሳስባል - ያስጨንቃል። ቅንነት ከሌለ ነገ ታሞ ብቻ ሳይሆን እሬሳውም አይገኝም፤ አጥንት ጉልጥምቱም የአመድ ራት። ከዚህ የምቀኝነት ማህበር ያልጨመርከኝ አምላኬ የተመሰገንክ ሁን። አሜን። ደህና ሰንብት።
- · ስለ ኢትዮጵያ የእስልምና ተከታዮች ስጋትነት፤
ይሄ እኔን ያደነቆረኝ ነጥብ ነበር። በአደባባይ
ደግፈናል፤ በጓዳ ደግሞ ስለምን „ድምጻችን ይሰማን“ ደግፈሽ ትጽፊያለሽ „የተሰወረ አጀንዳ አላቸው፤“ ወዘተ ወዘተ … ልቤን ከዚህ
ሲወልቁኝ ነበር። የሆነ ሆኖ ይሄ ስጋት ያለባቸው ቅን ወገኖችም ዶር አብይ አህመድ መድህን ስለመሆናቸው አብክሬ ልገልጽላቸው እውዳለሁ።
ድህረ ገፆችን ይጎበኛሉ፤ እና የጸሐፍትን መጸሐፍታቸውን በድህረ ገጹ በማስተዋወቁ ምክንያት ዲ.ዳንኤል ክብረትን በመድረክ በአደባባይ
አመስግነዋል።
ለአንድ ዲያቆን ድህረ ገጽ አክብሮት ብቻ ሳይሆን እዛ የሚወጡ ሃይማኖታዊ ጹሑፎችን ሁሉ ይታደሙባቸዋል። ለሃይማኖት አባቶች ያላቸው አክብሮት ልቅናው ከውስጥ ነው። አንዲህ ዓይነት ገጠመኝ፤ ታሪክም እኔ አይቼ አላውቅም። ሁለመናው ያሰበለ። አነጋገራቸው እኮ ወደ አቮው ያደለ ነው ረገጥ ሲያደርጉት „ድሮ በልጅነት በኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባቶች ዳዊት መድገም የተለመደ ባህል ነበር „ነበር ሲሉ“ ሊቃውነተ - ቤተ ክርስትያንን ነው የሚመስለው አነባበባቸው - ቃናው በራሱ።
ስለሆነም በኢትዮጵያ የእስልማ ዕምንት ስጋት የነበረባቸው ወገኖች ሁሉ ሃዲዱን በውስጥ ሰላም የሚያሰክን፤ የሚፈውስ አንዲህ ዓይነት ሥነ - ህይወት የሆነ ሊሂቅ ኢትዮጵያ አላት። የተረጋጋ መንፈስ አላቸው። የሰከነ ዕሳቤ ባለቤት ናቸው። የውስጥ ሰላማቸውን ለማጋራት የሚሄዱበት መንገድ ክህሎቱ የፋፋ ነው። ይመስጣል። በጎነትን ይሰጣል። ለቅንነት ንፉግ አይደለም። ያግባባል። እራስን ይፈትሻል። ህሊና። ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን። ይህ የፈጣሪ ሥራ ነው - ለእኔ።

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ
የተፈጠረ ሚስጢር።
"ሃሳብ ይፈስስ! ሃሳብ ይለምልም!"
(ዶር አብይ አህመድ።)
የኔዎቹ ለነበረን የመደማመጥ ማለፊያ ጊዜ እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ኑሩልኝ። ቸር ወሬ ያሰማን!
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ