መች ይሆን ጸሐይሽ?
?እቴጌ ኢትዮጵያ መች ይሆን ጸሐይሽ?
ሥርጉተ -
ሥላሴ 17.11.2017 (ሲዊዘርላንድ - ዙሪክ ።)
„የኃጢአያተኞችም ወገናቸው እንደ
ገለባ ክምር ነው። ፍፃሜያቸውም ለገሃነም ይሆናል።“
(መጸሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፳፩ ቁጥር ፱)
ስምጥ አሮጎ ይዞ ነፍስን ሲጎትተው
ቀኑ ተገትሮ ቁሞ ʼሚጠብቀው፣
ሌሊቱ ʼማይነጋው ጠፍር ተንትርሶ
በምሬት ተቀርፆ፤ በሀዘን ዳጉሶ።
እቴጌ ኢትዮጵያ መች ይሆን ሰናይሽ?
… እሜቴ ነፃነት እምትሳለምሽ?
የጠቡን ግድግዳ እዬመነዘረ
በኢትዮጵያ ጽናት እያመነዘረ፤
የጭንቅላት ካንሰር ትግራይ ላይ ጎልቶ
ፍቅር ኮሰኮሰ ልዩነት ጎልብቶ።
እቴጌ ኢትዮጵያ መች ይሆን ሰናይሽ?
… እሜቴ ነፃነት እምትሳለምሽ?
እጅግ ተንጠራርቶ በቅጥ ተንቦልቡሎ
ትዕቢት በትምክህት ጉሮ ሸባ ብሎ፤
ጥጋብ አገር ፈቶ እላፊ ዘልዝሎ
ማግስትን አራቁቶ፤ ፉከራው ቀጠለ /// ኧረ ዘራፍ¡ ብሎ።
እቴጌ ኢትዮጵያ መች ይሆን ጸሐይሽ?
… እሜቴ ነፃነት እምትሳለምሽ?
ድቃቂ አሽዋ በስርንቅ ተሠርቶ
ሽርክቱን ምናቡን በሰው ደም አርክቶ፤
በሳጥናዔል ግብር ህሊናው ተከቶ፤
ይታማሳል ሐገር፤ ይቆላል // ይፈጫል በፈንድሻ
ፈክቶ።
እቴጌ ኢትዮጵያ መች ይሆን ጸሐይሽ?
… እሜቴ ነፃነት እምትሳለምሽ?
ድርቀታማ ግራር በሟተት ተገምዶ
ዬቁልቋሉ ስሪት መኖርን ጎራርዶ፣
ማህበረ ሳዖል የሰው
ጭራቅ ዘንዶ፤
ትውልዱን አጨደው በጭካኔ ጎምዶ።
እቴጌ ኢትዮጵያ መች ይሆን እልፈትሽ?
… እሜቴ ነፃነት እምትሳለምሽ?
ታምሃል ይሉሃል „ጊዜ“ ታጥራለኽ፣
„ነገስ“ ትሆናለኽ?
ምሰህ ትምጣለኽ?
„በስትያስ“ ታስባለኽ? እንዴት ትሆናለኽ?
በዛሬ ውስጥ አልቀህ፤ በጭካኔ ወልቀኽ።
እቴጌ ኢትዮጵያ መች ይሆን እልፈትሽ?
… እሜቴ ነፃነት እምትሳለምሽ?
የግራዚያኒ ማገር ትግራይ ላይ ቆምሶ
ተበጠሰ ማተብ ፋሽስትን ቀድሶ።
ልብ የት ተፈጣረ? ለመሆኑ አለ?
የቅብጥርስ ጭቃሾኽ ገለባ እያለ።
እቴጌ ኢትዮጵያ መች ይሆን ማግሥትሽ?
… እሜቴ ነፃነት እምትሳለምሽ?
ሙሶሎኒ ልቡ ደም እንደ ጎረሰ
ቅሪቱን አውርሶ በሥሙ ነከሰ፤
በክብር ዘመነ ትውፊት ከሰከሰ
ዘመኑ ጠንዝሎ „ማረን“ ተከለሰ።
እቴጌ ኢትዮጵያ መች ይሆን ማግስትሽ?
እሜቴ ነፃነት እምትሳለምሽ?
ማህበረ - እርኩም፣ እረቂቅ ምስጣምስጥ ከፍሬ
ተዳቅሎ
አነቀዛት እሷን ውስጧነን ቀቅሎ፤
በማይጠፋ ነዲድ ሰብዕናን አክስሎ
ዐነባ ተፈጥሮ ድንኳኑ ተጓጉሎ።
እቴጌ ኢትዮጵያ መች ይሆን ትንግርትሽ?
?… እሜቴ ነፃነት እምትሳለምሽ?
·
ሥጦታ - ለኢትዮጵያ ዕንባ ይሁንልኝ። ተጣፈ
15.11.2017 (ዙሪክ - ሲዊዘርላንድ)
·
አንድ ለመንገድ - የልቤ አንተነህ የሆነ ጹሑፍ ሳተናው ላይ ስላገኘሁ የኔዎቹ ትታደሙበት ዘንድ በትህትና
እና በልዑቅ አክብሮት እንሆ …
„ጎንደር የተጠራው የወያኔ የማጭበርበሪያ ጉባኤ፥ ዶሮን ሲደልሏት በመጫኛ ጣሏት ነው – ጥሩነህ ይርጋ“
ምን „የማጨበርበሪያ“ ብቻ የማህበረ - ሽፍቶች፤ የማህበር - ሌቦች፤ የማህበረ - ዘራፊዎች፤ የማህበረ - ገዳዮች፤
የማህበረ - ሳዖሎች የማህበረ - ጥጋበኞች፤ የማህበረ - እርኩሞች፤ የማህበረ - ጃርቶች፤ የማህበረ - ወራሪዎች እንጦርጦስ እንጂ ///
አዶናይ ከመንበሩ ካለ - እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ