ዘመነኛዋ ትግራይ ግራጫ ጸጉር አላትን?
ለመሆኑ በብርሃን ጸዳል የተሽቆጠቆጠችው፤
ከሀገረ ቻይና እና ከብራዚል ጋር፤
ዓለምዐቀፍ ተሸላሚዋ
ዘመነኛዋ ትግራይ
ግራጫ ጸጉር አላትን?
ከሥርጉተ - ሥላሴ 31.10.2017 /ሲዊዘርላንድ - ዙሪክ።/
„ … እንሆም፣ ሁሉ እሾህ ሞልቶበታል፣ ፊቱንም ሳማ ሸፍኖታል፣
የድንጋዩም ቅጥር ፈርሷል።
/ መጽሐፈ ምሳሌ ተግሣጽ ምዕራፍ
24 ከቁጥር 30 እስከ 31/“
- እንደ በር።
በመጀመሪያ ጥናቱንና መቀነቱን
40 ዐመት ሙሉ በዕንባ ክርትት ለሚሉ ለኢትዮጵያ እናቶች እንዲሰጥልኝ አምላኬን እማጸነዋለሁ። በሥጋ የተለዩትንም ወገኖቼ ሰማዕትነታቸውን
ፈጠሪዬ ይቀበልልኝ ዘንድም እማጸነዋለሁ።
በማስከትል … ወደ ዋናው ጉዳዬ ከመሄዴ በፊት ግን የአዋዜ አዘጋጅ ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ የሰሞናቱን የአማራን የተደራጀና
የታቀደ ጭፍጨፋ አስመልክቶ የሠራው ዜና እጅግ ውስጥን የተረጎመ፤ ሩቅ አሳቢና መንገድ ጠራጊ ዕድምታ ስለነበረ እጅግ አድርጌ ላመሰግነው
ፈቀድኩኝ። ደፋር፤ ጥልቅ ትንታኔ
ነው። ቅርብ - ከሩቅ
ጥቃትን ያዋደደ ነው። ዓለም - ዓቀፋዊ ሰቅጣጭ የጭካኔ ዕውነታዎችን፤ ሁኔታዎችን በምልሰት
የቃኘበት መንገዱ ብጡል ነው። አማራ እኮ ሐገር አልባነቱ ተውጆበታል። የከፈለው ደም ከንቱም ሆኗል። ስለሆነም የአዋዜ የንጽጽሩ የአምክንዮ አቅሙ አንቱ ነው።
ለህሊና ቅድመ መሰናዶ
ልዩ ተቋምም ነው።
ለአማራ ሥነ - ልቦናዊ አኃቲነትም
በኲራት ነው። አጭር
ግን ልቅም ያለ፤
ልቁን የአማራን ዬዘር
ጥፋት ትልም በጥልቀት
የመረመረ፤ በስፋት ያስተዋለ፤
በውስጥነት የተቀበለ፤ የጉዳቱ
ልክ በአትኩሮት እንዲታይ
ፈር ቀያሽ የሆነ -
መጸሐፍ ነው። ተባረክ! http://www.satenaw.com/alemneh-wasse-awazes-news-commentary-day/
- ዛሬ እና ተመስጦው ….
አሁን ነው ሳተናው ላይ አንድ የተለጠፈ ነገር ያነበብኩት። „የትግሬ
ነፍስ ከሌላው ይበልጣል?“ ይላል ርዕሱ? አዎና! ምን ጥያቄ አለው። ነፍስ ቢባል ሁሉ ነፍስ እንዴት እኩል ይሆናል፤ የክትና
የዘወትር ነፍስ መኖሩ 26 ዓመት ሆነው እኮ። ምርጡ ነፍስ አይከሰስ
- አይወቀስ? እንጃ ሰማይ ቤትም … የሎቢ ሰራተኛ ይቀጥሩ ይሆናል።
እኮ! ስለምን አይበልጥም? ምርጥ ዘሮች
እኮ ናቸው፤ ወርቆች ሞት - እስራት - ስደት፤ ከሥራ መፈናቀል፤ ከሥራ መታገድ፤ ባይታዋርነት፤ በደል አንዳይነካቸው የአራስ ልጆች፤
የአንደኛ ደረጃ የዜግነት ደረጃ የተሰጣቸው ብርቆች፤ በፈለጉበት ቦታና ሁኔታ እንዳሻቸው በወንጀል ሳይቀር እንዲኮፈሱ የተፈቀደላቸው
… ቀያሾች፤ ናዛዦች፤ ፈራጆች፤ ቀዳሾች … ገዳዮች …
ይሄው ጹሑፍ ዝቅ ብሎ ደግሞ ስለ ህዳር መጀመሪያ ላይ የአማራና የትግራይ ሽማግሌዎች የሚሳተፉበት የሰላም ኮንፍረስ ለዛውም
በጎንደር ከተማ ላይ የሴራ ትልትል ደግሞ መረጃ ሰጥቷል። እኔ ቀልቤን ሳብ አደረገው እና አንብቤ ስጨርስ እንደ ወረደ ሳይሞረድ
ሞልቶ፤ ገንፍሎ ፈሶ ከተንሰራፋው መከፋት በጭልፋ ትንሽዬ ቀንጨብ አደርጌ ልል አሻኝ …
- የጉዳዬ ሆድ ዕቃ …
እም! ነው። ህም-ም! ነው። ህመም።
ግን ደግሞስ ከበታቿ ሥር ከወደቀችው ያቺ ምስኪን፤ የመከራ ሁሉ የመሞከሪያ ጣቢያ የሆነችው ቀዬ፤ የእኔ ናፍቆት ጎንደርዬ ከታላቋ
ሐገረ - ብርሃነ - ትግራይ ጋር እንዴት ተብሎ ይሆን ለድርድር መምከሪያነት ወይም መታደሚያነት የምትቀርበው? በእውነቱ ደረጃዋስ
ይፈቅድላታልን? ከቤንሻጉል ጉምዝ ክልል በታች፤ በጣም በታች ያለች፤ እጅግም የወረደች ተበልታ፤ ተመጣ፤ ተላምጣ ያለቀች ከተማ እኮ
ናት። ልጆቿ ደግሞ ከዬትኛውም የሃላፊነት ቁልፍ ቦታ የተገለሉ፤ በሚደያም ጨለማ የተፈረደባት። ምስኪንዬ ጎንደር … ለዳግም የሴራ ሹርባ ደግሞ ታጨች።
ወቼ ጉድ! አለ ያገሬ ሰው … እንዴት ይቀለዳል?
በዕውነቱ ዝርፊያው፤ ስርቆቱ ነው የሚያምረው … ስስቱና ስግብግብነቱ፤ አልጠግብ ባይነቱ ነው እንጂ ለታላቋ ትግራይ ህልመኛ ቀልዱ
አያምርበትም። ደም የለሽ ፍልስ ስለሆነ። ብናኝ ወዝ የለሽ የተላመጠ …. ነገር …
ብቻ ስለይገርም ነው። ብቻ ስለይደንቅም ነው።
ብቻ ስለአለማፈርም ነው። ምኑን መርዝ ደግሞ ሊቀብሩ ይሆን ህዳር
ገብ ሰሞናት 2010 ቀጠሮ የተሰጠው? የጎንደር ሽማግሌ የሚባለው እኮ የሐገሬ ልጆች … ያው ጎንደር ተወልዶ ያደገው የትግሬ
ሰው ነው። ካህነቱም እነሱው ናቸው። ነጋዴዎችም እነሱው ናቸው። ባለሃብቶችም እነሱው ናቸው። ነጭ ለባሾችም እንሱው ናቸው። ደጅ
አስጠኘወችም እነሱ ናቸው። ዳኞችም እነሱው ናቸው። አማካሪዎችም እነሱው ናቸው፤ አስተዳዳሪዎችም እነሱው ናቸው። ሰላዮችም እነሱ
ናቸው። አራጊ ፈጣሪው እነሱው - ዘመንተኞች ናቸው። ደርቡ ላይ ያሉ የተንጠራሩ፤ ቢጠሯቸውም ሩቅ የሆኑ። አማራ ብሎ ወያኔ በከለለው ወርደ ጠባብ መሬት ላይም ቢሆን በመሰሉ ዕድምታ
የተቆላላ ነው … ጎጃም ይሁን ወሎ፤ ወሎም ይሁን ሽዋ … ምን እነሱ ያልረገጡት ብቻ ሳይሆን አንበል ያልሆኑበት ዬት …
ህም! ያው ጎንደር ተወልዶ ማደግ ጎንደሬነት ነው።
ይህ መቼም አይካድም። ትግሬነትን ግን አይለውጥም ። አማራነትም አይተካም። አማራነትም - አማራነት፤ ትግሬነትም - ትግሬነት ነው።
ቅጂ የለውም የደም ማንነት። የደም ማንነት አይሸመትም - አይቀናምም። ድርድርም የለም። ሊኖርም
አይገባም። ጎጃምም፤ ሸዋም፤ ወሎም ቢሆን ይሄው ነው።
ጡርን ፍሩ! ተውት እባካችሁ! አትነህርሩት! በአስራሁለት አውታር ሰቅዛችሁ የያዛችሁትን
የቀራንዮን አንባ …
ግን ለምን አይተውትም ከካርታ ውጪ ያደረጉትን
መንፈስ። ደሙን ሲያፈስ፤ ዕንባውን ሲያዘራ፤ በቤንዚን ተርከፍክፎ ታሪካዊው ቦታ ቅዳሜ ገብያ ሳይቀር ሲቃጠል፤ የአጋዚው ቅልብ ወታደር
አልበቃ ብሎ በሱዳን ወታደር ለብሰው፤ ጠግብው ማደር የተሰናቸው የአንባጊዮርጊስ ድሃ አደግ ወንድ ልጆች በግፍ በዘመነ ሄሮድስ ሲጨፈጨፉ፤
ባለወንድ ልጅ እናት እንደ ድንግል ማርያም ልጇን ይዛ በርሃ ለበርሃ ስትንከራተት፤ በሺህ የሚቆጠሩ ልጆቹ ሲታሰሩ፤ ሲደበደቡ፤ በመርዝ
ሲገደሉ፤ ሲሳደዱ፤ ዓውደ ዓመታት ሲሰተጓጎሉ፤ ታቦታት ሲደፈሩ፤ የደረሰለት ለጎንደር አማራ የጎጃም አማራ ብቻ ነበር። ትግራይማ አንድስም ባለግራጫ አላዬንም - አልሰማነም። አልፎ እንኳን
ለትውስታ ለማንሳት የገዳዮች ብዕር ይሳናታል፤ ገዳዮች አካልን ብቻ ሳይሆን መንፈስንም መግደል ነው ተፈጥሯቸው። ገዳይነት በከረባትና
በገበርዲን ወይንም በተባ ብዕር አይሸወድም።
40 ዓመት ሙሉ ሳይቋርጥ የወልቃይትና የጠገዴ
ህዝብ ሲጨፈጨፍ፤ ከዘር ሲነቀል፤ ከርስቱ ሲነቀል፤ ከማንነቱ ሲነቀል የደረሰለት በሃሳብ ደረጃ እንኳን አንድም የትግሬ ሊቅ ወይንም
ባለግራጫ የለም። ከደጉ ከአቶ ገ/መድህን አርያ በስተቀር። ግን በእውነት
የትግራይ መሬትና ሽምግልና ይተዋወቃሉን? ለመሆኑ ዘመነኛዋ ትግራይ ሽማግሌ አላትን? መላ ኢትዮጵያ እንዲህ በሰቀቀን፤ በስጋት፤
በደም አላባ ተነክሮ እነሱ ከበሯቸውን ከመደለቅ መቼ ታቅበው?
ያ በዕመነቱ ጽናት፤ ያ ጥኑ ማተቡ እኮ ለኮከብ ሰግዷል። ለቀናቀን
አደግድጓል። ለወርቅና ለጨርቅ አጎብድዷል። ለሸቀጥ ተገዝቷል። „እዩኝ እዩኝ ያለ ገላ ደብቁኝ ደብቁኝ“ እንዳያሰኝ እንጂ፤
ለነገሩ ምን ሽምግልና ያስፈልጋል …
የተሰረቀውን ተራራ መመለስ። የተሰረቀውን መሬት
በሙሉ መመለስ። ሌሊት - ሌሊት የሚጓጓዘውን ቅርስ መመለስ። የታሰሩትን መፍታት። ከተከዜ ወዲያ ሰብሰብ ብሎ ለመቀመጥ መቁረጥ
- መወሰን። ጥጋብን በልክ ማደረግ። መንጠራራትን ትንሽ ትንፋሽ መስጠት። ዝቅ ብሎ የበሉበትን ወጪት ሰባሪነትን እንዲሰቀጥጥ መፍቀድ።
ቢያንስ የእግዜሩን በረዶ፤ የእግዜሩን ኡኡታ፤ የእግዜሩን የነገ ፍርድና ዳኝነት መፍራት ነው።
ፈጠሪ እኮ በአንድ የፍርድ ነውጥ እልም - ጥፍት - ውድም ሊያደርግ ይችላል። ተተኪውም ሲፈጠር ምን
ዓይነት ሆኖ ሊፈጠር እንደሚችልም አይታወቅም። ጡር መፍራት ጥሩ ነበር።
የሚሆነው አይታወቅም። የ40 ዓመት ዕንባ … ለሃጣን የመጣ ለጻድቃን ሆኖ እነዛ ገና የተፈጠሩት፤ ገና ሊፈጠሩ የሚታሰቡት ጮርቃ
የትግራይ ህጻናት ዕዳውን ከፍለው የሚጨርሱት አይመስለኝም እንዲሁ - ሳስበው። የሆነ ሆኖ ወንበር ላይ ቁጭ ብሎ መወያዬት ለጥጋበኞች
ይሁን፤ ለዘመንተኞች ይሁን፤ ለመሳፍንቶች ይሁን። ወይ ደግሞ ሱሪውን ለአወለቀ ለባህርዳሩ እንኮሸሽሌ ይሁን። በጨለማ ለተከዘነ፤
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አሳሩን ለከፈለ፤ ለሚከፍል ህዝብ፤ በቀዩ እንኳን መውጫ መግቢያ አጥቶ ሞቱን ለሚጠባበቅ የድርብ፤ ድርብርብ
ተገፊ ህዝብ ግን፤ ከስድስት፤ ከሰባት ለመሸንሸን የመሬት ሊኳንዳ
ቤት ለተከፈተለት ግፉዕን ቢያንስ፤ ተቆርምጣ በተሰጠችው እራፊ ቀዬው፤ ተኮርኩዶም ሆነ ተጨብጦ እንዲኖር በተሰጠችው ቅንጣቢ መሬት ሰላሙን መስጠት ብቻ ነው የሚያስፈልገው። ፍርድና
ዳኝነት ከእዮር እስኪመጣ ድረስ … በአባቶቼ የዕምነት ጽናት እኔ እተማመናለሁ። ጋሻዬ መከታዬ ይሄው ነው። እምጽናናውም …
- መልካሙ መንገድ ….
ባበላ፤ ባጠጣ፤ ለክፉ ጊዜ መጠጊያ በሆነ፤ ጉሮሮ
ባረጠበ እንደ ጣውንት ሌት ተቀን፤ ክረምት - ተበጋ ያን ቅን ህዝብ፤ ሰው በልቶ የጠገበ የማይመስለውን አስተዋይ ህዝብ ከመቀጥቀጥ
መታቀብ። በሥነ - ልቦና አቅም ደረጃው ይታወቃል። ጊዜ ቢሰጥም ከጸጋና ከተፈጥሮ አቅማዊ አምክንዮ ጋር ግን መመጣጠን አይቻል ነገር።
የአምክንዮ ሥነ - ልቦና አቅም፤ ብቃት ተፈጥሯዊ ካልሆነ በዘረፋ አይገኝ ነገር እንደ ተራራው… ዘረፋ „ልክን ማወቅ ከልክ ያደርሳል“ ይላሉ የጎንደር አማሮች ሲተርቱ … በልክ
ለመኖር መቁረጥና መወሰን። እዬተጠሉ ከመኖር ለባለተራ ደግሞ ቦታዋን ለመስጠት ወኔን መቋጠር ያስፈልጋል። በመላ ኢትዮጵያ አንደስም
እንኳን ህሊና ያለው ዜጋ ለአንድ ቀን የዘመነ ሄሮድስ ሥርዐትን ማዬትን የሚፈቅድ አይኖርም። ከልክ በላይ ሆነ ሁሉ ነገር።
ከመጠን አለፈ ሁሉ ነገር። ድንበር ጥሶ ፈሰሰ ሁሉ ነገር። ስልችት አላችሁን። ተውን … ልቀቁን … በቃችሁም! ኮንፈረንሱን
ለታላቋ ሀገረ ብርሃናማ ትግራይ አድርጉት፤ ለሞላለት … ለተባዳዩ፤
ለሀገር አልባው ግን ጭፈጨፋውን አቁሙለት … እሳርቱን ተግ አድርጉለት፤
- የመርዝ ችግኝ መትከያ ዕለት፤
አዎን፤ ህዳር መጀመሪያ 2010 ዓ.ም የሌላ የመርዝ
ችግኝ መትከያ ዕለት ነው - ለእኔ። መከፋታችን ሊገልጽ የሚችል ቃል አምላካችን አልፈጠረም። መቁሰላችን ሊገልጽ የሚችል ቃል መዘገበ
ቃላት ውስጥ የለም። ስለምን? እንተዋወቃለን። ስለምን? ወደ ጎንደር ይተመም እንደ ነበር በእኛ በዕድሜ እንኳን የምናውቀው ብዙ እጅግ ብዙ በርካታ ጉዳይ አለ። የታመቀ። ሰብዕና ስለማይፈቅድ ብቻ ነው ለበስ እዬተደረገ የሚገለጸው።
ያ ደግ ህዝብ፤ ያ የበሞቴ አፈር ስሆን ወላጅ ዛሬ ደግሞ … በቀዩ እንኳን መቀመጫ አጥቶ ቁንጣኑ አላስችል ባላቸው ጥጋበኞች ቁም
- ተሰቀል - ተቀመጥ - ተነሳ - ተቃጠል - ንደድ ይባላል የጎንደር አማራ። „ከአጋም የተጠጋ ቁልቋል ዘላለም ሲያለቅስ ይኖራል“
እንዲሉ … ጎንደር የተረገመው ትግራይ አዋሳኙ ሲሆን ነው … የሁሉንም ዓይነት በደል መሞከሪያ መፈተኛ ጣቢያ ያድርገውም ይሄው ነው።
የአረመኔነታቸው ቀፈት ሊጠግብ፤ የጭካኔያቸው ከርስ ሊሞላ አልቻለም። ግን ምን ፍጡር ናቸው?
- አንጀት አለው የጎንደር አማራ፤ ማተብ አለው የጎንደር አማራ … ሰባዕዊነት ደሙ ነው የጎንደር አማራ …
ኢሊባቡር ላይ፤ ከፋ ላይ፤ አንቦ ላይ፤ ግንጪ
ላይ፤ ነቀምት ላይ፤ በሰላሌ፤ በቤንሻንጉል ላይ የሚያልቀውስ ወገኑ አይደለምን? ነግሯችሁ የለም። „የኦሮሞ ደም ደሜ ነው“ ብሏል እኮ። አይገባችሁም። ሬሳ አስቀምጦ፤
ሬሳ አስቀምጣ የምትደልቅ/ የሚደልቅ የጎንደር አማራ፤/ ጎንደሪት አማራ የለችም። ቀኑ ሲደርስ እገልጠዋለሁ እኔ ለዓለሙ የሰላም
መሪ የሬቻን ዕልቂት በሚመለከት ውስጤን የገለጽኩበትን መንገድ … አስተዳደጌ ነበር ያነን ያስወሰነኝ። እንግዳ ሆኖ በድንገተኛ አደጋ
ምክንያት ላረፈ አንድ ዜጋ ወገኑ ሀዘንተኛውን ጎንደር ላይ መለዬት ይቸግራል። የትውፊቱ ልቅና ሰቅ ነው - የጎንደር አማራ።
እና የህዳር መባቾ 2010 ዓ.ም በምን አንጀቱ
ይሆን ከእናንተ ጋር በአንድ ማዕድ በቀዩ የሚታደመው? ለነገሩ ማተብ የሚባል ነገር አልሠራላችሁም። ጎንደርን ያቃጠላችሁ ለማን ልትሆኑ
እናንተ? ያቺ ዱር ላይ ጫካ ላይ የተገላገለች፤ ያቺ ትምህርት ቤት እንደዋጣች የቀረች ሚጡ ቶልቻ ታዳጊ ወጣት፤ ያ ለአካሉ ከፍን የሌለው ታዳጊ ከነደሙ ከንብል ብሎ እንዴት ተደርጎ ይሆን
በደም መሬት ላይ ሆኖ ደም ሊደራደር፤ ደምን ሊጎነጭ የሚችለው? ይቻለዋልን? ለእናንተማ ምን ይቸግራል … ውሸቱም - ዘረፋውም
- ማምታታቱም - ማጭበርበሩም፤ ቃል አባይነቱም፤ ሴራውም - ተንኮሉም - ምን ሲቸግራችሁ …።
እባካችሁን አማራን ለዛውም በተቃጠለ በቤንዚን
ባቀጠላችሁት መሬት ላይ፤ ለዛውም አቶ አባይ ወልዱን ያን ጨካኝ ሰው፤ ያን እብሪተኛ ሰው፤ ለዛውም ሱሪውን ላወለቀ አቶ ገዱን ልታስተናግድ
ጎንደር? በዚህ በሱባኤ ሰሞናቱ መልካሙን ተፈጥሮውን አትለውሱት በሬትና በምሬት። በስሙም አትነግዱ። በዚህ ወገኑን አጋ አስለይታችሁ፤
አስታጥቃችሁ ታስጨፈጭፋለችሁ፤ ጫካ ለጫካ ታሳድዳላችሁ በዚህ ደግሞ የእርቅ ኮንፍረንስ ትላላችሁ። ከሳጥናኤል ጋር፤ በደም ከተነከረ
ሃጣዕን ጋር … እንዴት ተብሎ? ያው የደማችሁን ሰዎቻችሁን ሰብስባችሁ አደረግን ብላችሁ ደግሞ ለብጡ … እንደ ለመደባችሁ … ሃሳብ
ደፍረው የሚገልጹትንም ልቅምቅም አድርጋችሁ ደግሞ ወደ ባዶ 6። … ለማንዘርዘሪያና … ለማጠለያ ነው አካሄዱ … የቀረውን ደግሞ
እርሾ ለማሳጣት …
እርግጥ ነው ያው እንደ ተለመደው የራሳችሁን ሰው
ትግራይ የሚኖረውን ትግሬ እና አማራ ክልል ባላችሁት የሚኖረውን ትግሬ በማገናኘት የሴራ መርህ ለመንደፍ ነው ጉንጉኑ - የተንኮል።
እነ አባ ተንኮሉ መቼም አያልቅባችሁ። … ወይ ደግሞ መቱ ላይ የአደባባይ ሲሳይ የሆነው ገመናችሁን መሰል ጎንደር ላይ ያለው ምሽጋችሁን ለማጠናከር። እንዳይነቃባችሁ ለማደንዘዣ ዕጽነት ለመጠቀም ይሆናል።
ጎንደር ያለ ትግሬ ምሽግ ሠርቶ እንዲቀመጥ እንደምታደርጉት የታወቀ ነው። ወይ ጎንደር ወይ ባህርዳር የግንቦትን 7ን ዓርማ አባዝታችሁ ሌላ ድራማ እንደምትሠሩ ሁሉ እዬጠበቅን
ነው። የሴራ ፍልስፍና ነውና መሪያችሁ … ሴራ ነው አምላካችሁም፤ ሸር ነው ሃይማኖታችሁ።
በተረፈ እነ አቶ/ ትባሉ/ ፊታውራሪ ወያኔ ልብ
ይስጠችሁ በቃችሁንን ስለተባላችሁ በቃን እንድትሉ ለዛ ያብቃችሁ፤ ቀናችሁ ናፍቆናል …. የምኑ ብላችሁ እንዳትጠይቁ … ልቅላቂ አልባ
ከዘመነ ሄሮድስ፤ ከዘመነ ፈርዖን የምንላቀቅበት ቀን ሽው ብሎናል፤ መረን የለቀቀው ጥጋባችሁ ከርፍቶናል፤ ድልዙ መስቃችሁ ጎፍንኖናል … የአታሞ ዳንኪራችሁ አደንቁሮናል …
ዕልፍ ነን እና ዕልፍነታችን ዕልፍ እናድርገው!
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ