ይታረዳል ጎንደር።
ይታረዳል ጎንደር።
ከሥርጉተ - ሥላሴ 13.11.2017 (ሲዊዘርላንድ - ዙሪክ)
„ዓይኑን የሚዘጋ ጠማማ አሳብን ያስባል፤ ከንፈሩን የሚነክስ ክፋትን ይፈጽማል።
(ምሳሌ ምዕራፍ ፲፮ ቁጥር ፴“)
የቸነፈር ቁርጠት - የውሉ መጋኛው፤
ተከዜም ደንበሩ ተገሷል ሁነኛው፤
ንውፀት ሆነ ርስትሽ መከፋት ግድግዳው።
የተጋሩ እናት ደልደል በይ እና …
ተኚ እንደ ልማድሽ ልጆች አሉሽና …
ወልደሽ አሳድጊ ዓለም እፈሺና …
ቀለብ ማቀበሉን ለጎንደር ሸኚና
ሐሤትን ቀድሽው - ድጠሽው ስብዕና።
እናትዓለም ጎንደር ወና ላይ ያለሽው
በባሩድ መቀቀል ፋታንም ያጣሽው
በሰቀቀን ኑሮ ምሳር የተጋትሽው፤
ዕንባሽ አላረገ መች ደርሶ ከደጁ
ይሄው ይደመጣል - አታሞ ዓዋጁ።
ገመዱ ተገምዶ ተከንድቶ ሳለ
መሬቱም እራደ ከውስጡ ከሰለ።
የትዕቢት ጭንቅላት ካለልኩ ሆኖ
ይቆላል ይፈጫል የሰው ደም ተከድኖ።
የ40 ዓመቱ ምጣድ ከሰሉ ይስቃል
የትውልድ ብርንዶ በዕለት ይቋደሳል፤
ያልፋልን ይጠብቅ በእምታ ደምቆ።
የወርቁ - የጨርቁ - የጉልበት ሰርዴታ
የጥርጥር - ዋሽንቱ የጥጋብ ዕንቢልታ።
በበቀል ተፈጭቶ በዘሩ ተቁላልቶ
ይታረዳል ጎንደር ልኳንዳ ተከፍቶ።
ለሆዱ ያደረ አብሮ እዬዘመረ
ትቢያ ያለብስሻል እዬመነዘረ።
የተጋሩ ሎሌ ማተቡን የበላ
ጥቃት ተንተርሶ ለከርሱ እያደላ።
እናት ጡት አጥብታ እሱነቷን ሰታ
እንዴት ይክዳታል በከፋተኝ ለታ?
እንዴት ይረሳታል በጨነቃት ለታ?
እንዴት ይተዋታል በጨለማት ለታ?
ናፍቆቴ ልበልሽ፤ ስስቴ ልበልሽ፤
መንፈሴ ልበልሽ፤ ልበልሽ እቴጌ ልበልሽ --- ልበልሽ፤
እመቤት ልበልሽ፤ ህሊና ልበልሽ
ታቦቴ ነሽና በውስጥ ልሳለምሽ
የበሞቴ እናት ሙያ በልብ ነሽ።
·
ሥጦታ ---- ከቀደምቱ የክ/ሐገራት ርዕሰ ከተማ በድህነት፤ በጉስቁልና፤ በልጅ እርድ፤ በርስት
አልቦነት
ምነና/ትንና
ላይ ለምትገኘው ጎንደር ይሁንልኝ። 13.11.2017 (ሲዊዘርላንድ - ዙሪክ።)
ካለ
ከመንበሩ እግዜሩ ይስጥልኝ። መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ