ጥላቻን ጥላቻ አያክመውም።
ጥላቻን ጥላቻ አያክመውም።
ሥርጉተ ሥላሴ 10.12.2017 ከጭምቷ፡ ሲዊዘርላንድ።
„እግዚአብሄርም ለሰሎሞን እጅግ
ብዙ ጥበብ እና ማስተዋል በባህር ዳር እንዳለ አሽዋ የልብ ስፋት ሰጠው።“
(መጸሐፍ ነገሥት ቀዳማዊ ምዕራፍ 4፬ ቁጥር ፳፱)
·
ማስተዋል በቅን ልቦና ስለማግሥት ሲባል።
አሁን ከአንድ የማህበራዊ ሚዲያ ትጉሃን ወንድሜ
አንድ ነገር አነበብኩኝ። ሃዘን ለሌላ ሃዘን በመገባበዝ እርካታ አያስገኝም። ጥላቻን ጥላቻን ሊያክመው በፍጹም አይችልም። በጥላቻ
ውስጥ መዳን የለም። በጥላቻ ውስጥ ምህረት የለም። በጥላቻ ውስጥ ተፈጥሮ የለም። በጥላቻ ውስጥ ዕምነት የለም። በጥላቻ ውስጥ ሃይማኖት
የለም። በጥላቻ ውስጥ ሰብዕዊነት የለም። በጥላቻ ውስጥ ማግሥት የለም። በጥላቻ ውስጥ ዘመን የለም። በጥላቻ ውስጥ ትውልድ የለም።
በጥላቻ ውስጥ ያለው ቂም ነው። ቂም ደግሞ በቀልን የወልዳል። በቀል አጥፊ እንጂ አትራፊ አይደለም። የበቀል መንገድ ነገን ያቃጥላል።
ከሞት የሚገኘው አመድ ብቻ ነው። ጥላቻ ሆነ በቀል ትንፋሹ የጸላዬ ሰናይ ነው። ከፈጣሪ ጋርም ያጠላል። እበሶ ቅድስት ድንግል ማርያም
እንደ እናትነቷ አብዝታ ታዝናለች። ጥላቻን የሚያድነው ሀኪሙ፤ ዶክተሩ ፍቅር ነው። ፍቅርን የሥነ - ልቦና ተግባር እንጂ የኣዋጅ
አይደለም። ለዚህም ዘግይቷል። ግን አብዝተን ማተኮር እና በዚህ ዙሪያ መስራት አለብን።
አሁንም ቢሆን ከግብታዊነት ወደ መረጋጋት፤ ከስሜታዊነት
ወደ መስከን ሊመልሰን የሚችለው ጸሎት ብቻ ነው። ከፀሎትም መዝሙረ ዳዊት። እነሱ አውሬ ይሁኑ፤ ጨካኝ ይሁኑ፤ ሌላው ይህን የአውሬነት
እና የጭካኔ መንፈስ እንደ መልካም ነገር መጋራት አይኖርበትም። ትግራይ የሚኖረው ህዝብ አጥፊዎችን ይተባበር። ሌላ ቦታ የሚኖረው
ግን ቢያንስ እግዚአብሄርን መፍራት አለበት። ትእግስትን፤ በልክ መኖርን፤ ፈርሃ እግዚአብሄርን ያስተምረው ለትግራይ ማህበረሰብ።
በዛ ላይ ህፃናት እና ነፍሰጡሮችም ይኖራሉ። በተጨማሪም ጨዋዎችም ይኖራሉ። ኢትዮጵያዊነት በዚህ ውስጥ ነው መታዬት ያለበት። በእግራቸውም
ከፈቀዱላቸው ነፍሳቸውን ይዘው እዬተረዳዱ ሁሎችም አካባቢውን ለቀው ይውጡ። ይህን የፈተና ጊዜ ማለፍ የሚቻለው አብዝቶ በመታገስ
እንጂ የጭካኔ ብድር በመመላለስ አይደለም። በጥፋት ላይ ዝብሪት አስፈላጊ አይደለም። „ሰከን“ ማለት ያስፈልጋል። ትንፋሽን መሰብሰብ።
በተደሞ ማስተዋል።
- · ምን መደረግ አለበት?
እኔ ይህንን ሃላፊነት ሊወጣ የሚችለው ከመዳህኒዓለም
በታች የቀደመው የመጀመሪያው ገዳማ ደብረ ዳሞ ብቻ ነው ብዬ ነው የማምነው። እንዲያውም ዘግይተዋል። እኔ በዚህ ዙሪያ ብዙ ጊዜ
አሳስቢያቸዋለሁ። ይህን የመከራ ቀን ግማድ መሸከም ያለባቻው አሁንም የደብረ ዳሞ ቅዱሳን አባቶቻችን ብቻ ናቸው። ይህን ሰቆቃ ማብረድ
የሚችሉት እነኛ መንኞች ብቻ ናቸው። መነኮሰ ማለት ሞተ ስለሆነ ሞታቸውን በምድር ሰማዕትነት ቀይረው ከባዕታቸው ወጥተው ወደ ግፋኑ
በፍጥነት በሰልፍ መሄድ አለባቸው። ሊሞቱ ይቻላሉ። ሊቋራርጧቸው ይችላሉ። ሊያቃጡሏቸውም ይችላሉ። ታላቅ ጸጋ እና በረከት በሰማይ
ያስገኝላቸዋል።
ይሂዱ ባህታውያኑ … ቀድመው ይሙቱ ከነዚህ ቀንበጦች
በፊት። ይህ የመረጡት የህይወት መስመር ነው። ሐሤት ሊያደርጉበትም ይገባል። ከዚህ በላይም ሰማዕትነት የለም። አሁን ደግሞ የሱባኤ
ወቅት ነው። ሌላ ጸጋ፤ ሌላ መክሊት እግዚአብሄር አዘጋጅቶላቸዋል። አባቶቻችን ፈተና ሲዘገይባቸው ፈተና ስጠን ብለው ይጸልያሉ፤
ሁለት ሱባኤም ይይዛሉ። መከራ ተፈልጎ አይገኝም - ለደናግሉ። እንዲህ ፈጣሪ አምላክ ፈቅዶላቸው በራሱ ጊዜ ከመጣ ደግሞ የሰማይ
በረከት ነው። የደብረ ዳሞን አባቶች ፈተና ግጠሙኝ እያለ ነው ከበራቸው ድረስ የሄደው። ስለዚህ ባዕታቸውን ለቀው ወጥተው ወደ ሞት
መገስገስ በፍጥነት አለባቸው። ገድል ይጻፉ።
በዚህ እሳት ውስጥ ሊቀቀሉ የተሰናዱትን የእግዚአብሄር
ፍጡራን ሳይሆን የነገ የትግራይንም ዕጣ ፈንታ ይወስነዋል። ከተማሪዎች በፊት እነሱ ስለቅድስና ደማቸውን ማፈሰስ አለባቸው። ዓለም
ለእነሱ ምናቸው ናት እና? ደግሞስ ከአናንያ፤ ከአዛርያን ከሚሳኤል፤ ከዳንኤል ከቀደሙት ቅዱሳን፤ ጻድቃን እና ሰምዕታት አባቶቻችን
አስተምኽሮ ምን ሆነ እና። የተጋድሎ ታሪክ እኮ እነሱ እንዲያነቡት ወይንም እንዲያስቡት ሳይሆን እንዲኖሩበት የተሰጣቸው መክሊታቸው
ነው። ስለዚህ ለትውልዱ ክርስትና ማለትን በተግባር ያሳዩ። ህይወታቸው ሃይማኖታችን፤ ማተባችን፤ ቅዱስ መጸሐፋችን ይሁን። ከዚህ
በላይ ሱባኤ፤ ከዚህ በላይ ጾም ጸሎት፤ ሰጊድ የለም።
የደብረ ዳሞ ቅዱሳን አባቶቻችን የእስከ ዛሬው
የምነና ህይወታቸው ክንፍ አውጥቶ ይጸድቅ ዘንድ የፈጣሪ ጥሪ ዛሬ ነው። ተደውሎላቸዋል። ደወሉን ሰምተው ይሂዱ። አብያተ ቤተክርስትያናትም
ሃይማኖታቸው ጎሳ ሳይሆን ክርስቶስ ደሙን የሰጣት ቅድስት ተዋህዶ ከሆነች በጋራ በተመሳሳይ ሰዓት የቤተክርስትያኑን ደወል በህብረት
ይደውሉ። አቅማቸው የሃይምኖት መሪዎች ፈጣሪያቸው ብቻ ነው። አባቶች ማተብ ያላቸው፤ ሃይማኖት ያላቸው የክርስቶስ ገበሬዎች ይሂዱ
ለብቸኞቹ የእግዚአብሄር ፍጥረቶች ፈጥነው ይድረሱላቸው። ይፍጠኑ! ለነዛ መጠጊያ ላጡ ነፍሳት። በቶሎ። እውን ለድንግል ክብር እና
ቅድስና ካላቸው እናታችን ከበለሃሳብ ነፍሳትን እንዳዳነቻቸው ሁሉ ቃልኪዳኑን እነሱም ይፈጽሙ። ይህ የሰማይ ጥሪ ነው።
አማራ ክልል በሚባለው ለአማር ወጣት ማን ተቆርቋሪ
ሲኖር ነው። አቶ በረከት? አቶ አለምነህ? ወይንስ አቶ አዲሱ ለገሰ? በመሬቱ ሲጨርሱት የኖሩ እኮ ናቸው። በመሬቱ ላይ ለአንባ
ጊዮርጊስ ህጻናት መቼ ደረሱላቸው? ለአማራ ተጋድሎ ግፉዕና ለታሰሩት አንድ ቀን ጩኸው ያውቃሉን? 20 ሺህ ወጣት ያን ፍዳ ሲከፍል
ደረሱን? አንድ ቅን ቢገኝ እንዲያው እንድርግ ቢል እንኳን አውቶብሱ እዛው ሳይደርስ መንገድ ላይ ያነዱታል። በአውሮፕላንም አይታሰብም።
ማን ፈቅዶ አውሮፕላኑን ሊያሰርፍ ይችላል? አዬር ላይ ያነዱታል። ትግራይ እኮ ሐገር ናት? ድንበር ጥሶ መግባት አይቻልም። አይፈቀደም።
አያችሁ የሹም ዶሮ እዚያ አትደረሱ የሚባለው እሽሩሩ ያመጣው መከራ እንዲህ ይስተናገዳል። ሌላም ዕዳ አለ። ኤርትራ ላይ በዝምታ
ያለው ቲፒዲኤም፤ የአክሱማዊት ኪንግደም ህልመኛ አቋምም ደንቡልቡል ነው።
የሆነ ሆኖ የእነሱን መንገድ የኢትዮጵያ ህዝብ
መከተል የለበትም። በፍጹም። የጥበብ ቤተሰቦችም ይህንን የበቀል አውራ ጎዳና መከተል የለባቸውም። ጥበብ በቀልን ትጸየፈዋለች። ጥበብ
ጥላቻን - ቂምን ተግፈትረዋለች። ጥበብ ለመጠፋፋት፤ ለመቃቃር አልተፈጠረችም። ጥበብ የሰው ልጅ ከሚያስበው በላይ ደረጃዋ ሰማያዊ
ነው። ልዑቅ።
- · ክውና።
በቀልን መጸዬፍ ቢያንስ ሞቱን፤ መከራውን ቅዱስ
ያደርገዋል። ሞቱን ክብር ያለው ያደርገዋል። ሞቱን የጸጋ ሞት ያደርገዋል። በፍጹም ሁኔታ በሌላ ቦታ የሚኖሩ ከትግራይ የሚወለዱ
ንጹሃን ሰላማቸው መታወክ አይኖርበትም። ኢትዮጵያዊነት በዚህ ፈተና ማለፍ ካልቻለ ኢትዮጵያዊነት ዕውነትም ቀብረነዋል እንዳሉት የወያኔ
ሃርነት ትግራይ ሱዎች ተቀብሯል ማለት ነው። አንሸነፍ። ጽናትን ከአባቶቻችን እና እናቶቻችን ውርሳችን እናድርግ። የጉዲትን ዘመን
ያለፉት አባቶቻችን በጽናታቸው ነው።
ሌላው ግን ወሎ ሆነ ጎንደር ተሰናድቶ መጠበቅ
አለበት። እንግዶቹን በፍቅር ለመቀበል። ወደ ኤርትራ ከሆነ ጉዞው ግን ከድጡ ወደ ማጡ ነው። ከእሳት ወጥቶ ወደ እሳት ነው የሚሆነው።
ይህም ዘላቂ መፍትሄ አይደለም። መግባት ይቻል ይሆናል ወደ ኤርትራ። መውጫው ግን ከተኖረበት መከራ በላይ፤ በላይ፤ በላይ ነው።
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ
የተፈጠረ ሚስጢር።
ቸሩን ያሰማን ፈጣሪያችን። አሜን።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ