እቴዋ ጎንደሪት ሲመጣ ገዳይሽ?
እቴዋ ጎንደሪት ሲመጣ ገዳይሽ?
ከሥርጉት ሥላሴ 15.11.2017 (ሲዊዘርላንድ
- ዙሪክ)
„በድሀ የሚያላግጥ ፈጣሪውን
ይሳደባል፤ በጥፋትም ደስ የሚለው ሳይቀጣ አይቀርም።“
(ምሳሌ ምዕራፍ ፲፯ ቁጥር ፭)
አንቺ ሆይ! ለውርዴትሽ …
አንጥፊ¡ ጎዝጉዢ¡
ታጥቀሽ - አደግድጊ¡
ገዳይሽ ሲማጣ ቄጤማ ነስንሺ¡
አረግርጊ¡ አረግርጊ¡ አረግርጊ¡
እቴዋ ጎንደሪት የስርዝ ሰርገኛ
እቴዋ ጎንደሪት የክስለት ቤተኛ
እቴዋ ጎንደሪት የመርዶ ቀስተኛ፤
አንጥፊ¡ ጎዝጉዢ¡
ታጥቀሽ - አደግድጊ¡
ገዳይሽ ሲማጣ ቄጤማ ነስንሺ¡
አረግርጊ¡ አረግርጊ¡ አረግርጊ¡
ጎጆሽ ጥሰት ገድሎት
ነፃነት ርቆት፣ መስፋፋት አራቁቶት
ግፉ እዮር ነክቶ፣ አቤቱታ ከርሞት
በክብሪት ማህበር ቃጠሎ ፈርዶበት
በቤንዚን ተቋማት ቅርስሽ ሲነድበት፤
አንጥፊ¡ ጎዝጉዢ¡
ታጥቀሽ - አደግድጊ¡
ገዳይሽ ሲማጣ ቄጤማ ነስንሺ¡
አረግርጊ¡ አረግርጊ¡ አረግርጊ¡
ወልቃይት ሲማቅቅ 40 ዓመት በሞላ
ጠገዴ ሲያለቅስ 40 ዓመት በሞላ
አዳርቃይ ሲያነባ 40 ዓመት በሞላ
ሲቀጣ አዲረመጽ 40 ዓመት በሞላ
ማይጸምሪ ሲባትል በዋይታ ሞላላ፤
ለደራጎን ቅርጫት ልታረገርጊ?¡
አንጥፊ¡ ጎዝጉዢ¡
ታጥቀሽ - አደግድጊ¡
ገዳይሽ ሲማጣ ቄጤማ ነስንሺ¡
የሰቲት ሰሊጡ ሲጋዝ በቀፈቱ
የሰቲት ጥጡ የትግራይ ልማቱ
የደበር/ወድአከር/ ወድአርባ ሲጭነው ጉልበቱ
ሙጫና ቀርቃኸው ሲሰደድ በባቱ፤
አወን - ለውርዴትሽ
… …
አንጥፊ¡ ጎዝጉዢ¡
ታጥቀሽ - አደግድጊ¡
ገዳይሽ ሲማጣ ቄጤማ ነስንሺ¡
አረግርጊ¡ አረግርጊ¡ አረግርጊ¡
አባወራ መክኖ መሬቱ ሲያነባ
ኮበሌውም ፈልሶ ባድማው ሲባባ
ጉብል አልባ ሆኖ ምሾ ሲነሰራፋ፤
መከራ ከርፍቶ መኖር ሲያንኮራፋ
አንጥፊ¡ ጎዝጉዢ¡
ታጥቀሽ - አደግድጊ¡
ገዳይሽ ሲማጣ ቄጤማ ነስንሺ¡
አረግርጊ¡ አረግርጊ¡ አረግርጊ¡
ልብ በይ እማማ
የመሆኗ ማማ …
ከልጆሽ ጓሮ ሲጫን በያይነቱ
ከማሳሽም አብራክ ሲጋፈፍ በክቱ
በቀይሽም ከብሮ ስታየው ፈንድሻ ጎልብቶ በብርቱ፤
አንጥፊ¡ ጎዝጉዢ¡
ታጥቀሽ - አደግድጊ¡
ገዳይሽ ሲማጣ ቄጤማ ነስንሺ¡
አረግርጊ¡ አረግርጊ¡ አረግርጊ¡
የዕትብትሽ ፍሬዎች በድርቀት ሲናኙ
በዬደረሱበት ባሩድ ሲሆን ቁርጡ
በእያሉበት ቦታ በግፍ ሲቃጠሉ
መድረሻ አልቦሽ ሆነው በግፍ ሲታደኑ፤
እትብትሽ ሲታረድ፤
ለባሩድ ሲማገድ …
አንጥፊ¡ ጎዝጉዢ¡
ታጥቀሽ - አደግድጊ¡
ገዳይሽ ሲማጣ ቄጤማ ነስንሺ¡
አረግርጊ¡ አረግርጊ¡ አረግርጊ¡
በመድፍ ጢስ ተውጠው ጽላታት ሲባክኑ
በነፃነት እጦት መስጊዶች ሲበኑ
በርትህም ድርቀት ምዕመን ሲመንኑ
ገዳማት ተደፍረው በትዕቢት ሲተክኑ፤
በደመነፈስ ዕብነት ከች ሲል አክሳሚሽ …
በልም ሊደቁስሽ - ሰልቆ ሊልግሽ - ጎብልልም
ሊልብሽ .. ህም - ህም … እምምምም
አንጥፊ¡ ጎዝጉዢ¡
ታጥቀሽ - አደግድጊ¡
ገዳይሽ ሲማጣ ቄጤማ ነስንሺ¡
አረግርጊ¡ አረግርጊ¡ አረግርጊ¡
ትኩሱ አይቀረው … ቀዝቃዛው አይቀረው …
ተራራው አይቀረው … ልሙ አፈር አይቀረው …
ለምለሙ አይቀረው … እንጨቱ አይቀረው …
አዕዝርት አይቀረው… እንሰሳት አይቀረው …
ሞተሩ አይቀረው - ቁሳቁስ አይቀረው…
ውሃሽም አይቀረው … መብራት ሃይል አልቀረው…
የተጋሩ አውሬ ሁሉን አግበስብሶ ቦዶነት አስቀረው።
እቴዋ ጎንደሪት የልብ አዘንተኛ …
…. ይህ ከሆነ ደስታሽ የምታልሚው
… ይህ ከሆነ ዕልምሽ የምታቅጂው
… ይህ ከሆነ ራዕይሽ የ40 ዓመት ተጋድሎሽ
እቴዋ ጎንደሪት በእንቅልፍ ውስጥ አልነቃሽ።
የልጅነት ወጉኑ፤ የልማድ ያባቱን
የከተማ ወጉን፤ የእድገት ትሩፋቱን
የገጠሩን ማርዳ፤ ድኮት አብነቱን
የሐሤት አልባሳት የተፈጥሮ ጌጡን …
…. ተነጥቀሽ - ተገፍተሽ - ተገለሽ - ተዘርፈሽ
- ተራቁተሽ - ተወርሰሽ … መንምነሽ …. መንምነሽ፤
ምናምንም ሁነሽ በግፍትር ተጥለሽ … አንደ ማበሻ ጨርቅ የትሜና ወድቀሽ …
ጥቃትንም ታጥቀሽ፤ ቀጤማ በትነሽ፤ ቀዩን ጃኖ
ለብሰሽ …. ልታደገድጊ መሰናዶ አሟልተሽ?!
ህም!
እምምምምምምምምም-ምምምምምምምምምም-ምምምምምም!
ገዳይሽ ሲመጣ ከሆነ አልልልልታሽ? ከሆነ ፍስሃሃሃሃሽ?
ከሆነ ሰናይይይይሽ ….?
እቴዋ ጎንደሪት ማተብሽን ቀበርሽ።
·
ሥጦታ … ትቢያ ለብሳ ለመኖር እንኳን ላልተፈቀደላት እቴዋ ጎንደር ይሁንልኝ።
(15.11.2017 - ዙሪክ)
·
ለድንግል ስደት
የፈቃድ ፆመኞች እንኳን ለፆመ - ጽጌ መፍቻ ለዕለተ - ቁስቋም አደረሳችሁ።
እግዚአብሄር
ይስጥልኝ። መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ