ጎንደር ያንቺ ለታ።

ጎንደር ያንቺ ለታ።
ከሥርጉተ - ሥላሴ 14.11.2017 (ዙሪክ - ሲዊዘርላንድ)

„ክፉ ሰው ዓመፃን ብቻ ይሻል፤ ስለዚህ ጨካኝ መልአክ ይላክበታል።“ (ምሳሌ ምዕራፍ ፲፮  ቁጥር ፲፩)

የትግራይ ልማቱ ለጎንደር ህልፈቱ
የትግራይ ጥጋቡ ለጎንደር ፍልሰቱ፤
የትግራይ ፍካቱ ለጎንደር ክመቱ
እንደ ሰንጋ በሬ ቅለባ ስባቱ።
ግራዚያኒ አለ ትንፋሹ ይገዛል
ትኩስን ሬሳ መቋደሻ ይሻል።
ማሳው ይታረሳል በደሙ ገበሬ፤
ተወረረች ጎንደር በተጋሩ አውሬ
በመቀስ አለቀ ተሸንሽኖ ፍሬ
ከሞት ላይ የሚኖር የጎንደር ዕንቡጥ
መድርሻ አጥቶ፤ መጠጊያ ተነጥቆ መኖር ይቧጥጥ።
የመጣ ቢመጣ የጥጋብ ማብረጃ …
የልጅ ግብር አምራች የህልፈት ምድጃ።
አንገቱን ቀርቅሮ ያድጋለኝ ትውልድ
ጎንደር መወለዱ ያሰላል ማጭድ
ያ … ቢያልም፤ ያ … ቢያቅድ መሸጋገሪያው …
የጎንደሩ ቀንብጥ መተላፊያው።
እጅሽ አመድ አፋሽ የደም ምንጭ ግብረኛ …
የሰው ልጅ በማቅረብ ዋና ማበርተኛ፤
ለንግሠ - ሥልጣኑ  ለቅብ መሸኛ።
መሬትሽ ምሽጉ መች መዳኛ ሆነሽ፤
ቀን እያሰገረ ያቀርባል ጥሬ ዕቃ፤
ይሉንታ ለሌለው የሥልጣን ዕቃዕቃ።
የመጣ ቢመጣ የሆነውም ቢሆን …
ያሰበውም ቢያስብ ያለመውም ቢሆን …
የከነዳው ደርሶ ግቡነን ቢያገኘው፤
ጎንደር ያንቺ ለታ ይወራረድ በያው።
ታሪክሽም ደምቆ ሲነገር ጎልብቶ፤ በታጠቅ ሲታ ….
አንገት ለማስደፋት ይከስማል ይሉንታ፤ ይታወጃል ሌላ የማታ - የማታ፤
ቀርቶብሽ መወደስ የቃላት ሙሽራ
አንጀት ይታረዳል በመታበይ ጎራ።
ታ ከፋዩ አንድዬም አይሰ
ለአንቺ የሆነለት ይከፋል አይልም።
ስለአንቺ ሳስበው፤ ሳስበው ሳስበው ሳስበው፤ ሳስበው ሳስበው ….
ሳወጣው ሳወርደው፤
ባልመው ባልመው - ባልመው፤ ባልመው ባልመው - ባልመው …
ልሰበስብ ሳሸው …
መንፈሴን አላመው።
ለምን ተፈጠረ ናፍቆት ʼሚሉት …
ለምን ተፈጠረ መውደድ ʼሚሉት …
ለምን ተፈጠረ ማፍቀር ʼሚሉት ….
ለምን ተፈቀረ ትዝታ ʼሚሉት
ለምን ተፈጠረ ሽውታ ʼሚሉት
የማይገፉት ጠላት የናት ኩላሊት።
ልቤንም ብሰጥሽ፤ ሁሉንም ብሰጥሽ መች ይበቃሽና፤
ያሳደገኝ ጡትሽ መክሊትሽ ሁነኛ።
·         የዚህ ሥነ - ግጥም ሥጦታ በዬትኛውም ዘመን የልጅ ቁርጥ ለምታቀርበው፤ ትቢያ ለብሳ፤ ድንጋይ ተንተርሳ ለኖረችው፣ ለምትገኘው ጎንደር ይሁንልኝ። ወደፊትም ከሟሟያነት ውጪ ጎንደር ቀን ይወጣለታል ብዬ ለመተንበይ በፍጹም ሁኔታ አቅም ያንሰኛል። ከዛ ለሚወለድ ሰው ራሱ የቤት ሥራ / አጀንዳ ጎንደር ሆና አታውቅም - ለፖለቲካ ማሟቂያ ብቻ ….  
·         ፎቶው ላይ የምታዮዋቸው እነኝህ ታዳጊዎች ሴት ህጻናት ደግሞ ዛሬ እንዲህ በመገፋት ክርፋት በውስጥ ሐዘን ኩርምት ብለው ያድጋሉ። እነሱም፤ ጫካውም፤ ዱር ገደሉም ነገ የሰው ጥሬ ዕቃ፤ የሰው ልጅ ብርንዶ አምራቾች ተረኞች ናቸው። አይቀርላቸውም። የዛሬው የመከራ፤ የጉስቁልና እድገት ለነገ የሌሎች የሥልጣን ምኞት ማወራረጃ ምቹ ድልዳል ነው። „ከፋኝ“ ያለ ሁሉ ጎንደር ሄዶ ይመሽጋል። በዙርና በጥልፍልፍ የጎንደር ሸበላ፤ የጎንደር ቀንበጥ፤ የጎንደር ሙሽራ ይታረዳል፤ ይታጨዳል። የጎንደር የተፈጥሮ ሃብት ይመነጠራል። ይቃጠላል፤ ይነዳል። ይወረራል። የጎንደር ትውልድ ካለ ተተኪ እንዲህ ይማቅቃል። መሬት ሐብት ነው። በሥልጣኔና በዕድገትም በኩል ሰላም በሚታወክባቸው ቦታዎች ፈንጅ ይታቀድላቸዋል። ገበሬው እራሱ ተረጋግቶ ማምረት እንኳን አይችልም። አይደለም በተለያዩ የጎንደር ከተሞች ብልጽግና ሊታለም ቀርቶ፤ ጎንደር ላይ የተፈጠረ ሂደት እራሱ አማራችነቱ መገለል በትልቁ፤ ካቴና ዙሪያ ገባውን፤ ሰኔልና ቹቻ፤ ዋይታና ደመር ብቻ ነው። ስለዚህም ከልብ ተሁኖ ሊታሰብበት፤ ሊመከርበት የሚገባ አምክንዮ ነው ስለ ጎንደር። ከግብር በኋላም ዞር ብሎ የሚያዬው የለም። እንመሰግናለንም እንኳን የለም። እንዲያውም ውለታው ቀርቶበት እንደ ሰው ስለተሰዋለት ነገር እንኳን ጠንከር ብሎ ስቅዛት - ውጋት ይከተላል። 
ስለሆነም ብልህነትን መሰነቅ አለበት ጎንደር ከልቡ ሆኖ፤ አላምጦ መዋጥ አለበት። ጎንደሬው ለሌላው የሚሰጠውን ትንሽ ቀንሶ ብጣቂ ነገር፤ እንዲያው ቁራጭ አትኩሮት በያለበት ሆኖ እትብቱን ይሰባት። ጎንደር ነገ እዬራቃት ነው፤ ረፍዷል - የዕውነት ረፈዷል። እልህን አምንጭቶና ከብክቦ በተደሞ በመሆን የትውልዱን ቀና ብሎ እኩል የሚታይበት ዘመን አንዲመጣ መትጋት አለበት። ይህ ካልሆነ የነገ የእርድ ገብያም፤ የብርድ ዘመንም ቀጣይ ነው። … በተለያዬ መልክ እና ቁመና በሰላ ስልት ጥቃቱ፤ ተፅዕኖው፤ ጭቆናው፤ መገለሉ ረቂቅ ነው። ሁልጊዜ እራስን፤ ውስጥን፤ ማንነትን በመሸለም ጎንደሬው የቀጣዩን ትውልድ መንፈስ ማትረፍ በፍጹም አይችልም። አንድ ቦታ ላይ መቆም አለበት። መቀበልንም ይልመድ። እንዲደራደሩት ያስገድድ። ልጆቹን ላልባሽነት ሳይሆን እንደ ሌሎቹ በሥማቸው ለማዬት ይጓጓ … ለዛ ይማስን፤ ለዛ ይታትር … ለዛ ይውጣ ይውረድ  … የጎንደር ቀጣይ ትውልድ ከስሞ ማዬትን ካልናፈቀው ….
የኔታ ሙሉቀን ጎንደር ላይ ስለተካሄደው የጤና ጉባዔ ቀይ ጃኖ ለባሾችን እና ብክነቱን ዘገባ ጽፎ አንብቤዋለሁየመርዶ ጃኖ ይሆን? በሉ አባጨጓሬው አቶ አባይ ወልዱ ሲመጡ ባለቀይ ጃኖዎቹ፤ የጥቃት ሰልፈኞች ልጆቻችሁን መሬት ላይ አንጥፋችሁ፤ በአበባ፤ በቄጠማ/ በጉዝጓዝ እልል ገዳዬ መጣ ብላችሁ ጠብቁበእግር ብረት ልጆቻችን እያደናችሁ ስላሰራችሁልን፤  ስለገደላችሁን፤ ዘሩን ስለ አመከናችሁት፤ ስለቀበራችሁን፤ ትብያ ስላለበሳችሁን፤ ውርዴትን ሰንግቻሁ ስላጠጣችሁን፤ ታሪካችን ሰርቃችሁ ስለቀማችሁን፤ ከአንገታችን በላይ በተስፋፊነት ስለጎረዳችሁን፤ ከሥራችን ነቅላችሁ የቁም እስረኛ ስለአደረጋችሁን፤ አሸባሪም ስለአላችሁን  „መከበር አለባችሁ¡“ ብላችሁ ሸር ጉድ በሉ ለግራዚያኒ ሐውልት ለቀትር እባቡ ለአቶ አባይ ወልዱ ልዑክ፤ ሌላማ ምን የቀረ ነገር አለ። ውርዴት ውርዴ ነው። ጉርጉሮች! በውነት አልቅሱ! በባዕቱ መተንፈስ ከማይፈቀድለት ህዝብ ተፈጥራችሁ ትቀልዳላችሁ። ያሉነን የነገ ትውልድ ልጆቻችን ይህን ይመስላሉ። የጤና አቋማቸውን ሆነ ውስጣቸውን በዚህ በለጠፍኩት ፎቶ ማዬት ይቻላል። ስለሆነም ቀዩን ጃኖ ለባለጊዜዎች ለነተጋሩ ለወርቃማ ምርጥ ዜጎች ተወት፤ ለእናንተ ካለልክ የተሰፋ ነው የሚሆነው - ታይታ ... የ6ኛ ደረጃ ዜግንት እንኳን የላችሁም … ይህን አለመረዳት በውነቱ ፍ - ግ - ነ - ት ነው።

„ጎንደር በተካሔደው 19 አገር አቀፍ የጤና ጉባኤ 2.7 ሚሊዮን ብር ባክኗል (ዬኔታ ሙሉቀን ተስፋው እንደ ዘገበው)“


እዬር ካለ ከመንበሩ እግዚአብሄር ይስጥልኝ። መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።