አማራነትህን በውስጥህ የጸደቀ ዕለት፤
አማራነትህን በውስጥህ የጸደቀ ዕለት
የመከራውን ጉድጓድ ጥልቀት ታዬዋለህ!
„ትእዛዝን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፤
መንገዱን ቸል የሚል ግን ይጣፋል።“
(መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፲፱ ቁጥር ፲፮)
·
ብአዴን የአማራ ህዝብ የሞራሉ
የብቃላ አጋፋሪ ነው።
„በባህር ዳር ፈለገ ህይወት ሪፈራል ሆስፒታል የወሊድ አገልግሎት ለማግኘት ብንመጣም በአልጋ እጥረት እየተቸገርን ነው፡-እናቶች“
- · ቁስለት።
በስውር ሴራ ለሁለት ትውልድ ለዘለቀ መከራ ተሸካሚነት ትክሻውን አዳላድሎ በለኝ ያለው
አማራ ዛሬ መከራውን በበርሚል ሳይሆን በውቅያኖስ ተዘፍቆበታል። ይህ መከራ ይቀጥል ዘንድ ደግሞ ዶር. ተስፋዬ ደምመላሽ በአጽህኖት
መርዛዊ ምክራቸውን በኩራት ይለግሳሉ። አማራ በራሱ ስቃዮች፤ በራሱ መከራዎች፤ በራሱ ማንነት ዙሪያ የሚደርስበትን ሁለገብ ግልጽና
ስውር ፍዳዎችን ተሸክሞ ወይንም ሰውሮ ዘመን እንብዛም እንዳለኮረፈባቸው ወገኖቹ ነፍሱን እንዳወጣ ሽጦና ለውጦ እንድርቺ እንድርቺ
ጨዋታውን ይቀጥል ባይ ናቸው የታሪክ ተመራማሪው የአማራ ሊህቁ።
- · እንዲህም እንሆ ሆነ፤ ሞት ሁልጊዜ አዲስ ነውና።
ዛሬ በአማራ ቴሌቪዥን አንድ እጅግ አሰቃቂ ዜና
ሰማሁኝ። የ26 ዓመቱ ተኝተህ በለኝ ውጤት ዛሬ በአማራ ርዕሰ ከተማ በባህርዳር ፈለገ ህይወት ሆስፒታል የአራስ እህቶቼን ሰቆቃ
በተደሞ ሆኜ ከሳተናው ድህረ- ገጽ አዳምጫለሁኝ። አራስና እናት እና አራስ ህፃን ልጇ ስሚንቶ ላይ ተኝተው ሌላ የስቃይ መከራ እንዲቀበሉ
መገደዳቸውን በዕይኔ አየሁኝ። እነዚህ እናቶች ከመህንነት ክትባት ያመለጡት የአማራ እናቶች ናቸው እንዲሁም በአማራ ክልል ኑሯቸውን
ያደረጉ ኢትዮጵያዊ እናቶች ናቸው። ለዚህም ነበር ኢህአፓ አማራ መሬት ላይ ለዛውም ቋራ ሌሎች በብሄራቸው መደራጀት ይገባቸውል፤
ነገር ግን አማራ በብሄሩ መደራጀት የለበትም በማለት ገና ከጥዋቱ ድንጋጌ ነድፎ የአማራ ወጣቶች ለኢህአፓ ጋሻ ጃግሬነት ብቻ ሲዋደቁ፤
ደማቸውን ሲያፈሱና አጥንታቸውን ሲከሰክሱ የኖሩት። በአንፃሩ ሌሎች ደግሞ ሃይላቸውን አጠናክረው፤ የራሳቸውን የቤት-ሥራ ሰርተው
ዛሬ በመንበረ ሥልጣኑ ላይ ተቀምጠው የራሳቸውን ወገኖች ብቻ ነጥለው ዓይንህ - ጥርስህ በማለት ለሰሚም የሚከበድ ዓይን ያወጣ ሥርዓት
ዘርግተው በሁሉም ዘርፍ በበቃና በበቀለ ሁኔታ ይገኛሉ። ምርጥ ዜጎች እነሱ ብቻ ናቸው። ሰሞኑን አንድ ዜና አዳመጥኩኝ። የመስቀል
በዓልን ምክንያት በማደረግ ነበር። „ብቸኛዋ ድንቅ ተዋናይት“ ሰላም ተስፋዬ በተጠዬቀችው የዲያፐር የማስተዋቂያ ሥራ ላይ በገንዘቡ
ባለመስማቷ ምክንያት፤ የእኛ የሚሏት ወገኖቿ ጉዳዩን በባለቤትነት ወስደው፤ አስፈራርተውም ይሁን ጉባ ሰጥተው ከድርጀቱ ጋር ተነጋግረውና
አግባብተው የአንድ ሚሊዮን ብር ሽልማት ይባል ስጦታ ይባል ተሰጣት። እንደገናም ገና ልጅ ስትወልድ፤ እሰቡት ገና አግብታ ስትውልድ
የፈለገቸውን ያህል ብትወልድም ድርጅቱ የነጻ የዲያፐር አገልግሎት እስከፈለገቸው ድረስ እንደሚያሟላም አዳምጫለሁ። እነሱ እንደዚህ
ናቸው። ዝንፍ የለም። ለወገኖቻቸው የማይሆኑትን ሆነው ይሆናሉ። https://www.youtube.com/watch?v=UOTYg-CJ94c
„Selam
Tesfaye I ሰላም ተስፋዬ በ1 ሚልዮን ብር ሰርፕራይዝ ተደረገች።“
የአማራ ወላድ ደግሞ ህክምና አጥታ በሆስፒታሉ ኮሪደር ላይ እስከ አራስ ልጇ ቀዝቃዛ ስሚንቶን
ነፍሷን አደራ ስጥታ መከራውን ታያለች። የራሄልን ዕንባ ኤሉሄ ትልበታላች። ለአንዱ ገነት ለሌላው ሲኦል፤ ለአንዱ ወርቅ ለሌለው
የዛገ ብረትንት፤ ለአንዱ የዲታነት ጣሪያ ለሌላው ደግሞ የትቢያ ተቀላቢነት ይህች ናት ኢትዮጵያ። አድሎ ዝርም ትውር
የማይልባት¡ የክትና የዘወትር የማይለይባት¡ ለጓል ትግራይ ብቻ የሆነች ኢትዮጵያን ማዬት … ሥርዕወ ትግራይ የብርሃንነት
ዘመናት ሊቀ ጵጵስና። ሌላዋ ቆንጂት ጓል ትግራይ ማረዬ ደግሞ ጎንደር ተወልዳ ያደገቸው ሞዴል፤ ተዋናይት ፍርያት የማነ ደግሞ
መስቀልን በሽልማት ተፍነሽንሻ ያውም በሀገረ አሜሪካን ላይ ተውባና ደምቃ 2010 እንኳንም የእኛ ብቻ ሆንክ ትለዋለች።
„https://www.youtube.com/watch?v=HXn6T7WiLv8 Ethiopia ሰበር ዜና! ተዋናይት ፍርያት የማነ በአሜሪካን አሸነፈች፤“ ሚዲያ ላይ ስትሄዱ በተወሰነች የጊዜ
ገደብ በዬቦታው በዜናው ልክ ሪፖርተሩ በሙሉ እነ ተጋሩ ናቸው። ቃለ ምልልስ የሚደርግላቸው ዬድርጅቱ ሃላፊዎች እንሱ ናቸው፤
ዘጋቢዎችም እነ ሰመረ ምሩጽ፤ እነ ዮሖንስ ፍሰሃ ወዘተ ወዘተ … ያቅለሸልሻል። ይሉኝታ የሚባል አልሰራላቸውም፤ ሚዛን የህሊና
የሚባልም እንዲሁ አልፈጠረላቸውም። ምኑን ጉድ ይሆን ፈጣሪ አምላክ የዶለብን? እሰከ መቼ? አይታወቅም። የምትቀር አንዲት የማሳ
ፍርፋሪ የለችም። መግዛት ማለትም፤ መርገጥ ማለትም፤ የበላይነት ማለትንም፤ ማግበስበስ ማለት፤ መጠቀም ማለትንም ተክኽነውበታል።
ይሄን ነው ሽምጥጥ አድርገው በጠራራ ጸሐይ የሚክዱት።
እዚህ ውጭ ሀገር አለሁ፤ ለአማራ ቆሜያለሁ የሚለው „የአማራ ድምጽ“ ደግሞ እንኳንስ እንደ እነ
አጀሬ ጠጋግኖ ደካሞችን ማብቃት ቀርቶበት በቅተው በተግባራቸው የበቀሉትን
ትንታጎችን የአማራ ጋዜጠኞችን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሥነ - ልቦናቸውን በስለት በተገኘው አጋጣሚ ይዋጋል። ይህ
የመረቀዘ የቂም ቤተኝነት በአማራ ወጣቶች ሥነ - ልቦና ላይ የተሳለ አዲስ የበቀል ሰይፍ ነው። አንድ የአማራ ድምጽ የአማራ
ወጣት ጋዜጠኞችን ማስተናገድ አቅቶታል። ለቃለ ምልልስ እንኳን ተጠይፏቸዋል። ብልህንት ከማን ጅልነት ከማን? ለማን ነው እዬሰራ
ያለው? ፍርድ ለራስ ነው ጎንደሬ እሰቡት፤ የመደዴ ጉዞ ዛሬን አያበረክት ነገንም አያሰክን። የቀደመ የተግባር ማሳ፤ በድካምና
በልፋት አብቅሎና አስበሎ፤ ምርጥ ዘርን በራስ ነፍስ የህሊና ቅኝት መቃኘት ሲጋበው እንዲህና እንዲያ … በስንቱ ይታዛን?
የድካምን ፍሬ አሳልፎ መስጠት …
·
ሌሎችስ?
የጎንደር እና የጎጃም ማህበራት አማራው የራሱን
የቤት ሥራ ሳይስራ ለደረሰበት መከራ እና እንግልት እንዲቀጥል በትትርና ይሰራሉ። እነቅፋቶችም ናቸው። እነ አቤቶ? እነ አቤቶ ደግሞ
በዕንባ ስንቅነት ኑሮውን በከተመው የአማራ ህዝብ ላይ የዓለም አቀፉን ማህበረስብ ሳይቀር በማሳመን ስቃዩ፤ ሰቆቃው፤ በደሉ፤ የዘር
ጥፋቱ ተጠያቂ አልባ፤ ተከሳሽ አልቦሽ በማድረግ ተግተው እዬሠሩበት ይገኛል። እንዲያውም በበዳይነት ክስም አለበት። አዬ አንተ ፈጣሪ
ከቶ የት ነው ያለኸው? ትናንትም፤ ዛሬም፤ ነገም በመከራ አዟሪት በግራና በቀኝ በፍዳ ጢስ ታፍኖ፤ ማንነቱ ታዳፍኖ ታሪክ አልባ
ሆኖ እንዲቀር የተበዬነበት አማራ ዛሬ አማራ ነኝ ማለቱን ሲይ የትናንት፤ የዛሬ፤ የነገ አዲስ የመከራ ቀንበር ተሸካሚነቱ በውልና
በቅጡ መረዳት ይችላል። ማግሥትም በምን ጥቁር ፈትል እዬተሸመነ ስለመሆኑ የእኔ ብሎ ሊያዳምጠው ብቻ ሳይሆን እልህን አምጦ ወልዶ
በሰከነ የተግባር ቋጠሮ የመከራውን ረግረግ ለመሻገር መቁረጥ አለበት። የራሱን ቡቃዮወች እቅፍ ድግፍ አድርጎ በመያዝም አብነታዊ
ጉዞ መጀመር አለበት።
ይህን ማድረግ ከተሳነው አማራነት በዳይነት፤ አማራነት
ጠፊነት፤ አማራነት ከሳሚነት፤ አማራነት ተፋቂነት መሆኑን የተቀበለ ትውልድ እራሱን እያቃጠለ በሬሳው አመድ የሚስቅ የጅሎች ዋናተኛ
መሆኑን መቀበል ይኖርበታል። የትግራይ ልጆች በዘመናቸው የቤት ሥራቸውን ሠሩ፤ አንተንም እራስህን አማራውን አስለፈው፤ ስንቅና ትጥቅ
ሆነህ፤ ደምህንም ገበርህ። እናም ብልጦቹ በአገኙት ድል ሙሉ ተጠቃሚና ሙሉ የፍስሃ ቤተኛ ሆኑ። ለወገናቸው ባላ እና ወጋግራ በመሆን
በዝርፊያም፤ በወረራም፤ ሌላውን በመጨቆንም፤ ሌላውን ረግጦ በመግዛትም ሁሉም ፈሰሱ ለብርሃናሟ ለታላቋ ትግራይ እና ተጋሯዊነት መሆኑ
የቤት ሥራቸውን ጊዜ ሳያጥፉ በፍላጎታቸው ውስጥ ሳይሾልኩ ተግተው በመስራታቸው ነው። ጠብ የምትል ጅልነት የለም ከእነ አጅሬ ቤት።
ቀዳዳው ሁሉ የሚወታታፈው አረርም መረረም በራሳቸው የደም ጋን ውስጥ ነው ክተት የሚለው።
·
የውክልና እርግጫ።
ትግራይ 5% የማይሞላ ህዝብ ይዛ በወረራ ዬያዘችውን
ወልቃይት፤ ጠገዴ፤ ራዕያን ህዝብ ጨምራ 35% እስከ 45 % ያለውን አማራ እንዳሻት ስትፈልግ በግርድና፤ ስትፈልግ በሎሌነት፤ ስትፈልግ
በአንጋችነት፤ ስትፈልግ በአጣቢነት፤ ስትፈልግ በአንጣፊነት፤ ስትፈልግ በጠራጊነት ሰጥ - ለጥ አድርጋ ቀጥቅጣ አማራን ትገዛዋለች። እሜታዋ ትግራይ ለዚህም ያመቻት
ዘንድ ልቧን የገጠመችለት ኤርትራዊው አቶ በረከት ስምዖን፤ በስውር ማንነት የሚባዝኑት አቶ አዲሱ ለገሰ፤ ትግሬው አቶ አለምነህ
መኮነን፤ ጉራጌው አቶ ንግሡ ጥላሁን፤ ኦሮሞው አቶ ደመቀ መኮነን እናም ሌሎቹን ከኢህአፓ በተገነጠለ ዝንጣፊ ያደራጃችውን ስጦ ብአዴን
በሚባል የከንቱ ከንቱ ድርጅት አማካኝነት በበላይነት አማራን እያሳረደች፤ እየረሸነች፤ እያሳደደች፤ እያሰረች፤ እዬወረረች፤ እዬከዘነች፤
ዘቅዝቃ ሰቅላ እዬገረፈች፤ ሥነ - ልቦናውን እዬቀጠቀጠቀች፤ የፈለገችውን ያህል እያጋፋፈች ትራሷን ከፍ አድርጋ ተንደላቃ በሰላምና
በሐሤት ትኖራለች። ለነገሩ ሌብነትም ሆነ ገዳይነት ይህ አረመኔነት የሚያስቀና ወይንም የሚያስመካ አይደለም። የነገን ትውልድ የሚያስቀጣ
እና ትወልድን የማያባረክበት ይሆናል። የህዝብ አንዲት ጠብታ የእግዚኦታ ዕንባ ፈሳ በከንቱ አትቀርም። እዬርን ታንኳኳለች። ፍትህዋም
ከመርግ የገዘፈ ማግሥትን ታመጣለች።
- · የርትህ የቀን ጥሰት።
ማወዳደር የሚቻለው ማወዳደር ከሚቻል ነገር ገር
ብቻ ነው። ማወዳደርም በማይቻልበት ሁኔታ ከፓሪሷ ከመቀሌ ከተማ ቀርቶ፤ ለኗሪዎቿ የነጻ ህክምና ከተሟላ አገልግሎት ጋር በገፍ ከሚናኝበት
ከሲዊዟ አዲግራት ከተማ ጋር እንኳን የአማራ ርዕሰ መስተዳደር በተባለው በባህርዳር ከተማ አራስ እናቶች ስሚኒቶ ላይ ተኝተው በተጨማሪ
በሽታ እነሆ በግፍ ይታረሳሉ 26 ዓመት ሙሉ። ይህ ነበር የብአዴን ተልዕኮና ግብ። ያልተሰራበት በጀት ተብሎ ወደ ትግራይ የሚተላለፍበት
ሚስጢርም ይኸው ነው። የሰቲት ሁመራ የነጭ ወርቅ ማለትም የደበር፤ የሰሊጥ፤ የጥጥ፤ እንዲሁም የወድአርባ መዋለ ንዋይ ተረፈ ዕሴት
እንኳንስ 27 ዓመት የአንድ ዓመቱ ገቢ ብቻ ዘመናዊ ሆስፒታል ባህርዳር ላይ በገነባ ነበር። ይህም ብቻ አይደለም ምርቱ አማራ ክልል
የሆኑት በባርነት፤ ቀረጡና ፈሰሱ ደግሞ በጌትነት ለትግራይ የሆኑ የብልጽግና ተቋማት ሁሉ በ27 ዓመት ሲመነዘር ዛሬ ትግራይ የደረሰችበትን
ጣሪያ የነካ የቁንጣን ዘመናዊነት መፎካከር በተቻለ ነበር። ነገር ግን ትግራይ አማራ ያለሆኑትን አጋሰሶቿን በአማራ ሥም አማራ መሬት
ላይ ተክላ አማራን ባልተወለዷት የድርብርብ፤ የንብርብር መከራ ተሸካሚ እንዲሆን ፈረዱበት። ከዚህ ጋር ተያይዞ የዓለም አቀፉ የግበረ-
ሰናይ ድርጅትም ርስተ ጉልቱ ትግራይ ላይ የከተመ ሲሆን ኢፈርት ሌላው የአዱኛው የማይነጥፍ ፏፏቴ ነው። ዝቀሽ ድሎት በዝቀሽ ጠበንጃ።
ጣና ላይ ተስቦ ትግራይ ላይ በፍሰሃ የሚንቦላካው
የአማራ አንጡራ ሃብት፤ አማራ መሬት ላይ ያሉ ጥቃቅን ጅምሮች በመብራትና በውሃ እጥረት ምክንያት ከስመው ባለሃብቶች የተረከቡትን
መሬት አስረክበው ሥራ ፈትነትን ተቀላቅለዋል። ይህ በ27 ዓመት ሲመነዘር ደግሞ ሌላው የአፓርታይድ ድርብ አሳርን ያሳያል። ይህን
ተሸክመህ ቀጥል፤ ለጽድቅ ይሆንሃል ነው የሚሉት የአማራው ሊሂቅ ዶር. ተስፋዬ ደምመላሽ አሜሪካ ላይ ዘመነው። ለግድለት ለክስመት!
እግዚኦ!
- · የራስ ባለአደራ።
ዛሬ የአማራ ወጣት ከውስጥ ተነስተህ ዕውነትን
በተባ ተግባርህ ሞግተህ የቤት ሥራህን መወጣት አጀንዳህ ማድረግ ይኖርበሃል። ጀመርኸውል መጀመሩ መልካም ቢሆንም ከግብ ማድረሱ ግን
ትውልዳዊ ተልዕኮህ ነው። በአንተ ሥም የተኮፈሰው የባህርዳሩ እንኮሸሽሌ በፍጹም ሁኔታ አንተን የማይወክልህ ስለመሆኑ የትግልህ ልብና
እንኩላሊት ሊሆን ይገባል። ራስህን ብቻ ሳይሆን ነገን መታደግ የምትችለው
ወስጥህን የሚያዳምጥ ውስጥህን ስታገኝ በቻ ነው። ልብህን ፈልገው። ተግተህ በውስጥህ ንጥረ ነገር ላይ መሥራት አለብህ - በተለይ
የአማራ ወጣት። ዛሬም የአንተ ነገም የአንተ ነው እና። ዕውነት ለመናገር በግጨው በደረሰው አስደንጋጭ ዜና ከጎናቸው በሃሳብ ለመገኘት
ያልፈቀድንበት ምክንያት አሳማኝ ቢሆንም፤ አራት ሆነው መግለጫ ሲሰጥ አንድ የአማራ አንደበት መስማት አለመቻላችን ደግሞ ቁጭታችን
እልህ ፈጥሮብን ከአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጎን የመሰለፍ ቀዳሚው ትውልዳዊ ድርሻች መሆን አለበት። ቄሮ እነኝህን የዘመን ጥበቦች በወል
እስገድዶ ያስመጣው በተጋድሎው ጥራት ነው። የአማራ ትውልድም ይህን ልብ ሊለው ይገባል።
ከውስጤ ሁኜ ሳስበው አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ብቻቸውን
ናቸው። አጋዢ እና እረዳት የላቸውም። አይዞህ ባይም በቅርብ የላቸውም። በእሾህ ታጥረው ነው የሚገኙት። ህመማቸውን፤ ስቃዬቸውን፤
ኑሯቸውን፤ ዛሬ ቁጭ ብለን በማስተዋል ብንመረምረው የሆዳቸውን አውጥተው የሚነግሩት አንድም ሰው ባጠገባቸው የእኔ የሚሉት የለም።
በሰላይ ተከበዋል። ሁላችንም የምናወርድባቸውን እሳት ከአናታቸው ላይ ነዶ አመድ ነው የሆነው። በሃሳብ አላገዝናቸውም። አይዞህ አላልናቸውም።
ከዛም ተነጥለው በእኛም መንፈስ ተነጥለው የሁለት ሀገር ስደተኛ ነው የሆኑት - ምስኪን። እንግዚአብሄር ይመስገን የለማውያን መንፈስ
በመከራ ቀናቸው የተገኘላቸው ቅዱስ መንፈሳቸው ነው ብዬ እኔ በግሌ አስባለሁ። የኦህዲድ ወላዊ ንዑድ መንፈስ ለአቶ ገዱ አንዳርጋቸው
ብቸኛው አጽናኝ መንፈስ ነው። ለዚህም ሊመሰገኑ ይገባቸዋል ኦህዲዶች። አሁን አሁን ሳስበው ይህ ረቂቅነት ኢትዮጵያን የሚታደጋት
የምልክት ደወል ይመስለኛል። በዚህ የፍቅራዊነት መንገድ ብቻ አውሬውን ታግሎ ማሸነፍ ይቻላል። መቼም አውሬው መርዙ ከሥረ መሠረቱ
ካልተነቀለ መዳንም መኖርም አይታሰብም እና።
የወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥርዕዎ መንግሥት ባለፈው
ዓመት ከኦሮሞ ብቻ ዘጠኝ ሚ/ሮች ሲሾሙ አንድም አማራ አልተሾመም ነበር። ያ ሹመት አማራን በፍጹም ሁኔታ ያገለለ ብቻ ሳይሆን የበቀሉን
ልኬታ በጉልህ ያሳዬ ነበር። አማራ በመንፈሱ ቅጥቅጥ ይሆን ዘንድም የተሴረ ነበር። ምን ታመጣላችሁ በማለትም በመታበይ ገዢው የወያኔ
ሃርነት ትግራይ የበቀሉ ጽዋ ማወራረጃ ነበር። ይህ በዚህ እንዳለ ውጪ ሐገር ደግሞ የአማራ መደራጀት እራሱ በአማራው ሊሂቅ ቀንዱ
የተመታ ሆኖ ተልፈስፍሶ እንዲቀር የተደራጀና የተቀነባበረ ዘመቻ ነበር። አንድ ጊዜ የጎንደር/ ሌላ ጊዜ የጎጃም ማህበር በማለት።
ይህ ብቻ አይደለም 2016 ለ2017 ለመርህ መንደፊያ የአውሮፓ ህብረት ባዘጋጀው ሪፖርት ላይ 5 ቦታ የኦሮሞያ ችግርን በጥልቀት
እና በተመስጦ፤ ሁለት ቦታ የኦጋዴን ችግር በተወሰነ ደረጃ ሲያነሳ ያን 20 ሺህ ወጣቶች የታሰሩበት፤ 26 ህጻናት አንባ ጊዮርጊስ
ላይ በሚሰቀጥጥ ሁናቴ በሱዳን ወታደሮች የተረሸኑበት፤ 50 የባህርዳር ነዋሪዎች በግፍ የተረሸኑበት፤ በዬቁጥቋጦው እጅግ በሚዘገንን
ሁኔታ ገዳያቸው ያልታወቁ ወጣቶች ተንጠልጥለው የታዩበት፤ የጎንደር ቅዳሜ ገብያ እና የደበረታቦር እስር ቤት ቃጠሎና ጥፋቱ፤ በተፈጥሮ
ላይ የወረደውን ግፍ ሪፖርቱ አግሎ፤ ነጥሎ፤ ዕወቅና ሳይሰጥ ነበር
ያለፈው። አንድም ቦታ „አማራ“ የሚል እንዳይገባባት ሆነ እጅግ በጥንቃቄ የተሰራ ነበር። ብዙሃኑን የ አማራ ማህረሰብ ቢመለከት
ተጋድሎውን ጥሶ ወይንም ደፍጥጦ፤ ብጣቂ ሰብዕዊነትም ሆነ ተፈጥሯዊነትም የፈለሰበት የደባ ተግባርን የተከተለ እጅግ አስተዛዛቢ ሪፖርት
ነበር። ለዚህም ነው ዘንድሮ ባለፈው ዓመትም በ2016 ሪፖርት መነሻነት በተደረሰው ስምምነት እና በተነደፈው መርሃ ግብር አማካኝነት
የተከናወኑ ተግባራት ላይ ተመሳሳይ ግድፈት በ2017 የታዬው። የ2017 ሪፖርትም ከአምናው የተለዬ የተሻለ ይሆናል ብዬ አላስብም፤
ስለገለማኝ ዘንድሮ አልፈተሽኩትም። በማን ፈቃድ እንደሚዘጋጅ ከታወቀ ትርፉ ድካም ብቻ ነው። ሥር አለው። ታቅዶ ነው የሚከናወነው።
ይህ አማራ መሆንን ሳይሆን ሰውን ማዕከል ማድረግ ብቻ በቂ ነው። ቅኖች ቀስቃሽ አያስፈልጋቸውም። በዚህ ውስጥ የነገ ኢትዮጵያን
ማሰብ ፈታኝ ነው።
- · አማራና የተስፋው የውጭ ሀገር አንባሳደሮች።
የአማራ ድርጀቶች አለነ ሲሉ ሰምቻለሁ፤ ከዬኔታ
አያሌው መንበር ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ። አልነበሩም። ቢኖሩማ ባለፈው ዓመት በሪፖርቱ ላይ ተነስቼ የጻፍኩት ጹሁፍ ከልባቸው
ገብቶ ማስገልበጥ በቻሉ ነበር። በተሄደበት መንገድ ሄደው። በሥላሴው
አዕማደ ሚስጢርም መንገድም ቢሆን። እነሱም ተምረዋል ሌላውም ተምሯል። እነሱም ወንድ ናቸው ሌላውም ወንድ ነው። የማይቻለውን፤
በማይደፈር ውስጥ ሆኖ ችሎ ማሳዬት ነው ጀግንነት ማለት። በሌላ በኩል ተስፋነት በማለት ሳይሆን ተግባር ላይ፤ መሬት ላይ በሚታይ
ሰብል ነው የሚለካው። ያን አድርገው ቢሆን ኖሮ ዘንድሮ የተዛባው ዕውነት ጠርቶ ማዬት በተቻለ ነበር። ሚዛኑን የጠበቅ እንዲሆን
የማደረጉን ሃላፊነት በፍጹም ሁኔታ አማራነታቸውን የተቀበሉት ድርጅቶች ትውልዳዊ ድርሻቸውን አልተወጡም። በሚቻልበት ሁኔታ እያሉ።
አውሮፓ ማህበር እኮ የፖርቹጋል ብቸኛ እርስተ ጉልት አይደለም። የእያንዳንዱ ሀገር ፓርቲዎች ሁሉ እዛ የራሳቸው ተጽዕኖ አላቸው።
አንድ ሰው ማግኘት እንዴት ያቅታል? 0% በ100% ላይ ተሆኖ አይዟችሁ፤ ተስፋችሁን ይዘናል ቢባል ለእኔ የውርንጫ ድካም ነው።
ወና። እርግጡን ብነግራችሁ የአማራ ሊቃናት - ተሸንፋችኋዋል።
አሁን ኢትዮጵያ መሬት እዬገዛ ያለው የአማራና
የትግሬ መንግሥት ነው ከመባል ወዲያ ምን መራራ ዜና መስማት፤ ምንስ ሃሞት ሪፖርት ይሆን የሚጠበቀው - ለአማራ ሊሂቃን። ሌላው
ከሲአይኤ ጋር መሥራትን፤ ከተለያዩ ሀገሮች ፕሬስ ድርጅቶች ጋር መሥራትን ጭራሽ የታሰበበትም አይመስልም። በ2017 መሸኛ እና በ2018
መግቢያ ላይ የታዬው የደባ ድርደር የበላይነት ያገኘው ሃሳብ በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ደግሞ ትራስን ከፍ አድርጎ ተኝቶ፤ የዛሬ
ዓመት የሚታይ ይሆናል። ውጪ ሀገር ለሊሂቃኑ ምን የተግባር ማሳ አለ ከሎቢ ሥራ ውጪ? ይሄ „ሁለገብ ትግል ነው ስልታችን“ የሚባለው
ቀልድ ነው። ተሞክሮ አልሠራም። አዬነው እኮ ህዝብን በበላህሰብ ከማስቀለቀል
በስተቀር። መጀመሪያ ከደጃፋችሁ ያለውን ሃላፊነት ተወጡ አቅሙ፤ ክህሎቱ፤ እልሁ፤ ረመጡ ከውስጥ ከሆነ። አንድ ትንታግ ተደማጭ የሆነ፤
ሞግቶ መርታት የሚችል ሊሂቅ አንዴት አማራ ይጣ? ለዛውም ቁልጭ ያለ በፖሊሲ ደረጃ የተነደፈ „ጸረ አማራ“ የግራ ቀኙ የማስፈጸሚያ
ፖሊሲ እያለ … አማራ እናት ሊሂቅ ልጅ አለወለደችንም? ከቶ የት ይሆን ያላችሁት?
ስለሆነም እኔ በግሌ ከዛ ብቻቸውን እጣ ነፍሳቸውን
በበለሃሰብ ተከበው፤ በሰላይ ተውጠው፤ መግቢያ መውጫቸው ተስንጎ በፍጥጫና በግልምጫ ያሉት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ምን እንዲያደርጉ
እንጠብቃለን? በሚቻል ሀገር ያልቻላችሁ የአማራ ሊሂቃን የቱ ላይ ይሆን ሰቀቀኑ ሆነስ በደሉ የከረፋችሁ? የቱ ይሆን የወገናችሁ
እንግልት የጎመዘዛችሁ? ተስፋ ብቻውን የነገ ስንቅ አይሆንም። ተስፋ ብቻውን ፕሮፖጋንዳ ነው። ፕሮፖጋንዳ ደግሞ ጤዛ ነው።
ከቂምና ከበቀል፤ ከምቀኝነት እና ከጥላቻ፤ ከቅናት
እና ከግል ኢጎ የጸዳ አንድ ጠንካራ ሚዲያ እንኳን ማቆም አልቻላችሁም የአማራ ሊሂቃን ተባብራችሁ። ብቻቸውን ወጣቶች በግራ በቀኝ
የሚሰነዘርባቸውን ወከባ ተቋቋሙ። ተፋለሙ። ኮከባችሁ፤ ንጋታችሁ አንድ የምርመር ጋዜጠኛ እንኳን አይዞህ ባይ አጣ። የሰብዕዊ መብቱ
ተሟጋች ጋዜጠኛ፤ የሥነ - ልቦና ሙሁሩ ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው ደከመ። አንድ ሰው ሊረዳው፤ ሊያግዘው፤ አይዞህ ሊለው ከቶውንም
አልቻለም። በዐለም አቀፉ ማህረሰብ የሚያገኘው ዕወቅና እንኳን ክብረታችን አላላችሁትም። የአማራ ሚዲያ ተብዬው እሱን ሲፎካክር ማየት
በራሱ ሽንፈት መሆኑን ያመለክታል። ሲጀመርም እኔ ተናግሬአለሁ። ሆድ ዕቃውን ስለማውቀው። አንዲህ ዓይነት ሰወች አይደለም ለማህበረሰብ
ጤና ሊሰጡ ቀርቶ ለራሳቸውም የማይሆኑ ናቸው። ነፍሳቸው አሉታዊ ነው። በግማሽ የተፈጥሮ ጸጋ ነው የሚኖሩት። ሌሎች ደክመው፤ ጥረው
ግረው፤ ተግተውም ያስገኙት ሰብልን በርስተ ጉልትነት ሲሰጠው፤ እኔ ይህ ከሰማይ የወረደለት ጸበል ተጠምቆበት ይፈውሰዋል ብዬ ነበር
… ግን የማይድን አይድንም፤ ይህን ሰላላና መላላ መንፈስ ተይዞም ከግብ ለመድረስ ህልም ነው - ለእኔ በግሌ። ሸር ክፉ ነገር ነው።
ስውርነትም የትውልድ ጸር ነው።
- · ጣውንትነት።
ይሄው ድውይ ነፍስ አሁን የአማራን አይን በአገኘው
አጋጣሚ ሁሉ እንሆ ይታገላል። ተሳከለትም። መንፈሱን የሚመታበትን ዘዴ አስልቶ ድምጽ በሌለው ባሩዱ አቃጠለው። እኔ አላዳምጠውም፤
ግን ዩቱብ ላይ የወጣት ጃዋር መሃመድ ቃለ ምልልስ የሚል አይቸዋለሁ። ይሄ መልካም ነገር ነው። ከፍቅር ትርፍ እንጂ ኪሳራ የለም።
እንዲህ ዓይነት መንገዶችም ህዝባዊ ጣዕም አላቸው። ነገር ግን የተመረጠበት ወቅት ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው ጫካ ውስጥ ስለወለዱ መከረኛ
የአማራ እናቶች እና ሞታቸውን በዘገበበት ወቅት ነበር። የአማራ ድምጽን ጋዜጠኛ ለዛውም አማራ ሳይሆኑ የሴራ መንገድ ስታስቡት የወያኔ
ሃርነት ትግራይን ሊፈታ የማይችል የሴራ መቃብርን ወጥነት፤ ሩቅነት በተመሳሳይ ሁኔታ ታዩታላችሁ። ሴራ ለተገፋ፤ ለተሳደደ ማንን
ሊጠቅም?
አውላላ ሜዳ ላይ ነበር የጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው
መንፈስ የተቀጠቀጠው። አንድ ለእናቱ እኮ ነው ይህ ወጣት። ለአማራ የግዞት ህይወት ብቸኛው ተመራማሪ ነው ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው።
የአማራ የጌጡ ህዋስ ነው። እሱን ለመታገል ነው ወጣት ጃዋር መሃመድን ለቃለ ምልልስ የተመረጠበት ምክንያት። ወጣት ጃዋር እኮ ከዘንድሮ
ይልቅ አምና ለአማራ ተጋድሎ በግሉ ሆነ እሱ በሚመራው ሚዲያውም እንደ ራሱ አንድ ዋቢ አጀንዳ የያዘው አብይ ጉዳይ ነበር። ለምን
ያን ጊዜ ቃለ ምልልስ አልተደረገለትም? ወጣት ጀዋር አህመድ የኦሮሞ ሚዲያ ኔት ወርክ አስተዳዳሪ ባለፈው ዓመት በተገለለው የአማራ
ተጋድሎ ዙሪያ የሚገርም አቅምም፤ ግልጽ አቋም ነበረው በተጋድሎው ዙሪያ። ከሌሎች አክቲቢስቶች ተለይቶ ጥርት ያለ መንፈስ እና የነጠረ
ግንዛቤ ነበረው።
የሆነ ሆኖ ያዬሁትና የታዘብኩት ነገር ትግሉ ለማን
ስለመሆኑ የውሉ ውልብልቢትን ለመያዝ እስኪቸግረኝ ድረስ አዲስ የሚበልጥ ትንታግ ቅንና ጨዋ የአማራ ወጣት ጋዜጠኛ እንዲወጣ በፍጹም
አይፈለግም። ደም ያስለቅሳል ማህጸንን? ህሊናን ያኮማትራል። ለማን ነው ለመሆኑ እዬተሠራ ያለው? ለአማራ ወጣት የማይሆን ሚዲያ
ከቶ የማን ተስፋ ሊሆን ነው የአማራ ድምጽ ከተባለ? ለአማራ መከራ ተማራማሪውን፤ ብቸኛውን አንድ ዓይኑን ነው የተፈታተነው፤ የታገለውም
መንገዱ ይጠዘጥዛል። … ጎንደርም ጥቁር ለብሳ ታልቅስ። አማራም ማቅ ለብሶ ያልቅስ። ኢትዮጵያም ጠቀራ ለብሳ ታልቅስ - ሴራ ሲነግሥባትና
እንዲህ ሲቅስስባት፤ ወጣቱ ሲፈራባትና ሲገለልባት፤ ተሰደው እንኳን ወጣት ጋዜጠኞች ሰብሳቢ የላቸውም - በተለይም አማራ ከሆኑ።
እንዲህ ዓይነት የስብአዊነት ጋዜጠኝነት/ ከጋዜጠኛ ወንድማገኝ ጋሹ በስተቀር በሌላ አልታዬም። በጨዋነት እና በሙሉ ሥነ - ምግባር
ቢመሳሰሉም ከእሱ በተሻለ ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው የወያኔ ማንፌስቶ የማስፈጸሚያ ህዋስ በሆነው የአማራ ትውልድ የዘር ምንጥረ ተኮር
ተግባሩ ይልቃል። እጅግ ደማቅም ጉልላት ነው። ለእኛ ለቅኖች ዘወዳችን
ነው። ለምቅኞች ደግሞ መቅሰፍታቸው ነው። የተፈራውም ለዚህ ነው። ቅናት የበላው መንፈስ የትውልድ ዕዳ ነው።
መከራ መስማት፤ መከራን ማዬት፤ ዕንባን ማደመጥ
የእለት ህይወቱ እንዲሆን የፈቀደው ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው ህይወቱን አመሰቃቅሎ እሰከ ዛሬ በሱባኤ ተጓዘ። ወጣትነቱንም ተላልፎ
እራሱን ረስቶ ስቃይን ፈቅዶ ተቀበለ። መከራ በተደመጠ ቁጥር፤ ፍዳ በተደመጠ ቁጥር፤ ሰቀቀን በተሰማ ቁጥር ሞት ያስመርጣል። በዬሰከንዱ
ስቃይ ሰቆቃ ማድመጥ፤ ያን መቻል ከሰው አቅም በላይ ነው። የሥነ - ልቦና በሽተኛ አለመሆኑ በራሱ የሚገርም ድንቅ ነገር ነው።
መኖሩ ለእኔ ብቸኛ ተስፋዬ ነው። የወሰነው ውሳኔም በጣም ትክክል ነው። እኔ ደስ ነው ያለኝ። ትውልዳዊ ድርሻውን እጅግ በሚያስደምም
ሙሉ ሞራላዊ ክህሎት የከወነ የዘመኑ ጀግናችን ነው። ወደ ህይወቱ መመለሱ የተገባ ነው። ላደረገው ትውልድ ከቶውንም ለማይረሳው ምዕራፍ
ከፋች ገድል ፈጣሪ አምላክ የልቦናውን ይሙላለት። ድንግልዬም ትከተለው። አሜን! ቢያንስ ቅኖች በህሊናችን በጸሎት አዘውትረን እንሰበው።
- · መፍቻ ለመሰንበቻ።
ብአዴን በአዲስ መልክ በአማራ ብሄረሰብ ደማዊ
ሚስጢር የበላይነት እስካልተዋቀረ ድረስ እንዲህ ተዥጎርጉሮ መፍትሄ ይገኛል ተብሎ ማሰብ በራሱ አይቻልም። በዬትኛውም ቦታ ያለ አማራ
ይህ ቋሚ፤ የማይደራደርበት አጀንዳው ሊሆን ይገባል። በአማራ መሬት ክልልህ ይህ ብቻ ነው ከተባለ አማራን „አማራ“ ብቻ ነው ሊመራው፤
ሊያስተዳድረው የሚገባ። 27 ዓመት እኮ ታዬ -በአጨዳ። ዛሬ ይህን ያሾለከ ዕለት ዳግሚያ ሞቱን ይሞታል - አማራ። አቅሙን፤ ጉልበቱን፤
መንፈሱን ትውልዱ ዘመን ባስረከበው የቤት ሥራው ላይ ተግቶ መሥራት አለበት። ቄሮ ለአማራ ተጋድሎ የደሙ ሚስጢር ነው። ቄሮ ለአማራ
ተጋድሎ የነፍሱ ማደሪያ ነው። ቄሮ ለአማራ ወጣት የእትብቱ ሁነኛ ዋቢው ነው። ቄሮ ለአማራ ልጅ ቅዱስ መንፈሱ ነው። ቄሮ ለአማራ
የደም ማህተሙ ነው። አማራ ለችግሩ - በችግሩ ዕለት በዕንባው ዕለት፤ እጅግ አጣብቂኝ በገባበት ወቅት ከጎኑ የተሰለፈው ቄሮ ለአማራ
ሩህ የስለት ልጁ ነው። በዚህ የመንፈስ ሃዲድ ብቻ የአማራ መፍቻ የለሽ ችግርን ደረጃ በደረጃ መሻገር ይቻላል። ኦህዲድ ብቻ ነው
ለአማራ ልቡን የሸለመው። በታሪክ እንዲህ ዓይነት የውስጥነት መሆንነት በመገኘት የተዘከረበት ወቅትና ጊዜ የለም። „የሚያድግ ጥጃ
ከገመዱ“ እንዲሉ እንዲህ ዓይነት የፍቅራዊነት ናሙናዊነትም በመንከባከብ የመንፈስን አቅም የትም ሳያፈሱ ለተገባው ብቻ መለገስ ይገባል።
„ሙያ በልብ።“ ከዚህ የተሻለ ሰማያዊ መንፈስና ዕንቁ ጊዜ ለአማራ ህዝብ የለም። ስለሆነም ከቅኖች ጋር አቅምን በመስተጋበር ማወደድ
ይገባል። „ልብ ያለው ሸብ።“
- · እርገት።
አንቺ እራስሽ ለምን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ
በአማራ ጉዳይ ላይ አትሰሪም የሚል ጥያቄ ሊያስነሳ ይችላል። እኔ የቀደመ ሁለት አጀንዳ አለኝ። አቅሜም ውስን ነው። እርእሱ እኔ
እምታገልለት „ድምጽ አልባዎቹ የኢትዮጵያ እናቶች/ ሴቶች ድምጽ የሚል“ ነው። የ40 ዓመት የእናቶች የእንባ ዘመናቸው ለእኔ ህመሜ
ነው። በዚህ ነው የምታወቀው። ከዚህ አጀንዳዬ መቼውንም አለውጣም። ነፍሴ ነው። እርግጥ ከዚህ ጋር ተያይዞ በወጣት ጋዜጠኛ ሴቶች
ላይም ልዩ ትጋት ነበርኝ። ለእኔ በአደባባይ ጋዜጠኛ እራሱን አስቀድሞ የውዳሴ ከንቱ ማህበርተኛ ሲሆን ከማዬት በላይ የተሳትፎ መስኬን
ምደረበዳ ያደረገ አጋጣሚ አልነበረም። ቅስሜን ሰብሮታል ያ እርምጃ። ለሌላው በካቴና ላሉት ጨርሶ አለማሳብ፤ ሃላፊነት የጎደለው፤
የተሰጠን ልበሙሉነት ምስክርነት የድርቀት ጎተራ ያደረገ፤ መንፈሴንም ያሸማቀቀ አሳዛኝ ቀን ነበር። ቃለ ምልልሱን ሳዳምጥ ደንግጬም
ነበር። አፍሬምአለሁ።
ከዚያ በኋዋላ በጋዜጠኞች ላይ እራሱን አስችዬ መጻፉን ሁሉ ከዛች ጽልመታዊ ቀን ጀምሮ አቁሜዋለሁ። እኔ ልታገልላቸው
እምፈቅድላቸው ጋዜጠኞች የማንፌስቶ ማህበርተኛ ላልሆኑት ብቻ ነው እንጂ፤ የሰውን ማዕከላዊ የነፃነት ህዋሳዊነት ለተላለፉት አይደለም።
ለዛውም የፖለቲካ አቋምን በኪስ መስጥሮ መያዝ ሲቻል እንዲያ የሚዲያ ቄጠማ ሲሆን ማዬት የልቤን ጣሪያን ግድግዳ እንዳያገግም አድርጎ
አፍርሶታል። አዝኛለሁ። ጽናቴንም ተፈታትኖታል። ስለዚህ እስር ቤት እያሉ ጋዜጠኞች የትኛው ምርጫቸው ስለመሆኑ ልብ መርማሪ አይደለሁም።
እንዲያውም አንድ ሰሞን ተሜ ተሰውሮ ስፍስፍ አድርጎኝ ነበር። ግን ተሜ ሲፈታ አቋሙ ምን ሊሆን እንደሚችል ስለማላውቅ ዝም አልኩኝ።
ከዚህ በተጨማሪም የፍቅር ተፈጥሮ እንደ አንድ የቀለም ትምህርት በት/ ቤት ደረጃ መሰጠት አለበት የሚል ሞጋች አጀንዳ ደግሞ ሌላው
የትኩረት መስኬ ነው። ዓለም አስፈሪ ሆነች። ከዚህ በላይ መሄድ አልችልም።
ራሱን የቻለ አጀንዳ ያላቸው የአማራ ተጋድሎ ታታሪዎች፤
የአማራ ማህበረሰብ የፖለቲካ ድርጅቶች መተንፈሻ ቧንቧቸው ሆነ የመረጡትን የትግል መሥመር ሥራ መሥራት ግዴታ አለባቸው። ዓላማቸውም
ሆነ ግባቸው በእርግጥም „አማራነት ይከበር“ ከውስጣቸውና ከህሊናቸው ከበቀ። ጊዜ የለም። ጊዜና ቦታ ደግሞ የማድረግን አቅም በመወሰን
የድልም የሽንፈትም ዳኛ ነውና።
የብአዴን የልግጫ ርግጫ ተያየዘዥ ምርኩዝ።
„ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ሆነበት የተባለውና ሁለት ጊዜ የተመረቀው የጎንደር የውሃ ፕሮጀክት መቋረጡ ተገለጸ“
„አማራነት ይከበር!“
የአማራ ተጋድሎ ወላዱ አብዮት መሪ፤ አብሪ፤ አሰባሳቢ፤
አደራጅ መርኽ።
„እንከባበር!“
የታጠቅ አንበሶች የ2010 የበዕለ - መስቀል
ብሄራዊ ጥሪ።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ