ሬሳ² አብረን እንቅበራቸው።

 

·       ሬሳ² ብረን እንቅበራቸው።

 

ዕለተ ሰኞ ማዕዶተ ጠባቂ

በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና

በቢሆነኝ የተብራራ ብራ

በሰብለ ህይወት አዝመራ

ለራህብ የሚራራ።

„ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁኝ።“

(ትምህርተ - ዕንባቆም ምዕራፍ 3 ቁጥር 17)








·       ሬሳ xሬሳ= ሬሳ²

·       ሙታን ማህበር።

አብረን ብንቀብራቸው ከተቀበረው የ አማራ ቀን ጋር ደስ ይለኛል።

ኑረውም አላመረባቸውም ማህበረ የቁም እንቅልፍ። ሎሌነትም አለው አይነት፤ ግርድናም አለው አይነት። ባርነትም አለው አይነት። እንደምን ለድንጋይ ዘመን ጠቀራ እንደዚህ የ እንብርክክ እንደሚሄዱ ይገርመኛል።

ለነገሩ ሙጃ ለከብት እንኳን አይውልም እንኳንስ ለሰው ልጅ። እኔ እሬሳ ቁሙ የሚሄድ ነው የሚሰለኝ። አብረን ተረዳድተን  እንጦርጦስ ብንልካቸው ምርጫዬ ነው። ሁሉ ነገር ኦነጋዊው ኦህዴድ ከ እናኝህ ሙታን ጋር ተመካክሮ፤ መስጥሮ ኢሁንታ ተሰጥቶበት ነው የሚከወነው።

እሰቡት ሬሳ ለድርድር፤ ሬሳ ለውል፤ ሬሳ ለክርክር ሲበቃ።

ሬሳ +ሬሳ= ሬሳ!

ማህበረ ሬሳ ሬሳነታቸውን የተሸከመው የሬሳ ሳጥን ህሊናቸው ገበርዲን እና ከረባት ሲሰቀለብት ግርም ይለኛል። እነኝህ ማሽንኮች የ ኢትዮጵያ፤ የስሜን ፖለቲካም ነቀርሳወች ናቸው። ኢትዮጵያን ከ አቶ ሌንጮ ለታ፤ ከዶር ዲማ ነግዖ ጋር ሆነው ቀበሯት። ለዚህ ነው አብረን እንቅበራቸው እምለው።

ማህበረ ከንቱ ልጅም ቤተሰብም ሊኖራቸው ይችል ይሆናል። አገር ውስጥም ውጭም። ግን የታሪክ አተላ ነው ልጆቻቸው ተሸክመው ይኖሩ ዘንድ የፈረዱባቸው። አወን አተለ። አንቡላም።

የአንቡላ ማንቆርቆሪያዎች የሞት ደመመን ተጭኗቸው በዕብነንነት እዬአረገዱ ይገኛሉ። ያልታደለ ከረባት እና ገበርዲንም ከ እነሱ ተጠግቶ አሳሩን ያያል። አቤቱታም አስገብቷል ሲባል ሰምቻለሁኝ። እሱም ጥሎበት።

 

 


ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

19.04.2021 

ከሙታን ማህበር የለም ተንሳኤ!

ከሬሳ ማህበር የለም ድህነት።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።