ውጽፍተ ወርቅ ሆይ እባክሽን ተለመኝን?
· ውጽፍተ ወርቅ ሆይ እባክሽን
ተለመኝን?
ዕለተ ሰኞ ማዕዶተ ጠባቂ
በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና
በቢሆነኝ የተብራራ ብራ
በሰብለ ህይወት አዝመራ
ለራህብ የሚራራ።
„የሰው ልጅ መንገድን ያዘጋጃል
እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“
በሰመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምለክ አሜን።
አንቺ የሰማይ እና የምድር ንግሥት ሆይ!
አንቺ የሰማይ እና የምድር እመቤት ሆይ!
አንቺ የሰማይ እና የምድር ልዕልት ሆይ!
እባክሽን ድረሽላት ለ ኢትዮጵያ!
እባክሽን ጠባቂ እረኛ ለሌላቸው ልጆሽ ድረሽላቸው?
አብክሽን እንባችን እሚያብስ ሙሴ ስጭን?
እባክሽን አይዟችሁ የሚል የአሮን በትር ስጪን?
እባክሽ የመፍትሄውን ጎዳና ቀይሽልን?
እባክሽን ከ ዕንባችን ጎን ቁሚልን?
እባክሽን አንቺ የንጽህና፤ የድንግልና፤ የቅድስና ብጽዕት እናታችን ሆይ
ድረሽልን?
መጽናናቱን፤ መረጋጋቱን አስልኪልን። ከልጅሽ ከወዳጅሽ አንድዬን ተማጸኝልን።
· ቅድስቴ ሆይ!
ዕውነቱን ብነግርሽ ውስጤ አለቀ፤
ውስጤ ተጎዳ፤
አቅመ ቢስነት ይሰማኛል።
ለሁላችንም አጽናኝ አረጋጊ መንፈስ ይልክልን ዘንድ ከአማኑኤል አማልጅን።
አስከፍተነዋል። ደስታችን ልክ አልነበረውም። ደስታችን በቅጡ አላስተዳደርነውም።
የተሰጠን ማስተዋል በውል አልተጠቀምንበትም እና ምርቃታችን ተነሳ። አብረንም
ወደቀን።
ኢትዮጵያ በማህበረ ዲያቢሎስ እጅ ወድቃለች። በባዕድ መንፈስ እዬነደደች
ነው።
እሙ እናት ዓለም፤ እናት ዓለም ሆዴ ድረሽላት። መልስሽን እጠብቃለሁኝ።
ጨንቆኛል እናት ዓለም። አይዟችሁ ባይ መንፈስ ቅዱስ ይላክልን ዘንድ ለኤልሻዳይ
አምላክ አሳስቢልን።
ድፍን ኢትዮጵያ ጭንቅ ላይ ነው። ድፍን አፍሪካም ጭንቅ ላይ ነው። ድፍን
ዓለምም ጭንቅ ላይ ነው።
ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አውሬ ያልሰከነ፤ ተናዳፊ፤ ተናካሽ፤ ተፈጥሮን ደርማሽ
ነውና እዬጨለመ ነው።
ንጋትን ንጋትን እንዲቀርብ አስደርጊልን። ይቻልሻል የቃል ኪዳን እናት
ድረሽልን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
19.04.2021
ወስብኃት ለእግዚአብሔር።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ