ኢትዮጵያዊ አይዛችሁ! ባለቤት የለውም። ስደት ላይ ነው።

 

·       ትዮጵያዊ አይዛችሁ! ባለቤት የለውም። ስደት ላይ ነው።

ዕለተ ማክሰኞ ማዕዶተ ይግቡ

በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና


በቢሆነኝ የተብራራ ብራ

በሰብለ ህይወት አዝመራ

ለራህብ የሚራራ።

„የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፡፡ መጽናናትን ያገኛሉና፡፡

(የተራራው ስብከት ማቲወስ ምዕራፍ 5 ቁጥር 4)

 

*   ማዕዶተ ይግቡ ባለቤት የሌላቸው ሁለመናወች የሚዳሰስብት።

 

·       ትዮጵያዊ አይዟችሁ በስደት ላይ! ባለቤትም የለውም።

·       ትዮጵያዊ ማጽናናትም ስደት ላይ ነው!

·       ትዮጵያ ከፍቷታል እምለውም ለዚህ ነው።

እንደዚህ ዘመን አረማሞ የለም። ድሃ የሚጠላ፤ ድሃ የሚጸዬፍ፤ ደሃን ማዬት የማይሻ፤ ገድሎ እንኳን አይዟችሁ! ማለት የሚሳናነው፤ ሰቅሎ አይዟችሁ! የሚል ቃል ለማውጣት ስቅለት የሆነበት፤ በሚሊዮን አፈናቅሎ ውስጡ በሐሴት ዳንኪራ የሚቧርቅ ከእንደዚህ ያለ አረመኔ ጲላጦስ መሪ ኢትዮጵ እጅ መወደቋ ውስጥ አለመሆኑ ይገርመኛል።

ዘመኑ ዘመነ ፍዳ መሆኑን የምታዩት ይህንን ጨለማ ሰብዕና አጅበው ምራን፤ ንዳን፤ እንደ ጋሬ ጎትተን የሚሉ ዕብን ሰብዕናዎች ናቸው። በዚህ የፍዳ ዘመን ወደ እንሰሳዊ ሰብዕና የተለወጠው ብዛት ወዘተረፍ ነው። ወደ እንሰሳ ስል ወደ ጫካው ማለቴ ነው እንጂ ውሾች፤ ፈረሶች እንደምን ታማኝ እንደሆኑ ጠፍቶኝ አይደለም።

·       ይዞህ! አይዞሽ! አይዟችሁ!

1.     ይዞህ!

ፆታው ታብዕት ለሆነ ወገን የሚሰጥ የርህርህና ስጦታ ነው።

2.    ይዞሽ

ፆታዋ አንስት ለሆነች ሴት የሚሰጥ የደግነት ሽልማት ነው።

3.    ይዟችሁ! አይዞን!

ለሰው ልጅ በሙሉ የሚሰጥ የርህርህና ትህትናዊ ስጦታ ነው።

·       ይዟችሁ! አይዞሽ! አይዞህ!

·       ይህ የርህርህና ልቅና፤ የደግነት ልዕልና፤ የሰውነት ማመሳከሪያ ብጹዕ ጸጋ ሰማያዊም ነው። ይህን ሰማያዊ ጸጋ ኢትዮጵያ ውስጥ ስደት ላይ ነው ያለው። ተጋድሎው ሰማያዊ ጸጋወች፤ ቅባዕወች፤ ስጦታዎች ሁሉ ስደት ላይ ስለሆኑ ወደ ቤተ -ቅድስናቸው ይመሰሉ ዘንድም መትጋትን ይጠይቃል።

·       በዚህ የጭካኔ የመቃብር ሥፍራ ዘመን ያላጠናነው ምንም ነገር የለም። አይዞህ! አይዞሽ! አይዟችሁ! አይከፈልበትም። በ ኦዳ ገዳ ሥርዕወ መንግሥት ግን ይህ አይታወቅም። ይህ ዕውቅና አይሰጠውም። ስለዚህም ነው አረመኔኔት ነግሶ የምናዬው። የ አሳ ግማቱ ከጭንቅላቱ እንዲሉ ሄሮድሳዊው ጠቅላይ ሚኒስተር አንዲትም ቀን በ አዬነው የ3 ዓመት የሞት መሪነት ዘመን አንድም ቀን ተስቷቸው አይዞህ አይዞሽ አይዟችሁ ቃል አውጥተው ሲናገሩ አልሰማነም። ጭካኔው ምቾት ይሰጣቸዋል፤፡ ሰው ሲንገላታ ሐሤት ያገኛሉ፤ ሰው ሲያለቅስ ፌሳታቸው ነው። የሰው ልጅ ሰቆቃ የሠርግ ውሏቸው ነው። ከዛቸው ጋር አብረው የሚሠሩትም በዚህው የ ጫካ አውሬነት ማዕቀፍ ውስጥ ይገኛሉ።

·       አይዟችሁ፤ አይዞህ፤ አይዞሽ ትህትናም ነው። ደግነትም ነው። ርህህርናም ነው። ለችግሩ ዕውቅናም መስጠት ነው። እሳቸው አይዞህ አይዞሽ አይዟችሁ ቃሉ ቢወጣ ላለው ወዘተረፍ ሰቆቃ ዕውቅና እንደመስጠት ይቆጥሩታል። ለዚህም ነው ከቃላቸው፤ ከ አንደበታቸው ተሰምቶ የማያውቀው። ይህ ልሙጥ የሆነ የሄሮድስ ሰብዕና ተሸክሞ ችግሩን ሁሉ ችላችሁ የምርጫ ካርድ አውጥታችሁ ምረጡኝም አለበት። ለዚህ ደመነፍስነት ከበቃ በላይም ሌላ አመከንዮ ቢኖር ቢደረግ የተገባ ነው። የሰናፍጭ ታክል ሰውኛ ጠረን ሳይታይባቸው እንሆ ሦስቱን ዓመት አጠናቀን ለሌላ ተጨማሪ 5 ዓመትመት ጉዞ ተጀመሯል።

·       አይዟችሁ! አይዞሽ! አይዞህ! ትውፊትም ነው። ኢትዮጵያዊ መለያችን። ግብራዊነታቸውን መገለጫ። የአብሮነታችን ዓርማ። የመተሳሰባችን - የመረዳዳታችን ጌጣችንም ነው። ዛሬ ደግሞ ስደት ላይ ነው። ያልተሰደደ፤ ያልተነቀለ፤ ቀዩን ለቆ ያልተባረረ አንዳችም መልካምነት፤ አንዳችም የደግነት ቃና፤ አንዳችም የእኛነታችን ሁነት የለም።

·       አውሬ መንፈስ አንደምን ሰውን ሊመራ ይችላል? ጭካኔ እንደምን አገር ሊመራ ይችላል? አይዟሁን የሸሸ ዕብድ መንፈስ እንደምን ውሎ ማደር ይችላል? አንዲትም ቀን ሊሰጠው የማይገባ ነው ይህ ዲያቢሎስ መንፈስ። እራቅኑን ያለ፤ ያለቀ፤ የወለቀ፤ የደቀቀ በክፋት የዘለበ፤ በጭካኔ የጨቀዬ፤ አረመኔ ሥርዓት መወገድ አለበት ብዬ ነው እማስበው።

·       ቀጠሮ አያስፈልግም።

ጸረ ሰው ጸረ ተፈጥሮን በቃ ለማለት! ግፉ እስከ አንገት ማሰሪያችን ደርሷል። በቃ!

 

 


ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

ሲዊዘርላንድ ቪንተርቱር።

27.04.2021

ተጋድሎዬ ለእኛዊነቱ አይዟችሁም ነው።

 
„እነሱን አትፍሯቸው አምላካችሁ እግዚአብሔር ስለ እናንተ ይዋጋል።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።