23/10/2021 ዬተፃፈ ነው። ፕ. ዶር መራራ ጉዲናም የጠቅላይ ሚኒስትርነትን ቦታ ምኞተኛ ናቸው። ቢሯቸው ግን ዕብድ የዘራው አዝመራ …… መጥኔ ለኢትዮጵያ ……… #ማደራጀት።
23/10/2021 ዬተፃፈ ነው። ፕ. ዶር መራራ ጉዲናም የጠቅላይ ሚኒስትርነትን ቦታ ምኞተኛ ናቸው። ቢሯቸው ግን ዕብድ የዘራው አዝመራ …… መጥኔ ለኢትዮጵያ ………
ማደራጀት በብዙ መልኩ ይከወናል። መስከ ብዙ ህብራዊ የሆነ የሙያ ዓይነት ነው።
በመምህራን ውስጥ የወላጅነት፣ የትውልድ ግንባታ ግዙፍ ድርሻ አለ፣ በህክምና ውስጥ የሰባዕዊነት መጠነ ሰፊ ድርሻ አብሮ አለ። እያንዳንዱ ሙያ ኤቲክሱ በሚፈቅደው ውስጥ ብዙ ተፈጥሮ ተኮር መልካም ጅረቶች አሉ።
በማደራጀት ውስጥ የመጀመሪያው አህዱ ጉዳይ እራስን ማደራጀት ነው። ከዚህ የሚቀጥሉት ሃሳብን፣ ራዕይን፣ ፍላጎትን፣ አቅጣጫን፣ ትልምት፣ ውሳኔን፣ አቋምን ማደራጀት ይጠይቃል።
አንድ መፅሐፍ ፀሀፊ ቢጋር ይኖረዋል የተግባሩ ቅደም ተከተል የሚያወጣበት፣ ዕርዕስ፣ የፊት ሽፋን፣ የጀርባ ሽፋን፣ መቅድም፣ መግቢያ፣ ጭብጥ ማጠቃለያ፣ መፍቻ እነኝህ በምዕራፍ፣ በዋና ዕርዕሰ ጉዳይ፣ በንዑስ ርዕሰ ጉዳይ ይደራጃሉ።
ከዚህ በላይ አንዳንድ ፀሐፍት ከተመክሯቸው ሊነሱ እና መዳረሻቸው ያው ሊሆን ይችላሉ፣ በጥናት መሰል ለሚያተኩሩ ጭብጡን የሚያጠብቁ ማጣቀሻዎችን ሊጨምሩ ይችላሉ። ለሁልም የተደራጀ ሃሳብ ያስፈልገዋል።
አንድ ሰው ራዲዮ ፕሮግራም ቢኖረው መግቢያው፣ ሙዚቃው፣ ዕርዕሰ ጉዳዩ፣ ማጠቃለያው፣ በዛ በተሰጠው የጊዜ ማዕቀፍ አብቃቅቶ ለመከወን ቢጋር ያስፈልገዋል።
ማደራጀት ሲባል ሰውን በማህበር፣ በዕድር፣ በቁቤ፣ ወይ በተቋም ማደራጀት ብቻ አይደለም። የተበተነን መንፈስ የመሰብሰብ፣ የተዝረከረከን ቤት በቅጡ በቀላል አያያዝ ማራኪና ሳቢ አድርጎ ማሰናዳት፣ ለሥራም ቀልጣፋ በሆነ ሁኔታ የማደራጀት አቅም ይጠይቃል።
እኔ ስፅፍ የሰውን ህሊና ሥነ - ልቦና አቅጣጫ እያሳዝኩ ነው። አትኩሮት ያጡ ጉዳዮችን ኮልኩዬ በቂ አትኩሮት ግንዛቤ እንዲያገኙ ማድረግ ነው።
ሙግት ላይ እሰራ በነበረበት ጊዜ የሃሳብ ፍሰት አንድ አቅጣጫ ብቻ እንዳይዝ፣ ያ ሃሳብ ብቻውን ተፅዕኖ እንዳይፈጥር ሚዛን ማስጠበቅ ነው ዓላማውም ግቡም።
ያ የሃሳብ፣ የዕውቀት፣ የምልከታ ህብራዊነት ኢንተግሪቲ ይፈጥራል። በልጆች ላይ በተለይ ይህን መሰል ተግባር ቢከወን ልጆ የሰፋ ምልከታ ሞጋች ሰብዕና ይኖራቸዋል። ያ ደግሞ ለጠራ ሃሳብ ልቅና እና ልዕልና መሰረት ነው።
የማይታይ ረቂቁ የተጋድሎ መስክ የሰውን ህሊና በተደራጀ የሃሳብ ሂደት ማልማት ነው። ይህ መስኖ በተፈለገው ያህል እንዳይቀጥል ችግሩ ሰፊ ነው። ፁሁፎች ሲታገዱ መስመሩ ይቆራረጣል። የሚያግቱት ወይንም የሚያሳግዱት አቅመ ቢስ ስለሆነ ሊያደርጉት የሚችሉት ያን ብቻ ነው።
አሁን የአቶ ልደቱ አያሌው፣ የኢንጂነር ይልቃል እና የአቶ እስክንድር መንግሥታዊ ዕገዳ የተደራጀ ሃሳባቸው ሃዲድ እንዳይኖረው የሰነፎች ገመድ ነው።
በዚህ ውስጥ በአማራጭ ሃሳብ የተባ ትውልድ ለመፍጠር ጋዳ ነው። ለዚህም ነው ከታቱ ያልተወጣው።
ሲጠቃለል በግለሰብ የሚፃፋ፣ የሚመሩ የኃሳብ ሠራዊት፣ የብዕር ፈንጂ ተደራጀሁ ከሚለው ተቋም የተሻለ ትውልድን በህሊና የማነፅ አቅም አለው። በተለይ ጥላቻ፣ ቂም በቀል፣ ኢጎ፣ ከሌለው። ኃላፊነት እና ተጠያቂነት በጠበቀ ሁኔታ ከተሰራበት ስኬት አለው። ለምን ቢባል የቢሮክራሲ እስር ስለማይኖርበት።
እንደ አጤ አብይ አይነት በቅምጥ ፍላጎት ውስጥ መንፈሱ የከተመ መከራ ያለባት አገር ግን ይህ ዕውን ሊሆን አይችልም። ግንቦት 7 ቢሆን ይኽው ነው መስመሩ። አቅም ማቀጨጭ፣ መቅበር፣ ማገድ መማገድም።
የሆነ ሆኖ የሃሳብ ድርጁነት ቅንነት ካለው ትውልድ የመገንባት አቅሙ አንቱ ነው። መደራጀት ጥበብ ነው። መክሊቱ ካልተዛባ።
ይህን ፎቶ ለአብነት እዩት። በዚህ ቢሮ አይደለም ሥራ ለ5 ደቂቃ መቀመጥ ይቻላልን? አንድ ደብዳቤ ለማውጣት እንደምን ይቻለል? የፖለቲካ ሳይንቲስ ሙሁር፣ መምህር፣ የብሄራዊ ድርጅ መሪ?
እንደምን ይሆን ቢሯቸውን የሚመሩት? ወግ አይቀር አገር መሪ ለመሆን እራሳቸውን አጭተዋል። የማደራጀት ሚስጢር በዚህ ይመሳጠር?
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
እናስተውል።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ