#የአማራ ማህፀን የ30 ዓመት ህማማት አቶ ደመቀ መኮነን።23/11/2023 ዬተፃፈ ነበር።

 

23/11/2023 ዬተፃፈ ነበር።
#የአማራ ማህፀን የ30 ዓመት ህማማት አቶ ደመቀ መኮነን።
ዕለተ ሰንበት ማዕዶተ ርትህወሰባዕዊነት
በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና
በቢሆነኝ የተብራራ ብራ
በሰብለ ህይወት አዝመራ
ለራህብ የሚራራ።
"ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ።"
(ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯)
የአማራ እናት ማህፀን አንድነት ነኝ ሲል ለዛ ማገዶ እሷ ናት።
 May be an image of 5 people and phone
የዜጋ ነኝ ሲባልም እሷ የቄራ ናት። የብሄራዊ ነኝ ሲባልም የልጅ ልኳንዳ ቤት አቅራቢ እሷ ናት። አማራ ነኝ ብሎ ሲመጣም እሷ ናት።
ለእሷ መገደል፣ መፈናቀል፣ ለልጇ መታገድ ግን አንድም ከጎኗ የሚቆም ድርጅት የለም። አንድም። አንድም የለም። እንደ ግለሰብ እምንቆም ብንኖርም የቆምንለት ነፍስ እኛኑ ተዋጊ ሆኖ ያርፋልዕድሉን አግኝቶ ለወግ ሲበቃ።
እኔ እምለው አንድ ነገር አለኝ። ይሳካለት እና ይካደኝ። አሁንም እምለው ይህንኑ ነው። እኔው ልማገድ የቁሩት ከሞት ይትረፋ እና ይካዱኝ። መካዱ ብቻ ሳይሆን ይታገሉኝ። ችግር የለም። የእነሱን ትቼ ለባለተረኞች ባለ ካቴና አይታክቴ ደግሞ እንደ አሙሏ ትማገዳለች።
ስለ አቶ እስክንድር እና ሰርኬ የዛሬ 15 ዓመትም ከጋዜጠኛ ብያንካ ጋር እታጋል ነበር ዛሬ ብቻዬን እታገላለሁኝ። ይኽው ነው ጥሪዬ። አያውቀኝ፣ አላውቀው። ሆላንድ መጥቶ ነበር። አልሄድኩም። ዙሪክ ቢመጣም አልሄድም።
የሆነ ሆኖ እነኝህ ተሰውረው የቀሩ የአማራ ልጆች ናቸው። የማናውቃቸው ብዙ ናቸው። በወለጋ ብዙ በጣም ብዙ። በነገሌ ቦረናን አሁን ስለተቆጣጠሩት ብዙ ይኖራሉ።
ህወኃት በያዛቸው በስሜን ወሎም እንዲሁ። የአማራ እናት ማህፀን ቄራ ነው። ይህን ለማስቆም የረባ አስተሳሰብ ያለው የፖለቲካ አቅም የለም። ትነት ብቻ። በቃ ትነት ብቻ። መጀመር እንጅ ፍፃሜ አልቦሽ ዳንኪራ። የምርኮኛው ብዛት የወረፋው ብዛት በሰልፍ ነው።
አሁንም የአማራ ውክልና ያልሆነ ሰው ተመርጦበታል። ዶር አንባቸው መኮነን ተገድሎ አቶ ደመቀ መኮነን እንዲቀጥሉ የተደረገበት ሚስጢር ይህው ነው።
አማራ መንግስት ኑሮት አያውቅም። አቶ ደመቀ መኮነን የአማራን ህዝብ አይወክሉም። ፌክ ናቸው። በዛ በላይ ዲስፕሊኑን መሸከም አይችሉም። ወንጀል ፈፅመዋል። ሰብዕናቸው ሙሉዑ አይደለም።
ጭምት መሆናቸውን ስቼ አይደለም። ብዙ አይናገሩም። አሳቻ ናቸው። ኢትዮጵያን እዬተበቀሉ እንዳሉ ይሰማኛል። ኦርቶዶክስ ተዋህዶንም። ሌላም የገዘፈ የሰብዕና ጥሰት አለባቸው። ከዚህቀደም ቅርናት ስል ፅፌበታለሁኝ።
የዳኑ መስሎኝ ነበር። አልዳኑም። የሆነ ሆኖ በአማራ እናት ደም ሸቅጠዋል። በቃቸው። በቃቸው። አብን የሳቸው ሱቅ በደረቴያቸው ነው። እንደ አሻቸው የሚያሾሩት።
በተመድ ስብሰባ ላይ ተገኝተው የመኮንኖችን ጭፍጨፋ ሲገልጡ የአማራ መኮንኖች ለማለት አልደፈሩም። ዝም ያልኩት ህወኃት እንዳይደላው ብዬ ነው።
አሁን ደግሞ አቶ እስክንድር ነጋ በእስር ቤት ተደበደበ። በቃ ከዚህ በላይ ጥቃት። ደስ ያለው ደስ ይበለው። ዓለም አቀፋ ማህበረሰብ ማወቅ ባለበት ልክ ማወቅ አለበት።
ከጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ በፊት በስሙ በተቀመጠው ግዑዝ ጋር የአማራ ልጅ በቅድሚያ መፋለም አለበት።
ቤት ሳያፀዱ በረንዳ አይገባም። ቅድሚያ ተጠያቂው ልጁን ውጭ ልኮ የሚያንፈራስሰ ምክትል ጠቅላይ ሚር// ውጭ ጉዳይ ሚር አቶ ደመቀ መኮንን ሊሆኑ ይገባል።
ልጆቻችን በዬዘመኑ የሚታፈኑት በስምምነት ነው። ጲላጦሱ አለቃ አቶ ደመቀ መኮንን ናቸው። ፀረ አማራ፣ ፀረ ሰሜን፣ ፀረ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ካፒቴን ደመቀ መኮነን በቃህ ሊባሉ ይገባል። በቃቸው። ገርዝዘዋል። ሻግተዋል።
በደም ነቅዘዋል። በበቀል በክተዋል። በሴራ ጨቅይተዋል። በሸፍጥ በክተዋል። ማሽንክም አረንዛም ናቸው። አዲስ አበባን ለኦሮምያ አሳልፈው የሰጡ አርዮስም ናቸው።
ካህዲም ናቸው። እንጥፍጣፊ የመታመን ቅርፊት የላቸውም። ስለሆነም በቃህ ማለት ይገባል። ለዚህ ሁሉ የ30 ዓመት ግፍ፣ ገደላማ ዘመን የዳረጉት የሳቸው መሰሪ ክር የሰፋው ጉዞ ነው። ክፋ አይናገሩም። አይለፈልፋም።
አይክለፈለፋም። ግን የልባቸውን አድብተው ይፈፅማሉ። ዶር አንባቸው መኮነን እንዴት እንደጣሉት ማዬት በቂ ነው። ይህን ብቻ በማጥናት ደመቀ ማን ነው የሚለውን ማወቅ ይቻላል። በዚህ ልክ ኢትዮጵያን በመሩበት ዘመን ለኩት?
ግርም ብሎኛል በተመድ ስብሰባ ንግግሩን አይተው ከደናግላን ጋር ሰወች ሲያለካኩ? አለመታደልን ያመሳጥራል። ንግግሩ ደረጃውን የጠበቀ ነበር።
ጥያቄው ኢትዮጵያ በዛ ልክ በአካልስ በመንፈስስ አለች ወይ ነው? ቀድሞ ነገር እነሱ እራሳቸው የኢትዮጵያን ልቅና በልዕልና ከውስጣቸው ያምኑባታል ወይ ነው?
እስክንድርን ያሰረ አመራር? ብጄ አሳምነውን ፅጌ በአደባባይ የረሸ አመራር ኧረ በህግ? ሰርክ በሰው ደም የሰከረ አመራር?
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
23/10/2021
በቃን አረንዛ አመራር!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።