ሌላው አዋሳ ላይ የአቤል ደም ይጮኃል ብለውን ነበር፣ የእሳቸው የደም ዘመንስ እዮርን አድነኝ አይል ይሆን? oct 20.2020

 

ሽሽት እና የሙት ዓመት።
የትናንት የፓርላማ ውሎ ሽሽት በበዛ ሁኔታ፣ መውቲነት በፍፅምና አይቻለሁ። ኃላፊነትን ወስደው አያውቁም ሄሮድስ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ሽሽት ላይ ናቸው፣ እሳቸው የማይሸሹት ቢኖር ብልጭልጭታን ብቻ ነው። ለምን ብትሉ የገዳን ወረራ፣ የገዳን አስምሌሽን፣ የገዳን ዲስክርምኔሽን ስለሚጋርድላቸው።
አፋር በ100 ቀኑ የሥራ ፕላናቸው የመጨረሻ የክልል ጉብኝታቸው ነበር። ደረግ የወደቀው ሰው በመግደሉ ነው ብለው ነበር። የአመክንዮ መፋለስ ወይንም የትንታኔውን ጮርቃነት በቀንበጥ ብሎጌ ሞግቻቸዋለሁ።
አሁንስ ነው ጥያቄው በሰርክ ሰው እዬሞተ ነው። በመንግሥት ሎጅስቲክ በሚደገፍ ሽፍታ። እና የመንግስታቸው ስንብት እንደምን አልታያቸውም። በሳቸው ሎጅክ አማካኝነት። አገላለፁ የቀጣይነት ቃናም አለው።
ሌላው አዋሳ ላይ የአቤል ደም ይጮኃል ብለውን ነበር፣ የእሳቸው የደም ዘመንስ እዮርን አድነኝ አይል ይሆን?
 
 No photo description available.
በዚህው በዓዋሳ ጉባኤ አንድ ተናጋሪ ባቀረቡት ነገረ የበርበሬ ገብያ አማካኝነት ምን ገብያው ብቻ ያልታመመ ማን አለ ብለው ነበር፣ እና ትናንት የጤናቸው ስለመሆኑ አንድ የፌስቡክ ጦማሪ አቶ ሻንቆ ካሳይ የጣፋትን አንብቤ ነበር።
ግን ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ያንግዜ የታማሚ ማህበርተኝነታቸውን ነግረውን ነበር እና ተሻላቸው ወይንስ ባሰባቸው ይሆን?
በጥቅሉ በትናንቱ የሙልጭታ ጭለጣ መውቲነት አዬሁኝ። አምላኪዎቻቸው፣ በፍቅር እፍ ያሉት ሁሉ ምኑን አንስተው ምኑን ከምን እንደሚያደርጉት ያያቸው ሰው።
ለዛቸው መጣጣ፣ ቃናቸው ሾጣጣ፣ አምክንዮቸው የተላመጠ አገዳ ነው የሆነው። የገረመኝ ከሁለት ሳምንት በፊት ገበሬው የፖለቲካ ውክልና የሌለው መሆኑን ጥፌ ነበር።
እስከ ትናንት ድረስ ማህበራዊ መሠረታቸው ዲታዎች ነበሩ፣ ትናንት ወደ ገበሬው ዳርዳር ሲሉ ነበር። ተማሪ ብሄር የለውም እንዳሉት ሁሉ አማራ ገበሬም ስላለው ከሃቅ ጋር ምን እና ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ያያቸው ሰው።
የሚገርመው በተፈጥሮ አደጋ በወንዝ ሙላትም፣ በአንበጣም የተቀጣው ምላዕት አነሰ ባይ ናቸው። ሳስበው በዓለም ደረጃ የህዝብ ቁጥር ከተቀዬሰው ፕላን ጋር መስተዋድድ ያላቸው ይመስላል።
በጎርፍም በአንበጣም አንድ ሚሊዮን የሚሆን ሁለመና ተጎድቷል ለሳቸው ይህ ትንሽ ነው። ምኑ ተነክቶ አይነት? ኢትዮጵያ እሳቸውን የተወ ከዚህ የባሰ መቅሰፍት ሁሉ ለማኝ ነው የሚመስሉት። አፋቸውን ሞልተው ጉዳቱ ትንሽ ነው ይላሉ። ምን ዓይነት ቤተሰብ እና ማህበረሰብ እንዳሳደጋቸው ፈጣሪ ይወቀው?
በጉዳቱ፣ በቀውሱ ጭንቀት፣ ኃዘን ድንጋጤ ሳይሆን እርካታ ነው ያዬሁት። እና እኒህ ሰው እና የኢትዮጵያ ህዝብ በዬትኛው ድልድይ ይገናኙ ይሆን?
አዲስ አበባን በሚመለከት እኔን ያመነ አልነበረም። አዲስ አበባን ለኦሮምያ ያስረከቡት 5 ቀን 2011ዓም ነበር። ስለቋንቋ አንስተው ያንጨባረቁት ሃቅ የሚገልፀው የውስጣቸውን የውሳኔ የውኃ ልክን ነበር።
ማጠቃለያ።
ጠቅላዩ አለቁ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
ኢትዮጵያ አምላክ ካላት መድህን ይስጣት ፈጣሪዋ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።