ክፋነት ስለምን ዓለምን ገዛት? ለምን? ክፋትን ጭካኔን የሚቋቋም ተቋም ለመገንባት ሃሳቡም ስሌላት።

 May be an image of 3 people, tree and text

ክፋነት ስለምን ዓለምን ገዛት? ለምን? ክፋትን ጭካኔን የሚቋቋም ተቋም ለመገንባት ሃሳቡም ስሌላት።
 
"ጥበብን አግኝ ማስተዋልን አግኝ አትርሳም፦
ልጄ ሆይ ከአፌ ቃል ፈቀቅ አትበል፦
አትተዋት ትደግፍህማለች"
ምሳሌ ምዕራፍ ( ፬ ቁጥር ፭)
 
ክፋነት ዓለምን እያስተዳደረ ነው። ጭካኔም ዓለምን እዬናጣት ነው። ምክንያቱን ለዘጠኝ ዓመታት ያህል መረመርኩት። የመፍትሄ ሃሳቡን እንደመጣልኝ #ለተመድ እና #ለአውሮፓ ህብረት ላኩኝ። የተከበሩት ተቋማት አክብረው መልስ ሰጡኝ። ግን ምንም አክሽን የለም። 10 ፖስተር አሰርቼ መለጠፍ ፈለግሁኝ። 
 
ግን ፕሮፌሽናሎች ቢሠሩት ብዬ አማከርኳቸው። ሽልንጉ እናቴ በምን አንጀቴ። ከዛ አንድ ቀን ዩቱብ ቻናል ከፈትኩኝ። እንዴት እንደሚሠራ አላውቅም። ባለሙያ እንዲያግዘኝ ጠዬኩኝ። ሲዊዝሻ ላይ ባለሙያ ውድ ሆነ። በቃ ዋናው የቃላት ፖስተር መሥራት ነው። እኔ ሳልፍ አንድ ቅን ሰው ዓለምን ሞግቶ ዕውን እንዲያደርገው ነበር ሃሳቡ። በቃ አዌርነስ መፍጠር። የፍቅር ተፈጥሮ ካሪክለም ተነድፎለት ልክ እንደ ማህበራዊ ሳይንስ እና የተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ትምርት ይሆን ዘንድ ነው ሙግቴ። 
 
መነሻዬ አንድ ጀርመናዊ ወጣት #ታዋቂ ለመሆን ያሳፈራቸውን የጀርመን ዊንግ አውሮፕላን ተሳፋሪወች እሱ ፓይለት ነው ፈቅዶ ከተራራ ጋር ማጋጨት ነበር ህልሙ። አሳካ። ሙሉ 15 ቀን CNN (ሲኤንኤን) ላይ የሚገርም ሽፋን አገኜ። ልዕልት አንጌላ ሜርክል ጠቅላይ ሚር ነበሩ የጀርመን። ሰፊ ሃዘን ነበር። አውረፕላን ውስጥ የነበሩ ለልምድ ልውውጥ የሚጓዙ #ተማሪወች ነበሩ። 
 
አስከሬናቸው ሲለቀም #አንሰፈሰፈኝ። ዓይኔ ቅል ቅል እስኪያክል ድረስ አለቅሳለሁ። እንቅልፍ አጣሁኝ። ያን ጊዜ አውሮፓን በተለይ ፈረንሳይን የአክራሪነት ጦስ ይንጣት ነበር። በዚህ ውስጥ ነው #ክፋነትን#ጭካኔን የት አመጣነው ብዬ ምርም የጀመርኩት። ብዙ አሰቃቂ ነገሮች በህይወቴ አይቻለሁ። ግን ያን ጊዜ ሃሳቤ ተሰብስቦ ስለምን #ክፋነት#ጭካኔ አብሮን ሳይፈጠር ሊመራን ቻለ ብዬ በጣም ሰፊ ጊዜ ወስጄ አሰብኩት።
 
ዬደረስኩበት ማጠቃለያ እኛ ስንወለድ ፈጣሪያችን መስለን ንፁህ ሆነን ሳለ #ክፋነትን የሚቋቋም ተቋም ስንወለድ ስለማይጠብቀን ለክፋነትም ለጭካኔም ተጋልጠናል ከሚል መደምደሚያ ደረስኩኝ። እና ዓለምን እጅግ ፈራኋት። ምን መደረግ አለበት ብዬም ከራሴ ጋር መከርኩኝ። ሰው ወዶ እና ፈቅዶ #ክፋም // #ጨካኝ አይሆንም። ክፋነት ጨካኝነትን ሊቋቋሙ የሚችሉ ተቋማት ስለሌሉን ይህ ተፈጠረ ብዬ እራሴን አሳመንኩኝ።
 
ሳስበው በሰው ላይ ሰው የሚቀናው ነገር፤ የሚሰራው ክፋት ሁሉ መጣብኝ። ዓለምንም አሰብኳት። የሰው ለሰው ግንኙነት እዬደበዘዘ ማሽን አፍቃሪ ጄነሬሽንም መፈጠሩን አዬሁ። የትም ቦታ ለሰው ያለ አመለካከት መቀነሱንም አስተዋልኩ። ይህ ሊሆን ግድ ነበር። 
 
ለምን።
 
1) ዓለማችን ለፍቅር ተፈጥሮ #ካሪክለም የላትም።
2) በፍቅር ተፈጥሮ ላይ አንድም ቀን የዓለም #አጀንዳ ሆኖ ውይይት ተካሂዶበት አያውቅም።
3) በፍቅር ተፈጥሮ ላይ ተግተው የሚሠሩ #የምርምር ተቋማት የሉም።
4) የፍቅርን ተፈጥሮ የሚንከባከብ ዓለም ዓቀፍ ዕውቅና #ተቋም የለም።
5) ፍቅር ፍልስፍና ነው። ነገር ግን የፍቅር ተፈጥሮ #ፈላስፋ የለውም።
6) ፍቅር ሳይንስ ነው። ይሁን እንጂ የፍቅር ተፈጥሮ #ሳይንቲስት ዬለም።
7) ፍቅር የዕውቀት ዘርፍ ነው። ነገር ግን በፍቅር ተፈጥሮ የሚሰራ #ኤክስፐርት የለም።
8) የፍቅር ተፈጥሮ ተፈጥሯዊ ነው። ነገር ግን ለተፈጥሮው ልቅና እና ልዕልና የሚተጋ #የምርም ተቋም የለም።
9) ፍቅር ሙያም ነው። ነገር ግን #የሙያ ዕውቀት ለማዳበር ዩንቨርስቲወች፤ ኮሌጂወች፤ ኢኒስቲቲዮወች የሉትም።
10) የፍቅር ተፈጥሮ ግሎባል ነው። ነገር ግን ግሎባል የሆነ ዕውቅና ያላቸው #ኢቬንቶች ተዘጋጅተውለት አያውቁም።
11) የፍቅር ተፈጥሮ ፍትኃዊ ሆኖ የእኔ የሚለው #የሚዲያ አክሰስ ቴሌቪዥን፤ የራዲዮ ፕሮግራም የለውም።
12) የፍቅር ተፈጥሮ አናባቢም ተነባቢም ሆኖ ምንም ዓይነት #በፕሬስም ዕድሉ ልሙጥ ነው። ቋሚ መጋዚን፤ ቋሚ ጋዜጣ፦ በራሪ ፁሁፍ የለውም።
14) የፍቅር ተፈጥሮ የላቀ አኗኗሪ ሆኖ ነገር ግን #ለሙዚዬም፤ ለቤተ - መዘክር፤ ለቤተ - መፃህፍት የሚሆኑ ተግባራት አልተጀመሩም። ውርስ ትውፊት ለመሆን የሚችልበት ህንፃወች አልተጀመሩለትም።
15) የፍቅር ተፈጥሮ የቤተሰብ ምሥረታ ላይ ታላቅ ድርሻ ኑሮት በቤተሰብ ደረጃ #ሚኒ ዲስከሽን ሩም እንኳን አልተፈጠረለትም።
 
እና ክፋት ቢፈነጭ፤ ክፋነት ቢይል፤ ጭካኔ ቢንሰራፋ ምን ይደንቃል? ፍቅር ስል የሰው ልጅ ከሚተካው ሂደት በላይ ይሄዳል። አጠቃላይ ለሰው ልጅ ሐሤት የተፈጠሩትን #አኗኗሪ የተፈጥሮ ፀጋወችን ይጨምራል። አሁን እኔ የሳተ ጎመራ ላርባ ያስደስተኛል፤ የወፎች ዝማሬ፤ የውሃ ፏፏቴ እወዳለሁ። ፈረስ እና እርግብም እወዳለሁ። ጥጃ እና ጫጩትም እወዳለሁ። የወፍ ዝርያ ቀለማት ይስቡኛል። እሰበስባለሁም። ደመና እጅግ አድርጌ አደንቃለሁ። ይህ ሁሉ ፍቅር ነው። ብሄራዊ ሰንደቄን አፈቅራለሁኝ። ማህሌት ይመስጠኛል።
 
ቅኖችን እወዳለሁ። የዕውነት አርበኞች ይማርኩኛል። ፍፁም ታማኞች ነፍሴን ይገዟታል። ስለ ሰው የሚተጉ አትኩሮቴ ናቸው። በፍቅር ተፈጥሮ ውስጥ ልሥራ ብላችሁ ስትጀምሩ አይደለም እሺ #አይ ፍቅር ሆኖ ታገኙታላችሁ። ምህረት፤ ይቅርታ፤ እቅፍ፤ ኑሩልኝ የፍቅር ተፈጥሮ ነው። ደህና አደራችሁ፦ አረፈዳችሁ፦ ዋላችሁ፦ አመሻችሁ፦ አይዟችሁ፤ ቅንነት፦ የፍቅር ተፈጥሮ ነው። ደህና እደሩ የፍቅር ተፈጥሮ ነው። አመሰግናለሁ ፍቅር ነው። ሥጦታ ፍቅር ነው። ሽልማት ፍቅር ነው፤ ተስፋ፤ በጎ ምኞት፤ ማመን ፍቅር ነው፤ መሳቅ ወዘተ ……
በእናቴ መራራ እጅግም ጥልቅ የውስጥ ሀዘን ተቋረጠ እንጂ ምንም ሳላውቅ ከዜሮ በታች ጀምሬ ዩቱብ ቻናሉ ጥሩ ሂዶ ነበር። መዳህኒታቸውን በሙሉ እጃቸው አድርጎ እንዴት ዝግጅቴ ተስፋ እንደሆነላቸው የሚጽፋልኝ የውጭ አገር ዜጎች ነበሩ። ጥልቅ ስለሆነ ጊዜም ማሰብም ማገናዘብም ይጠይቃል። በዳታ ለማስደገፍ ተንቀሳቅሶ ለመሥራትም አክሰሱ የለኝም። ብቻ ለአሰራር እንዲያመቸኝ በዘርፍ ዘርፍ ለይቼ እሰራ እና ኮንፓክት ሳመሪም ይኖረዋል። ስጀምር ብታዩት ሃሳቡ በእህል ዘር ብጀምረውም ግን እኔም ሳዬው እስቃለሁኝ። አልሰርዘውምም። መነሻ ነው። መጸሐፍቶቼም የመነሻ ሃሳብ ነው ያላቸው።
 
#ግን አለማችን አንድም ………
 
ርትህ፤ ትዕግሥት፤ መቻቻል፤ መተማመን፤ መሳቅ፤ እሺ፤ ይሁን፤ አመሰግናለሁ፤ አክብሮት፤ ትህትና፤ ደግነት፤ መልካም ሰው፤ ምስጉን ሰው፦ አብሮነት፤ ህብራዊነት፤ መኖር፤ ምህረት፤ እርቅ፤ ይቅርታ፤ መተንፈስ፤ አይዟችሁ፤ ቅንነት፤ ዕውነት፦ ተስፋ፥ እቅፍ! አክብሮት፤ ሰላምታ፦ ተፈጥሯዊነት ወዘተ በእነኝህ ሥሞች የሚጠሩም ትምህርት ቤቶች የሏትም። ሥም እራሱ የዕውቀት ዘርፍ ነው። 
 
ሲጠቃለል ዓለማችን ጆሮ ባትሰጠውም እኛ እራሳችን እዬቆነጠጥን፤ እዬገሰጽን ብዙ ነገሮችን መግራት ይቻላል። መልካም ዜና አይደለም የሚዳረሰው ተሎ። እሱ አድማጭ የለውም። የምንፈቅደው ውስጣችን ዳሜጅ የሚያደርገውን ነው እኛ እራሳችን። ለሌሎች እንዲዳረስ የምናደርገውም ይኽው ነው።
ውዶች ክበረቶች እና አዱኛወች። ዛሬ በብዕር አስገዳጅነት የታቀደው ቀርቶ አብረን ቆዬን።
 
 እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ቸር ሁኑልኝ። አሜን።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
21/06/024
የፍቅር ተፈጥሮ እኛን ሰጠን፤ እኛንም ለፍቅር ተፈጥሮ እንስጥ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።