የማንነትን ብዛት #መስፈር አይቻልም። ማንነት Homogeneous #አይደለም Heterogeneous ነው። በንግግር ጥበብ ፕረዘንቴሽንም ላይ ትልቅ ሮል ያላቸው ጉዳዮች ናቸው እነኝህ መንትዮሽ።

 May be an image of 1 person, smiling and jewelry

የማንነትን ብዛት #መስፈር አይቻልም። ማንነት Homogeneous #አይደለም Heterogeneous ነው። በንግግር ጥበብ ፕረዘንቴሽንም ላይ ትልቅ ሮል ያላቸው ጉዳዮች ናቸው እነኝህ መንትዮሽ።
"አሁንም ልጆቼ ሆይ ስሙኝ፦
ከአፌም ቃል አትራቁ።"
(መጽሐፈ ምሳሌ ፭ ቁጥር ፯)
 
ማንነት አንድ ሰብ ወይንም አንድ ማህበረሰብ፤ ወይንም አንድ ዞግ በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ ወጥነት መኖራቸው ብቻ እድርገን ልንመለከት አይገባም። የአንድ እናት እና አባት ልጆች #በፆታቸው ተመሳሳይ ሆነው፤ አንድ ቤት #አንድገው፤ አንድ ሰፈር #ኖረው፤ አንድ ትምህርት ቤት #ተምረው፤ አንድ #ሥልጠና ወስደው፤ አንድ ቢሮ እዬሰሩ አንድ ሊሆኑ ፈጽሞ አይችሉም። ዕይታቸው ምርጫቸው ርዕያቸው ግባቸው ወጥ ሊሆን ቀርቶ ሊመሳሰልም ላይችል ይችላል። የራስ እና የእግር አሻራ ልብ የበሉ። የተወለድንበት ዕለት፤ ሰዓት ቀናት እና ወቅታትም የራሳቸው ተጽዕኖ አላቸው። 
 
ከአባት ዘር ወደኋላ ሲቆጠር፤ ከእናት ዘር ወደኋላ ሲቆጠርም በአንዱ የሚከሰት በሌላው የሌለ ሊሆን ይችላል። ትንሽ ለማብራራት የአግር እጣቶቼ አንገተ ደፋታ ናቸው። የአጎቴ የልጅልጅ ይህን ይዞ ተወልዷል። ለእሱ ፍቅሬ ደግሞ የተለዬ ነው። እኔ ስናፍቃቸው ያን እንደሚዩ ነግረውኛል። እኔ ተማሪ እያለሁ 11ኛም/12ኛም ክፍል በደረጃ ነው የፈፀምኩት። ምርጫዬ ባይወሎጂ እና ኬሚስቲሪ ነበር። አንዱ ምርጫዬ ህግ ሌላው ባይወለጅስት ሌላው አስትሮነመር ነበር። አሁን ያልኳችሁ የአጎቴ የልጅ ልጅ ባይወለጅስት ነው። (ዶር) ሌላው ፖለቲካል ሳይንስ ነው። ሁለቱም ከእኔ የተወሰነ ዝንባሌን ወርሰዋል ማለት ነው።
 
በሌላ በኩል ደግሞ አንዱንም የማይመስል ገጠመኝ ይኖራል። አብረን አድገን በኋላም ያደጉ ያሳድግኳቸው እህት እና ወንድሞች እኔን ፈፅሞ አይመስሉም አንዳቸውም እኔ እምሰራውን አይከታተሉም። አያውቁትምም። አክሰሱ እያላቸው። እኔም እነሱን #አልመስልም። በጣም የተራራቀ ፍላጎት እና ርዕይ ነው ያለን። ማንነት #አለቀ የሚባል ጥግ የለውም። 
 
አይኖረውም። እኔ ጎንደር ተወለድኩ ሲዊዝ እኖራለሁ። በፖለቲካ ዘርፍ የማህበረሰብ አደራጅ ነበርኩ ጋዜጠኛ ሆንኩኝ። ጸሀፊ፦ ብሎገር፦ ዩቱበር፦ ገና ይቀጥላል።
ሌላም አለ አንድ ሰው ከሌላው የሚለዬው አሻራው ብቻ እንዳይመስላችሁ። 
 
የውስጥ ኦርጋን አቀማመጣችንም #በአህጉር እዬተመደበ ነው። ይህምብቻ እንዳይመስላችሁ #የመጠኑ ጉዳይም ይለያያል። አንዳንድ በሙሉ ዕድሜ ያሉ ሰወች የልባቸው መጠን የ14 ዓመት ታዳጊ ሊሆን ይችላል ሳይዙ። አንድ ሰው በትክክል ወጥ በሆነ መልኩ መሰሉን ሊያገኝ አይችልም። እንኳንስ በአስተሳሰብ። አስተሳሰባችን እኮ የሚሊዮን የውስጥ ኦርጋኖቻችን የውጭ አካላቶቻችን ቅምረት ነው። ሁሉም ተሳትፎ አለው። 
 
ድርጅት የሰወች ፍላጎት ማሰሪያ ነው። በሌላ እርሰ ጉዳይ አብራራዋለሁ። የሆነ ሆኖ አንድ ድርጅትን የመሰረቱ ሰወች ተመሳሳይ ፍላጎት ለተወሰነ ጊዜ ነው የሚቀጥለው። ይህ ልዩነት በውስጣቸው ማንነት ላይ ጠቅ የሚያደርግ የውስጥ ይሁን የውጭ ክስተት ሲፈጠር ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ሂደቱ እራሱ የወጥ ፍላጎቱን ቁርኝት #ሊያፈራቅቁት ይችላሉ። ከእኛ እንደብርቅ ነው የሚታዩት "#የብልጽግና" አጀንዳ አራማጆች ዕለታዊ ዜና ፋኖ ተሰነጠቀም ይህን በጥልቀት ያለማዬት ችግር ነው። አብሮ የጀመረ አብሮ እንዲዘልቅ የሚያስችሉ ሁኔታወች ከሌሉ ልዩነት ተፈጥሯዊ ነው።
 
በአንድ ሰው ውስጥ የፊት አቀማመጡ #ክብ#ኦባል፤ ከአንገት በላይ ረዘም ወይንም አጠር ያለ፤ ከወገብ በታች ረጅም ወይንም አጭር፤ ቀይ፤ ዳማ፤ ጠይም፤ ጤናማ ወይንም ህመም ያለበት፤ ህመሙ ጊዚያዊ ወይን ቋሚ፤ አንድ ወይን ከአንድ በላይበሽታ፦ የቀለም ምርጫው፤ የመኖር ፈሊጡ፤ የባህሪው አወቃቀር፤ የሙያው ዓይነት እና ደረጃ፤ የሃይማኖቱ ዓይነት፤ የፖለቲካ አቋሙ፤ ዜግነቱ፤ የትዳር ሁኔታ፤ የልጅ ሁኔታ፤ የማንበብ አቅሙ፤ የማድመጥ ሁኔታው #ወዘተረፈ #ማንነት በውስጡ ይዟል። አንዱ ሰው ስለማንነቱ ልፃፍ ቢል መፀሐፍ በመፀሐፍ ይሆናል። አንድ ሰው እራሱ ለእኔ #ሄትሮጅነስ ነው። ሆሞጅንዬስ አይደለም ብዬ ወደ ማመን ይቃጣኛል። የእኔ ፍልስፍና ነው ይሄ።
 
በዚህ ወዘተረፈ ማንነት ወጥ ባልሆነ ማህበረሰብ፤ በቅይጥ ማህበረሰብ ውስጥ በወጥ ፖለቲካ #ጎረይና ካልተሰበሰባችሁ ጤነኝነት አይመስለኝም።"መበልፀጉ" ባፍንጫዬ ይውጣ ያለ አፍንጫህን ሰንጌ አስውጥኃለሁ ነው ግብግቡ። ሌላው ደግሞ " ብልጽግናችን ለራያችን" የሚለው የአብይዝም ኃይል ደግሞ #አታስተጓጉሉን ብሎ እስረኛ ሲፈታ እንኳን የቆጣጠራትን #ቁርሾ እያጣቀስ ብትመልሱልን ወደ ካቴና ማለትም የተገባ አይደለም በተደላደለ አገር ተቀምጦ።
 
በምንም ታምር፤ በመቼውም ጊዜ #ህሊናውን #አከራይቶ የሚኖር ትውልድ አይኖርም። ዛሬ መንገዱ ሰልቷል። ማህበራዊ ሚዲያው እኮ ተፈጥሮ የሰጣችሁን ፀጋ ተጠቀሙ። #ፏም // #ቧም በሉ እኮ ነው። "የብልፅግና" ክልል ካልገባችሁ ተብሎ ይህ ሁሉ ማት በዛ ደግ ህዝብ ላይ ሊፈስ ባልተገባ ነበር። መሪነት ይህን ሁሉ ሊያገናዝብ ይገባል። መሪነት እራሱን እንደ አንድ ኦብጀክት ወስዶ እኔስ ብሆን ታፈን፤ ተገደል፤ ተሰወር ብባልስ ብሎ ሊያስብ ይገባል። አንድ መሪ ትክክልነቱ ሳይታይ ትሆነኛለህ ተብሎ ሲፈተሽ መሆን ሲሳነው መፋጠጥ ያለበት ከራሱ ማንነት የውስጥ መሻት ጋር ሊሆን ይገባል።
 
የፖለቲካ ድርጅት የሚባል ደዌ ኢትዮጵያ ከመጣ ወዲህ ትውልድ የሚመተረው #ልጠቅልህ /// #አልጠቀለልም ነው። በዬዘመኑ አውራ ሆኖ የሚወጣ የፖለቲካ ፓርቲ አለ። እሱ ዶሚናንስ ልሁን ነው ትውልድ የሚነቀልበት ሁነት። #ገብር// #አልገብርም ነው። በውነቱ ስስታምነትም ባለፈም #ሰገብጋባነት ነው። 
 
የእራሱ አንደበት ተሰጥቶት በእኔ አንደበትነት ብቻ ማለት ሲኦልነት ነው። ኢትዮጵውያን አብልተው አጠጥተው ያሳደጉን ወላጆቻችን ነፃነታችንን ነው። ሰብለ©ሕይወት ስባል እና በክርሥትና ሥሜ ሥርጉተ©ሥላሴ ስባል ትፍስህት አገኛለሁ። ኮንፊደንሱ የሚመጣውም እራሴን በመሰጠቴ ነው። የራሴ እንደራሴ እኔ መሆኔን ተመግቤ አድጌያለሁ። ይህን ሊቀይር // ሊለውጥ የሚሻ ማናቸውንም ኃይል አሻም ማለቴም የተገባ ነው። ልጥፍ - ቁሮ ስለማያስፈልገኝ።
 
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ድርጅቶች ጠያፍ የሆነው የግል ነፃነትን የመንሳት ባህል የአማራ ፖለቲካ ሊያርመው ይገባል። እንጂ በዛ መጭ ሊል አይገባም። ኢትዮጵያዊነታችን ሆነ አማራነታችን የሚያመሳስለን ቢሆንም ግን እኔ የኔ በምለው መሥመር መሰሌም የእኔ በሚለው መሥመር መጓዝ የተገባ ነው። አብረን መጓዝ ከተቻለ እሰዬው ነው። ካልተቻለም እንቅፋት መሆን አይገባም።
 
ቀደም ብዬ ባነሳሁት ሃሳብ ላይ እማክለው አብረው ሳይጀምሩ ግን መሃል መንገድ ላይ አብረው ሊቀጥሉ የሚችሉም ሊኖሩ ይችላሉ። መልሰውም እነሱም በሂደት አስገዳጅነት ወጥ ጭንቅላት ወጥ ተመክሮ ስሌለ ለጊዚያዊም ለረጅም ጊዜም መለያዬት ሊገጥም ይችላል። ይህ ተፈጥሯዊ ነው። እንደ ድክመት ወይንም እንደ ዝለት ሊታይ አይገባም።
 
ቁምነገሩ ይህን ጠንቅቀን ስናውቅ ከ10 ሚሊዮን ህዝብ በላይ ያላት ኢትዮጵያ በነፍስ ወከፍ ሄትሮጂኒዬስ የሆነ ማንነት እንዳለ መቀበል ለዛም ሰፊ ልቦና እና የተረጋጋ መንፈስን ይጠይቃል። ይህ ማለት በሌላ ቋንቋ ራስን ማደራጀት፤ ባደራጁት ራስነት ላይ የተስተካከለ የመሪነት አቅም ማፍለቅ ይሆናል። ይህ ደግሞ ትውልዱን በተረጋጋ የሃሳብ አደረጃጀት ማነፅ ይቻላል።
 
በዓለም ያሉ ጦርነቶች በጥልቀት ስትመዝኗቸው መሠረታዊ አምክንዮወች ይህ ነው። የራሽያን እና የዩክሬንን እንመልከት። ራሺያ ዩክሬን ኔቶ ከገባች ስጋት ይኖርብኛል ነው። ዩክሬን ደግሞ ሉዓላዊ አገር ነኝ ያሻኝን አደርጋለሁ። በተሸራረፋት የሶብዬት ህብረት አገሮች ኃያል ሆኜ እወጣለሁ ሃሳቤ ፍላጎቴ ይግዛህ አባት አገር ራሺያ ነው ዩክሬናውያን የሚሉት። በኋላስ? ነው የአባት አገር ራሽያ ጥያቄ። አሰላለፋን ደግሞ እዩት። 
 
ርዕዮታለማዊ ይመስላል። ቁጭ ብለን በእኛ ዘመን ያልሰለጠነ ኋላቀር ህዝብ ነው ጦርነት የሚወደው የሚባለውን በ21ኛው ምዕተ ዓመት ሥልጣኔን ሥልጣኔ ሲያወድመው፤ አመድ ሲያደርገው አዬን። 
 
ጉግሱ ልጠቅልል /// አልጠቀለልም ነው። ያለቀው ንብረት፦ ስንት በጎ ነገር ይሠራ ነበር? የተፈታው፦ የፈለሰው ቤተሰብ ስሜት ሚዛን ማውጣት አይቻልም። ራሺያ እራሷን የገነባችበት ማንነት አላት። ኔቶም ራሱን የገነባበት ማንነት አለው። ዩክሬንም ራሷን የገነባችበት ማንነት አላት አንዱ ሌላውን ለመጫን፤ ለማስገበር ሳይሆን ተተኪው ትውልድ የህግን ሉዓላዊነት ይቀበል ዘንድ ከጦርነት የሚቀድሙ ጥረቶች፦ ግንዛቤወች ሊኖሩ ይገባ ነበር። ማንነት በገብያ ህግ አይተዳደርምና። 
 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
21/06/024
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።